፩ ሃይማኖት
8.97K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ደብረ ብርሃን
@And_Haymanot
ደባርቅ
@And_Haymanot
ፍኖተ ሰላም
@And_Haymanot
ድሬዳዋ

በኦርቶዶክሳውያን እያተደረገ ያለው የጥፋት ዘመቻ አሁንም እንደቀጠለ ነው!
ድሬዳዋ በሙስሊም ቄሮዎች መታመስ
ከጀመረች 4 ቀንዋ ነው! ከትናንት ማታ ጀምሮ የጥይት እሩምታ ያልተለያት ሲሆን አሁን ከከተማው ወጣ ብሎ ያለውና ከመድኃኔዓለም ቤ/ክ ቀጥሎ በሚገኘው የጋራ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ
ፍጥጫው ብሷል! ኣጥፊዎቹ በድንጋይ የቤተክርስቲያኑን ጣራ በርና መስኮት እየሰበሩት ነው! ቤ/ክን ለመከላከል ከመጡት ምዕመናን ብዙዎች እየተሰበሩ ጭንቅላታቸው እየተፈረከሰ ደማቸው እየፈሰሰ ነው:: የከተማው ፖሊስ ከኣጥፊውቹ ይልቅ ኦርቶዶክሳውያኑን እያጠቃ ይገኛል! አሁን ትንሽ እንደተረጋጋ
ቢነገርም በድሬ ያላችሁ ካህናትና ዲያቆናት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የማሕበራት አባላት ሁላችሁም እንሆ ለቤ/ክ ሰላም ተነሱ! እኛም በጸሎት፣ በስልክ እየደወልን በማጽናናትና
ላልሰማው በማሰማት ወገኖቻችንን እንርዳ! ...
#ዓይኖች_ሁሉ_ወደ_ድሬዳዋ
Binyam ZeChristos
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
የአስሩ ማኅበራት ኅብረት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡኑ ማትያስ የአፈጻጸም ሪፖርት አቀረበ!!
ትላንት መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ.ም ÷የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአሥሩ ማኅበራት ኅብረት÷ለብፁዕ ወቅዱስ አቡኑ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የአፈጻጸም ሪፖርት አቀረበ፡፡ በሪፖርታቸውም ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ፣ ከአዲስ አበባ ከንቲባና ከክልላዊ
መንግሥታት ጋር ያደረጉትን ውይይት፣ የተደረሰባቸውን ሰምምነቶችና በቀጣይ መደረግ ሰለሚገባቸው ጉዳዮችም
ለቅዱስነታቸው አቅርበውላቸዋል፡፡
ለአዲስ አብያተ ክርስቲያን መትከያ፣ ለመካነ መቃብር፣ ለባሕረ ጥምቀት እና ለመስቀል ደመራ በዓል አከባበር እንዲሁም ለራስ አገዝ ልማት የሚውሉ ቦታዎች በሕግ አገባብ እንዲሰጡ፤
በተለያዩ አህጉረ ስብከት የሚገኙና የተወረሱ የቤተ ክርስቲያን ቤቶች እና ሕንፃዎች እንዲመለሱ፤ በቤተ ክርስቲያን ይዞታ ሥር ለሚገኙ፣ በቀጣይ በሚደረስባቸው ስምምነቶች ለሚመለሱ እና ዐዲስ ለሚሰጡ ቦታዎች፣ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና/ወይም ደብተር እንዲሰጥ፤ ርእዮተ ዓለም መር ከኾኑ ስሑት ትርክቶች የተነሣ በሃይማኖታዊ ማንነታቸው ምክንያት ብቻ ለልዩ ልዩ
አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጥቃቶች ተዳርገው፥ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ፣ ከማኅበራዊ ኑሮ የተገለሉ፣ ከሓላፊነት ቦታቸው እና ከሥራ መደባቸው የተባረሩ፣ ዛሬም በዚሁ ጫና ውስጥ የሚገኙ
ኦርቶዶክሳውያን ተገቢውን ፍትሕ እንዲያገኙ፤ የቤተ ክርስቲያንን
ትክክለኛ ማንነት እና አገራዊ ውለታ በአገባቡ የማይገልጹ፣ሕጋዊ እና መዋቅራዊ ድጋፍ ያላቸው የሚመስሉ፣ ሌሎች እምነቶችን ለበቀል የሚያነሣሱ በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳውያንን
ለጥቃት ያመቻቹ እና ያጋለጡ ስሑት ትርክቶች እንዲታረሙ፤ ለሕዝብ አገልግሎት የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ሓላፊነት አላግባብ በመጠቀም፣ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ ልዩ
ልዩ ስልታዊ ጫናዎችን ያደረሱ፣ ቀን ቀጥረው የተከሠቱና ለመከላከል የሚቻሉ ጥቃቶችን ያላስቆሙ፣ ይብሱኑ ጥቃቶቹን ያቀዱና ያቀነባበሩ ባለሥልጣናት፣ በገቢርም የፈጸሙ ቡድኖች እና ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ የሚያስችሉ በአብዛኞቹ
ክልሎች ላይ ሰምምነቶች ላይ መደረሱን ለቅዱስነታቸው በሪፖርታቸው እንደገለጡላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ግፍና በደል እጅግ እያዘኑ እንደሆኑ የገለጡት ቅዱስነታቸው÷ዛሬም ኀዘናቸውን መቆጣጥር አቅቷቸው ውስጣዊ ኀዘናቸውን በዕንባ ጭምር መግለጣቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቅዱስነታቸውም የአሥሩን ማኅበራት ኅብረት ጥረትና ትጋት አድንቀው፤ አሰፈላጊ በሆነ ሁሉ እንደሚያግዟቸው
ቃል ገብተውላቸዋል፡፡ኅብረቱ ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ኮሚቴ ጋርም ይወያያል፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
መስቀል በኢትዮጵያ


✞ ተወዳጆች በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!!! አደረሳችው ✞


❖ "ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ" ገላ 6፥14 ❖

@And_Haymanot

ኢትዮጵያ ሃገራችን የክርስቲያን ደሴት ከመባሏም በላይ የእግዚአብሔር ቸርነት ያላት የበረከት የረድኤት ሀገር ናት ይኽም የጌታ ግማደ መስቀል በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል

☞ አመጣጡም የኢትዮጵያ ነገሥታት የግብጽ ካሊፋዎች ሀገረ ገዥዎች በኃይል ይጋፏቸው ስለነበር የግብጽ ሀገር ገዥዎች ደግሞ የግብጽን ክርስቲያኖች (ኮፕታውያን) ያሰቃዩአቸው ነበር ስለዚህ ይህ አለመግባባት እንዲወገድና የግብጽ ክርስቲያኖች ዕረፍት እንዲያገኙ በማሠብ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ከግብጽ የአህናስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስንና አባ ማዕምር የሚባሉ ሉዑካን ወደ ኢትዮጵያ መጡ በዚያን ጊዜ አጼ ሠይፈ አርዕደ አርፈው የልጃቸው ልጅ አጼ ዳዊት ነግሠው ነበር እነዚህ ልዑካን በኢትዮጵያውያንና በግብጻውያን ነገስታት መካከል ያለውን ቅራኔ አስወግደው ሲመለሱ አጼ ዳዊት በነበራቸው ቀና መንፈስ አቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ እሌኒ ንግስት አስቆፍራ ከአስወጣችው ከጌታ ግማደ መስቀል ክፋይ ለበረከት እንዲልኩላቸው ወርቅ፣ አልማዝ፣ ገጸ በረከት አስጭነው ወደ ኢየሩሳሌም መልዕክተኞችን ላኩ መልእክተኞቹም ኢየሩሳሌም ደርሰው ገጸ በረከቱን ለፓትርያርኩ ከሰጡ በኃላ ፓትርያርኩ፦

፩፦ የጌታን ግማደ መስቀል፣ የቀኝ በኩሉን ክፋይ
፪፦ ጌታ ላይ አይሁድ የጫኑበትን (ያረጉለት) አክሊለ ሶኩን
፫፦ ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ የእመቤታችን ስዕል ላኩላቸው።

መልዕክተኞቹም ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አጼ ዳዊት መልእክተኞቹን ለመቀበል ሲሄዱ የተቀመጡባት ባዝራ ፈረስ ጥላቸው መሞታቸውን ታሪካቸው ይናገራል መስቀሉ ወደ ሀገራችን የገባው #መስከረም 10 ቀን ነው መስቀሉ የተቀመጠው መስከረም 21 ቀን በወሎ ክፍለ ሃገር በግሸን ማርያም ነው

በዚህ ሁኔታ የገባው የጌታ መስቀል ዛሬም ድረስ ተአምራዊ ነው ይህም ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመስቀል ያላትን ታላቅ አክብሮትና ፍቅር የገለጸችበት አብይ ምስክር ነው ሕዝቡም ለመስቀል ያለውን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ይነቀሰዋል፣ በልብሱ ላይ ይጠልፈዋል ይህ ደግሞ የሚያሳየው መስቀል በኢትዮጵያውያን ዘንድ ምን ያህል ክብር እንዳለው ነው።


☞ ከተለያዩ ማዕድናት የሚሰራው መስቀል ትርጉም፦

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸው ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው ብለው አባቶች ያስቀመጡትን ማየት ይገባል።

ከብረት ቢሰራ ክርስቶስ የተቸነከረበትን ችንካር ለማመልከት ነው
ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ክርስቶስን ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለብህ ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው
ከእንጨት ቢሰራ ክርስቶስ የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው
ከብር ቢሰራ ተስፋን፣ ዕድልን ያመለክታል ይኸውም ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ ቤዛን በደሙ ከፍሏልና በእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል


መስቀል ለእኛ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ ጽንዐችን፣ ቤዛችን፣ መድኃኒታችን ነው "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና" /1ኛ ቆሮ 1፥18/ ለቅዱስ መስቀል ክብርና ስግደት ይገባል ምክንያቱም በመዝ 131፥7 ላይ "እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን" ተብሎ ተጽፏልና።

❖ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
❖ በዓለም ጥበብ ለሚኖሩ እውነት ተስኗቸው
❖ ለጠቢብ ሰው በመንፈስ የሚኖር
❖ የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው
❖ ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው

ያለ መስቀል ክርስትና ያለ ተጋድሎ ቅድስና የለም!!!

✞ አምላከ ቅዱሳን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ጽላት ላይ ይጻፍልን!!! አሜን ✞✞✞

ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ከመሰዉያዉ እና ከመስዋዕቱ የቱ ይበልጣል ? መስቀሉወይስ መስቀሉ ላይ የተሰቀለዉ?

@And_Haymanot

የተሃድሶ መናፍቃን የመስቀሉን ክብር አይቀበሉም የተቃውሟቸው መንገድም ፍጡርን ከፈጣሪ እኩል ክብር የምንሠጥ አድርገው ምዕመኑን ሊያታልሉ ይጥራሉ
የኑፋቄያቸው አላማም የክርስቶስ ኢየሱስን የደሙ እንጥፍጣፊ ያረፈበትን መስቀል፤አይጠቅምም ብለን እንድንተው ይተጋሉ
★ ★ ★
ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስትያን ፤ለልጆቹዋ ፤ ለአምላክ የሚሰጠውን አምልኮ ፤ምስጋ፤ስግደት ና ክብር ፤ ለቅዱሳኑ ና ለነዋየ ቅድሳቱ ከሚሰጠው አክብሮትና ምስጋና ስግደት ለይታ ታስተምራለች፡፡ ነገር ግን እንደ ሉተርያውያን፤የሐይማኖት ድርጅቶች የጌታ የሆኑትን ሁሉ ባጠቃላይ በመናቅ ባለማክበር ና በማንቁዋሸሽ፤ የጌታ
እውነተኛ ድህነት እንደማይገኝ ና ይልቁኑ በምትኩ እሱ የመረጣቸውን ቅዱሳንና የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ ማክበር የአንድ ክርስትያን ሐይማኖታዊ ግዴታ እንደሆነ ትላንትም ዛሬም ነገም እስከ አለም ፍጻሜ ታስተምራለች፡፡
★ ★ ★
መደ ጥያቄው መልስ ስንመለስ ኦርቶዶክስ ተወህዶ መቼም ቢሆን መቼም፤ የክርስቶስን የመስቀል ላይ ቤዛነት፤ምንም ነገር ፤እንደማይተካው ስለምታውቅ ፤በአመቱ በሙሉ በቅዳሴዋ በኪዳንዋ፤ በማህሌቷ ፤በምህላው ጸሎቷ ባጠቃላይ በሁሉም የአምልኮ
ስርዐቷ፤ ላይ የክርስቶስ፤ስጋን እና ደም፤እንድንቀበል፤ ልጆቹዋን ታስተምራለች፤ትመክራለች፤ ንስሃ ግቡ በማለት ታበረታናለች፡፡ ቅዱሳኑ እራሱ ታስበው በሚውሉበት ቀን፤ ፍቅረ ክርስቶስ/የመስቀሉ ቤዛነት ቅዱሳኑንን ምን ያህል አለምን እንዲንቁ እንዳዳረጋቸውና ለስሙ ሲሉ
የታገሱትን መከራ ለልጆቹዋ ታስተምራለች፡፡
★ ★ ★
እለት እለት በሚካሄደው የቅዳሴ ስርዐት ላይ ከሌሎች በደሙ ድነናል ብለው
መፈከር ብቻ አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ተለይታ ድህነት በመፈክር ሳይሆን ጌታ ባዘዘው መሰረት
“””ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው””
ዮሐ 6፥53 የሚለዉን ቃል መሰረት በማድረግ ለምዕመኗ ሁልጊዜ
ሳታቋርጥ የጌታን ስጋን ደም ታቀብላለች፡፡
★ ★ ★
ነገር ግን በዘመናችን የተነሱት መናፍቃንና የበኩር ልጆቻቸው
የተሃድሶዎ መናፍቃን፤ ቅድሥት ቤተክርስትያን ክርስቶስን አትሰብክም ለቅዱሳኑ ና ለነዋየ ቅድሳቱ እና ለጌታ ቅዱሳን የሚሰጠው ክብር አያስፈልግም፤ ብለው ሲሟገቱን እናያቸዋለን፡፡ በዚህም የተሳሳተ ትምህርት ብዙዎችን ፤ጌታችሁን አገኛችሁ ብለው ከስላሴ ልጅነት ፤ማህተባቸውን አስበጥሰው ወደማይወጡበት የጨለማ ህይወት ና ፤
ከባለጸጋዋ ቤተክርስትያን አውጥተው ባዶ አዳራሽ አውርሰዋቸዋል፡፡
★ ★ ★
~~~የክርስቶስን የመስቀል ላይ ቤዛነት ማንም ምንም ሊተካው እንደማይችል ኦርቶዶክስ ታስተምራለች ከላይ በገለጽኩዋቸው መልኩ ፡፡
ነገር ግን ይሄ ቤዛነት የተከፈለበት መስቀል ፤የጌታ ክቡር ደሙ የተንጠባጠበት መስቀል ፤የጌታ ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት መስቀል፤ሴጣንና ሰራዊቶቹ ድል የተደረጉበት መስቀል፤በሚገባ መክብር አለበት ብላ በየአመቱ በመስከረም 16 ታሪካዊ አንድምታውን ባለቀቀ መልኩ ታከብረዋለች፡፡
★ ★ ★
ቅዱስ መስቀሉ መክበሩ ፤የክርስቶስን ቤዛነት በይበልጥ ያጎላል እንጂ የክርስቶስን ቤዛነት አያስረሳንም፡፡
የሀዲስ ኪዳን መስዕዋት የቀረበበት የክርስቶስ ቅዱስ መስቀል ከከበረ በእርሱ ላይ ያለው ክርስቶስ ይከብራል ምክንቱም የመስቀሉ ባለቤት እራሱ ባለቤቱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነውና።
★★ ★
ማስረጃ ማቴ23፥20-23
20 ---በመሰውያው የሚምል በእርሱ ይምላል በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል።
21 ---በቤተ መቅደስ የሚምል በእርሱና በውስጡ በሚኖረው ሁሉ ላይ ይምላል።
22 ---በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።
"ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 13:7)
★ ★ ★
ስለዚህ መናፍቃንና ልጆቻቸው ተሃድሶዎች ሆይ መስቀሉን
የሚጥል ፤በላዩ የተሰቀለውንም ይጥላል ይህ ደግሞ እጅግ በጣም አሳፋሪ ፤ ነውር ና፤ ሀጥያት የሚለው ቃል የሚያንሰው ነው፡፡
★ ★ ★
ስለሆነም መናፍቃን፤ ክርስቶስን ያከበራቹሁና ያስከበራችሁ እየመሰላችሁ ከክርስቶስ ህብረት ፍጹም እየራቃችሁነውና፤ ሳይመሽባችሁ፤ ጥላችዋት ወደ ሄዳችሁባት፤ አማነዊቷ ጌታና የጌታ የሆኑትን ሁሉ ወደያዘችው የ ከርስቶስ ደጅ ወደ ተሰኘችው ቅድስት ቤተክርስትያን ከራሳችሁ የፍልስፍና አለም ወጥታችሁ የጨዋይቱ ልጆች ተብላችሁ፤ ተመለሱ፡፡
#ፈጣሪንም_ከፍጡር_ጋር_ማወዳደር_ይብቃችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጋምቤላ

የመስቀል የደመራው ዝግጅት እንዲህ ባማረ መልኩ ደምቋል
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ወይንዬ

በአሁን ሰዓት በ Jtv ልዩ የመሥቀል መርሃ ግብር
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
.+"የመስቀል ወፍ"+.

@And_Haymanot

ይህች ወፍ በአገራችን በኢትዮጵያ "የመስቀል ወፍ" በመባል
ትታወቃለች፡፡ ምክንያቱም ለተወሰኑ ወራት ያህል በሌላ ሥፍራ ተሰውራ ቆይታ የመስቀል በዓል (መሥከረም 17) ሲያቃርብ ብቅ ብላ ስለ ምትታይ ነው፡፡
.
እንግዲህ ከዚች ወፍ የዘንድሮ 2012 ዓ.ም የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ትልቅ ትምህርትን እንማራለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
መችም እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ሕዝቡን ያስተምራል፡፡ ኢዮ.33፡14
.
ዛሬስ ልዑል እግዚአብሔር ይህችን ወፍ ምክንያት አድርጎ ቢያስተምረን ማን ይከለክለዋል? ይህች ወፍ የመስቀሉ ፍቅር ከገባቸው ከኢትዮጵያውያን
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ጋር የመስቀሉን በዓል
በዝማሬና በምሥጋና ለማሳለፍ ለበዓሉ አከባበር የሚያስፈልገውን
ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቃ ከበዓሉ ቀደም ብላ በየ አከባቢያችን
መገለጧ የሚገርም ትርዒት ነው፡፡
ደግሞም ይህች ወፍ ለመስቀሉ ትልቅ ፍቅር ያላት ነው የምትመስለው፡፡
መናፍቃን ግን የዚህችን ወፍ ያህል እንኳ ዕውቀት አጥተው ከዕውቀት ነፃ በሆነ አመለካከት መስቀሉን እየተቃወሙ
ሆዳቸውን አምላካቸው አድርገው ክብራቸውን በነውራቸው ሽጠው
የመስቀሉ ጠላቶች ሆነው መመላለሳቸው የሚያሳዝን ነው፡፡ ፊል.3፡18
.
በእርግጥም የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት መናፍቃን ሞኝነት፥ አላዋቂነት፥ መሀይምነት፥ ድንቁርና... ቢሆንም ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው። 1ቆሮ.1:18
.
ምናልባት የመስቀሉ ፍቅር ያልገባችሁ ሰዎች! እስኪ ወፊቱን ጠይቋት!
ለምን ይሆን በመስቀል በመስቀል በዓል ላይ የምትመላለሰው? ለምንስ ይሆን ትኩረቷን በመስቀሉ ላይ ያደረገችው?
ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?
1ቆሮ.11:14
.
ይህች ወፍ የሙጥኝ ብላ ትኩረቷን በመስቀሉ በዓል ላይ በማድረጓ ትምክህቷም ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ትምክህት ነው የሚመስለው፡፡ ገላ.6፡14
.
እንግዲህ ይህች ወፍ የመስቀሉን ነገር የዘነጉ ሰዎች እንዲያስቡበት ቀደም ብላ መጥታ ከእግዚአብሔር በተሰጣት
ልዩ ዜማ የበዓሉን መድረስ ታበሥራለች፡፡
.
በቃ ምን አለፋችሁ! ወፊቷ አስተውሎ ለተመለከታት ሰው ሁሉ ስለ መስቀሉ ፍቅር በጥበብ የምትሰብክ ልዩ ሰባኪት ናት፡፡ ስለዚህ ልብ ብላችሁ ተመልከቷት ግብዣዬ ነው፡፡
.
አድራሻችሁ ከመስቀሉ ሥር የሆናችሁ ሁሉ መልካም የመስቀል በዓል የሠላምና የፍቅር በዓል ይሁንላችሁ!
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አስታርቂኝ


አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/ 
ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም 

አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ 
አስታርቂኝ ጫካ ውስጥ ቆሜአለው 
አስታርቂኝ ሥራዬ አሳፍሮኝ 
አስታርቂኝ ዘወትር አነባለው 
አስታርቂኝ ልጄ አዳም ብሎ 
አስታርቂኝ አምላኬ ሲጠራ 
አስታርቂኝ እነሆኝ ለማለት 
አስታርቂኝ አንደበቴ ፈራ 
አዝ ------------ 
አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ 
አስታርቂኝ ከገዛ አባቴ 
አስታርቂኝ ከቤቴ ኮበለልኩ 
አስታርቂኝ ይሻለኛል ብዬ 
አስታርቂኝ ገፍቼ ወጥቼ 
አስታርቂኝ የቤቴን ገበታ 
አስታርቂኝ ልበላ ተመኘሁ 
አስታርቂኝ የእንስሳት ገፈራ 
አዝ--------- 
አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ 
አስታርቂኝ አሁን ተነሥቼ 
አስታርቂኝ ይቅርታ ልጠይቅ 
አስታርቂኝ እግሩ ስር ወድቄ 
አስታርቂኝ ልጅነቴ ቀርቶ 
አስታርቂኝ አድርገኝ ባርያህ 
አስታርቂኝ ከሞያተኞችህ 
አስታርቂኝ እንደ አንዱ ቆጥረህ 
አዝ ------ 
አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለው 
አስታርቂኝ አባቴ አይቶኝ 
አስታርቂኝ ወደእኔ ሮጦ 
አስታርቂኝ አቅፎ ነው የሳመኝ 
አስታርቂኝ ጠፍቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ተገኘልኝ አለ 
አስታርቂኝ ሞቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ደግሞ ሕያው ሆነ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot
                    
+ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማን(The Martyrdom of St. Arbsima (Repsima) the Virgin) በተመለከተ ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይሉናል?


በዘማርያም ዘለቀ

የሻሸመኔ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች 'አሁን በቅርብ የመጣች....' በሚል ጸያፍ አነጋገር ሲዘልፉ ይደመጣሉ፡፡ በውኑ ስለ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በትርጓሜ መጻሕፍት አልተነገረምን?!

👉 የመጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ይናገራ!! መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶቾ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባቡና ትርጓሜው አዳኝተን(ዳኛ አድርገን) እንዲህ እንላቸዋለን፡፡

❖ ጸሎት ዘጎርጎርዮስ ቅድመ ግብዓተ መንጦላዕት(ወደ መቅደስ ከመግባት አስቀድሞ ጎርጎርዮስ የጸለየው ጸሎትን) ሲተረጉም:- ዲዮቅልጥያኖስ(Emperor Diocletian) መልከ መልካም ብላቴና ፈልጋችሁ ሥዕሏን ሥላችሁ አምጡልኝ ከዚያ በኋላ እሷን ታመጡልኝአላችሁ ብሎ ሠራዊቱን በያገሩ ሰደደ፤ ይህች አርሴማ ፸፪ (72) ያህል ደናግል ይዛ ከተራራ ላይ ወጥታ ተቀምጣለች፤ ኸያ ዓራቱ ደናግል፤ የቀሩት መዓስባን(ያገቡ) ናቸው፡፡ እመ ምኔቲቱ አጋታ(Agatha(Ghana)) ትባላለች። እየፈለጉ ካለችበት ደረሱ፡፡ ሥዕሏን ሥለው ወስደው ሰጡት፡፡ መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል፤ እስዋን አምጡልኝ አላቸው፡፡ እስዋም እንዳስፈለጋት አውቃ አርማንያ ወረደች፡፡ እሱም ከዚያ እንደ ወረደች አውቆ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፤ እንዲህ ያለች ብላቴና ወዳገርህ መጥታለችና አስፈልገህ ስደድልኝ ብሎ ላከበት፡፡ ቢያስፈልግ አገኛት፤ ቢያያት እንደ ፀሐይ ስታበራ አያት፤ ይህችንማ ለራሴ ምን ይዤ ለሱ እሰድለታለሁ ብሎ እመ ምኔቲቱን ይህችን ብላቴና ለምኝልኝ አላት፡፡ አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ነገር አጸናለሁ ብላ ይሁን አለችው፡፡ ኋላ ግን ለሰማያዊ መርዓዊ ለክርስቶስ አጭቸሻለሁና ይህ ርኩስ እዳያረክስሽ እወቂ አለቻት(told her that she must not forsake her true Bridegroom, the Lord Jesus Christ)፡፡ ብላቴኖች ሰዶ አስወስዶ መልኳን አይቶ ብታምረው ተራምዶ ያዛት፤ ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ወቃችው፡፡ ንጉሥ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት፡፡ ከዚያ አያይዞ መላውን አስፈጅቷቸዋል፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ያልሆነ ስራ ማሰራት ኋላ ማጸጸት ልማዱ ነውና መልኳ ትዝ እያለው እህል ውሃ የማይቀምስ ሆነ፡፡ ብላቴኖቹ ሲሞት እናያለን? አደን እንጂ ኃዘን ያስረሳል፤ አደን ይዘነው እንሂድ ብለው ይዘውት ሄዱ፡፡ በዚያ ባለበት ዕሪያ ሁኖ ቀርቷል፡፡ ማን ባዳነልን እያሉ ሲጨነቁ መልአክ ለእኅቱ ከጎርጎርዮስ (Saint Gregory, Bishop of Armenia) በቀር የሚያድንላችሁ የለም አላት። በሃይማኖት ምክንያት ተጻልቶት ከአዘቅተ ኲስሕ አስጥሎት ነበርና የሞተ መስሏቸው ደነገጡ፡፡ መልአክ ላንዲት መበለት ነግሮለት አንድ ፥ አንድ እንኩርኩሪት እየጣለችለት ፲፭ (15) ዓመት ያህል ኑሯል፡፡ የኒህ ክርስቲያን አምላክ ጽኑ እንጂ ነው እንዳለ ብለው ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማስታወቅ ገመዱን ወዘወዘው ሐብሉን ቢስቡት ከሰል መስሎ ወጥቷል፡፡ ወንድሜን አድንልኝ አለችው፡፡ ያለበትን ታውቂውአለሽን አላት፡፡ አዎን አለችው፡፡ አስቀድሞ አጽመ ሰማዕታት ያለበትን አሳይኝ ብሏት አሳየችው፡፡ ዓፅመ ሰማዕታትን አስቀብሮ በዪ ውሰጂኝ አላት፡፡ ይዛው ሄደች፡፡ አንተ ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን አለው፡፡ ወአድነነ ርእሶ ወአንገሥገሠ ርእሶ ከመ ኦሆ ዘይብል ይላል፡፡ ግዕዛኑን (አዕምሮውን) አልነሣውም ነበርና ይሁን አለው። እንዳይታበይ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶለት ጸልዮ አድኖታል፡፡ አስተማረው አሳመነው አጥምቀኝ አለው፡፡ ማጥመቅስ ሥልጣን ካላቸው ሂደህ ተጠመቅ፤ ለኔ ስልጣን የለኝም አለው፡፡ የአንጾኪያውን ሊቀ ጳጳስ አስመጥቶ ተጠምቋል፡፡ {መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባብና ትርጓሜው፤ ሥርዓተ ቅዳሴ፤ ምዕራፍ ፪፤ ገጽ. 20 -21}


✞ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት፤ ቃል ኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ Their intercession be for us, and Glory be to Our God, forever, Amen.✞✞✞

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
ለአዲስ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ገቢ ተማሪዎች

እንኳን ለከፍተኛ ትምህርት አበቃችሁ እያልን በምትሔዱበት ቦታ ሁሉ መልካም የትምህርት ዘመንን እየተመኘን ክርስቲያን በሁለት በኩል እንደተሳለ ሠይፍ ሊተጋ ይገባዋልና በምትሄዱበትና በሄዳችሁበት ከአለማዊ ትምህርት በተጨማሪ በመንፈሳዊ ትምህርታችሁ ጠንክራችሁ በተለይም ሊያስቷችሁ ተዘጋጅተው ከሚጠብቋችሁ ከሃድያን ራሳችሁን ጠብቃችሁ በግቢ ጉባኤ በሚዘጋጁ መርሃ ግብሮች እንድታሰተፉና በሃይማኖታችሁ እንድትፀኑ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለአዲስ ገቢዎች በማዳረስ ተባበሩ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰበር ዜና
ቤተ ክርስቲያን የጥቃት መከላከል ግብረ ኃይል ታቋቁም ዘንድ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ

@And_Haymanot

ለቤተ ክርስቲያን መብት መከበር እስከሞት መሥዋዕት ለመኾን መሥራት አለብን ሲሉም አክለዋል፡፡ ዛሬ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. በተጀመረው የጥቅምቱ ሲኖዶስ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግራቸው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
ምልዐተ ጉባኤው ሊመለከታቸው ከሚገባቸው ወሣኝ የተባሉ ነጥቦች መካከል ትኩረት እንዲደረግባቸው አመላክተዋል፡፡

• ፩. በሀገራችን በተፈጠረው ያለመረጋጋት ክስተት አብያተ
ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ካህናትና ምእመናን ተገድለዋል፤አሁንም ስጋቱ እንዳለ፣ ከቀረበልን የአህጉረ ስብከት ዘገባ ሰምተናል፤ በዐይናችንም ዐይተናል፤ ነባር የቤተ ክርስቲያናችን
ይዞታዎች ሥልጣንን መከታ ባደረጉ ወገኖች እየተነጠቁ ነው፤ምእመናን በሚደርስባቸው የማያባራ ተጽእኖና አድሎ ከቀያቸው እየተፈናቀሉና እየተሰደዱ ነው፡፡ ይህ ድርጊት እንዲቆም እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት መኾን ከዚህ ጉባኤ አባላት ይጠበቃል፡፡

• ፪. መንግሥትም በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የሃይማኖት ክብር ነፃነትና እኩልነትን በሚሸረሽሩ የታችኛው መዋቅር ባለ ሥልጣናት ላይ የማያዳግም የእርምጃ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለብን፡፡

• ፫. በውስጣችን ያለው ያልዘመነ አሠራርም የምእመናንን ልቡና እያቆሰለ የሚገኝ ሌላው መንጋውን ለመጠበቅ የተሰጠንን አደራ እንዳንወጣ እንቅፋት የኾነብን ጉዳይ ነው፤ ይህንን ችግር
ከሥር መሠረቱ ነቅለን በማጽዳት ማስተካከል አለብን፡፡

• ፬. ቀደም ሲል የተጠኑትን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ችግር መፍትሔና የመሪ ዕቅድ ጥናቶች ይህ ዐቢይ ጉባኤ በወሠነው መሠረት በአስቸኳይ ይተገበር ዘንድ ጠበቅ ያለ መመሪያ ሊያስተላልፍ ይገባል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ በብልሹ አሠራር አዙሪት የሚታመስ የቤተ ክርስቲያን አሠራር ሊኖር አይገባም፤
በዚህ ዓመት አሠራራችንን ሁሉ አስተካክለን ወደ መንጋ ጥበቃና ወደ ልማት ሥራችን በፍጥነት መሸጋገር አለብን፡፡

• ፭. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን ዙሪያ መለስ ጥቃት ለመመከትና ለመከላከል ብሎም ለማስቆም አንድ የጥቃት መከላከል ግብረ ኃይል እንዲሁም በየአካባቢው የሚሰነዘሩት ጥቃቶች፣ወከባዎች፣ ተጽእኖዎችና አድሎአዊ አሠራሮችን እየተከታተልን ትክክለኛ መረጃ የሚያቀርብ የተዋስኦ (ኮሙኒኬሽን) ግብረ ኃይል በአሁኑ ጉባኤያችን አቋቁመን ቤተ ክርስቲያናችንንና
መንጋችንን ከመከራ እንድንታደግ የሀገራችን ሰላምና የሕዝባችንን አንድነትን በጽኑ እንድናስጠብቅ አባታዊ
መልእክታችንን እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰበር ዜና

ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤
“እየተቃጠለንና እየተገደልን አንሰበሰብም፤ ልጆቻችን ያሉበት
ሔደን እዚያው አብረን እንቃጠላለን፤ እንሞታለን”/ብፁዓን አባቶች/
• በኦሮሚያ ልዩ ልዩ ከተሞች በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን
ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው አስከፊ ጥቃት እና ግድያ ሳቢያ ቅዱስ ሲኖዶስ የምልአተ ጉባኤውን ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤
• የተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለብዙኀን መገናኛዎች እና ለዓለም ኅብረተሰብ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያሰማውን መግለጫ እያረቀቁ ነው፤
• ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለመከላከያ ሚኒስትሩ እና ለሰላም ሚኒስትሯ ለመጨረሻ ጊዜ የሚደርስ ደብዳቤም እያዘጋጁ ነው፤
• በባሌ፣ በአርሲ፣ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በድሬዳዋ እና በአዳማ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን፣ የአክራሪዎች እና ነውጠኞች ሰለባ እየኾኑ ነው፤ ቤታቸው እና ንብረታቸው እየተጠቃ ነው፤ አስከፊ
እልቂት ማንዣበቡ ተገልጿል፡፡
•በትላንትናው እለትም ቅዱስ ሲኖዶሱ ፀሎተ ምህላ ማወጁ ይታወቃል።
ምንጭ: ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የመንግሥት ልኡክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋራ ይነጋገራል፤

ምልአተ ጉባኤው በሚቀርቡ
ማስረጃዎች ላይ መምከሩን ቀጥሏል
በተወሰኑ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ከተሞች፣በኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለውን የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ጥቃት እና ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም በማድረግ ጉዳይ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የፌዴራል መንግሥት ልኡክ፣
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን እንደሚያነጋግር ተጠቆመ፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ለማ መገርሳንና የሰላም ሚኒስትሯን ወ/ሮ ሙፈሪአት ካሚልን ያካተተው ይኸው ልኡክ፣ ምልአተ ጉባኤውን፣ ዛሬ ዓርብ፣ ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ላይ ያነጋግራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ትላንት ጠዋት የሦስት ቀናት የጸሎት እና የምሕላ ዐዋጅ ካወጣና የሰላም ጥሪውን ካስተላለፈ በኋላ የቀጠለውን መደበኛውን የስብሰባ ሒደት በድንገት በማቋረጥ፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የደረሱ የጉዳት እና የስጋት መረጃዎችንና
ሪፖርቶችን እያሰባሰበ መወሰድ ባለበት አቋም ላይ መወያየት ጀምሯል፤ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ደብዳቤ ለመጻፍና መግለጫም ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደኾነ
መገለጹ ይታወሳል፡፡ “በአሁኑ ሰዓት መሥመር እየለቀቀ የመጣውን፣ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን እየደረሰ ያለው ማቆሚያ የሌለው ጥፋት በጥብቅ ማቆምን ይመለከታል፤” በሚል ርእስ የተዘጋጀው ጽሑፍ በዋናነት፣ የክልል የጸጥታ ኀይሎች በአካባቢው እያሉ ቢጠየቁም ሊታደጉን አልቻሉም፤ ስለዚህ በአስቸኳይ አፋጣኝ ርምጃ በመውሰድ ጥቃቱን እንድታስቆሙልን የሚል እና
የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የቅዱስ ሲኖዶስ የምልአተ ጉባኤን በአስቸኳይ እንድታነጋግሩን በማለት የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ አጽንዖት ተሰጥቶት ተገቢ እና አፋጣኝ ምላሽ
የማይሰጠው ከኾነ ግን፤ ለሚደርሰው የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መንግሥት ሓላፊነቱን እንደሚወስድ፤ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናንን በማስተባበር እና ችግሮች ወደተፈጠሩባቸው ቦታዎች በመሔድ ከአማኞች ጋራ አብረው ሰማዕትነት ለመቀበል እንደሚገደድ
የሚያስጠነቅቅ ነው፡፡
ምንጭ : ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ከመንግሥት ጋራ የሚደረገው ውይይት ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና የሚያረጋግጥ ሊኾን ይገባል፤ “ለቋሚ
ስጋታችን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ውል ላይ መደረስ አለበት”

• መግለጫውን ከውይይቱ በኋላ ለመስጠት ታስቦአል፤ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶች ይመደባሉ፤
***
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ከሚመራው
የመንግሥት ልኡክ ጋራ የሚያደርገው ውይይት፣ የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ቋሚ የጥቃት እና የተጽዕኖ ዒላማ እየኾነች ለምትገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቋሚ
የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት የሚደረስበት ሊኾን እንደሚገባው ተጠቆመ፡፡
ብሔርንና ቋንቋን ዐቢይ እና ቀዳሚ የማንነት መገለጫ ከማድረግ አልፎ በአመዛኙ የጠርዘኝነት ዝንባሌ የሚታይበት ያለፉት 27 ዓመታት የአገራችን የፖሊቲካ አስተሳሰብና ሥርዐት፣ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ምልክትና ተቋም ኾና የኖረችውን
ጥንታዊትና ታሪካዊት እናት ቤተ ክርስቲያን፣ የጥቃትና የተጽዕኖ ዒላማ ማድረጉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚገታ ባለመኾኑ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንግሥት ቋሚ የደኅንነት ዋስትና በሚሰጥበት ኹኔታ ላይ በግልጽ ሊነጋገር እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ ባለፉት ኹለት ቀናት ብቻ ለግለሰብ ድጋፍ በሚል በተለያዩ
የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተካሔዱ ሰልፎች፣ በቅጽበት የብሔርና የሃይማኖት መልክ ይዘው፣ ወገን ለይተው ምእመናንና ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዒላማ ያደረጉበት ኹኔታ እየተለመደ
መምጣቱ የደኅንነት ዋስትና ውሉ የግድ አስፈላጊ መኾኑን ያሳያል፤ ተብሏል፡፡
ካህናትንና ምእመናን በአሠቃቂ ኹኔታ በመግደል እና አብያተ ክርስቲያናትን በማቃጠል፣ ንብረታቸውን አውድሞና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን አሽመድምዶ ከቀዬአቸው በማፈናቀል እየተገለጸ
ያለው ጥቃትና ተጽዕኖ በመሠረቱ፣ ርእዮተ ዓለማዊ እና መዋቅራዊ መነሻ እንዳለው አፈጻጸሙ በግልጽ የሚያሳይ
በመኾኑ፣ ከመንግሥት የሚጠበቀው የደኅንነት ዋስትናም በዚያው ትይዩ፣ መዋቅራዊና ሥርዐታዊ እንጂ በቃላት ሽንገላና ባዶ ተስፋ ሊታለፍ እንደማይገባው ተገልጿል፡፡

መዋቅራዊ እና ሥርዓታዊ የደኅንነት ዋስትናው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የብሔርና የሃይማኖት አክራሪዎች ተከታታይና ቋሚ የጥቃት ዒላማ እየኾነች ያለችበትን
ሐቅ በነባራዊነት አምኖና ተቀብሎ ጥቃቱን ከማስቆም እንደሚነሣ አስተያየት ሰጪዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ይኸውም፣ ቅምጥ/ ግልጽ የደኅንነት ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በጋራ ለይቶና የጸጥታ ዕቅድ አውጥቶ የታሰበውን ጥቃት አስቀድሞ ያመክናል፤
ይከላከላል፤ አደጋ ሲደርስም በፍጥነት ደርሶ ጉዳትን ይቀንሳል፡፡

በዚህ ረገድ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን የሀገራዊ ሰላምና ደኅንነት ዋነኛ አጋር ለማድረግና በዘላቂነት አብሮ ለመሥራት
ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋራ ግልጽ ስምምነት ላይ መድረስ ይኖርበታል፤
ብለዋል፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ሌላው መዋቅራዊ እና ሥርዐታዊ የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጫ፣ የሰሞኑን ጨምሮ በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ሲፈጸም ሓላፊነታቸውን ያልተወጡ፣በቀጥታ ይኹን በተዘዋዋሪ ተባባሪ የኾኑ ባለሥልጣናትን በሕግ ተጠያቂ በማድረግ፣ ተጎጂዎችንም በተገቢው በመካስ ፍትሕን ማረጋገጥ ነው፡፡
ሦስተኛው እና መሠረታዊው ደግሞ፣ በኢሕአዴጋዊ ርእዮተ ዓለም እና ፕሮግራም መነሻነት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ማንነቷና አገራዊ ውለታዋ ተዘንግቶ፣ የአንድ ወገንና የጨቋኞች
አጋር ተደርጋ በትውልዱ ዘንድ የተሣለችበትን ያለፉት 27 ዓመታት ስሑት ፖሊቲካዊ ትርክቶች፣ ከመንግሥት የሥልጠና እና የትምህርት ሰነዶች እንዲታረሙ ማድረግ እንደኾነ
አብራርተዋል፡፡

ምልአተ ጉባኤው፣ ዛሬ ቀን 10፡00 ላይ ከባለሥልጣናቱ ጋራ ከሚያደርገው ውይይት ቀደም ብሎ፣ ከ17ቱ አጀንዳዎቹ መካከል በአስቸኳይነት የለያቸውን፣ የ2012 የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በጀት መርምሮ ያጸድቃል፤ በግንቦቱ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው የሠየመውን የሀገራዊ ሰላም እና አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ
ጥናት እና ሪፖርት ላይም ይነጋገራል፡፡
ከዚኹ ጋራ በተያያዘ፣ የጥቃት መከላከል እና የኮሚዩኒኬሽን ኀይለ ግብሮችን(በአጀንዳው ውስጥ በተቀመጠበት አገላለጽ፥ “የሕዝብ ግንኙነት እና የወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ”) የማቋቋም ጉዳይንም እንደሚያነሣ ይጠበቃል፡፡
ከግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ማግሥት ተቋቁሞ ሲንቀሳቀስ የቆየው የመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት አስተባባሪ ኮሚቴም፣ የፈጸማቸው ተግባራት በዐቢይ
ኮሚቴው ሪፖርት የተካካተ ሲኾን፣ የሀገራዊ ሰላም እና አንድነት ዐቢይ ኮሚቴው አካል ኾኖ የሚቀጥልበት ይኹንታ ከምልአተ ጉባኤው እንደሚሰጠው ተጠቁሟል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከባለሥልጣናቱ ጋራ ከተወያየና
ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶችን
ከመደበ በኋላ፣ ቀሪ አጀንዳዎችን በሌላ ጊዜ ተረጋግቶ ለማየት በመቅጠር መደበኛ ስብሰባውን በአጭሩ እንደሚያጠናቅቅ
ተነግሯል፡፡
ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ


ከሚራራልን ፍቅር ከሆነው
ዘላቂ ሰላም ከእግዚአብሔር ነው
ይህን እወቂ ይህን ተረጂ
በልብሽ ጉልበት ለርሱ ስገጂ

አዝ ❖ ❖ ❖
በሠይፍ ያልቃሉ ሠይፍ የሚያነሱ
የሚራራልን ሲፈርድ ንጉሱ
በቀል የርሡ ነው አይደለም ያንቺ
በጸጋው ታጥረሽ በጸሎት በርቺ

አዝ ❖ ❖ ❖
ይህ ውጣ ውረድ ይህጉስቁልናው
በእግዚአብሔር ነው መከራ ማብቂያው
ሰላም ይሁን ሲል ይሆናል ሰላም
ያሳየሽውን ፍቅር አይረሳም

አዝ ❖ ❖ ❖
ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሀገሬን
በየሔድኩበት መጠሪያ ስሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ፀሃይ
አሁን ይዘርጋ እጅህ ከሰማይ

አዝ ❖ ❖ ❖
እንድትፈራርስ ጠላት ሸምቋል
ብርቱዉን ጉልበት ከአፈር ደባልቋል
ይህን ግፍ አስብ ዘንበል በልላት
ካንተ በስተቀር መሔጃ የላት
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@And_Haymanot
ሰበር ዜና
Share
@And_Haymanot

የመንግሥት ልዑካን ቤተ ክርስቲያን ትራዳቸው ዘንድ ተማጸኑ

ዛሬ ዐርብ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ለማነጋገር ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
የመጡት የመንግሥት ባለሥልጣናት ቤተ ክርስቲያን ትራዳቸው ዘንድ ተማጽኖ አቅርበዋል፡፡ ወደ ጉባኤው የመጡት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ
መኮንን፣ የመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ፣ የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የፌድራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ናቸው፡፡
ለእነዚህ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አባቶች ኹለት
መሠረታዊ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸዋል፡፡
*አንደኛ ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ ነገ ይሻላል በማይባል ጥቃት ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህ ያላባራ ጥቃት ይቆም ዘንድ መንግሥት የሚሰጠው ዋስትና አለን?
*ኹለተኛ፡- ጥቃት አድራሾችን ለይቶ ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ያለው ቁርጠኝነት እስከምን ድረስ ነው? የሚሉ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች በተጨማሪ ብፁዓን አበው “አንዳንድ ወገኖች ቤተ ክርስቲያንን ሲላቸው በፊውዳል ስም፣ ሲላቸው በነፍጠኛ ስም፣ ሲላቸው በአንድ ጎሳ ስም እየፈረጁ ስሟን ሲያጠለሹ ታግሰናል፡፡ ግን ይህ አልበቃቸውም፡፡ ወደ አካላዊ ጥቃት ዘምተዋል፡፡ አሁን የምንጠይቃችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡
እርሱም ችግሩን ለመቆጣጠር አቅም አላችሁን? የሚል ነው፡፡ አቅም ከሌላችሁ አሁኑኑ ንገሩን፤ እየሞተ የሚቀጥል
አይኖርም፡፡” በማለት ፍርጥም ያለ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በአንጻሩ ከፍተኛ የምንግሥት ባለ ሥልጣናት አበውን በማመስገን ለጥያቄው መልስ ሰጥተዋል፡፡ በጥቅሉ አቅም አለን፣ እየተነሣ ያለውን አቧራ በአንድ ጀምበር ጸጥ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ ግን
መግደልን ይጨምራል፡፡ የመግደልን መንገድ ደግሞ የመጣንበት ስለኾነ አልፈለግነውም ነበር፡፡ ከእንግዲህ ግን
ትዕግስታችን ተሟጥጧል፡፡ የጎሰኝነት እና የሃይማኖት ጽንፈኝነት ከፍተኛ ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡ ነገራችን ሁሉ ሳቅ እና ሐዘን ኾኗል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ብዙ
ሥራ አጥ ወጣት አለን፡፡ ይህንን ወጣት ጽንፈኞቹ በቀላሉ እየዘወሩት ይገኛል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ተረዱን እርዱንም፡፡
እናንተ ወደ ተቃውሞ ከሔዳችሁ ማን ነው ከጎናችን የሚቆመው? እርዱን እርዱን ነው የምንለው፡፡ ለልጅ ኹለትም
ሦስትም ዕድል ይሰጣል፤ አሁንም ዕድል ስጡን፡፡ የተጠየቁትን ጥያቄዎች መሠረት አድርገን ርምጃ መውሰድ
እንጀምራለን፡፡ ለጠቅላይ ሚንስትሩም ነገሩን እናደርሳለን በማለት ተሰናብተዋል፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot