፩ ሃይማኖት
8.98K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
#ሰበር_ዜና


👉 ብዙ ሚሊዬኖች በስሩ ያሉት የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት በጽኑ አውግዟል።

@Meserete_Yared_Asasa

"ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ” ት. ኤርምያስ ፳፭፥፮

✞ ይሄ ቃዱስ ቃል የአምላካችን ከባድ ግሳጼ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው እግዚአብሔር አምላክ ሁለት ጊዜ ምድርን በታላቅ የቁጣ መቅሰፍት የመታትና የሰው ልጆችን በእሳትና በታላቅ የጥፋት ውሃ ያጠፋበት ዋና ምክንያት አስቀያሚ በሆነ ኃጢአት ነው፡፡ ይሄ ሰውን በእሳትና በውሃ እንዲጠፉ ምክንያት የኾነው አሁን በሀገራችን መነጋገሪያ እየሆነ ባለው ግብረ ሰዶም በመፈጸሙ ነው፡፡ ይሄ በሀገራችንም በሃይማኖታችንም ነውር የኾነው ድርጊት፣ ኃጢአት እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በብሉይ ኪዳንም፣ በሐዲስ ኪዳን ላይም ተደጋግሞ ተገልጿል፡፡ በኖኅ ዘመን በጥፋት ውሃ፣ በሎጥ ጊዜ ደግሞ በእሳትና በዲኚ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ቀጥቷል። በኦ.ዘፍ ፮ ፥፮ “እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥በልቡም አዘነ” ተብሎ ተጽፏል፡፡

✟ አሁን ደግሞ የእመቤታችን የአስራት ምድር ተብላ የምትጠራው ሀገራችን ለጉብኝት በሚል ምክንያት ግብረ ሰዶሞች ይህችን ቅድስት ሀገራችንን ከመጎብኘታቸው በላይ የቤተክርስቲያናችንን ቅዱስ ቦታዎች ላይም ከመሄድ አንቆጠብም ብለዋል፡፡ በሮሜ ምዕ. ፩ ፤፳፯፤ ላይ “እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው፤ እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። የሚለውን በተማርንበት ምድር በእኛ ጊዜና በእኛ ምድር ላይ አጨብጭበን አንቀበልም፡፡

✥ ይሄን የነውር ሥራ የዕለት ተግባራቸው የሆኑ ሰዎች ወደሀገራችን ሲመጡ በቀላሉ ከአንድም ሶስት ነገሮችን ይጥሳሉ፡፡
1ኛ ሕገ - ቤተክርስቲያናችንንና የፈጣሪ ትዕዛዝ፣
2ኛ. የሀገራችን ወንጀለኛ መቅጫ ህገ - መንግስት፣
3ኛ. የኢትዮጵያውያንን ባህል፣
የፈጣሪን ትዕዛዝ በማለፍ የሚመጣ ቁጣ ምን እንደኾነ ከላይ አይተናል፡፡ “ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ”ም ብሏል፡፡ እኛም በፈጣሪ የተወገዘውን ከሚያደርጉት ጋር በማበር፣ ዝም በማለት ፈጣሪን አናስቆጣው፡፡

በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 629፡- “መሠረት ግብረ ሶዶማዊነት በእስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ቅጣቱም ከ1 አመት በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ከባድ ሁኔታ እስሲያጋጥም ከ 10 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ያስቀጣል” ይላል፡፡ ይሄ አንቀጽ በህጉ ላይ እያለ እነሱን ወደሀገራችን እንዲገቡ መፍቀድና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ህዝቡንም ባህሉንም መናቅ ነው፡፡

☨ እኛ ኢትዮጵያውያን ከባህላችን አንጻር እንኳን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ይቅርና በተለመደው በህግ ባልተሳሰረ በሚፈፀም ግንኙነት ላይ ያለን ምልከታ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ወደ ሀገራችን ሊገቡ ያቆበቆቡ ሰዶማውያን ወደሀገራችን እንዲገቡ መፍቀድ የሀገራችንን ባህል መናቅ፤ ሀገራችን የምትመራበት ህግንም መናድ ነውና የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ እልባት ሊሰጥ ይገባል፡፡

የእኛም የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት አንድነት ተግባሩን በፅኑ የምንቃወምና የምናወግዝ መኾኑን እናሳውቃለን፡፡

✞ሀገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃት!✞✞✞

ሁልም #ሼር! #shareበማድረግ ይደግፍ።


@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
የማንቂያ ደውል🔔

የማንቂያ ደወሉ ጉባኤ ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2012ዓ.ም በገርጂ ጊዮርጊስ ያመሻል። ልብ በሉ የሰማዕታቱ አጽም ያረፈበት
ቤተክርስቲያን ነዉ። እንደተለመደዉ መምህር እስቻለው በመጀመርያው ክፍል ያገለግላል ከዛም ታላቁ መምህራችን መምህር ምህረተአብ በክፍል ሁለት ትምህርት አስደማሚዉን የማንቂያ ደዉል ይደወላል ። ለሰማዕታቱ ጧፍ በህብረት እናበራለን። የማንቂያ ደወሉ ጥምረት ዘማሪያን :መሳሪያ ተጫዋችና የተዋህዶ ወጣቶች በተሰጣቸዉ ጸጋ ያገለግላሉ ። የደብሩ ስብከተ ወንገል ከሰንበት ት/ቤት ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ዝግጅት አደርገዋል።11:00 ማንቂያዉን
ለመደወል የተቆረጠለት ሰአት ነዉ።
ታዲያ ከዚህ ጉባኤ ይቀራል? አይቀርም።

ይሄ መልእክት በተቻለ ፍጥነት #ሼር ይደረጋል፤

👉 ማክሰኞ ፡- ቀራንዮ መድኃኔዓለም
👉 ረቡዕ፡- ቦሌ መድኃኔዓለም
👉 ሐሙስ፡- ጉለሌ ሩፉኤል
👉 አርብ :- ናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot