፩ ሃይማኖት
8.96K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
Channel photo updated
"ከሰማይ መስቀል፣ ጽዋ...መውረዱን በቅዱሳት ገድላት መገለጹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለምን???
@And_Haymanot
✞ ፩. የንዋያተ ቅድሳት መውረድ፤
እንደ ገድለ ቅዱስ ላሊበላና ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ባሉ ገድላት ላይ ከሰማይ መስቀል፣ ጽዋ...መውረዱ ተገልጧል።
አብርሃም በፍጹም ሃይማኖት መታዘዙን ይገልጥ ዘንድ አንድ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ እግዚአብሔር ሲፈትነው እርሱም "እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃለሁ።" ያለኝን ዘነጋውን? ወይንስ ተወው? ብሎ ሳይጠራጠር ልጁን ይዞ በቀረበ ጊዜ
እግዚአብሔር ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ የታሰረ ነጭ በግ እንደወረደለት ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ዘፍ.22፥3-19።
በሰማይ በግ የሚያረባ ኑሮ ነውን? በጭራሽ!! በአምላካዊ ተኣምር የተገኘ እንጂ። ለሙሴም እግዚአብሔር ሁለት ጽላቶችን የሰጠው ጸፍጸፍ(ሰሌዳ) ሰማዩን ከየት አምጥቶት ነው? ቢባል
በአምላካዊ ተኣምር መገኘቱን ከመግለጥ ያለፈ በምርምር
አይደረስበትም። ዘጸ.32፥1-16። ለእስራኤል ዘሥጋ የወረዳው መናም ይህንኑ አሳባችን ያስረግጣል። ዘጸ.16።
✞ አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር እሱ ባወቀ ለእሥራኤል ዘሥጋ ከሰማይ ሥጋ ማውረዱን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል/ዘኁ.11፥1-34/። በሰማይ ቄራ ኖሮ ነው? በማኅበር የተደራጁ ሥጋ አራጅ ማኅበራት በሰማይ አሉ?
❖ ከሰማይ ሰው የሚበላውን ያውም ከአይሁድ ሰንበት/ ከቅዳሜ/ በቀር በየቀኑ ትኩስ፥ ትኩስ ሥጋ ከሰማይ እንደዝናብ ያዘነበ አምላካችንን ከየት አመጣኸው? ሳንል አምነን በፍጹም
ምስጋና ከተቀበልን ብርሃናዊ ቅዱስ መስቀል፥ ጽዋ...ከሰማይ ቢወርድ ከየት አመጣኸው? ልታደርገው አትችልም ሊለው የሚደፍር ማነው???
ከሰማይ ስለወረደው መስቀልና ጽዋ የሚጠይቁ ቢኖሩ ለነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ከሰማይ እንጎቻና በማሰሮ ውኃ
ያወረደለትን እግዚአብሔር/1ኛነገ.12፥6/ በትክክለኛ እምነት ሆነው በጸሎት ቢጠይቁት ይገልጥላቸዋል።
እነዚህን ለመሰሉ ነገሮች ሁሉ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን "ከግብር አምላካዊ ተገኙ።" ትላለች። ይህም ስለ ጽላቶቹ "... ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸባቸው
የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።" ዘጸ.32፥16 የሚለውን መሠረት
ያደረገ ነው።

✞ ፪. የሰንበት መናገር፤
❖ በድርሳነ ሰንበትና በቅዳሴ አትናቴዎስ እንዲሁ በሰዓታቱ ላይ ሰንበተ ክርስቲያን እንደምትናገር መገለጹ አንዳንድ ሰዎችን
ያሳስባቸዋል ። ሰንበት አካል የላት/እጅ፣ እግር፣ አፍ፣ ...የላት/ እንዴት? የሚል ጥያቄ የሚፈጥርባቸውም አልጠፉም።
በመጀመሪያ እንደ ሰንበት ያሉ ረቂቃን አካላትን በሰውኛ ዘይቤ መግለጽ በጥንት መጻሕፍት ዘንድ የተለመደ ነው።
(Personification) ይሉታል። በአይሁድ ጥንታዊ መጽሐፍ በታልሙድ "ረቢ ሐኒና በሰንበት ዋዜማ ፀሐይ በምትገባበት ጊዜ እንዲህ አለ፤ ኑ ንግሥት ሰንበትን እንቀበላት ዘንድ እንሂድ፤ ሙሽራዬ ሆይ ነይ ሙሽራዬ ሆይ ነይ።" እንደሚል ተመዝግቧል
[The Babylonian Talmud, seder mooed sabath II,
London 1938, P.588]።
ከሥነ ፍጥረት ምሥጢር አንጻር ስንመለከተው ደግሞ ዕለታት የሁለት ፍጥረታት አንድነት ናቸው። የጨለማና የብርሃን። ጨለማና ብርሃን ሁለትነታቸው ሳይቀር በአንድነት ቀን ወይንም
ዕለት ይባላል። ስለዚህ ስለ ሰንበት መናገር ማለት የእነዚህን የሁለቱን አንድነት መናገር ማለት ነው። ይህም የነፍስን ነባቢነት ከሥጋዊ ብልት(ከሰውነት ክፍል) ከአፍ ከምላስ ጋር ተዋሕዶ እንደሚገለጠው ያለ ነው። ይህም ተዋሕዷቸውን ለመናገር
እንጂ ግዘፍ አካል አላቸው ለማለት አይደለም። ፍጥረት እስከ ሆኑ ድረስ ደግሞ ለፈጣሪያቸው ይናገራሉ መልስም ይሰጣሉ። እኛ ለምን አልሰማናቸውም ሌላ ጥያቄ ነው። ፍጡር ለፈጣሪው
የማይመልስ ከሆነ ችግሩ የፍጥረቱ ሳይሆን የፈጣሪ ነው ወደ ማለት ጥልቅ ክህደት ውስጥ ያስገባል። ሎቱ ስብሐት(ለእርሱ ክብር ይግባው)ና ፈጣሪያቸው እንዳያውቁት አድርጎ ፈጥሯቸዋል ያሰኛል።
ለእርሱ ክብር ምስጋና ይግባውና እርሱ የፈጠረው ሁሉ ምሉዕ ስለሆነ "መልካም እንደሆነ አየ፤" ተብሎ ተገልጿል።
ዘፍ.1፥1-22። ስለዚህ ሰንበት ልትመሰክር ትችላለች። ቋንቋው
ግን በልሳነ ሰብእ(በሰው ቋንቋ) ላይሆን ይችላል። ጌታችን በተሰቀለበት ዕለት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ መሬትና መቃብር የመሰከሩት በሰው ቋንቋ ሳይሆን ለሰው በታወቀ በተረዳ ተኣምር
እንደሆነው ሁሉ የሰንበትም እንደዚሁ ይሆናል። በቅዱስ መጽሐፍ መሬትና ውኃ ፍጥረታትን እንዲያወጡ ሲታዘዙ ሰምተው ፈጽመዋል። የሰውን ጆሮ የመሰለ ጆሮ ግን አልነበራቸውም።
ከእርሱ ለሚወጣው ቃል ስለ ፈቃዱም የሚታዘዙና የሚመልሱ ሆነው ለራሳቸው በሚስማማ ጸጋ ከብረው ተፈጥረዋልና። ቅዱስ ዳዊትም "አቤቱ ውኆች አይተውህ ፈሩ።" /መዝ.76፥6/ ያለው
አምላካቸውን ዐውቀው መታዘዛቸውን ለመናገር እንጂ የሰውን የመሰለ ዓይነ ሥጋ አላቸው ለማለት እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ከዚህ አንጻር ሰንበት ትናገራለች።
"ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።" መዝ.113፥3 ሲል ባሕር የምታይበት እንደ ሰው ዓይን አላት? የዮርዳኖስ ወንዝስ ወደ ኋላው የተመለሰው እንደ እኛ እግር
ኖሮት ነው? "መልሶም። እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች
ይጮኻሉ አላቸው።" ሉቃ. 19፥40። መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የቢታንያ ድንጋዮች እንደሚጮኹ ሲናገር ድንጋዮች እንደ ሰው ልሳን፥ አፍ አላቸው ማለቱ ነውን? ለእኛ ለፍጡራን ድንጋይ
ግዑዝ በድን አካል ቢሆንም ለፈጣሬ ዓለማት ለቅድስት ሥላሴ ግን እሱ ባወቀ እንዲናገሩ ያረጋቸዋል፥ ሥራም ያሰራቸዋል።

✞ አካል ስለሌላት አትናገርም ማለት አካል ሳይኖራት እንዴት አከበራት ብሎ እግዚአብሔርን እንደ መተቸት ይሆናል።
"እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።" ተብሎ
ተጽፏልና። ዘፍ. 2፥3።
፠ በአጠቃላይ ገድላትን በሚገባ ለመረዳትና በገድልና በትሩፋት
የኖሩትን አበውና እማትን/እናቶችን/ ሃይማኖትና ምግባር መያዝ፤ በመንገዳቸውም መጓዝ ተገቢ ነው። ያለበለዚያ የይመስለኛል እምነት መድረሻው ክህደት፤ የክህደትም መደምደምያው ሞት ነው።
by ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
\\\አይናችን ነሽ ማርያም///
አይናችን ነሽ ማርያም አንችን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሃሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ!!!
አዝ፡፡፡
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
ባሽዋላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
አዝ፡፡፡፡
ገብተሻል ላትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነው ባንችነው የጠፋው ተገኝቶ
አዝ፡፡፡፡፡
ወይኑንያፈራሽው የወይን ሐረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሸን በቀራኒዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
አዝ፡፡፡፡፡
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ፀዋሪተ ፍሬ ያዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
አዝ፡፡፡
ከሃገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
ባደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጂ
ለፃድቃን አይደለም ለሃጣን አማልጂ
አሜን ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን
ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጥቅምት 20/2011 ዓም
¶ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ የተሃድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ በቸልተኝነት የሚመለከቱ አንድ አንድ አህጉረ ስብከቶችን አስጠነቀቀ ።
¶ በተሃድሶ መናፍቃን የተዘረፉ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሐብት ንብረቶች በሙሉ በህግ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
¶ ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው ከያዛቸው አጀንዳው አንዱ በሆነው ፥ በተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ዙሪያ የሰመረ ውይይት በማድረግ ይህንን የተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በውስጥም በውጭም ያሉ አህጉረ ስብከቶች ፥ በቸልተኝነት የሚመለከቱ
ካሉ ፥ አበክረው በጉዳዩ ዙሪያ እንዲሰሩ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል ።
¶ # እነዚህን መናፍቃን ማሽሞንሞኑ ይብቃ ! ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ በአህጉረ ስብከት ደረጃ እስከ አጥቢያ
አብያተክርስቲያናት ድረስ የፀረ ተሃድሶ መናፍቃን መኃቀፍ ያላወቀሩ አንድአንድ አህጉረስብከቶች ባስቸኳይ አቋቁመው
እንዲሰሩና አስቀድመው ያቋቋሙ ደግሞ ያለመዘናጋት ጠንክረው እንዲሰሩ ከስምምነት ላይ ደርሷል ።
¶ በዚሁ አጋጣሚ የተሃድሶ መናፍቃን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሙዳይ 12 million ብር ዘርፈው በዱከም(Dukem ) ከተማ ፥ባለቤትነቱ የአቶ በጋሻው እና የአቶ
አሰግድ በመሆን ለምንፍቅና አገልግሎታቸው በEconomy
ረገድ እንዲደግፋቸው ያቋቋሙትን Koyla (ቆይላ ) የህትመት ፋብሪካ ለባለቤቷ ለቤተክርስትያን በህግ ያስመልሳል ተብሎ ይጠበቃል ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጥያቄ፡- "አባትና እናት የትውልድም ቁጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።" ዕብ.7፥3-5።

ይህን ገጸ ንባብ በማንበብ ብቻ በመያዝ መልከ ጼዴቅ ሰው አይደለምን? ሰው ከሆነ ለምን እናትና አባት የሉትም ይላል? ከአባታችን ከአዳምና ከእናታችን ከሔዋን በቀር ከእናት አባት ያልተገኘ ፍጡር ሰው አለ? ወዘተ...የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
❖ "አባትና እናት.." አልቦ ዘዘከረ ሎቱ አበ ወኢእመ የሚለው ለመልከ ጼዴቅ እገሌ አባቱ እገሊት እናቱ ብሎ የተናገረለት መጽሐፍ የለም ሲል ነው።
"...የትውልድም ቁጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፥..." ወአልቦ ጥንት ለመዋዕሊሁ ወኢማኅለቅት ለሕይወቱ ሲል ደግሞ በዚህ ቀን ተወለደ በዚህ ቀን ሞተ ብሎ የተናገረለት መጽሐፍ የለም ማለቱ ነው፤ ምነው በስንክሳር ተጽፎ የለምን ቢሉ በሌዋውያን መጽሐፍ ስላልተጻፈ እንዲህ አለ።

መጻሕፍተ መነኰሳት ሁለተኛ መጽሐፍ "ፊልክስዩስ" ላይ ክፍል 2፤ ተስእሎ 17፤ ገጽ 39 ላይ "አባትና እናት...የሉትም" የሚለውን ገጸ ንባብ ይዘው 'መልከ ጼዴቅ ወልደ እግዚአብሔር ራሱ ነው' ላሉት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ፦ የነገደ ካም ትውልዳቸው ነገዳቸው በኦሪት ባይጻፍ ነው እንጂ እናት አባት አሉት። ሐሴል ሳሌምን፤ ሳሌም ሜልኪን፤ ሜልኪ ደግሞ ሜልኪንና መልከ ጼዴቅን ይወልዳል፤ እናታቸው ሰሊማ ትባላለች። አባታቸው ጣዖት ያመልክ ነበርና መልከ ጼዴቅን ጠርቶ ከበጎቹ መርጠህ ለጣዖት የምንሰዋው በግ አምጣልኝ አለው፤ አባቴ ይኸ ጣዖት ምን ይረባናል አለው፤ እምቢ ብለህ እንደሆነ አንተን እሰዋሀለሁ ብሎ ያዘው። እናቱ ትወደው ነበርና ባይሆን በዕፃ(ጣ) ይሁን እንጂ ልጄን አትሠዋብኝ አለችው፤ ዕፃ ቢጥል በታላቁ ወጣበት፤ ሊሠዋው ይዞት ሄደ። እናቱ አይታ ወንድምህን ሲወስድብህ ዝም ትላለህን አለችው፤ ወደ ጌታ ቢያመለክት ከሰማይ እሳት ወርዶ አባቱንም ወንድሙንም በልቷቸው እርሱ ብቻ ቀረ። ከዚህ በኋላ ወደ ዮርዳኖስ መጥቷል ብሎ ነግርዋቸዋልና እንዲህ አለ። ይላል።

❖ "አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።" ዮሐ.8፥56 ትርጓሜው፦ አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር አበ ብዙኃን አባታችን አብርሃምን ዮርዳኖስን ተሻግረህ ሒድ ምሳሌውን ታያለህ አለው። ዮርዳኖስን ተሻግሮ ቢሔድ መልከ ጼዴቅ ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት ይዞ ተቀብሎታል፤ ምሳሌ ነው። መልከ ጼዴቅ የጌታ፤ የቀሳውስትም ይሉታል፤ አብርሃም የምእመናን፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት፤ ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት የሥጋው የደሙ ምሳሌ። ወባረኮሂ(መልከ ጼዴቅ አብርሃምን ባረከው፤ አብርሃም ቡሩኩ ለእግዚአብሔር ብሎ)።

❖ "...ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።" ዕብ.7፥3-5 ማለት፦ የወልደ እግዚአብሔር ክህነት በመልከ ጼዴቅ ክህነት አምሳል ጸንቶ ለዘለዓለሙ ይኖራል። ጌታ መልከ ጼዴቅን በምን ይመስለዋልና አምሳሊሁ(ተመስሎ) አለ ቢሉ መልከ ጼዴቅ በስንዴ በወይን ያስታኩት ነበር፤ እሱም ሥጋውን ደሙን በስንዴ በወይን ሰጥቶናልና፤ መልከ ጼዴቅ ሹመቱን ከእገሌ ተሾመው አይባልም ከእግዚአብሔር ተሾሞታል፤ እሱንም(ጌታችንም) ሤሞ አቡሁ ይለዋልና፤ የመልከ ጼዴቅ ሹመት ለእገሌ አለፈ አይባልም፤ የጌታም ሹመት ለእገሌ አለፈ አይባልምና።
"የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው። " ዕብ. 7፥2 ሲል የመጀመሪያ የስሙ ትርጓሜ መልከ ጼዴቅ ማለት ንጉሠ ጽድቅ ማለት ነው። የኹለተኛው ስሙ ትርጓሜ ንጉሠ ሳሌም ማለት ንጉሠ ሰላም ማለት ነው። የሀገሩ ሰዎች ሔደው ንገሥልን ብለውታል፤ ያስጠበቀኝን(አጽመ አዳምን) ትቼ አይኾንም ብሏቸዋል። እንዲህ ግን ስለኾነ ቢከራከሩ እውነት ይፈርድላቸው ነበርና ንጉሠ ጽድቅ፤ ቢጣሉ ያስታርቃቸው ነበርና ንጉሠ ሰላም አለው። ይህን ለምን አነሳው ቢባል በትሩፋቱ ያጸደቀን/ያከበረን/ ንጉሠ ጽድቅ(የእውነት ንጉሥ)፥ በደሙ ያስታረቀን ንጉሠ ሰላም(የሰላም ንጉሥ) መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለማለት ነው።
by ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው እግዚአብሔር ነው፡፡
@And_Haymanot
መጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ ለቅዱሳን መስገድ አንደሚገባ ያስረዳል፡፡ በዘፍ. 27፡29 “አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን
የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።” ብሎ ልጁን ያዕቆብን የባረከው ይሥሐቅ ነበር፡፡ ይህን ምርቃት ማግኘት የነበረበት የያዕቆብ ታላቅና በኩር የነበረው ኤሳው ቢሆንም ያዕቆብ በእናቱ ብልኃት
ታግዞ ተመረቀ፡፡ ይሥሐቅን እንዲህ ብሎ እንዲመርቅ ያደረገው እግዚአብሔር አምላክም የአብርሃም ፣ የይሥሐቅና የኤሳው አምላክ በመባል ፋንታ የአብርሃም ፣ የይሥሐቅና የያዕቆብ
አምላክ ተባለ፡፡ አምላካችንን ሙሴ ማነህ ብሎ በጠየቀው ጊዜም ራሱን ሲገልፅ እርሱ ራሱን ለአብርሃም ለይሥሐቅና
ለያዕቆብ የሚገለጥና ምድረ ርስትንም ሊሰጣቸው ቃል እንደገባ ለሙሴ ገልፆለታል፡፡ ስለዚህ በይሥሐቅ አንደበት አድሮ ያዕቆብን የመረቀው እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህንን የሚጠራጠሩ ቢኖሩ
እንኳን የይሥሐቅን ምርቃት የፈጸመው /እንዲደርስ ያደረገው/ እግዚአብሔር ነው፡፡ ታዲያ አምላካችን ለቅዱሳን የሚገባን ስግደት የሚቃወም ቢሆን ይሥሐቅን “ሕዝብም ይስገዱልህ”
ብሎ ሲመርቅ አይገሥጸውም ነበርን? ባይገሥጸው እንኳን “ልጆች ይስገዱልህ” ብሎ የመረቀ ይሥሐቅን ምርቃቱን
ባለመፈጸም /እንዲደርስ ባለማድረግ/ ቃሉ ልክ እንዳልሆነ አያሳይም ነበርን? ደግሞስ ለፍጡር በሚገባ መስገድ ስሕተት ቢሆን ከብዙ ዘመን በኋላ ያዕቆብ ከነቤተሰቡ ለኤሳው በመስገድ
የአባቱን የይሥሐቅን “ስሕተት” ይደግመው ነበርን? ከዘፍ.37-41 ድረስ የፃድቁን የዮሴፍን ታሪክ እናገኛለን፡፡ በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ለዮሴፍ እንደሚሰገድለት የሚተነብይ
ሕልም አሳየው፡፡ “እኔ ያለምሑትን ሕልም ስሙ፡ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናሥር ነበርና፤ እነሆም የእኔ ነዶም ቀጥ
ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከበው እነሆ ለኔ ነዶ ሰገዱ” /ዘፍ.37፡7/፡፡ ወንድሞቹ ከሕልሙ የተነሣ እንደሚሰግዱለት ተረድተው ወንድማቸው ዮሴፍን ይበልጥ
ጠሉት፡፡ ለቅዱሳን አንሰግድም ብለው ቅዱሳንን የማያከብሩ ሰዎች በትዕቢት ራሳቸውን ከቅዱሳን በላይ በማድረግ፣
ወንድማቸውን ዝቅ ያደረጉትን የዮሴፍን ወንድሞች ይመስላሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህንን እንዲረዱት ዮሴፍ ነዶ በተባሉት በወንድሞቹ ብቻ ተሰግዶለት የሚቀር ሳይሆን በሌሎች ፍጥረታትም ዘንድ እንደሚከብር ሲገልፅላቸው ዮሴፍን ሌላ ሕልም ዐሳየው፡፡ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፣ እነሆ
ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” / ዘፍ.37፡9/፡፡
እግዚአብሔር ተናግሮ ነገር አይቀርምና ወንድሞቹ እንዳይሰግዱለት፣ እንዳይገዙለት ሽተው ሊገድሉት ቢሞክሩም፣ ጉድጓድ ውስጥ ቢጥሉትም፣ ለነጋድያን ቢሸጡትም በሀገራቸው ሊፈጽሙት የከበዳቸውን ሐቅ ርሐብና ድርቅ ሲመጣ በባዕድ
ምድር በግብፅ ሊያደርጉት ግድ ሆኖ ወንድሞቹ ለዮሴፍ መስገዳቸው አልቀረም፡፡ “የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በግምባራቸው በምድር ላይ ሰገዱለት” /ዘፍ.42፡6/፡፡

ለቅዱሳን አንሰግድም የሚሉ ሰዎች ምንም እንኳን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሊያጠፉት ሽተው ቢሰርዙና ቢደልዙትም፣ በቀላል አማርኛ በሚል ፈሊጥ ቃሉን ቢዘነጥሉትም፣ ጥቅስን ዘንጥሎ በመጣል ጉድጓድ ውስጥ ቢጥሉትም፣ አውጥተው ለሥጋዊ
ስሜትና ለዓለም ክህደት ቢሸጡትም ርሐበ ነፍስ ድርቀተ መንፈስ ሲመጣ በሀገራቸው፣ በሕይወተ ሥጋቸው ያላደረጉትን እውነትን በሲዖል እንኳን ለማድረግ መጓጓታቸው አይቀርም፡፡
“የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ” እንዳለ ኢሳይያስ /ኢሳ.60፡14/፡፡ በምድር ምጽዋት የነፈገውን አልአዛርን በሲዖል በአብርሃም አማላጅነት እንደለመነው ነዌ፡፡ /ሉቃ.16፡20-31/፡፡ ጳዎሎስንና ሲላስን ለመሰሉ ቅዱሳን ለእናንተ የሚገባው ስግደት ሳይሆን መታሠር ነው ብለው ደብድበው ካሠሯቸው ሰዎች መኃል
አንዱ የሆነው የእሥር ቤቱ ጠባቂ በእሥር ቤቱ ውስጥ በነጳውሎስ ዝማሬ ምክንያት ከደረሰው ታላቅ መናወጽ በኋላ
ከሥራቸው ተደፍቶ ሰገደላቸው፡፡ “ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ” /ሐዋ.16፡29/ እንዲል ግብረ ሐዋርያት፡፡ የቅዱሳኑን ዝማሬ ሰምቶ እሥር ቤቱን አናውጾ ጠባቂውን እንዲሰግድ
ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?

☞እግዚአብሔር ቃል በቃል ለቅዱሳን ስግደት እንደሚገባ የተናገረበት ቦታን ለሚሻ ደግሞ እነሆ፡~ በራእየ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ላይ ሁለት የቤተክርስቲያን ጠባቂዎችን እናገኛለን፡፡ አንደኛው በሰርዴስ የሚገኘው
መልአክ /ጠባቂ/ ሲሆን አንደኛው ደግሞ የፊልድልፍያ ቤተክርስቲያን መልአክ /ጠባቂ/ ነው፡፡ የሰርዴሱ ጠባቂ ሥራው በአምላክ ፊት ፍጹም ያልሆነና በቁሙም ሞተሀል የተባለ ሲሆን እንዲነቃና ንስሐ እንዲገባ አግዚአብሔር አዟል፡፡ እንዲህ ካላደረገ ግን እንደሚፈርድበት “እመጣብሃለሁ” ሲል ነግሮታል፡፡ የፊልድልፍያው መልአክ /ጠባቂ/ ግን በእግዚአብሔር ፊት
የተወደደና ቅዱስ ነበርና እግዚአብሔር እንዲህ አለው “ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ፤ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ትንሽ ቢሆን ቃሌን
ጠብቀሃልና ስሜንም አልካድህምና፡፡ እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ
አደርጋቸዋለሁ” /ራእ.3፡8-9/፡፡
ለቅዱሳን ስግደት አይገባም የሚሉ ምንኛ ያልታደሉ ናቸው? “የተከፈተ በር ሰጥቼሀለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም” የተባለላቸውን ቅዱሳንን የሚመሰገኑበትን የጸጋ በር ሊዘጉ
የሚሮጡ ምንኛ ምስኪኖች ናቸው? “እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር” የተባሉ ክርስቲያን ሳይሆኑ ክርስቲያን ነን የሚሉ ነገር ግን
የሚዋሹ ምንኛ አሳዛኝ ናቸው? እነሆ ክርስቲያን ሳይሆኑ ክርስቲያን ነኝ በሚል ቅዠት ቅዱሳንን የማይወዱ የሰይጣን
ማኅበር አባላት መባላቸው እንዴት የሚደንቅ ነው? እንደ ቅዱሳን ሁሉ እንዲሠጣቸው ተፈጥረው እነርሱ ራሳቸው ተላልፈው መሠጠታቸውና ባይወዱም እንኳን በቅዱሳን እግር ፊት
መስገዳቸው የማይቀር መሆኑ እንዴት ግሩም ነው? በተዐብዮ ራሳቸውን እኔም እንደ እገሌ ቅዱስ ነኝ የሚሉ ዘባቾች ቅዱሳንን በትሕትናቸውና አንዱ ለአንዱ በመስገዳቸው የሚወድ እግዚአብሔር “እንዴት እንደወደድሁህ ያውቁ ዘንድ
አደርጋቸዋለሁ” ብሎ ለቅዱሳን ቃል መግባቱ እንዴት ያለ ምሥጢር ነው?
ይቆየን።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን?" ቅዱስ ኤፍሬም
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ፡፡ እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን እንዲህም እንላለን☞Open
ጥያቄ፡- በጥምቀት ጊዜ ወልድ እየተጠመቀ ባለበት ሰዓት አብ የምወደው ልጄ ይኽ ነው ሲል ወልድ እታች እየተጠመቀ ከሆነ አብ በምን ቃልነት ተናገረ?? ወልድ የአብ ቃሉ
ከሆነ...
@And_Haymanot
መልስ፦ ጥያቄው በቀጥታ የአካልን ትርጉም የሚያመጣ ነው።.. አካልና ባሕርይን ትርጉማቸውን በትክክል መረዳት ለምሥጢረ ሥላሴና ለሥጋዌ በጣም አስፈላጊ ነው።
*አካል ማለት "ቀዋሚ"፣ "እኔ ነኝ ባይ" ተብሎ ተተርጉሟል።..
*አብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ማወቂያቸው፣ ወልድ የአብና
የመንፈስ ቅዱስ መናገሪያ ቃላቸው፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የአብና የወልድ ሕይወታቸው መሆኑ የታወቀ የተረዳ ነው።.. በመሆኑም ክርስቶስ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ፡ አብ በሰማይ ሆኖ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" አለ።.. ይህን ያለው አብ በወልድ ቃልነት ነው። ቢሆንም ግን "በሰማይ ሆነህ የምወደው ልጄ ይህ ነው ያልከው ማን ነኝ ትላለህ?" ብለን ብንጠይቅ "እኔ ነኝ"(እኔ
ነኝ ባይ እንዳልነው) የሚመልስን እግዚአብሔር አብ ነው .. ምክንያቱም በህልውናው በሚኖር በወልድ ቃልነት ቢናገረውም ("ቢናገረውም" እንኳ ስንል እርሱን እያመለከትን ነው) ተናጋሪነት
የተለየ አካልነት (እኔነት) ስለሆነ አብ ነው እንላለን ... ይህ የህልውናቸውን ብቻ ስንናገር ነው።.. ሌላው ቀላል አመክንዮ
ደግሞ ".. የምወደው ልጄ" ማለቱ እርሱ አባት (አብ) እንደሆነ በዚያውም ማስረዳቱ ነው።
* ነገረ ድኅነት ላይ።.. ሥላሴ ዓለምን አድነዋል ተብሎ በደንብ ይነገራል። እንደውም ስለ አብ መጽሐፈ ኪዳን ዘሠርክ "..ወበሞተ ወልድከ ቤዘውከ ወዘተገድፈ ኀሠሥከ.." ማለትም
"በልጅህ ሞት አዳንህ። የጠፋውን ፈለግህ።" ተብሎ ተነግሯል። ማዳን (አድኅኖት) የሥላሴ ቢሆንም መሰቀል ግን ለወልድ ብቻ የሚነገር ነው። በተለየ አካሉ ያደረገው ነውና።.. "የተሠቀልከው
እኔ ነኝ ባይ ማን ነህ?" ብንል.. ወልድ መሆኑ ላይ እንደርሳለንና።.. ማዳን ግን ሥልጣናዊ ነው።.. ስለሆነም አብም
አዳነ፡ ወልድ አዳነ፡ መንፈስ ቅዱስ አዳነ ይባላል።... *ሌላ ማንጸሪያ ልጨምር፡- ነገረ ትንሣኤ። ጌታን ማስነሳት የሥልጣን (የኃይል) ሥራ ነው ስልሆነም ምንም ምሥጢር ሳይፋለስ "አብ አስነሳው" ተብሏል፤ "መንፈስ ቅዱስ አስነሳው"
ተብሏል፤ እሱ ራሱ "በሥልጣኑ ተነሣ" ይባላል።.. ሥልጣናቸው አንዲት ናትና ምንም እንግዳ አይሆንም።.. ከሙታን ስለመነሣት ሲነገር ግን "ወልድ ተነስቷል" ይባላል እንጂ ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ ይህ አይነገርም። ምክንያቱስ? ከሙታን ተለይቶ መነሳት ልክ እንደ ልደትና ስቅለት "የተለየ አካል" ሥራ ነውና።
by zemaryam zeleke
@And_Haymanot
@And_Haymanot
አስታርቂኝ


አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/ 
ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም 

አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ 
አስታርቂኝ ጫካ ውስጥ ቆሜአለው 
አስታርቂኝ ሥራዬ አሳፍሮኝ 
አስታርቂኝ ዘወትር አነባለው 
አስታርቂኝ ልጄ አዳም ብሎ 
አስታርቂኝ አምላኬ ሲጠራ 
አስታርቂኝ እነሆኝ ለማለት 
አስታርቂኝ አንደበቴ ፈራ 
አዝ ------------ 
አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ 
አስታርቂኝ ከገዛ አባቴ 
አስታርቂኝ ከቤቴ ኮበለልኩ 
አስታርቂኝ ይሻለኛል ብዬ 
አስታርቂኝ ገፍቼ ወጥቼ 
አስታርቂኝ የቤቴን ገበታ 
አስታርቂኝ ልበላ ተመኘሁ 
አስታርቂኝ የእንስሳት ገፈራ 
አዝ--------- 
አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ 
አስታርቂኝ አሁን ተነሥቼ 
አስታርቂኝ ይቅርታ ልጠይቅ 
አስታርቂኝ እግሩ ስር ወድቄ 
አስታርቂኝ ልጅነቴ ቀርቶ 
አስታርቂኝ አድርገኝ ባርያህ 
አስታርቂኝ ከሞያተኞችህ 
አስታርቂኝ እንደ አንዱ ቆጥረህ 
አዝ ------ 
አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለው 
አስታርቂኝ አባቴ አይቶኝ 
አስታርቂኝ ወደእኔ ሮጦ 
አስታርቂኝ አቅፎ ነው የሳመኝ 
አስታርቂኝ ጠፍቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ተገኘልኝ አለ 
አስታርቂኝ ሞቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ደግሞ ሕያው ሆነ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot
                    
🌍 እመቤታችን አለም ሳይፈጠር በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር 🌍
@And_Haymanot
በመጀመርያ ጊዜውን ባርኮና ቀድሶ ለዚህ ያደረሰን ለልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እንዲሁም የፅድቃችን ምክንያት ለሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ምስጋና ይድረሳት
አሜን።

ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ ከሚለው አፕሊኬሽን የተወሰደ።
እመቤታችን አለም ሳይፈጠር በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር!!!
ይህንን ቅዱስ ቃል ስንናገር ተረፈ ሉተራውያን ለምን ይሆን ያዙኝ
ልቀቁኝ የሚሉት ???
.
.
.
[ መቅድመ ተኣምረ ማርያም ]
እግዚአብሔር አለምን ከመፍጠሩ በፊት ስለሚፈጥረው አለም አያውቅም ነበርን ???
የአለምንስ ፍፃሜ አያውቅምን ???
የእግዚአብሔርን ፍፁም አዋቂነት የሚያምን ሁሉ አያውቅም ሊል
አይችልም።
ራሱ ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ( ማቴዎስ 25 ቁጥር 34 )
በዚህ ትምህርቱ አለም ሳይፈጠር እመቤታችን በመታሰቧ ብቻ ሳይሆን ከእርሷ ሰው ሁኖ ዓለምን ማዳኑ በእለተ ምፅአትም በቀኙ የሚቆሙትና በግራ የሚቆሙት ሁሉ መታወቃቸው ተፅፏል።
አለም ሳይፈጠር ስሉስ ቅዱስ በፈቃ ድ አንድ መሆናቸውና የአካላዊ ቃል ከእመቤታችን ሰው መሆኑ መታወቁ ብቻ ሳይሆን በሰው ድህነትም ስላሴ መደሰታቸው ለማስረዳት ጌታችን
መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፤ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ
አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። ( ዮሐንስ ምዕ 17 ከቁጥር 20-21 )
ይህ ንግግር አካላዊ ቃል በተዋህዶ ሰው በመሆኑ ሰውን መውደዱን አብ ቅድመ ስጋዌ በስጋዌ መደሰቱን ለመግለፅ
የተነገረ ነው።

እመቤታችን በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር የሚለውም ስጋዌው አለም ይታወቃል ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑ መታወቁም እርሷ አለም ሳይፈጠር
ተመርጣለች ታውቃለች ለዚህም ታስባ ትኖር ነበር ማለት ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ይህን በዚህ መልክ የአምላክ ሰው መሆን መታወቁ ትክክል ነው ነገር ግን እመቤታችን ገና ሳትወለድ
እንዴት ልትታወቅ ትችላለች ?
የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ፦
፤ ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። ( መዝሙር ምዕ 139 ቁጥር
16 ) በማለት የማያዳግም ምላሽ ሰጥቶናል። ቅዱሱ ወደፊት የሚመጣው ነገር ከመኖሩ በፊት አንድስ እንኳ
ሳይቀር በመፀሀፍ ቀድሞ መፃፉን ከነገረን ስለ እመቤታችን እንዲህ መባሉ ከቅዱስ መፀሀፍ ልዩነት እንደሌለው ያሳየናል። አንዳንዶቹ ደግሞ የእግዚአብሔርን አዋቂነት ቢያምኑም
እመቤታችን ብቻዋን አታውቅም የሚል መከራከሪያን ያመጣሉ ይህ ንግግራቸውም እራሳቸው ለእመቤታችን ያላቸው አመለካከት ወይም ያሳየናል እንጅ አይናቸውን ጨፍነው መካድ
የሚፈልጉ መሆናቸውን የቅዱሳት መፀሀፍት እውቀታቸውን
ሊያሳይ አይችልም። እግዚአብሔር ሁሉንም ያውቃል ስለሁሉም ግን አልተናገረም አልተፃፈም ትንቢት የተነገረላቸው ወይም በስራቸው
እግዚአብሔርን ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኙት እርሱ ያወቃቸው
ብቻ ናቸው።
🔍 ነብዩ ኤርሚያስን ፦ በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ
ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። ( ኤርምያስ ምዕ 1 ቁጥር 5 ) ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ሌሎቹን በእናታቸው ማህፀን
አያውቃቸውም ሳይወለዱና አድገው የሚሆኑትን ሳይሆኑ
አስቀድሞ አያውቅም ማለት አይደለም ቅዱስ ዳዊት ፦
💠 መዝሙር ምዕ 22 ቁጥር 10 ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ። ( መዝሙር
ምዕ 22 ቁጥር 10 ) እንዳለ ሁላችንንም አስቀድሞ ያውቀናል። ነብየ እግዚአብሔር ኤርሚያስ የተናገረው ግን በተለየ ሁኔታ ትንቢት የተነገረላቸው ሰወች አስቀድሞ የሚሆኑትና ቅድስናቸው የታወቀላቸው መሆኑን መናገር ነው። ለአህዛብም ነብይ አድርጌሀለሁ ያለው ገና ሳይወለድ ነው።
ነብይነትን ተሽሞ ወይም ተቀብቶ በምድር ላይ ከመጣ በኋላ
አይደለም። ነገር ግን ከተወለደና ካደገ በኋላ የሚደርስበት መዓረግና
ቅድስና አስቀድሞ ( ቀድሞ ) የሚታወቅ መሆኑን መናገሩ ነው።
💠 ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲወስ ሲፅፍለት ፦.ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤
( 1ኛ ጢሞቴዎስ ምዕ 1 ቁጥር 18 )
ያለው በጢሞቲወስ በስም ተጠቅሶ ትንቢት ተነግሮለት አይደለም።
ነገር ግን ስለ ሐዲስ ኪዳን ካህናትና ሐዋርያት የተነገረው ለእርሱ የተነገረ መሆኑ የታወቀ በመሆኑ ነው።
ሥጋዌውን ዓለም ሳይፈጠር እግዚአብሔር ያውቀዋል ፣
ያስበዋል ማለትም እመቤታችን ታስባ ትኖር ነበር ማለት ነው።
።።።።።።።///።።።።።።
#በዓለም_ሳይፈጠር_በፊቱ_ቅዱሳንና_ነውር_የሌለን_በፍቅር_እንሆን_ዘንድ_በክርስቶስ_መረጠን ። ( ኤፌ ምዕ 1 ከቁጥር 4 እስከ 14 )
እመቤታችን አለም ሳይፈጠር በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር የሚለው የተኣምረ ማርያም መቅድም ምንም አይነት ሕፀፅ የለውም መፀሐፍ ቅዱስም ይደግፈዋል።
።።።።።።።///።።።።።።።።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ባይነት
የእናታችን የድንግል ማርያም አማላጂነት
የቅዱሳን ፀሎት የመልዐክት ፈጣን ተራዳኢነት ከምናምነው ጋር
ይሁንልን አሜን።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
🌍 እመቤታችን አለም ሳይፈጠር በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር 🌍
@And_Haymanot
በመጀመርያ ጊዜውን ባርኮና ቀድሶ ለዚህ ያደረሰን ለልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እንዲሁም የፅድቃችን ምክንያት ለሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ምስጋና ይድረሳት
አሜን።

ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ ከሚለው አፕሊኬሽን የተወሰደ።
እመቤታችን አለም ሳይፈጠር በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር!!!
ይህንን ቅዱስ ቃል ስንናገር ተረፈ ሉተራውያን ለምን ይሆን ያዙኝ
ልቀቁኝ የሚሉት ???
.
.
.
[ መቅድመ ተኣምረ ማርያም ]
እግዚአብሔር አለምን ከመፍጠሩ በፊት ስለሚፈጥረው አለም አያውቅም ነበርን ???
የአለምንስ ፍፃሜ አያውቅምን ???
የእግዚአብሔርን ፍፁም አዋቂነት የሚያምን ሁሉ አያውቅም ሊል
አይችልም።
ራሱ ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ( ማቴዎስ 25 ቁጥር 34 )
በዚህ ትምህርቱ አለም ሳይፈጠር እመቤታችን በመታሰቧ ብቻ ሳይሆን ከእርሷ ሰው ሁኖ ዓለምን ማዳኑ በእለተ ምፅአትም በቀኙ የሚቆሙትና በግራ የሚቆሙት ሁሉ መታወቃቸው ተፅፏል።
አለም ሳይፈጠር ስሉስ ቅዱስ በፈቃ ድ አንድ መሆናቸውና የአካላዊ ቃል ከእመቤታችን ሰው መሆኑ መታወቁ ብቻ ሳይሆን በሰው ድህነትም ስላሴ መደሰታቸው ለማስረዳት ጌታችን
መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፤ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ
አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። ( ዮሐንስ ምዕ 17 ከቁጥር 20-21 )
ይህ ንግግር አካላዊ ቃል በተዋህዶ ሰው በመሆኑ ሰውን መውደዱን አብ ቅድመ ስጋዌ በስጋዌ መደሰቱን ለመግለፅ
የተነገረ ነው።

እመቤታችን በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር ነበር የሚለውም ስጋዌው አለም ይታወቃል ከእመቤታችን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑ መታወቁም እርሷ አለም ሳይፈጠር
ተመርጣለች ታውቃለች ለዚህም ታስባ ትኖር ነበር ማለት ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ይህን በዚህ መልክ የአምላክ ሰው መሆን መታወቁ ትክክል ነው ነገር ግን እመቤታችን ገና ሳትወለድ
እንዴት ልትታወቅ ትችላለች ?
የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ፦
፤ ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። ( መዝሙር ምዕ 139 ቁጥር
16 ) በማለት የማያዳግም ምላሽ ሰጥቶናል። ቅዱሱ ወደፊት የሚመጣው ነገር ከመኖሩ በፊት አንድስ እንኳ
ሳይቀር በመፀሀፍ ቀድሞ መፃፉን ከነገረን ስለ እመቤታችን እንዲህ መባሉ ከቅዱስ መፀሀፍ ልዩነት እንደሌለው ያሳየናል። አንዳንዶቹ ደግሞ የእግዚአብሔርን አዋቂነት ቢያምኑም
እመቤታችን ብቻዋን አታውቅም የሚል መከራከሪያን ያመጣሉ ይህ ንግግራቸውም እራሳቸው ለእመቤታችን ያላቸው አመለካከት ወይም ያሳየናል እንጅ አይናቸውን ጨፍነው መካድ
የሚፈልጉ መሆናቸውን የቅዱሳት መፀሀፍት እውቀታቸውን
ሊያሳይ አይችልም። እግዚአብሔር ሁሉንም ያውቃል ስለሁሉም ግን አልተናገረም አልተፃፈም ትንቢት የተነገረላቸው ወይም በስራቸው
እግዚአብሔርን ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኙት እርሱ ያወቃቸው
ብቻ ናቸው።
🔍 ነብዩ ኤርሚያስን ፦ በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ
ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። ( ኤርምያስ ምዕ 1 ቁጥር 5 ) ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ሌሎቹን በእናታቸው ማህፀን
አያውቃቸውም ሳይወለዱና አድገው የሚሆኑትን ሳይሆኑ
አስቀድሞ አያውቅም ማለት አይደለም ቅዱስ ዳዊት ፦
💠 መዝሙር ምዕ 22 ቁጥር 10 ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ። ( መዝሙር
ምዕ 22 ቁጥር 10 ) እንዳለ ሁላችንንም አስቀድሞ ያውቀናል። ነብየ እግዚአብሔር ኤርሚያስ የተናገረው ግን በተለየ ሁኔታ ትንቢት የተነገረላቸው ሰወች አስቀድሞ የሚሆኑትና ቅድስናቸው የታወቀላቸው መሆኑን መናገር ነው። ለአህዛብም ነብይ አድርጌሀለሁ ያለው ገና ሳይወለድ ነው።
ነብይነትን ተሽሞ ወይም ተቀብቶ በምድር ላይ ከመጣ በኋላ
አይደለም። ነገር ግን ከተወለደና ካደገ በኋላ የሚደርስበት መዓረግና
ቅድስና አስቀድሞ ( ቀድሞ ) የሚታወቅ መሆኑን መናገሩ ነው።
💠 ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲወስ ሲፅፍለት ፦.ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤
( 1ኛ ጢሞቴዎስ ምዕ 1 ቁጥር 18 )
ያለው በጢሞቲወስ በስም ተጠቅሶ ትንቢት ተነግሮለት አይደለም።
ነገር ግን ስለ ሐዲስ ኪዳን ካህናትና ሐዋርያት የተነገረው ለእርሱ የተነገረ መሆኑ የታወቀ በመሆኑ ነው።
ሥጋዌውን ዓለም ሳይፈጠር እግዚአብሔር ያውቀዋል ፣
ያስበዋል ማለትም እመቤታችን ታስባ ትኖር ነበር ማለት ነው።
።።።።።።።///።።።።።።
#በዓለም_ሳይፈጠር_በፊቱ_ቅዱሳንና_ነውር_የሌለን_በፍቅር_እንሆን_ዘንድ_በክርስቶስ_መረጠን ። ( ኤፌ ምዕ 1 ከቁጥር 4 እስከ 14 )
እመቤታችን አለም ሳይፈጠር በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር ነበር የሚለው የተኣምረ ማርያም መቅድም ምንም አይነት ሕፀፅ የለውም መፀሐፍ ቅዱስም ይደግፈዋል።
።።።።።።።///።።።።።።።።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ባይነት
የእናታችን የድንግል ማርያም አማላጂነት
የቅዱሳን ፀሎት የመልዐክት ፈጣን ተራዳኢነት ከምናምነው ጋር
ይሁንልን አሜን።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ክርስቶስ


✞ "ክርስቶስ" የሚለው አጠራር ሥረ መሠረቱ ጽርዕ (ግሪክ) ነው። ቅቡዕ (የተቀባ) የሚል ትርጉም አለው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በክርስቶስ ያመኑ፡ ማኅተመ መንፈስ ቅዱስን እንዲያገኙ የሚቀቡት "Chrism" (ቅባት) ወይም ሜሮን ይቀባሉ፤ ሥርዓቱም "Chrismation" (ምሥጢረ ሜሮን) ይባላል። በክርስቶስ ያመኑ ምሥጢሩ ሲፈጸምላቸው "ቅቡዓን" (በመንፈስ ቅዱስ የተቀቡ) መባላቸውን እናስተውላለን።.. እርሱን በጸጋ መስለው ወደሚኖሩበት ሃይማኖት ስለገቡ፤ እርሱ ወልድ ሲባል፡ እነሱም ውሉድ ይባላሉ፤ እርሱ ቅቡዕ ሲባል እነሱም ቅቡዓን (ክርስቶሳውያን) ይባላሉ።.. "ርኢኬ ዘከመ ያስተባዝኅ ክርስትናሆሙ በከመ ክርስቶስ ውእቱ፡ ወይሰምዮሙ መሲሓውያነ በከመ መሲሕ ውእቱ፤ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ የክርስቲያንን መጠሪያቸውን እንዳባዛ ተመልከት፡ እርሱም መሲሕ እንደሆነ መሲሓውያን ይላቸዋል" (መጽ. ምሥ. ንባብ ዘበዓለ ሃምሳ ቁ. 65) በማለት ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ሰግላዊ እንደተናገረ።.. ወደ ዋናው ርእሰ ጉዳያችን እንመለስ።

"ክርስቶስ" የሚለው የወልደ እግዚአብሔር ስም፤ ራሱ ወልድ ለአድኅኖተ ዓለም ከሁለት ባሕርያት በፍጹም ተዋሕዶ አንድ ባሕርይ ሆኖ ሲገለጥ የተሰጠው ስም ነው። ክርስቶስ (ቅቡዕ) የቃልነቱ ብቻ ስም አይደለም፤ የትስብእቱ ብቻ ስም አይደለም። በተዋሕዶ ሰው ሲሆን የተሰጠው ስም ነው እንጂ። ከሥጋዌ በፊት ክርስቶስ አልተባለም። "ወእነግር አነሂ ከመ ኢመፍትው እስምዮ ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእንበለ ትስብእት፡ ወኢለትስብእት ዘእንበለ መለኮት፤ ክርስቶስሃ ይሰመይ። ወእምቅድመ ትሥጉት አልቦ ዘይሰምዮ በዝንቱ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ" (የ ማቴ 1፡ 16 አንድምታ ትርጓሜ) ተብሎ እንደተነገረ።

ቅብዓት ማለትም ክብር (መክበር) ማለት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅቡዕ (የከበረ፤ ክብር ያገኘ) መባሉ በትስብእቱ (በሥጋው) ነው እንጂ በቃልነቱ አይደለም። ከላይ የጠቀስነው ወንጌል ትርጉም ክፍል ላይ "ወዝ ስም ክርስቶስ ወፍካሬሁ ቅብዓት ምስለ አምጣነ ትስብእቱ ረከቦ ለዋሕድ" በማለት ይገልጸዋል። በዚሁ መረዳት ያለብን ነገር ጌታ ሲቀባም፡ ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው፤ የቅጽበተ ዓይን ያህል እንኳ የጊዜ ልዩነት አለመኖሩን ነው።

በመዝሙር መጽሐፍ "አፍቀርከ ጽድቀ ወዐመፃ ጸላእከ፤ በእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ" (መዝ 44) ተብሎ የተነገረውን እንመልከት። ጽድቅን (ሰው መሆንን) ወደድህ፡ ዐመፃን (ሰው አለመሆንን) ጠላህ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር (እግዚአብሔርነትህ) በተዋሕዶ አከበረህ (አዋሐደህ) ብለን እንረዳዋለን። እግዚአብሔር ቀባህ፡ እግዚአብሔርነትህ ቀባህ ቢባል ምሥጢሩ አንድ ነው። በሥላሴ ያለች የአክባሪነት ሥልጣን አንዲት ናትና። ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ስንናገር "እግዚአብሔር አስነሳው"፣ "እግዚአብሔርነቱ አስነሳው"፣ "በራሱ ሥልጣን (ሀይል) ተነሳ" ብንል ምንም ልዩነት እንደሌለው ሁሉ። ... ስለዚህም ስለ ክርስቶስ "ለሊሁ ቀባዒ፡ ወለሊሁ ተቀባዒ" (ራሱ አክባሪ፡ ራሱ ከባሪ) ተብሎ ይነገራል።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሰው ፍጡር ሆኖ ሲንቀን
እግዚአብሔር ግን አምላክ ሆኖ
ያከብረናል ያከበረን አምላክ
ይከብር ይመስገን ለዘለአለም!
🙏 አሜን 🙏
ቤተ ክርስቲያን: አገር አቀፍ የሰላም እና ስብከተ ወንጌል ስምሪት ልታካሒድ ነው
@And_Haymanot
• ሥልጠናን፣ሕዝባዊ ውይይትንና ዕቅበተ እምነትን ያካተተ ስምሪት ነው፤
• እስከ ታኅሣሥ መጨረሻ ድረስ፣52 አህጉረ ስብከትን ለማዳረስ ታቅዷል፤
• በወቅቱ ፈተናዎች፥የካህናትና የወጣቶች መብትና ግዴታ ላይ ያተኩራል፤
• በሰማዕትነትና በሚዲያ አጠቃቀም ረገድ ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት ያነቃል፤
*
• ከ9ሚ. ብር በላይ በጀት ተመድቧል፤250 ጠቅላላ ልኡካን ይሳማሩበታል፤
• በእያንዳንዱ ስምሪት በሊቀ ጳጳስ የሚመሩ 5፣ 5 ልኡካን ይሳተፉበታል፤
• ዓላማውን የሚያስፋፉ ንኡሳን ኮሚቴዎች በየአህጉረ ስብከቱ ይቋቁማሉ፤
• ካህናትና ምእመናን ከአቀባበል ጀምሮ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፤
*
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ ከነገ በስቲያ ኀሙስ፣ ታኅሣሥ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል የሚዘልቅ የአገራዊ ሰላም እና የስብከተ ወንጌል ስምሪት ሊያካሔድ ነው፡፡

በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለውና በቀላሉ የሚገታ የማይመስለው የሰላም ዕጦት ችግር ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሔደው የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባው ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት የተዘጋጀው ስምሪቱ፣ ቤተ ክርስቲያናችን በሰላም ዕጦት የሚገጥማትን ተግዳሮት የምትቋቋምበትና ለአገራዊ ዕርቅና ለሕዝብ አንድነት መጠበቅ ያላትን ታሪካዊና ብሔራዊ ሚና የምትወጣበት እንደኾነ ተገልጿል፡፡

ስምሪቱ፥ የሥልጠና፣ የሕዝባዊ ውይይትና የዕቅበተ እምነት መርሐ ግብሮችን ማካተቱ ተጠቅሷል፡፡ ካህናትን በሚያሳትፈው ሥልጠና፦ የካህናት ድርሻ በሀገር ሰላም፣ የካህናት መብት እና ግዴታ፣ የካህናት ኖላዊነት(እረኝነት)፣ የካህናት መሪነት እና ዕቅበተ እምነት በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እንደሚሠራ ተጠቁሟል፤ የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች መብት እና ግዴታ፣ ወጣትነት እና ሰማዕትነት፣ ወጣትነት እና ወቅታዊ ፈተናዎች እንዲሁም መንፈሳዊ ወጣት እና የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በሚሉ ርእሶችም የሰንበት ት/ቤት እና የአካባቢ ወጣቶችን የሚያነቁና የሚያስገነዝቡ ዐውደ ትምህርቶች መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

በአገር ሰላም እና በሕዝብ አንድነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩት የውይይት መርሐ ግብሮች፣ ከቤተ ክርስቲያን ምእመናን ውጭ የኾኑ ዜጎች የሚሳተፉበት ሕዝባዊ አቀራረብና ይዘት እንዳላቸው ታውቋል፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሰብሳቢነት የተቋቋመውና 6 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ መምሪያዎችና ድርጅቶች፣ ከሰንበት ት/ቤቶች አገር አቀፍ አንድነት፣ከማኅበረ ቅዱሳን፣ ከነገ መለኰት ምሩቃን ማኅበር እና ሌሎች መንፈሳውያን ማኅበራት እንዲሁም ከመንፈሳውያን ኮሌጆች ተውጣጥቶ የተቋቋመና 15 ጠቅላላ አባላትን ያቀፈ የሥራ አስፈጻሚ ዐቢይ ኮሚቴ፣ በአምስት ንኡሳን ኮሚቴዎች በመደራጀት፥ ተሳታፊ ልኡካንን የመመልመል፣ የስምሪት ቦታዎችን የመለየትና አስፈላጊውን በጀት አጥንቶ የማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ ተነግሯል፡፡

250 ጠቅላላ ልኡካን የሚሳተፉበት ይኸው መርሐ ግብር፣ 52 የሀገር ውስጥ አህጉረ ስብከትን እንደሚሸፍንና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ወጪ የተደረገ 9 ሚሊዮን ብር የማስፈጸሚያ በጀት እንደተመደበለት ታውቋል፡፡ እያንዳንዱ ስምሪት 5፣ 5 ልኡካን የሚይዝና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ እንደሚኾን ተጠቅሷል፡፡ ስምሪቱን በአህጉረ ስብከት ደረጃ የሚያቀናጁ፣ ሥልጠናውንና ውይይቱን እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ የሚያስፋፉ የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የማኅበራት ተወካዮች፣ የመንግሥት አካላትና የአገር ሽማግሌዎች ንኡሳን ኮሚቴዎች በየክፍሎቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት ይቋቋማሉ፤ ተብሏል፡፡

ካህናት፣ ምእመናንና ወጣቶች፣ ለልኡካኑ አቀባበል ከማድረግ ጀምሮ የአካባቢያቸውን ችግሮች በማሳወቅ፣ በመወያየትና መፍትሔ በማስቀመጥ በሥልጠናውም በሕዝባዊ ውይይቱም በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከነገ በስቲያ በይፋ የሚጀመረው የሀገራዊ ሰላምና ስብከተ ወንጌል ስምሪት ቀዳሚ ተሳታፊ ልኡካን፣ በነገው ዕለት በሥራ አስፈጻሚ ዐቢይ ኮሚቴው የተዘጋጀ ገለጻ/ኦሪየንቴሽን/ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንደሚሰጣቸው ታውቋል፡፡ ጠቅላላ የስምሪት መርሐ ግብሩን እስከ ታኅሣሥ 26 ድረስ በማጠናቀቅ፣ በውጭ አህጉረ ስብከት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመቀጠል መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፦ ሐራ ዘተዋዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሳታቋርጡ ጸልዩ
"ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተፀምዶ መዋል አይችልም አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው
ድምፅ ሳይኾን አሳብ ነው፤ እጅ ሳይኾን እደ ልቦናን ማንሣት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም
አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፣ ደረትህንም ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከኾነ ጸሎትህ ሥልጡን
ነው።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ -
(አምስቱ የንስሐ መንገዶች መጽሐፍ ገጽ 32 -
#በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​✞ እንስሳት ከአምላክ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው ያውቃሉ? ✞
@And_Haymanot
እንስሳት ተንኮለኞች አይደሉም፡፡ በዘፈቀደ የሚንቀሳቀሱ ይምሰሉ እንጂ አንዳንዴ ከሰው የሚሻሉበት አጋጣሚ አይጠፋም፡፡ አይዋሹም፡፡ አያታልሉም፡፡
የአምላካቸውን ህልውናም አይክዱም፡፡ ለዚህም ይመስላል አምላክ በእነርሱ
በኩል ጥበቡን የሚገልጸው፡፡ በአገራችንም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ታዲያ ሰው በማይታዘዝበት ዘመን ቅዱሳን እንስሳትንም ሆነ ነፍሳትን ሲያዙ ማየት አዲስ አይደለም፡፡

እንደ ንቡ ሚካኤል ባሉ ቦታዎችም እንስሳት እና ነፍሳት የአምላክን
ጥበብና ቸርነት ሲገልፁ ይታያሉ፡፡
.
ከታች የሚታዩት በግሪክ አገር በተሰሎንቄ አቅራቢያ ከሚገኘው የኤቶስ ተራራ
(Mount Athos) የተገኙ ምስሎች ናቸው፡፡ ይህ ተራራ የብዙ ቅዱሳን መኖሪያ በመሆኑ በዓለም ይታወቃል፡፡ ታዲያ በዚህ አካባቢ የሚገኙ ንቦች በቅዱሳን ስዕላት ላይ ቀፎን ይሰራሉ፡፡ ሆኖም ግን በአርኪቴክት የተሰመረላቸው ይመስል የሚሰሩት በቅዱሳኑ ዙሪያ ለክተው ነው፡፡ በምንም ተዓምር የቅዱሱን/የቅድስቷን
ፊት ደግሞ አይነኩም፡፡

የእግዚአብሔር ሥራ አይደንቀም?
.
ምስሉን የሰጠኝን ወንድማችንን Carlito Frédéric Cadiou በክርስትና ስሙ
ገብረእግዚአብሔር ብላችሁ በጸሎት አስቡልኝ፡፡ እኔንም ወንድማችሁን
ገብረመስቀልን በጸሎታችሁ አስቡኝ ።
ይቆየን
Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
❖ "ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤ በኃጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል።"
መዝሙረ ዳዊት 58:10


ምን ለማለት ፈልጎ ነው?

መልስ፦ ንጉሥ ዳዊት የተናገረው ስለ ክርስቶስ ነው። ጻድቅ የተባለው እርሱ ነው (በእኛም "ጻድቀ ባሕርይ" መባሉን እናውቃለን)። እርሱም የሚበቀለው ኀጢአትን፣ ሞትን እና ዲያብሎስን ነው ይላል መጣፉ ... "በኀጢአተኛውም ደም እጁን ይታጠባል" ሲል ድል መንሳቱን መናገር ነው።[ምንጭ፦ Orthodox Study Bible]፥
@And_Haymanot
@And_Haymanot