፩ ሃይማኖት
8.94K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ተዋህዶ እና ቅብዐት

#ፍኖተ_ጽድቅ_ዘተዋሕዶ
በተዋሕዶ እና በቅብዐት መካከል ስላለው ሰፊ ልዩነት ሁሉም ያውቅ ይረዳ ዘንድ ሁሉም በየሞባይሉ ሊጭነው እና ሊያነበው የሚችለው መተግበሪያ በወንድማችን በዲ.ን ጌታሁን አማረ
ተዘጋጅቶ ቀረበልን፡፡ ይህን መተግበሪያ ለሠራልኝ ወንድሜ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው፡፡
ይህ መተግበሪያ ደብረ አሚንን የሚተካ አይደለም፡፡ መሠረታዊ የሆኑ ልዩነቶቻችንን ከሦስቱ የቅባት መጻሕፍት ሀሳብ በመነሣት የሚተነትን መተግበሪያ ነው፡፡ የትም ሆነው አውርደው ሊጭኑት
የሚችል ሲሆን መተግበሪያውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ግን 20 ብር መክፈልና የመክፈቻ የምስጢር ኮድ መቀበል ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ዝቅተኛ ዋጋ መተግበሪያውን ያቀረብነው
ሁሉም ሰው እንዲያነበው በማሰብና ከዚሁ በሚገኘው ገቢም ወደፊት ለምሠራቸው ሥራዎች የማንንም እርዳታ ላለመጠየቅ በማሰብ ነውና እንደ ገንዘብ ሰብሳቢ እንደ ነጋዴ እንዳትቆጥሩኝ
አበክሬ እማጸናለሁ፡፡ ገንዘቡን ለመላክ ሞባይል ባንኪንግን መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዴት መላክ እና የምስጢር ኮድ መቀበል እንደሚቻል መተግበሪያውን አውርዳችሁ ስትጭኑት በዚያ ላይ
ያሳያችኋል፡፡

አፕሊኬሽኑን ለማየትና ለመጫን https://play.google.com/store/apps/details?id=org.goranda.finotetsidk
.....
ከመልካሙ በየነ የፌስቡክ ገፅ የተወሠደ፡፡
መተግበሪያውን(Application) እኛም በዚሁ ይዘንላችሁ ለመቅረብ ቃል እንገባለን፡፡ ፩ ኃይማኖት
Share share share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
"የበለስ ቅጠል ሰፊና ደስ የምታሰኝ ናት፤ ወደ ጥፋት የምትወስደው የኃጢአት መንገድም ሰፊ በር ናት፡፡ የበለስ ፍሬ
ሲበሉአትና ሲያላምጡአት ጣፋጭ ናት፡፡ ኃጢአትም ሲሠሩአት ደስ ታሰኛለች፡፡ ከሠሩአት በኋላ ግን [እንደ በለሲቱ] መከራን ታመጣለች፡፡ በሚሠሩአት ጊዜ ጣፋጭ፥ ከሠሩአት በኋላ ግን መራራ ናትና እርስዋን ከመሥራት ሽሽ፡፡"

~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
¶ በዩጋንዳ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች በሚገርም ፍጥነት
እየጨመረ ነው ። በ2019 ቁጥሩ 1 million ደርሷል ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
👍1
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን


የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን ብለን አንጠራም ይላሉ እነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚሉት ጉባኤውን ብቻ ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት አበውን መሠረት አድርገን የተቀደሰውን ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን እንለዋለን ነገር ግን የተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት፦
@Meserete_Yared_Asasa

✞ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው እነርሱም፦

፩ኛ፦ የተወሰነ ቦታ (ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን)፦ ይህም በዘፀ 25፥8 ላይ "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" በሚለው በአምላካችን ቃል መሠረት በፈቃደ እግዚአብሔር የተገኘ በመሆኑ ነው ስለዚህ ለአምላካችን ማደሪያ የምንሰራው መቅደስ ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

፪ኛ፦ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት፦ ቅዱስ ጴጥሮስ በ1ኛ ጴጥ 5፥13 ላይ "ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" በማለት ባስተላለፈው መልእክቱ ላይ የገለፀው በባቢሎን ያለችውን የክርስቲያኖች ማሕበር ወይም ጉባዔን የሚያመለክት ነው ስለዚህ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

፫ኛ፦ እያንዳንዱ ክርስቲያን፦ ይህም ከያዕቆብ የተወለደ ሁሉ ቤተ እስራኤል እንደሚባል ሁሉ በመንፈሳዊና በምስጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ ቤተ ክርስቶስ እንደማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ 3፥17 ላይ "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ብሏል ይህ ቃል እኛ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችንን ያመለክታል ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል።

☞ በእንግሊዝኛ #Church ፣ በጀርመንኛ #Kirche ፣ በደች #Kerke የሚሉትና ሌሎች ተመሳሳይ ስሞች ሁሉ #Kyriakon ከሚለው የግሪኩ ቃል የተገኙ ናቸው ትርጉሙም፦ "ማንኛውንም የክርስቶስ የሆነ ነገር" ማለት ነው ይህም ቃል ከመነሻው ለቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ስያሜ ይውል የነበረ ነው የላቲኑም ቃል "አቅሌስያ_Ecclesia" እና ከእርሱ ወጥተው በልዩ ልዩ የላቲን ቤተሰብ ቋንቋዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ተመሳሳይ ቃላት ሁሉ በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋሉት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመጥራት ነበር የላቲኑ ቃል መነሻው የግሪኩ "አቅሌሲያ" ሲሆን የቃሉ ትርጉምም "የራስ ገዝ ከተማ የዜጎች መሪ ጉባኤ" ማለት ነው።
@Meserete_Yared_Asasa

❖ ሐዋርያት በተለያየ ቦታ በቤተ ክርስቲያን ይሰበሰቡ ነበረ ይህም፦

ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በጽርሐ ጽዮን በኢየሩሳሌ ተሰብስበው ሳሉ ነበር/የሐዋ 2፥1/
ሐዋ 11፥26 ላይም "በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ" ተብሎ ተጽፏል።

✞ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ቤተ ክርስቲያንን በቅዱሳን ስም ትሰይማለች ይህም አስቀድሞ በነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ተነግሮ ነበር "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ /ኢሳ 56፥4-5/ ብሎ በተናገረው መሠረት አብያተ ክርስቲያናት በቅዱሳን ስም ይጠራሉ የመጀመሪያዋም ቤተ ክርስቲያን የተሠራችው በፊልጵስዩስ ከተማ ሲሆን ይኼውም በ34 ዓ/ም ነው።

✞ ቤተ ክርስቲያን "የሰማይ ደጅ" ትባላለች አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራእይ መላእክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት፣ እግዚአብሔርም በላይዋ ተቀምጦባት ያያትን ቦታ "ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው" አለ /ዘፍ 28፥17/ ያዕቆብ ቦታውን ያከበረበት ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ተጠብቆ ዛሬም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከብርበታል።

የተሃድሶ መናፍቃኑ ከላይ ያየነውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች ባለመረዳት ምንፍቅናቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስባል በሐዋ 17፥24 ላይ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" የሚለውን ኃይለ ቃል በመጥቀስ ለማወናበድ ይጥራሉ።

@Meserete_Yared_Asasa
☞ ለመሆኑ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" ማለት ምን ማለት ነው?

✞ የእግዚአብሔርን አነዋወር በተመለከት ቅዱሳት መጻሕፍት በልዩ ልዩ መንገድ ገልጠውታል ለምሳሌ፦
በሰማይ የምትኖር /ማቴ 6፥9/፦ ይህም ክብሩን ለመናገር ነው
ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ /ዮሐ 6፥56/፦ ይህም ማለት በጸጋ አድሬበት እኖራለው ማለት ነው
ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን /መዝ 131፥7/፦ ይህም በአንድ በኩል እግሮቹ የቆሙበትን መስቀል በሌላ በኩልም መቅደሱን ነው

❖ በመሆኑም እግዚአብሔር ሰው በሠራው ቤት አይኖርም ማለት አይወሰንም ማለት ነው የአሕዛብ ጣዖታት በቤተ ጣዖቱ ወይም መኖርያቸው ነው በሚባለው በኦሊምፐስ ተራራ የተወሰኑ ናቸው እግዚአብሔር ግን ለመገለጫው ቦታ ይመርጣል ማለት በዚያ ቦታ ይመሰናል ማለት አይደለም ክርስቲያኖች "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" ተብለናል /1ኛ ቆሮ 3፥16/ ያ ማለት በጸጋ አድሮባችሁ ይኖራል ማለት ነው እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ውጭ የለም ማለት አይደለም፣ ወይም ደግሞ በእንተ ተወስኖ ይኖራል ማለት አይደለም።

ስለዚህ ተወዳጆች ይቺ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን የማትታደስ እንደመሆኗ መጠን የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አያስፈልግም ከሚሉት ሀሰተኛ ትምህርቶች እራሳችንን ጠብቀን በንጽህቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችን ጸንተን መኖር ነው የሚገባን የተሃድሶ መናፍቃኑም ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ተረድተው፣ ልብ ገዝተው በክርስቶስ ደም ወደ ተመሠረተችውና የገሃነም ደጆች ወደ ማይችሏት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ይመጡ ዘንድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጸሎት ነው።

❖ በዓለት ላይ ነውና ያቆማት አጽንቶ
❖ በደሙ ነውና የቀደሳት ዋጅቶ
❖ ይጠብቃልና ጠባቂዋ ተግቶ
❖ የገሀነም ደጆች አይችሏትም ከቶ

✞ አምላከ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ጠላቶች ከተሃድሶ መናፍቃን ይጠብቅልን አሜን!!!✞

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
"በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡ ... እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረበት መንገድ እንደ ምን እንደሚለይ፣ ከሰው አሠራር ይልቅ እንደ ምን ተቃራኒ እንደ ኾነ ተመልከቱ፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ ሰማይን ዘረጋ፤ ከዚያም የምድርን መሠረት አስቀመጠ፡፡ አስቀድሞ ጣሪያን ከዚያም መሠረቱን ሠራ፡፡ እንደዚህ ያለ አሠራርን ያየ ማን ነው? እንደዚህ ያለ ነገርን የሰማ ማን ነው? ሰዎች ምንም ይሥሩ ምን ከጣሪያ ጀምረው መሠረት ሊያኖሩ አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ካዘዘ ግን ኹሉም ፈቃዱን ይፈጽማል፤ ለሰው የማይቻለውም ለእርሱ ይቻላል፡፡"


~ ኦሪት ዘፍጥረት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.፪፥፲-፲፩ ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
"ብዙ ሰማዕታት ወደ ሞት እየኼዱ ብዙውን ጊዜ አመድ መስለው ታይተዋል፤ ፈርተዋል፤ ርደዋል፤ ተንቀጥቅጠዋል፡፡ ንዑዳን ክቡራን እንዲኾኑ ያደረጋቸው ግን ይኸው ራሱ ነው ምንም እንኳን ሞትን ቢፈሩትም ቅሉ ስለ ክርስቶስ ብለው ግን ሊቀበሉት ወደ እርሱ ኼደዋልና፡፡"


ቅዱስ ዮሐ.አፈ.፣ ውዳሴ ጳውሎስ፣ ድር. ፮
"እምነት ያለ ሥራ (ምግባር) የሞተ ነው፤ ሥራም ያለ እምነት እንደዚሁ የሞተ ነው፡፡ በእምነታችን ሕፀፅ የሌለብን ብንኾንም እንኳን ምግባር ግን ከሌለን እምነታችን ብቻውን ምንም አይጠቅመንም፡፡ ልክ እንደዚሁ በጎ ምግባራትን ለመሥራት ብዙ መከራዎችን ብንቀበልም እምነት ግን ከሌለን ምንም አይረባንም፡፡"


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦሪት ዘፍጥረት፣ ድር.፪፥፲፬ ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
"500 ምዕመናን በደቡብ ኦሞ ተጠመቁ!"
* **** * * ******
@Meserete_Yared_Asasa


መናፍቃን በወረሯት በደቡብ ክልል ባገባደድነው በጥር ወር ብዙ ነፍሳት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጠምቀው ተመልሰዋል። ወንጌል ያልደረሳቸው የደቡብ ኦሞ ህዝቦች በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩት አምነው ተጠምቀዋል፡፡ በዚህም ወቅት በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት ከ500 በላይ ምዕመናን ሲጠመቁ ለመጠመቅ የተመዘገቡትም ከ500 በልጠዋል። በደቡብ ኦሞ በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት የተጠመቁ ኢ-አማንያን፦
+በ05/4/2011 ከ151 በላይ ኢ-አማኒያን ተጠምቀዋል፡፡
+በ16/5/2011 በሳላማጎ ወረዳ በዳኩባ ቀበሌ ከ161 በላይ ሰው ተጠምቋል፡፡
+በ27/5/2011 በሳላማጎ ወረዳ በወይዴ ቀበሌ ከ183 በላይ ሰዎች ተጠምቀዋል፡፡
በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት በሙርሲ ሃና የተለያዩ አብያተክርስቲያናት እየታነጹ ይገኛሉ፡፡
(መረጃውን ያደረሰኝ መ/ር አማኑኤ ነው - ከደቡብ ኦሞ)
30/05/2011 ዓ.ም (ሐሙስ)
የካቲት 2 - የበረሃው ኮከብ የአባ ጳውሊ ዕረፍት

@Meserete_Yared_Asasa

በዚህች ቀን በግብጽ በርሃ ታላቅ አምድ ወደቀ፤ ይህም የባህታውያን ሁሉ አለቃቸው የሆነ አባ ጳውሊ ነው። ስርዓተ ብሕትውና በጳውሊ ስርዓተ ምንኩስና በእንጦኒ ተጀምሯል ይላል፤ ጳውሊ አባቱ ባለጸጋ ነበር ሲሞት ለታላቅ ወንድሙ በጴጥሮስ እጅ አድርጎ ኋላ አካለ መጠን ሲያደርስ ከፍለህ ስጠው ብሎት ተናዞ አረፈ፤ አባ ጳውሊ አካለ መጠን ሲደርስ “ደረስሁ ልጅ ፈላሁ ጠጅ” የአባቴን ገንዘብ ከፍለህ ስጠኝ አለው አይሆንም አልሰጥህም አለው ምነው ቢለው ልጅ ነህ ታጠፋዋለህ ብዬ ነው ይለዋል አላጠፋውም ስጠኝ ይለዋል ግድማ ካልኸኝ ብሎ ብዙውን አስቀርቶ ጥቂቱን፤ መልካሙን አስቀርቶ ተራ ተራውን ሰጠው አባ ጳውሊ በዚህ ተበሳጭቶ ዳኛ ጋር ሄደ በመንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አየ አባቴ ባለጸጋ ነበር ሞተ ይሄም ባለጸጋ ነበር ሞተ እኔስ ነገ እሞት የለምን ብሎ ወደ ወንድሙ ተመልሶ ወንድሜ ገንዘቡ ላንተ ይሁን ትቼልሃለው ብሎ ከቤት ወጠ፤ መጀመሪያ ለ 3 ቀን ከመቃብር ቤት ገብቶ ጸለየ በ3ኛው ቀን ከሰማይ ግማሽ ህብስት ወረደለት፤ ገረመው፤ ፈጽሞ ሳይለዩ እንዲህ ከሆነማ ፈጽሞ ቢለዩማ እንደምን ያለ ተአምር በተደረገ ብሎ አናብስት አናምርት አካይስት አቃርብት ካሉበት ነቃዐ ማይ ልምላሜ ዕፅ ከሌለበት ድሩክ ለተአቅቦ ይለዋል ዘር ተክል ከማይገኝበት ከጽኑ በርሃ ገባ፤ የሰው ፊት ሳያይ ለ 80 ዓመት በተጋድሎ ኖሯል። ምግቡን ግማሽ ህብስት በየቀኑ የሚያመጣለት ቁራ ነበር።

የእረፍቱ ቀኑ ሲደርስ ከአባ እንጦንስ ጋር በእግዚያብሔር ፈቃድ ተገናኝተው ብዙ ነገር ተጨዋወቱ በተለይም በኋለኛው ዘመን ስለሚነሱት መነኮሳትና፤ ግብጽ በሙስሊሞች እንደምትወረር ብዙ ምስጢር አወሩ፣ ብዙ ትንቢትም ተናገሩ፤ ከዚህ በኃላ አባ ጳውሊ አስኬማ መልአክ አምጣልኝ ብሎ ይልከዋል፤ አባ እንጦስ ወደ ገዳሙ ሄደ የ2 ቀን ጎዳና ነው ሲመለስ በርሃው ላይ ሰማያውያን መልአክ ሰፍረውበት ሲዘምሩ ሲያመሰግኑ አየ፤ ልብን የሚመስጥ የእጣን መዓዛም አሸተተ፤ ምንድር ነው ? ብሎ አንዱን መልአክ ይጠይቀዋል አባ ጳውሊ ሞቶ ነፍሱን እያሳረግን ነው ይለዋል ይሄን አስኬማ አምጣልኝ ብሎኝ ነበር ምን ላድርገው? ይለዋል፤ ጸሎት አድርሰህ አድርግለት፤ ደግሞም መቃብሩን የሚቆፍሩ አንበሶች ይመጣሉ ቦታውን ለክተህ ስጣቸው አለው፤ ወደ ገዳሙ ሲገባ እጁን መስቀልያ እንደዘረጋ ሞቶ አገኘው የሚጸልይ እንጂ የሞተ አይመስልም ነበር አስኬማውን አድርጎለት ሲያበቃ ከራስጌው ቆሞ ኤልያስ ልበልህ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ልበልህ እያለ አለቀሰለት፤ ሁለት አንበሶች መቃብሩን ቆፈሩለት ገንዞ ቀበረው። 80 ዘመን ሙሉ ለብሶት የኖረው የሰሌን ልብስ ነበረችው ወስዶ ለሊቀ ጳጳሱ ለአባ አትናቴዎስ ሰጠው፤ በዚህች ልብስ አባ አትናቴዎስ ብዙ ተአምራትን ሰረቶበታል ይልቁንም ሙት አስነስቶበታል።
የአባቶቻችን የከበረች በረከታቸው ድል የማትነሳ ረድኤታቸው ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው ከእኛ ጋር ትሁን።

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
በቀጥታ መልሱ?????

@ዙሪያ ጥምጥም ሳትሄዱ በቀጥታ ቃል በቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ጠቅሳችሁ መልሱን ለሚለው የአርሲሳን(የመናፍቃን) ጥውየት(ጥመት) እንዲህ እንመልስላቸዋ!፦
[[[[[[ @And_Haymanot ]]]]]]]
መጽሐፍ ቅዱስ 66ቱ ብቻ ነው የሚል በራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃል በቃል ተጽፎ አለ??? እኛ የምንቀበለው ስላሉ
የራስ አቋም ጠቅላላ ሀቅ ተደርጎ ሊወሰድ ፈጽሞ አይገባም። "እመቤታችን ድንግል ማርያም ጸልያ ታስምራለች፥
ታድናለች" የሚል ቃል በቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ የተጻፈ ጥቅስ አምጣና ልመን የሚል 'ኢዩ ጩፋ ጋር ልጅህን ውሰድ፥ ፎቶውን ይዘህ ናና ጸልዮ ልጁ ይድንልሃል' ለሚለው ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ ሳያገኝ እንዴት አምኖ ሄደ???
☞ "ግሸን እየሄዳለሁ፥ ጻድቃኔ ማርያም አልቀርም፥ ሽንቁሩ ሚካኤል እጠመቃለሁ፥ ደብረ አስቦ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እሳለማለሁ።" ለሚለው 'ማርያም ቤተ ክርስቲያን፥
ጻድቅን ሰማዕታት ቤት ሂዱ የሚል ጥቅስ አለ?' ብሎ ሲጠይቅ 'ፓስተር ሱራፌል ጋር፥ እስራኤል ዳንሳ ጋር ሄድኩ፥..." ሲል
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ 'ፓስተር እከሌ ጋር ሂድ የሚል አለ?' ቢባል አንዳች መልስ አለው?
☞ የስንት ፓስተሮች ስም በየመንገዱ እየለጠፈ፥ 'እንዳይቀሩ፥ እንዳያመልጦዎ' ለሚለው የአንድም ፓስትር ስም መጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ሳይኖር፥ 'ፓስተር እገሌ ጸልዮልን ተፈወስኩኝ' ለሚለው ጥቅስ ሳያሳዩን፤ አቡነ ተክለሃይማኖት፥ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ የሚል ስማቸው ቃል በቃልና በጸሎታቸው መዳን እንደሚቻል ቃል በቃል መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አምጡ ይሉናል።

❖ እንዳውም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ በስም የተጠቀሱትን ቅዱሳንን ነው የምንቀበለው የሚሉን ከሆነ፦

፩. መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ በኋላ አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር "ቅዱስ" የሆነ ሰው በቃኝ፤ ገነት መንግሥተ ሰማይ ኮታው ሞልቷል አልቀበለም፥ አትቀበሉ ብሏል??? እንኳን ቅዱሳን በዙ ልንል ቀርቶ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትማ እንሂድ
ከተባለ ሁላችንም ቅዱሳን እንድንሆን ታዘናል። "እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።" 1ኛጴጥ. 1፥15-16
እንዲል።
፠ ከሊቀ ሐዋርያት ከቅዱስ ጴጥሮስ የበለጠ መምህር ሊያመጡልን ይችላሉ???....በፍጹም!!!...ቆይ ግን እንደ ቃሉ ሰምሮልን ሁላችንም "ቅዱሳን' ብንሆን ሁላችንም ቅዱስ ሆነን 'ኢየሱስን' ከደነው፥ ሸፈነውኮ ማለታችሁ አይቀርም።

፪. መጽሐፍ ቅዱስ በስም ከተጠቀሱ ቅዱሳን ውጭ አንቀበለም.ካሉ መናፍቃኑ ለምን ራሳቸውን 'ቅዱሳን' ብለው ይጠራሉ? ስም ዝርዝራቸው አለ?
☞ ገድል፥ ድርሳን አያስፈልግም፥ ጸረ ወንጌል ነው እያለ 'ፓስተር እገሌ የጻፋት ድንቅ መጽሐፍ ግን የእከሌን ሕይወት
ቀየረ¡' ይሉናል።
☞ ኢዩ ጩፋን ለማግኘት አስፓልት ዳር
ብርድ ሲቀፈቅፈው የሚያድር እኲይ ትውልድ "አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ደጅ የሚያድርን ቅዱስ ሕዝብ መተቸቱ Morally ያስኬዳል? በምን አግባብ?....እስቲ ጥቅስ አምጡልና?!!...
☞ ለጻድቃኔ ማርያም ጠበል(የተቀደሰ ውሃ) ና ጸበል(የተቀደሰ እምነት(አፈር)) ለፈውስ አገልግሎት አውሉት የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ አጥብቆ አምጡ እያለ፤ የተጸለየበት Highland
ውሃና አዮዲን ጨው ግን ያለጥቅስ ውሰድ ይለናል። የነሱ ተኣምራቱ ሁሉ 'ወንጌል' የእኛ ተረት ተረት ነዋ¡¡¡.....
☞ ለምንድነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮን ሁሉ 'ለእነሱ መልስ በሚሆን መልኩ ቢመለስ' እያልን በ Protestant View ብሎም አስተሳሰብና ስሜት ልክ ቀደን የምንሰፋው?...መናፍቃኑ ይኼን አልቀበልም ስላሉ "እውነት" እነሱ ስላልተቀበሏት ለእነሱ ስትል ሐሰት ትሆናለች?....
☞ የእልህ ወንጌል የለም!....'ኢየሱስ ብቻ ያድናል' ማለት እግዚአብሔር አብስ?....እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስስ?....'አይ እኛ 'ብቻ' ስንልኮ ያለማንም እርዳታ ብቻውን ያድናል!' ለማለት ፈልገን ነው ካሉ ያለማንም እርዳታ ብቻውን ማዳን፥ ሁሉንም
ማድረግ ከቻለ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ታዲያ እግዚአብሔር ከሆነና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ነገር ብቻውን ማድረግ ይችላል ብለው የእውነት
ካመኑበት ምን ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ አብ ይለምናል ይሉናል???? ...ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያምና.ቅዱሳን ካላቸው ርጉም ጥላቻ የተነሳ በግብር ይውጣ ይለፍፉታል እንጂ... ማዳን፥ መግደል የአብ፥ የወልድ፥ የመንፈስ ቅዱስ እኩል ሥልጣን እንጂ የወልድ ብቻ አይደለም።

እግዚአብሔር ያድናል ማለት በእግዚአብሔር ኃይል ቅዱስ ጳውሎስ ድንቅ ተኣምራትን አድርጎ አላዳነም ማለት አይደለምኮ!...በተለይም 14 ቅዱሳን መልዕክታቱ ይኼው ቅዱስ ወንጌል ነውና በትክክለኛ ትርጓሜ ለሚገለገልባቸው እስከ ዘላለም ሲያድን ይኖራል። የቅዱስ ጳውሎስ ፲፬ ክታቦቹ ፬ ቱ ወንጌላትን ከደነ? ሸፈነ? የሐዋርያት ሥራ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለምን የኢየሱስ ሥራ አይልም ነበረ? የማቴዎስ፥ የማርቆስ፥ የሉቃስ፥ የዮሐንስ ወንጌል መባሉ የክርስቶስ ወንጌል
ባለመባሉ ተከደነ?

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶም ትክክል፥ ሌላውም ቤተ እምነት እንደየራሱ ትክክል ብሎ መቁጠርና ሁሉም የሕይወት መንገድ ማለት ትልቅ ስሕተት ነው። ምክንያቱም ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት Didache (c. 100) በተባለው መጽሐፍ ሲናገሩ በመጀመሪያ ምዕራፍ (Chapter 1) ላይ There are two ways, one of life and one of death በማለት ነው።
እዛም ቤት ችግር የለም፥ እዚህ ብትሆንም ችግር የለም የሚል ወንካራ አካሄድ እጅግ አደገኛ ነው። ፀረ ሐዋርያት አቋም ነውና።
☞ ጥልቅ ንባብን የሚወድ ትውልድ ብንሆን ኖሮ ይኼ ሁሉ
ጥርጥር ባልመጣብንም፥ እንዲህም እርስ በእርስ ባልተጨራረስንም ነበር።
by፡- ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
Photo
"ዘመቻ ጸረ-ተሐድሶዉ ተጀምሯል!"
** ******** ******
ከቤተክርስትያን በምንፍቅባቸዉ ሲወገዙ የዋሃን ያሉባትንና የመንግስት ካድሬዎችም ሽፋን የሚሰጡላቸዉን የደቡብ ክልልን ተሐድሶ መናፍቃን መፈንጫቸዉ ሊያደርጉ ሰሞኑን
እየተርመሰመሱ ነዉ፡፡ አርባምንጮች ከሰሞኑ ከቤተክርስትያን ተወግዘዉ ነገር ግን የቤተክርስትያን ንዋያት የሆኑትን
በአዳራሻቸዉ መቀለጃቸዉ ሊያደርጉ ሲታትሩ ደርሰዉ ቤተክርስትያናቸዉን አስከብረዋል፡፡ ዘመቻዉ ጎፋ ሳዉላ ደርሶ
እነሆ በዛሬዉ ኪዳነምህረት በምትበግስበት ዕለት ወጣቶች
ኪዳነምህረትን አንግሰዉ ከተማዋን እየዞሩ በሃገር፣ በሚስትና በሐይማኖት ቀልድ የለም! እያሉ ተሐድሶ ላይ የሞት አዋጅ እያወጁ ይገኛሉ፡፡ መሎ ኮዛዎችም ጸረ-ተሐድሶ ዘመቻ ሊጀምሩ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

እኛም በያለንበት ሆነን ጸረ ተሐድሶ
ዘመቻዉን እንደግፋለን!! ጎፋዎች ከጎናችሁ ነን! ማንም የፈለገዉን የማመን መብት አለዉ፤ ነገር ግን በቤተክርስትያን ላይ ሲያላግጥ በንዋየ ቅድሳት ላይ
ሲዘባበት ዝምታ አያሻም!!
# በሃገር_በሚስትና_በሐይማኖት_ቀልድ_የለም !

ምንጭ፡ ንሽኩር
16/06/2011 ዓ.ም (ቅዳሜ)
A.A blh
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
Photo
የክተት አዋጁ

የጦርነት አይቀሬነት እና የጣሊያን ጦር ቅብጥብጥነት እያየለ ትግራይን በመውረሩ ኢትዮጵያም ለፍልሚያ ተዘጋጀች። ዝነኛው
የአፄ ምኒልክ የክተት አዋጅም ነጋሪት እየተጎሰመ ተለፈፈ።
“እግዚአብሄር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ
አኖረኝ፤ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡
ከእንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለእኔ ሞት
አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖትን የሚለውጥ፣ በፊት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን
በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ
ሰው ከአሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም፡፡ አንተም እስካሁን
አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት
የሌለህ ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘንህ
እርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፡፡ አልምርህም፡፡ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም…”(አፄ ምኒልክ)
@And_Haymanot
የጸሎት ጥበብ

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን የተማረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን እንደሚገባ’ው አድርጎ ሲያነጋግረው ከዚያን ጊዜ አንሥቶ መልአክ ይኾናል፡፡ ነፍስ ከፈቃዳተ ሥጋ ሰንሰለት ነጻ
የምትወጣው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሕሊና ከፍ ከፍ የሚለው በዚህ መንገድ ነውና፤ ማደሪያችን ወደ ሰማይ የሚሻገረው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው ግብረ ዓለምን የሚንቀው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው የቱንም ያህል ነዳይ ወይም ባሪያ ወይም ተራ ወይም ዝቅ ያለ ቢኾንም እንኳን በንጉሡ ዙፋን
ፊት የሚቆመው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከተው የንግግርን ውበት ወይም የቃልን ርቱዕነት ሳይኾን
የመንፈስን ንጹህነት ነውና፡፡ በዚህ መንገድ መጥተን ወደ አእምሮአችን የመጣውን ብንናገርም እንኳን፥ ጸሎታችን ግዳጅ የሚፈጽም ኾኖልን እንመለሳለን፡፡

እንግዲህ ይህን ማድረግ ምን ያህል ቀላል እንደ ኾነ ታስተውላለህን? በዚህ ዓለም ሰዎች ዘንድ አንድ ሰው ሌላውን
ሰው ለመለመን የንግግር ክህሎት (ብልሐት) ያሻዋል፡፡ የሚለመነው ሰው በቀላሉ የማይገኝ ከኾነ ደግሞ አጃቢዎቹን ማሳመን ይኖርበታል፡፡ ጥሮ ለፍቶ ካገኘው በኋላም ጉዳዩን በዝርዝር ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እግዚአብሔርን ለማናገር ግን የዚሁ ተቃራኒ ነው፡፡ ከተሰበረ ልብ በቀር ሌላ ምንም ምን አያስፈልግም፤ ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚከለክል ማንም
አይኖርም፡፡ “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም” ይላልና (ኤር.23፡23)፡፡ የምንርቀው እኛ ነን እንጂ እርሱ ዘወትር ቅርብ ነው፡፡

እግዚአብሔርን ለማነጋገር የንግግር ክህሎት (ብልሐት) አያስፈልገንም የምለውስ ለምንድን ነው? እንዲያውም ብዙ ጊዜ ድምፅም ቢኾን አያስፈልገንም፡፡ አንተ በልብህ ብትናገርና
እግዚአብሔርን ማናገር እንዲገባ’ህ ብታናግረው እርሱ ጸሎትህን ለመስማት ዘንበል ይላል፡፡ ሙሴ ጸሎቱ የተሰማው
በዚህ መንገድ ነውና፤ ሐና ጸሎትዋ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ ብሎ ሕዝቡን ለማራቅ የሚቆም ወታደር የለም፤ አሁን ሰዓቱ አይደለም ብሎ የሚከለክል ዘበኛም የለም፡፡ እግዚአብሔርም፡- “አሁን ላነጋግርህ አልችልም፤ ሌላ ጊዜ ተመለስ” አይልም፡፡ ይልቅ ልታነጋግረው
በመጣህበት ቅጽበት አንተን ለመስማት ይቆማል፡፡ የምሳ ሰዓትም ቢኾን፣ የእራት ሰዓትም ቢኾን፣ እጅግ አስቸጋሪ ጊዜም
ቢኾን፣ በገበያ ቦታም ቢኾን፣ በመንገድ ላይም ቢኾን፣ በባሕር ውስጥም ቢኾን፣ በዳኛ ፊት በምትቆምበት በችሎት ፊትም
ቢኾን፥ እግዚአብሔርን ብትጠራው መጥራት እንደሚገባህ አድርገህ እስከ ጠራኸው ድረስ ጸሎትህን እንዳይሰማ
የሚከለክለው ግድግዳ የለም፡፡
ምንጭ፡- ገ/እግዚአብሔር ኪደ
@And_Haymanot
@And_Haymanot