፩ ሃይማኖት
8.94K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
"ጾም እና አሳ "

@And_Haymanot
አሳን በጾም ለምን አንበላም? አሳን በተመለከተ ብዙ ግዜ ጥያቄ ይነሳል፤ በፆም አሳ ለምን አንበላም? ጌታ ለሐዋርያቱ አሳን አበርክቶ ሰቷቸዋል፤
ሐዋርያቱም አሳ በልተዋል፤ ደግሞም እኮ በድሮ ግዜ አሳ ይበላ ነበር ይህ አሁን የመጣ ታሪክ ነው ይሉናል ለምን አሳን በጾም አንበላም ብለው ብዙ ግዜ ይጠይቁናል። ለመሆኑ አሳን በጾም ለምን አንበላም?
ሁለተኛ የሚያነሱት ሀሳብ አሳ ደም የለውም ከተራክቦ ነፃ የሆነ እንስሳ ነው ስለዚህ በፆም ወቅት ይበላል ይላሉ።
እውነታው ግን ይሄ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጾምበት ወቅት ሐዋሪያት አይጾሙም ነበር። በእምነታቸውም መሉ አልነበሩም ሐዋሪያት ለመጀመሪያ ጊዜ ጾምን የጾሙት ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ በአረገ
ጊዜ በተነሳ በ40ቀን በአረገ በ10 ቀን ጰራቂለጦስ መንፈስቅዱስ ለሁሉም ሐዋሪያት ከላከላቸው በኋላ ወደ ዓለም ሂዳችሁ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀመዝሙርቴ
አድርጓቸው ብሎ ሲያዛቸው ለአገልግሎት ከመሰመራታችን
ስራችን የታቀና ይሆን ዘንድ እንፁም ብለው ለአንድ ወር ያክል ፆሙ የሐዋሪያት ፆም ብለን ከበዓለ ሀምሳ በኋላ የምንፆመው ፆም ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳ በፆም ወቅት
እንደማይበላ ሁሌም ታስተምራለች ከዚህ በፊትም ዛሬም ወደ ፊትም ታስተምራለች "ጅሮ ያለው" ይስማ እንዲል ቅዱስ
ወንጌል ። ምዕመናን በፆም ወቅት እኮ ይሄ ይበላል ይሄ አይበላም የምንለበት ወቅት አይደለም። ፆም የስጋ ፍላጎታችንን ለነፍስ የምናስገዛበት ወቅት ነው። አሳ ከፍተኛ ፕሮቲን እንዳለው የማይካድ ሀቅ ነው ታዲያ ከፍተኛ ፕሮቲን እንዳለው ካውቅን በፆም ወቅት ከበላነው ምኑን ፆምነው ስጋችን እየደለብነው
ነፍሳችን እየከሳች ነው። ጾም እኮ ጊዚያዊ የሆነወን ስጋን ዘለዓለማዊ ለሆነችውለነፍስ ማስገዛት ነው።

ኢትብልሁ ሥጋ ዘእንበለ አሳ ይለናል በቀኖና ቤ/ተ/ክ ይህም ሥጋ አትብሉ አሳን ጭምር ማለት ነው።ሌሎች ግን ሥጋ አትብሉ ከአሳ በቀር ብለው ተርጉመውታል ይህ ግን ልክ
አይደለም። ዘእንበለ የሚለው ግዕዝ ጭምር ወይም በቀር ተብሎ ይተረጎማል። ምሳሌ እናቅርብ፦ “እግዚአብሔር ፈጠረ ኩሉ አለም ዘእንበለ ትል” ሲል እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ፈጠረ ትልን ጭምር ይባላል እንጂ ከትል በቀር አይባልም። ስለዚህም
አሳን ጭምር አትብሉ ማለት ይሆናል ማለት ነው።
318ቱ ርቱሃነ ሐይማኖት አበው አባቶቻችን በጾም ክርክር ቢነሳ ለጾም አድሉ ከመብል አለመብላት እጅግ ይሻላልና ብለው አልፈዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ በዳግም ምፅአት ሲመጣ ለፍርድ የምትቆመው ስጋችን ሳይሆን ነፍሳችን ናት። ስጋችንን ለነፍሳችን አስገዝተን በቀኙ ቁመን ተስፋ የምናደርጋትን
መንግስተ ሰማይትን እንድንወርስ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃዱ
ይሁን
✞ፆሙን የፍቅር የበረከት የረድኤት ያድርግልን✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot
"ለኦርቶድክሳውያን መልዕክት!"

@And_Haymanot

ይሄ የህዝብና ቤት ቆጠራን አስመልክቶ ብጽዕ አቡነ አብርሃም ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ያስተላለፉት መልዕክት ነው። ወገኖቻችንንም በማሳወቅ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታችን ነው!!

👉 "ከፊታችን የሕዝብና ቤት ቆጠራ አለ፡፡ አደራ እምነትን/ ሃይማኖትን በተመለከተ ስትሞሉ ክርስቲያን ብቻ እንዳትሉ፤ ብዙ አይነት ክርስቲያን አለ፡፡ መሙላት ያለባችሁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ / ክርስቲያን በሚል ይሁን፡፡ ይህንንም ለሌሎችም አድርሱ…" ብፁዕ አቡነ አብረሃም የባ/ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ።


@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቃል …ብቻ ሲናገር የሞተ ይነሳል
ቃል… ብቻ ሲናገር ድውኝ ይፈወሳል
ቃል… ብቻ ሲናገር የእውር አይን ይበራል
ቃል… ብቻ ሲናገር ለምፃሙ ይነፃል
ቃል …ብቻ ሲናገር ንፋሱ ፀጥ ይላል
ቃል… ብቻ ሲናገር ባህር ይከፈላል
የድንግል ማርያም ልጅ ክብሩ ይስፋ።
…አይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና
ይገበዋል ክብርና ምስጋና።
ማዳንህን የሚወዱ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ
【መዝሙር 89:14】
አሜን ክብር ለድንግል ማርያም ልጅ ለክርስቶስ ኢየሱስ ይሁን።
※ እግዚአብሔር ታላቅ ነው
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞በጌቴ ሴማኔ✞

በጌቴ ሴማኔ፣ በአትክልቱ ቦታ(2)
ለእኛ ሲል ጌታችን፣ በዓለም ተንገላታ(2)

አዳምና ሔዋን፣ ባጠፉት ጥፋት(2)
እኛም ነበረብን፣ የዘላለም ሞት(2)
መስቀል ተሸክሞ፣ ሲወጣ ተራራ(2)
ይገርፉት ነበረ፣ ሁሉም በየተራ(2)
ድንግል አልቻለችም፣ እንባዋን ልትገታ(2)
እያየች በመስቀል፣ ልጇ ሲንገላታ(2)
በአምላክነቱ፣ ሳይፈርድባቸው(2)
እንዲ ሲል ፀለየ፣ አባት ሆይ ማራቸው(2)
በረቂቅ ሥልጣኑ፣ ሁሉን የፈጠረ(2)
በሰዎች ተገርፎ፣ ሞተ ተቀበረ(2)
ፍቅሩን የገለጸው፣ ተወልዶ በስጋ(2)
ኢየሱስ ጌታ ነው፣ አልፋና ኦሜጋ(2)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቅድሰት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ)

@And_Haymanot

ቅድሰት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡
‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ክቡር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡ የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ቅዱስ›› የሚለው ቃል ለሰዎች፡ ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ፡ ለዕለታት ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡
እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም ይህንን ሲያስተምረን ነው፡፡ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡
ብርሃን ከጨለማ ጽድቅ ከኃጢአት ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና›› ያለንም ለዚህ ነው፡፡ /1ተሰ 4÷7/ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች እንዲህ ገልጾላቸዋል ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሰማያዊ ሥፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ብሎ ካመሰገነ በኋላ ‹‹ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳን ንጹሐንና ያለነውር በፍቅር ያደርገን ዘንድ ለእርሱ መረጠን›› ኤፌ 1፡3-4 አስቀድሞ ስለወደደንና ስላከበረንም ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጅቶ በእጆቹ ካበጀን በኋላ የሥነ ፍጥረት ዘውድ አድርጎ በገነት አኖረን ፡፡( ዘፍ 1፡26፤መዝ 8፡1)
የቀደመው አዳም አታድርግ የተባለውን በማድረጉ በንዝህላልነትና በስንፍና በከይሲ ዲያብሎስም ምክር ተዋረደ፡፡ በሞተ ሥጋ ላይም ሞተ ነፍስ ፤በርዕደተ መቃብር ላይ ርዕደተ ሲኦል ተፈረደበት፡ በባሕርዩ ሞት ገባበት፡ ተዳደፈ፡፡ ክፉ ፍትወታት የሚያጠቁትና የሚያሸንፉት የዲያብሎስና የኃጢአት ባርያ ሆነ፡፡ በማይለወጥ ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ግን ጠፍተን እንድንቀር አልተወንም፡፡ በሰጠን ተስፋ፡በተቆጠረው ሱባኤና በተነገረው ትንቢት መሰረት ዘመኑ ሲደርስ በተዋህዶ ሰው ሆነ፤ የተዋረደ ሥጋችንን አከበረ፡፡ በከበረ ደሙ ዋጀን፤ ከኃጢአታችን አጠበን፡፡ በእርሱ ምክንያት የእግዚአብሔር ልጆች ተባልን ፡፡ጌታችንና መድኃኒታችን ሰው የሆነውና ለመዳናችን የሆነውን ዋጋ ሁሉ የከፈለው ለእኛ ያለውን ፍቅርና ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ለእኛ ለማሳየት ነው፡፡ ‹‹ ነገር ግን የኃጢአትን ሥራ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለውን አሮጌውን ሰውነታችን እንደሆነ ይህን እናውቃለን ›› የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ (ሮሜ 6፡6) እኛን ወደ ቀደመ ክብራችን ለመመለስ የተከፈለውም ዋጋ ታላቅ ከሆነው የጋብቻ ምስጢር ጋር በማያያዝ እንዲህ ገልፆታል ‹‹ ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርሰቲያን ራስዋ አዳኝዋም እንደሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና … ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ራሱንም ስለእርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ፡፡ በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳትና ያነጻት ዘንድ የነጻችና የተቀደሰች ትሆን ዘንድ እንጂ በላይዋ እድፈት ወይም ርኩሰት እንዳይገኝባት ቤተ ክስቲያኑን ለእርሱ የከበረች ያደርጋት ዘንድ…›› ኤፌ 5፡23-28 ስለዚህ ጌታችን በደሙ ኃጢአታችንን እንደ ቸርነቱ ይቅር ብሎናል፡፡ኤፌ 1፡7 ከእንግዲህ የራሳችን አይደለንም፡፡ በሰውነታችንም ኃጢአትና ዐመፃን ልናደርግበት አይገባም፡፡‹‹በዚህ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አታንግሷት፤ ለምኞቱ እሺ አትበሉት፡፡ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጉ እንጂ ሰውነታችሁን ለኃጢአት የዐመፅ የጦር መሣሪያ አታድርጉት፤ ሰውነታችሁንም ለእግዚአብሔር የጽድቅ የጦር መሣሪያ አድርጉ››ተብለናል፡፡ (ሮሜ6፡12-13)
የተወደዳችሁ ምዕመናን እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚቀበለውን ህይወት ለመኖር አንፈልጋለን ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ብንመላለስ ነው? መልሱን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮቱ ከንቱ ነው፡፡ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ወላጆች የሌሉአቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በችግራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ ርኩሰት ሰውነትን መጠበቅ ነው፡፡›› በማለት ይመልስልናል( ያዕ 1፡26-27)፡፡ በክርስቶስ ደም የተቀደሰና የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችንን በዓለም ከሚገኝ ርኩሰት መጠበቅ የሰማያዊ ርስት ወራሾች ያደርገናል፡፡ በዓለም የሚገኘውን ርኩሰትም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሥጋ ሥራ›› በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹እርሱም ዝሙት፣ርኩሰት፣መዳራት፣ጣዖት ማምለክ፣ሥራይ ማድረግ፣ መጣላት፣ ኩራት፣ የምንዝር ጌጥ፣ ቅናት፣ ቁጣ፣ ጥርጥር፣ ፉክክር፣ምቀኝነት፣ መጋደል፣ ስካር ፣ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው፡፡›› እነዚህን የሚያደርጉ ሰዎችም ከመንግስተ እግዚአብሔር በአፍአ ወይም በውጭ እንደሚቀሩ ሲያስረዳ ‹‹አስቀድሜ እንደነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም›› ብሏል ( ገላ5፡19)።
በሕይወታችን ሁሉ የምግባርና የሃይማኖት ፍሬ አፍርተን መገኘት ለቅድስና የጠራንን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ እነዚህንም ነገሮች ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የመንፈስ ፍሬዎች ›› ብሏቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ምጽዋት፣ ቸርነት፣ እምነት፣ ገርነት ንጽሕና›› ናቸው፡፡ ገላ 5፡22 እግዚአብሔር ማደርያው ይሆን ዘንድ የመረጠውን ሰውነታችንን እርሱ የሚከብርበትን ሥራ ልናደርግበት ያስፈልጋል፡፡ ‹‹በሕይወት የሚኖሩትም ስለ እነርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞተውና ለተነሣውም እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው የሚኖሩ እንዳይሆኑ እርሱ ስለሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ›› እንደተባለ በሕይወታችን ሁሉ ፋቃዱን በመመርመርና በመፈጸም በቅድስና ልንኖር ይገባናል፡፡ 2ቆሮ 5፡15 ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣በማኅበራዊ ኑሯችን፣ በምንበላው ምግብ፣ በምንለብሰው ልብስ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን
በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል(ዕብ 12፡1)። ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@And_Haymanot
@And_Haymanot
ምኩራብ ሙሉ ንባቡን ለማንበብ
👉 https://tttttt.me/And_Haymanot/1313
Share Share
@And_Haymanot
** ምኩራብ ***

@And_Haymanot

በዓብይ ፆም ከ<<ቅድስት>>ቀጥሎ ያለው የእሁድ ሰንበትና የተያያዘው ሳምንት << ምኩራብ >>ይባላል።<<ቤተ
መቅደስ>>ወይም ክርስትናን ከእግዚአብሔር የተቀበሉ ወገኖች
ተሰብስበው ወደ ፈጣሪያቸው የሚፀልዩበትና በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ለመላው የሰው ዘር የተሰጡትን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋዎች የሚያገኙበት የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚቀበሉበት ቦታ <<ቤተ ክርስቲያን>> እንደሚባል ማለት ነው።
በህገ ኦሪቱ እምነት ጸንተው የቀጠሉት አይሁድ ዛሬም የጸሎት ቦታቸውን << ምኩራብ >>እያሉ ይጠሩታል።
የዚህ ስያሜ ሚስጢር እንደሌሎቹ ሁሉ ስፋትና ጥልቀት አለው። ይኸውም እግዚአብሔር አብ እውነተኛና የተቀደሰ ማደሪያው ይሆን ዘንድ ጥንቱንም በመለኮታዊ ቸርነቱና ጥበቡ የሠራው
ኋላም በመጨረሻ ዘመን በልጁ መስዋዕትነትና የምሕረት ቃልኪዳን ለሥርየት አብቅቶና በትንሳኤ ሕይወት አድሶ ለዘለዓለማዊ ህልውና ያዘጋጀው <<ቤት>> ወይም <<ሕንፃ>>
በፍጡር እጅና በተፈጥሮ ቁሳቁሶች የተሰራውን ሳይሆንእርሱ በአርአያውና በመልኩ የፈጠረው ራሱ <<ሰው>>መሆኑ ተረጋግጦ የሚታወስበት የሚነገርበትና የሚታወቅበት ሰሞን ከዚች ዕለተ እሁድ ጀምሮ ባለው ሳምንት በመሆኑ ነው።
1ኛቆሮ.3፥16፣ዘፍ.1፥26 ይህንም እውነታ ደቀ መዛሙርቱ የሆኑት ሐዋርያት ሳይቀሩ የተረዱትና የተገነዘቡት መምህራቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመስቀል መከራ ሞቶ ከተነሣ መንፈስ ቅዱስም ከወረደላቸውና ካደረባቸው በኋላ መሆኑን በዕለቱ የሚዘመረው፤የሚሰበከውና
የሚነበበው የነበያቱ ትንቢትና የአዲስ ኪዳኑ ምስራች እንዲህ በሚሉ ቃላት እያብራሩ ያመለክታሉ፦ <<እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልአኒ ትእይርቶሙ ለእለ ይትዔብሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻእክዋ በጾም ለነፍስየ።>> ማለትም
<<የቤትህ ቅናት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ
ወድቋልና ሰውነቴን በጾም ቀጣኋት።>>ዮሐ.2፥16
ደግሞም የአይሁድ የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ በሙክራብም
ላሙን፣በጉን ርግቡን የሚሸጡትንም የሚገዙትንም ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ ከገመድ የተሰራ አለንጋን አበጀ። በጉን ላሙንም ሁሉንም ከሙኩራብ አስወጣ። የለዋጮችንም ወርቅ
በተነ፤መደርደሪያቸውንም አፈረሰ። የርግብ ሻጮችንም ወንበር ገለበጠ። ርግብ ሻጮችንም ይህን ከዚህ አውጡ ወዲያ በሉ የአባቴን ቤት የገበያ ቦታ አታድርጉት አላቸው።ማቴ.21፥12
ደቀ መዛሙርቱም <<የቤትህ ቅናት በላኝ>> የሚል ቃል ተጽፎ እንዳለ አስታወሱ። አይሁድም መልሰው ለዚህ ድርጊትህ ምን ምልክትን ታሳያለህ አሉት።ጌታችንም ኢየሱስም ይህን ቤተ
መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛውም ቀን አነሳዋለው ብሎ መለሰላቸው። አይሁድም ይህን ቤተ መቅደስ በአርባ ስድስት ዓመታት ተሠራ አንተስ በሦስት ቀኖች ውስጥ ታነሳዋለህን አሉት። እርሱ ግን<<ቤት>>ስለተባለው ስለሰውነቱ ቤተ መቅደስ ነገራቸው።

ከሙታን በተነሳ ጊዜም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንደነገራቸው አሰቡ በመጻሕፍት ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በነገራቸው ነገርም አመኑ። ዮሐ.2፥19-23 ታላቅ ምሥጢራዊ መልዕክት ያለውን ይህን የአምላክ ቃል
ለማጠናከር ተያይዘው ከሚጠቀሱት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃላት መካከል እንዲህ የሚሉት ይገኛሉ።
<<አንትሙሰ ሕንፃ እግዚአብሔር አንትሙ!...ኢተአምሩኑ ከመ
ታቦቱ ለ እግዚአብሔር አንትሙ ወመንፈሰ እግዚአብሔር ኅዱር
ላዕሌክሙ። >>ማለትም << የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ...እናንተ የእግዚአብሔር ታቦቱ ቤተ መቅደሱም
እንደሆናችሁ የእግዚአብሔር መንፈስም አድሮባችሁ እንደሚኖር አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ያውም እናንተ ናችሁ።1ኛ ቆሮ.1፥16 ወይስ
ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው
የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን?... የእግዚአብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት የሚያኖር ማን ነው? እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና።>> << ምኩራብ >> በተባለው በዚህ እለተ እሁድና ተያይዞ ባለው
ሳምንት ውስጥ የእነዚህ ምስጢራውያት ቃላት ማጠቃለያ ፍቺ ተብራርቶና ተስፋፍቶ ይነገርበታል። ሰው የሆነውን አምላክ እንዲያ እንደ እሳት ያቃጠለው ቅንዓት የተነሳሳበት የሰዎች እጅ በሠራውና<< የእግዚአብሔር ቤተ
መቅደስ >>ተብሎ የርኩሰት ተግባር የተፈፀመበት በሚዘመርበት ሕንፃ ውስጥ ሲካሄድ ባየው አሳዛኝ ሁኔታ አለመሆኑ ይግለጽበታል።
ነገር ግን ራሱ እግዚአብሔር የዘለዓለም ማደሪያው ይሆን ዘንድ በመልኩ ፈጥሮ ያነፀው ሰብአዊው አካል የክፋት መንፈስ
መፈንጫና መጫወቻ ሆኖ መኖሩን በማወቁ መሆኑ ይነገራል። እንዲሁም ከገበያ የርኩሰት መደብርነት አጥርቶ በቅድስናው ያነፃው ይን ሰው የሠራውንና የሚያፈርሰውን በድን ህንፃ ሳይሆን፤ራሱ የለበሰውን የሰውነት አካል የመሰለውን የሰውን ሁሉ ሕያው ልቡና የመሆኑ ምሥራች ይታወጅበታል።
ለዚህ የእግዚአብሔር እውነት ቅዱስ እስጢፋኖስ <<ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት እኔም በሦስተኛው ቀን አነሳዋለው።>> ብሎ የተናገረውን የራሱን ቃል ራሱ የፈፀመውን ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን በመምሰል የመጀመሪያው መስካሪ ሆኖ በሰማዕትነት
ተሰውቶበታል። ይህም <<ሰማይ ዙፋኔ ነው።ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት።ለእኔ ምን አይነት ቤትን ትሰራላችሁ ይላል ጌታ ወይስ የማርፍበት ሥፍራ ምንድን ነው?ይህንስ ሁሉ እጄ የሰራችው
አይደለምን?እንዳለ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።>> ሲል ይኸው ሰማዕት የነብዩን እየጠቀሰ በተናገረው ደግሞም ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ እምላክ እርሱ የሰማይና
የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም። እርሱ ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም። በሚለው በሐዋርያው ቃል ተረጋግጧል።ዮሐ.7፥47
የሰንበት ረድኤትና በረከት ይደርብን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ይቆየን።
ምንጭ፦የኢየሱስ ክርስቶስ ጾምና ስቃዩ ከዘወረደ እስከ ጰራቅሊጦስ ከሚለው መጽሐፍ
አዘጋጅ፦ ሊቀ ኅሩያን የማነብርሃን ገበየው
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ከፊታችን የሕዝብና ቤት🏘 ቆጠራ አለ፡፡ አደራ እምነትን/ሐይማኖትን በተመለከተ ስትሞሉ ክርስቲያን ብቻ እንዳትሉ፤ ብዙ አይነት ክርስቲያን አለ፡፡

መሙላት ያለባችሁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ / ክርስቲያን በሚል ይሁን፡፡ ይህንንም ለሌሎችም አድርሱ…
👉"ብፁዕ አቡነ አብረሃም
Share
@And_Haymanot
"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡
ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል፡፡ እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት
ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
☞~በኢያሪኮ ከኤልሳዕ ምንጭ ዋናውን መንገድ ወደ ቀኝ በመተው በግራ በኩል ባለው ጐዳና በመጓዝ ቆሮንቶስ ተራራ ሥር ተራራውን በእግር ተጉዘው ያገኙታል። ይህም ጌታችን መድኅን አለም ክርስቶስ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት የጾመበት ሥፍራ #ገዳመ_ቆሮንቶስ ነው።

☞~በእዚህ ላይ ሆኖ የኢያሪኮን ከተማ ልምላሜ፣ የዮርዳኖስን ወንዝ ሸለቆ፣ የአሞን ተራራ የተባለውን አርቆ አሻግሮ ለማየት ይቻላል። ጌታ በቆሮንቶስ ተራራ የተፈተነበትን በእግረ ሥጋ ረግጦ፣ በዓይን ዓይቶ ምስክር ለመሆን እንዲያበቃን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሐ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር


... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሐ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሐ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን?
የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡
አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡
ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሐ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው?
ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡
እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሐ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡

"ሕማማት" ከተሰኘው ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ የተወሰደ



✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
ከቅዱስ ያሬድ መዝሙር


ለቤተክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ።
ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው።
ለርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተትን የቻለ።
የበደለውም በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ።
አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ።

@And_Haymanot