Forwarded from መሠረተ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ዘአሣሣ
ባትወለድ ኖሮ……
መለኮትን ያህል - በእጅ እንደ መጨበጥ - በሆድ እንደ መወሰን
ምን ክብር ይገኛል - ምን ምጡቅ ልዕልና? - ምንስ ገላጭ ልሳን?
ባትወለድ ኖሮ - ብላቴናዋ ባትኖር - ያች የምስጢር ማህደር
ተራ ተዓምር ሁሉ - እንደ አምልኮት - በሆነብን ነበር፡፡
ባትወለድ ኖሮ - እሷን ተመልክተን - መመኪያ ባላልናት
በሔዋን ተስፋ ውስጥ - ብርሃንን አዝላ - ደምቃ ባላየናት
የተዘጋች ገነት - ቀድሞ እንዳጣናት - ርስታችን ባላልናት፡፡
አዳም ባልተጽናና - ደሙም ባላቆመ - ሲፈስ በኖረ
“ህይወቴ ነሽ” ብሎ - ሔዋንን ባልጠራት - ተስፋው ባልነበረ
የማግሰኞም እርሻ - ዘርን ባላስገኘ - ባዶውን በቀረ
ሁሉም ይቀር ነበር - ሰውም በውድቀቱ - እንተቸገረ
ባትወለድ ኖሮ - አሁን አይኖርም ነበር - ጥንት እንደ ነበረ፡፡
ትንቢትን ባላየን - ይወለዳል ብለው - ተስፋ ባልሰነቁ
“ክንድህን ከአርያም ላክ” - ብለው ባልተጽናኑ - ፊቱ ባልወደቁ
ዘርም ባልቀረልን - እንደ ተበተንን - ከቤት እንደ ወጣን
ባላወቅን እረኛ - ጋጣ እንደሌለን - ማደሪያ እንዳጣን
እንደ ከንቱ ፍጥረት - በምድር እንደሚቀር - እንደ ዱር ቀበሮ
ሰው በሆነ ነበር - ያች እንቁ ፍሬ - ባትወለድ ኖሮ፡፡
ምስራቃዊት መቅደስ - የታተመችን በር - ህዝቅኤል ባላየ
የሙሴ ሐመልማል - በነበልባሉ ’ሳት - ተዋህዶ ባልቆየ
ረዥሙ ተራራ - ለዳንኤል ባልታየ - ተስፋ ባልሰነቀ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም ጠፍቶ ነበር - ያኔ እንደ ወደቀ፡፡
ቴክታና ጴጥርቃ - (እ)ራዕይ ባላዩ - ህልም ባልታያቸው
ከጥጃ ጨረቃ - እንደምትወለድ - ባልተነገራቸው
ከጨረቃም ፀሃይ - ዓለምን ሲያበራ - ባልተመለከቱ
የጨለማ ዘመን - በዘለቀ ነበር - ልክ እንደበፊቱ፡፡
ሄርሜላና ማጣት - ሃናን ባልወለዷት - ተስፋም ባልቀረበ
ኢያቄም ባልመጣ - ከይሁዳ ነገድ - ድኅነት ባልታሰበ
ባልተነገራቸው - በስተ እርጅናቸው - ባላዩ' ደስታ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም መራር ነበር - በመጣፈ ጥፈንታ፡፡
መልአኩም ባልመጣ - ብስራቱን ባልሰማን - ቃል ስጋ ባልሆነ
ልደቱን ስቅለቱን - ትንሳኤውን ባልሰበክን - ሁሉ በባከነ
ባትወለድ ኖሮ - እመአምላክን ባናይ - ያችን የድኅነት በር
ምክንያት ፈጥረን ሞተን - መልሰን ለመዳን - ምክንያት ባጣን ነበር፡፡
(አክሊሉ ደበላ ሚያዝያ 30/2006ዓ.ም)
@Meserete_Yared_Asasa

ዘማሪ ዳግማዊ!
«ኣድሳለሁ ያለው ኣዳሹም ፈረሰ
በልብ ተሐድሶ #ዳግም ተመለሰ»
... እንኳን በሰላም ተመለስክ ዘማሪ ዳግማዊ! የተሐድሶን ኑፋቄ በዝማሬዎችን ትበቀል ዘንድ ያብቃህ። በአንዱ መመለስ ምክንያት ብዙዎች ደስ አለን። በቅርቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ፣ የዳግማዊ ይፋዊ ይቅርታና የተሐድሶ ሴራ ማጋለጥን እንጠብቃለን። በውስጥ ለጠየቃችሁን ሁሉ ከላይ ድብዳቤውንም እነሆ ብለናል፡ የበለጠውን እውነታ እንዲሁም ስለ አገልግሎቱ ነገር ዝርዝርሩን እንመለስበታለን።
@And_Haymanot

"ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም።"
ሉቃ 15፥24

ያከብርዋ
ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት/2
ወኩሉ ፍጥረት ዓሳት ወአናብርት/2/
እለውስተ ደይን ያእረፉ ባቲ
እስመ ባቲ አእረፈ እምኩሉ ግብሩ /2/
ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት /2/
ጻድቃን በገነት
ፍጥረታት በሙሉ አሳዎችና አንበሬዎች
በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ /2/
በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት/2
ወኩሉ ፍጥረት ዓሳት ወአናብርት/2/
እለውስተ ደይን ያእረፉ ባቲ
እስመ ባቲ አእረፈ እምኩሉ ግብሩ /2/
ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት /2/
ጻድቃን በገነት
ፍጥረታት በሙሉ አሳዎችና አንበሬዎች
በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ /2/
በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
❤ አቤት ፍቅር! ❤
🙏 አቤት መውደድ! 🙏
@And_Haymanot
ዓለምን ከነግሳግንሱ ቢፈጥረው ☞ ለእኛ፤
ነቢያትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
ሐዋርያትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
መላእክትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
አንድያ ልጁን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
መንፈሱን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
መጻሕፍትን በእግዚአብሔርኛ ሳይኾን በሰውኛ ቋንቋ ቢያስጽፍ
☞ለእኛ፤
መጻሕፍትን የሚተረጕሙ ሊቃውንትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
ቤተ ክርስቲያን ቢታነጽ ☞ ለእኛ፤
ሰባክያንን ቢልክ ☞ ለእኛ ነው፡፡
@And_Haymanot
🔴 ወንድሞቼ! እኅቶቼ! ታድያ የዚኽን ድንቅ አባት ፍቅር መግለጽ ይቻላል?
ታድያ የዚኽን ወዳጅ መውደድ እንዴት መግለጽ ይቻላል?
🙏 እባካችኁ ይኽን ከመሰለ ጌታ አንራቅ፡፡
🙏 እባካችኁ ይኽን ከመሰለ አፍቃሪ አንሽሽ፡፡
🌍 ዓለም ብትወደን ውሸቷን ነው፡፡
ዓለም ዛሬ ብትወደን ነገ ልታስለቅሰን ነው፡፡
🌍 ዓለም ዛሬ ብታከብረን ነገ ልታዋርደን ነው፡፡
🌍 ዓለም ዛሬ ብታለብሰን ነገ ልታራቁተን ነው፡፡
🌍 ዓለም ዛሬ ተኙ የምትለን ነገ እንቅልፍ ልታሳጣን ነው፡፡
@And_Haymanot
🔴 ወንድሞቼ! እኅቶቼ! የአባታችንን ጥሪማ ተመልከቱልኝ “ኑና እንዋቀስ” /ኢሳ.1፡18/፡፡ “እኔው ሳልኾን እናንተው ራሳችኁ ራሳችኁን ወቅሳችኁ ኑና እንታረቅ” እኮ ነው እያለን ያለው፡፡
እኛ ተጣልተነው ርሱ እንታረቅ ይላል፡፡
እርሱ ተበድሎ እርሱ ይክሳል፡፡
🙏 እባካችኁ ፍቅሩን እንረዳለት፡፡ ፍቅሩን እንድንረዳ እንኳን የሚፈልገው እኛ እንድንጠቀም ነው፡፡ ለሕይወት እንጂ ለሞት አልፈጠረንማ!!!
✞ አቤቱ! አንተን የሚያዩ ዓይኖች እንዴት ንዑዳን ክቡራን ናቸው?
🙏 እባካችኁ ንስሐ እንግባና ከወዳጃችን ጋር እንታረቅ!!!
🙏 እባካችኁ ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንቅረብና በሕይወት
እንኑር!!! እስኪ ፍቅሩን እንቅመሰው፡፡
Share

ደጅ ጠናሁ
@And_Haymanot
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞ የሐዲስ ኪዳን ካህናት ✞
@And_Haymanot
በመንፈሳዊ ልደት አምጠው እንዲወልዱና በጥምቀት በኩል
ለሚገኘው ዳግም ልደት ኃላፊነት የተጣለባቸው እነዚህ ካህናት
ናቸው፡፡ በካህናት አማካኝነት ክርስቶስን እንለብሳለን፤ [በጥምቀት] ከወልደ እግዚአብሔር ጋር አብረን እንቀበራለን፤
ለተቀደሰው ራሳችን (ለኢየሱስ ክርስቶስ) ሕዋሳትም (ብልቶችም) እንኾናለን፡፡ ስለዚህም ካህናት ከነገሥታትና
ከገዢዎች የበለጠ ሊፈ’ሩ ይገባቸዋል፡፡ ከሥጋ ወላጆች የበለጠም ሊከበሩ ይገባቸዋል፡፡ የሥጋ ወላጆቻችን ከደምና
ከሥጋ ፈቃድ የተነሣ የሚወልዱን ሲኾኑ ካህናት ግን እውነተኛ ነጻነትና ታላቅ ጸጋ ለኾነው ከእግዚአብሔር ለምናገኘው ልደት ሥልጣን ያላቸው ናቸውና፡፡
የብሉይ ኪዳን ካህናት ሰውነትን ከለምጽ የማንጻት ሥልጣን ነበራቸው፤ እንዲያውም የማንጻት ሥልጣን ሳይኾን የነጹ መኾን አለመኾናቸውን መመርመርና የነጻውን ነጽቷል ብሎ ማወጅ ብቻ ነበር፡፡ እንዲህም ኾኖ ግን ካህናት ምን ያህል ይከበሩ እንደ ነበር ከመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ይቻላል፡፡ የዘመነ ሐዲስ ካህናት ግን ሥልጣን የተቀበሉት በሥጋ ለምጽ ላይ ሳይኾን በነፍስ ለምጽ ላይ ነው፤ ከተመለከቱ በኋላ ንጹህ መኾኑን አለመኾኑን
ለመመርመር ሳይኾን በእርግጥ እና በፍጹም ለማንጻት ነው፡፡ ስለኾነም የዘመነ ሐዲስ ካህናትን ከሚነቅፉ ከዳታንና ከማኅበሩ የበለጠ እጅግ የተረገሙ ናቸው፤ ከእነርሱ የባሰ ቅጣትም የሚገባቸው ናቸው፡፡ ዳታንና ማኅበሩ ምንም እንኳን ያልተሰጣቸውን ክህነት ይገባናል ብለው ቢነሡም ቅሉ ክህነትን በተመለከተ ግን ከፍ ያለና የተከበረ አመለካከት ነበራቸው፡፡
ክህነቱን የፈለጉትም ለእርሱ ከነበራቸው ጉጉትና ፍላጎት የተነሣ ነበር፡፡ የዘመነ ሐዲስ ክህነት የሚንቁ ግን ሀብተ ክህነት
በሐዲስ ኪዳን ካለበት አማናዊ ደረጃ ከደረሰና ከበፊቱ በበለጠ የከበረ ከኾነ በኋላ በተቃራኒው መንገድ ኾኖ ሳለ ከእነ ዳታን የበለጠ ድፍረትን ያሳያሉ፡፡ የማይገባውን ክብር በመፈለግ
መኻከልና ይህን ታላቅ ክብር በማቃለል መኻከል ያለው የንቀት ልዩነት እኩል አይደለምና፡፡ ነገር ግን ማጣጣል ከማድነቅ የሚለየውን ያህል የዘመነ ሐዲስ ክህነትን ማቃለል በብሉይ
ኪዳን የማይገባውን ክብረ ክህነትን ከመመኘት ይልቃል፡፡ ታዲያ ይህን ያህል ታላቅ ክብር የምትንቅ ምን ዓይነት ጎስቋላ ነፍስ ትኖራለች? ሰይጣናዊ ዝንባሌ ያደረባት ካልኾነች በቀር እንዲህ
የምታደርግ ነፍስ ትኖራለች ብዬ በፍጹም አላስብም፡፡
@ዮሐንስ አፈወርቅ፥ በእንተ ክህነት፥ 3፥6
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ለኦርቶዶክሳዊያን
======= share ===========
ይህ የቢራ ፋብሪካ እኛ የምንፀልይበትን የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስን ስዕል እና ስም ላለፉት 96 አመታት በየመጠጥ ቤቱ ቆሻሻ ላይ አስጥሏል። ቢራዉን ባለመጠጣት ይህን አሳፋሪና አስነዋሪ ታሪክ ማስቆም የኛ የኦርቶዶክሳውያን ሀላፊነት ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ክርስቶስ ፍቅር የተሰዋ ሰማዕት እንጂ የመጠጥ ስም አይደለም!
ይህን መልዕክት ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን እንዲደርስ ሀሳቡን በማጋራት የድርሻችንን እንወጣ፣ ዘመቻው ድርጅቱ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስም እና ስዕል መጠቀም እስኪያቆም ይቀጥላል።

፩ ሃይማኖት
Photo
እንቃወማለን!!
ይህንን በተቀደሰች ምድራችን ያውም በመካነ ቅዱሳን ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናት ላይ ሊካሄድ
የታሰበውን የግብረ ሰዶማውያን ጉብኝትና ርኩስ ስራቸውን በይፋ እንቃወማለን
❝ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ
ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው
በላያቸው ነው።❞ ዘሌ 20:13
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot

የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም??
"ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' የሚል የድፍረት ቃል እየተናገሩ ነው፡ የቶቶ ባለቤት ዳን ዌር
የቶቶ አስጎብኚ ድርጅት መስራች እና ባለቤት ዳን ዌር ''በተፈጠረው ነገር በጣም አዝኛለሁ። ወደ ኢትዮጵያ
የምናደርገውን ጉዞ ግን አንሰርዝም'' ሲሉ ለቢቢሲ ገልጠዋል። ''የየትኛውም የሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው የሚያስፈራው ነገር ያለ አይመስለኝም። የማንንም ሃይማኖት ልንጋፋም ሆነ
የራሳችንን አስተሳሰብ በሰዎች ላይ ለመጫን አይደለም ወደ ኢትዮጵያ የምንሄደው። እንዳውም ባህሉን ለማየትና ለመረዳት እንዲሁም ለማድነቅ ነው የምንፈልገው።'' ጉብኝቱን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተመለከቱት ምላሽ በጣም እንዳሳዘናቸው የሚናገሩት ዳን፤ "የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲከታተለው
ማሳሰብ እፈልጋለሁ" ብለዋል። የአስጎብኚ ድርጅቱ ባለቤት በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንደማይሰርዙ አስረግጠው ተናግረዋል። ''ወደ ኢትዮጵያ እንሄዳለን። ነገር ግን አሁንም
ቢሆን ለደህንነታችን እንሰጋለን'' ይላሉ።
ዳን ጉዳዩን ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሚያሳውቁ፤ በተጨማሪም ስለ ጉብኝቱ ግዙፍ የዜና ተቋማት እንዲያውቁ እናደርጋለን ይላሉ።
''ወደ ኢትዮጵያ ስንሄድ አደጋ ቢደርስብን ዓለም በሙሉ ይመለከተዋል። በዚህም የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ እና ሃይማኖት መጥፎ ስም እንዳይሰጠው መጠንቀቅ አለባቸው።'' ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በጉዳዩ ላይ የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ከ120 በላይ የኦርቶዶክስ ማህበራት ስብስብ የሆነው ሰልስቱ ምእት የማህበራት ህብረት በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን በኢትዮጵያ ሊያደርጉ
ያሰቡትን ጉብኝት በማስመልከት የተቃውሞ ድምጹን ለማሰማት
ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም መግለጫ ለይ የማህበራት ህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት
ሊቀ ትጉሃን ደረጀ ነጋሽ ለቢቢሲ እንደገለፁት ''ቶቶ የሚባል አስጎብኚ ድርጅት በቅዱስ ላሊበላ እና ሌሎች መዳረሻዎች ላይ መጥተው ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፋለን የሚሉትን በመቃወም፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ የሃይማኖት አባቶች ለጉዳዩ
ትኩረት እንዲሰጡ እና ህዝቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ነው መግለጫውን መስጠት ያስፈለገን'' ብለዋል።
ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን የጉብኝት ፕሮግራም በማዘጋጀት የሚታወቀው ቶቶ ቱርስ በኢትዮጵያ ከአራት ወራት በኋላ ለ14 ቀናት የሚዘልቅ የጉብኝት መርኃ ግብር አውጥቶ ጎብኚዎችን
እየመዘገበ ይገኛል። በአንድ ሰው 7 ሺህ 900 የአሜሪካን ዶላር የሚጠየቅበት ይህ የጉብኝት ፕሮግራም በሁለት ሳምንት ቆይታው አርባ ምንጭ፣
ደቡብ ኦሞ፣ የጣና ገዳማት፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱምን እና ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ለማስጎብኘት መርሃ ግብር ቀርጿል።
ሊቀ ትጉሃን ደረጀ የማህበራት ህብረቱ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎቹ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የለባቸውም የተባለበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤ ''በሃገሪቱ ህግ ድርጊቱ ወንጀል ነው።
ከቀላል እስከ ከፍተኛ እስራት ያስቀጣል። ስለዚህ የኢትዮጵያን
ሕግ ተላልፎ መምጣት አይችሉም። ሁለተኛ ድርጊቱ በሃይማኖት
የተወገዘ ነው። በባህልም ጸያፍ ነው።'' ብለዋል። ''አርማቸውን ይዘው ላሊበላ ላይ እንገናኝ በማለት የዋጋ ተመን
አውጠተው መንቀሳቀሳቸው የድፍረት ድፍረት ነው'' ሲሉም አክለዋል።
ይህ "እኩይ ተግባር" ከሃገራችን መውጣት አለበት የሚሉት ሊቀ
ትጉሃን ደረጀ፤ ''ሕጉ ተሻሽሎ መጥበቅ አለበት። የግብረ-ገብ ትምህርት መሰጠት አለበት" ብለዋል፤ አክለውም ይህን ጉብኝት ተቃውመን አናቆምም።'' በማለት 'ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም'
የሚባል የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነትን የሚቃወም ከኦርቶዶክስ፣ እስልምና፣ ካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የተውጣጣ ሃገራዊ ማህበር እንደሚቋቋም ጨምረው ተናግረዋል።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ዝግጅት ክፍል ነው፡
***
መላው ኢትዮጲዮጲያውያን ይህንን ጥዩፍ ተግባር ከቃል ባለፈ
በተግባር የሚገለፅ ተቃውሞ ለማሰማት እንነሳ፡፡
ኢትዮጵያ ሐገረ እግዚአብሔር

❤1
«ምን እናድርግ?» (ሉቃ ፫፥፲፬)
@And_Haymanot
ልጆቼ ሆይ «ምን እናድርግ?» ብላችሁ ራሳችሁን ስትጠይቁ በመጽፍ ቅዱስ ላይ በመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ የተነገረውን ቃል አስቡ! ይህን ኃይለ ቃልም ታገኛላችሁ፦ «ጭፍሮችም ደግሞ፥
እኛደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ በማንምግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ» እንደተባሉ ልብ በሉ!።
ልጆቼ ሆይ፦ ምን እንደምታደርጉ ልንገራችሁ? ይህ እውነተኛና የታመነ ቃል ነው የምነግራችሁ! በማንም ላይ ግፍ አለመሥራት፣ በማንም ላይ በሐሰት አለመመስከርና አለመክሰስ፣በማንም ላይ ያልተገባ ጉቦና የተለየ ጥቅማ-ጥቅም አለመጠየቅ፣በማንም ላይ
በሥልጣንህ ተመክተህ ፍርድ አለማጓደል፣ በማንምላይ በፍቅረ
ንዋይ ተጠምደህ ራስህንም ሌሎች ሠዎችንም በገንዘብ አለመደለል፤ ለሀገርህና ከአንተ አገልግሎት ለሚጠብቅህ ሕዝብታማኝ መሆንን አለመዘንጋት፤ በላብህ ዋጋ ሕይወትህን
ማጣጣም እንዳለብህም ተረዳ፤ ግፍን፣ ተንኮል፣ ሸርን፣ አሻጥርን፣ ሤራን፣ምቀኝነትን፣ ከሕይወትህ አስወግድ፤ ትህትናን፣ ፍቅርን፣ የዋህነትን፣መልካምነትን፣ ሠናይ ምግባርን፣ አርቆ አሳቢነትን፣ ልበ ሠፊነትን፣ገርነትን፤ ገንዘብህ አድርግ።
ልጆቼ ሆይ፦ ምን እንደምታደርጉ ልንገራችሁ? ከትንሹ እስከትልቁ፣ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከሕግ አውጪ እስከ ሕግ
አርቃቂ፣ከወታደር እስከ ባለሥልጣናት ድረስ፤ ከቀራጮች እስከ ጭፍሮች፣አጠቃላይ ሕዝቡ ሁሉ ይሄ አማናዊ ቃል ለራሱ ገንዘብ ሊያደርግ ይገባል፤ ከላይ የተጠቀሱ እኒህን ነገሮች ስትፈፅሙ የመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ ቃል ሕይወታችሁን በሐሴት ያረሰርሰዋል፤ እናንተም«ምን እናድርግ?» ብላችሁ ለጠየቃችሁት
ጥያቄም የእግዚአብሔርምላሽ ይሄ ነው።

❗️ጅማ ዩኒቨርስቲ
@And_Haymanot
❗️ጅማ ዩኒቨርስቲ ጥንቃቄ ይደረግ!
ሰሞኑን ጅማ ዩኒቨርስቲ ነጠላ ለብሰው እንዲገቡ ያደረጋቸው ጉዳይ ቢኖር በበር ላይ ያሉት የጥበቃ አካላት የሌሎች እምነት ተከታይ ተማሪዎች እንደፈለጉ ለብሰው ሲገቡ እና ሲወጡ ለይተው መከልከል ስላልቻሉ እንጂ ከሴኔት እንዳልሆነ ተገልፆልን ነበር ፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ ከሆነ ነጠላ መልበስን ለይቶ ለመከልከል ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪው ወዳልተፈለገ ነገር ሊመራው ይችላል፡፡ የሚጎዳውም ከኦርቶዶክስ ወገን መሆኑም ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ጅማ ዩኒቨርስቲ ህጉን መለስ ብሎ ቢገመግምና እየደረሰ ያለውን ጫና አይኑን ገልጦ ቢመለከት መልካም ነው፡፡
ማሳሰቢያ:- ኦርቶዶክስ ተማሪዎች ሁሉንም ነገር በስርዓቱና በህግ አግባብ ጠይቁ ይህንን ምክንያት አድርገው ጠብ ሊጭሩ የሚሹ አሉና ነው፡፡
@And_Haymanot
@Ahati_Haymanot ያግኙን

#ሰበር_ዜና
👉 ብዙ ሚሊዬኖች በስሩ ያሉት የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት በጽኑ አውግዟል።
@Meserete_Yared_Asasa
"ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ” ት. ኤርምያስ ፳፭፥፮
✞ ይሄ ቃዱስ ቃል የአምላካችን ከባድ ግሳጼ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው እግዚአብሔር አምላክ ሁለት ጊዜ ምድርን በታላቅ የቁጣ መቅሰፍት የመታትና የሰው ልጆችን በእሳትና በታላቅ የጥፋት ውሃ ያጠፋበት ዋና ምክንያት አስቀያሚ በሆነ ኃጢአት ነው፡፡ ይሄ ሰውን በእሳትና በውሃ እንዲጠፉ ምክንያት የኾነው አሁን በሀገራችን መነጋገሪያ እየሆነ ባለው ግብረ ሰዶም በመፈጸሙ ነው፡፡ ይሄ በሀገራችንም በሃይማኖታችንም ነውር የኾነው ድርጊት፣ ኃጢአት እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በብሉይ ኪዳንም፣ በሐዲስ ኪዳን ላይም ተደጋግሞ ተገልጿል፡፡ በኖኅ ዘመን በጥፋት ውሃ፣ በሎጥ ጊዜ ደግሞ በእሳትና በዲኚ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ቀጥቷል። በኦ.ዘፍ ፮ ፥፮ “እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥በልቡም አዘነ” ተብሎ ተጽፏል፡፡
✟ አሁን ደግሞ የእመቤታችን የአስራት ምድር ተብላ የምትጠራው ሀገራችን ለጉብኝት በሚል ምክንያት ግብረ ሰዶሞች ይህችን ቅድስት ሀገራችንን ከመጎብኘታቸው በላይ የቤተክርስቲያናችንን ቅዱስ ቦታዎች ላይም ከመሄድ አንቆጠብም ብለዋል፡፡ በሮሜ ምዕ. ፩ ፤፳፯፤ ላይ “እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው፤ እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። የሚለውን በተማርንበት ምድር በእኛ ጊዜና በእኛ ምድር ላይ አጨብጭበን አንቀበልም፡፡
✥ ይሄን የነውር ሥራ የዕለት ተግባራቸው የሆኑ ሰዎች ወደሀገራችን ሲመጡ በቀላሉ ከአንድም ሶስት ነገሮችን ይጥሳሉ፡፡
1ኛ ሕገ - ቤተክርስቲያናችንንና የፈጣሪ ትዕዛዝ፣
2ኛ. የሀገራችን ወንጀለኛ መቅጫ ህገ - መንግስት፣
3ኛ. የኢትዮጵያውያንን ባህል፣
የፈጣሪን ትዕዛዝ በማለፍ የሚመጣ ቁጣ ምን እንደኾነ ከላይ አይተናል፡፡ “ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ”ም ብሏል፡፡ እኛም በፈጣሪ የተወገዘውን ከሚያደርጉት ጋር በማበር፣ ዝም በማለት ፈጣሪን አናስቆጣው፡፡
✝ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 629፡- “መሠረት ግብረ ሶዶማዊነት በእስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ቅጣቱም ከ1 አመት በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ከባድ ሁኔታ እስሲያጋጥም ከ 10 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ያስቀጣል” ይላል፡፡ ይሄ አንቀጽ በህጉ ላይ እያለ እነሱን ወደሀገራችን እንዲገቡ መፍቀድና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ህዝቡንም ባህሉንም መናቅ ነው፡፡
☨ እኛ ኢትዮጵያውያን ከባህላችን አንጻር እንኳን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ይቅርና በተለመደው በህግ ባልተሳሰረ በሚፈፀም ግንኙነት ላይ ያለን ምልከታ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ወደ ሀገራችን ሊገቡ ያቆበቆቡ ሰዶማውያን ወደሀገራችን እንዲገቡ መፍቀድ የሀገራችንን ባህል መናቅ፤ ሀገራችን የምትመራበት ህግንም መናድ ነውና የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ እልባት ሊሰጥ ይገባል፡፡
✔ የእኛም የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት አንድነት ተግባሩን በፅኑ የምንቃወምና የምናወግዝ መኾኑን እናሳውቃለን፡፡
✞ሀገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃት!✞✞✞
ሁልም #ሼር! #shareበማድረግ ይደግፍ።