፩ ሃይማኖት
8.95K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
🎄🎄 የገና ዛፍ 🎄🎄
🎉🎊🎁 🎁 🎁 💥🌲
የገና ዛፍ የባእድ አምልኮ ስርኣት ነውና ከሀገራችን በአፋጣኝ ልናስወግደው ይገባናል!!!
በምዕራቡ ዓለም የክረምቱ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ይረግፋሉ። ልምላሜ አይታይባቸውም። ፅድ ግን በተፈጥሮው ይህን አስቸጋሪ ወቅት ተቋቁሞ የማለፍ ኃይል አለው። በመሆኑም ፅድ ክፉውን ዘመን /ክረምቱን/ ተቋቁሞ መልካሙ ዘመናቸው እስኪመጣላቸው ድረስ በልምላሜ ይቆይላቸዋል። ይህም ሳተርን /ደጉ አምላካቸው/ ከክፉው
አምላክ ለመሸሸግ በፅድ ውስጥ ተደብቆ ይኖራል ብለው ያመናሉ ምዕራባውያኑ። እናም ብራ ሲሆን /በእኛ መስከረም ጠባ እንደምንለው ነው/ የደጉን አምላክ ‹‹የእንኳን ደህና መጣህ›› በዓልን በድምቀት ያከብራሉ።

ተወዳጆች ሁላችንም ለቤተክስቲያናችን ዘብ እንቁም!! በየቤታችንም ገዝተን የምንጠቀም እንዲሁም በየሆቴሎች የሚደረገውንም ለሆቴሎቹ ማኔጀሮች
በትህትና በማግባባት የባህል ወረራው እና የባእድ አምልኮ ልምምዱ ባፋጣኝ እንዲቆም የበኩላችንን እንወጣ!!!!

ቱሪስቶች ቤታቸው እንዳሉ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው በምትል ማደንዘዣ እንዳታዘናጉን አደራ!! ቱሪስት የገዛ ቤቱን ስርኣት ለማየት አይመጣም!!! የሚመጣው የእኛን ስርኣት ለማየት እንጅ የራሱን ሀገር ስርኣት ለማየት አይደለም።
ባዕድ አምልኮ መሆኑን ተረድተን ይህን ከማድረግ እንቆጠብ፡፡
....ይቆየን [በዚሁ ርዕስ በስፋት እንመለሳለን]
Share በማድረግ ይህን ለምናውቃቸው እናሳውቅ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አንድ ነገር እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ ተመሳስለው የገቡ ቄስ መስለው፣መነኩሴ መስለው፣ ሰባኪ መስለው ስህተትን ለሚዘሩ መናፍቃን ቦታ የለኝም።
ካንሰርን ካልቆረጡት እንደ ማይድን ሁሉ እነዚህንም ቆርጠን እናስወግዳቸዋለን መቀሱ በእጄ ነው! ነገር ግን ንስሃ እንድትገቡ ቀድሜ እመክራችኋለው አባ ሄኖክ በሬ 24 ሰዓት ክፍት ነው።"
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ከተናገሩት የተወሰደ
14/04/2011
@And_Haymanot
@And_Haymanot
🙏🙏ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ🙏🙏

እንኳን አደረሳችሁ
Channel photo updated
🎄 የገና ዛፍ 🎄
🎉🎊 🎁 🎁 🌲
@And_Haymanot

🎄 የገና ዛፍ የነጮች የባዕድ አምልኮ መገለጫ መሆኑን ያውቃሉ? የገና ዛፍ ታሪክና አመጣጡ የገናን ዛፍ የት መጣውን /ምንጩን/ ስናጤነው ቅዱሳት
መጻሕፍት እንዲህ ይነግሩናል። በዞራስተርን የሁለት አማልክት
ዕምነት የሚያምኑት ምዕራባውያን አዲሱን ዓመታቸውን /2017/
ተቀብለዋል። በዞራስተርን የሁለት አማልክት ዕምነት መሠረት ክፉውና ደጉ የተባሉ ሁለት አማልክቶች አሉ። እንደ ዕምነቱ አስተሳሰብ ከሆነ እዚህ ምድር ላይ የሆነው እየሆነው ያለውና
የሚሆነውም ማንኛውም ነገር በሙሉ የሚከናወነው በእነዚህ በሁለቱ አማልክቶች ፉክክር ነው። ክፉው አምላክ ከሰለጠነ /የበላይ ከሆነ/ በምድር ላይ ክፉ የሆኑ ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። በተቃራኒው ደግሞ ደጉ አምላክ ከሰለጠነ በጎ ነገሮች ይከሰታሉ
ማለት ነው። ምዕራባውያኑ ታዲያ ደጉን አምላካቸውን ማለትም ጣዖታቸውን ሳተርን ብለው ይጠሩታል።

በምዕራቡ ዓለም የክረምቱ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ይረግፋሉ። ልምላሜ አይታይባቸውም። ፅድ 🎄 ግን በተፈጥሮው ይህን አስቸጋሪ ወቅት ተቋቁሞ የማለፍ ኃይል አለው። በመሆኑም ፅድ ክፉውን ዘመን /ክረምቱን/ ተቋቁሞ መልካሙ ዘመናቸው እስኪመጣላቸው ድረስ በልምላሜ ይቆይላቸዋል።
💫 ይህም ሳተርን /ደጉ አምላካቸው/ ከክፉው አምላክ ለመሸሸግ በፅድ ውስጥ ተደብቆ ይኖራል ብለው
ያመናሉ ምዕራባውያኑ። እናም ብራ ሲሆን /በእኛ መስከረም ጠባ
እንደምንለው ነው/ የደጉን አምላክ ‹‹የእንኳን ደህና መጣህ›› በዓልን በድምቀት ያከብራሉ። ምስጋና ለፅዱ ይሁንና ደጉ አምላካቸውን ደብቆ ስላቆየላቸው ባለውለታ ስለሆነ የደጉን አምላክ የእንኳን ደህና መጣህ በዓል
ሲያከብሩ ታዲያ ፅድን ለበዓላቸው ማድመቂያነት ይጠቀሙበት ነበር። ይኸው ትውፊታቸው ዛሬም ድረስ አለ። በአጭሩ ከጥንት ጀምሮ እነርሱ ይኽን በዓል የሚያከብሩት ሳተርን ለተባለው
ጣዖት /ደጉ አምላክ/ ያደርጉት የነበረው ሥርዓት ነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን በአዋጅ
ካስፋፋበት ጊዜ ጀምሮ በውጭው ዓለም ጥንት የነበሩ ብዙ ጣዖታዊ በዓላት ክርስቲያናዊ በዓል ሆነው አሁንም ድረስ በብዙ ሀገራት እየተከበሩ ይገኛሉ። /ነገር ግን ልደትንና ትንሣኤን ጨምሮ ሌሎችም በዓላት ቢሆኑ ሥርዓታቸውን በጠበቁ መልኩ የሚከበርባቸው አንዳንድ ሀገራት እንዳሉ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ
ለማስገንዘብ ይወዳል።/

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ይኸው እስከዛሬ እኛም ይኽንኑ የባዕድና የጣኦት አምልኮ በዓላቸውን በእነሱው ልማድ መሠረት የፅድ የገና ዛፍ እየሠራን
ስናከብርላቸው ኖረናል። አባቶቻችን ሲናገሩ ‹‹እግዚአብሔር ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰው ሆኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበቡ እጅግ ረቂቅና ጥልቅ ነው›› ይላሉ። እንዴት ደስ የሚል
አገላለፅ ነው!!! ታዲያ ምን ዋጋ አለው? አለመታደል ሆኖ ይሁን አሊያም አለማወቃችን ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋን ይግባውና እጅግ ድንቅ የሆነውን የጌታችንን የአምላካችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ከእንደዚህ ዓይነቱ ምዕራባዊ የጣዖት በዓል ጋር ቀላቅለን እናከብራለን።
@And_Haymanot
👉 ይህ እጅግ አሳዘኝ ነገር ነው በእውነት! በአንድ ወቅት በምዕራባውያን የገና በዓል ሰሞን በ‹‹BBC channel 4›› ላይ የበዓል መርሀ ግብር /program/ ቀርቦ ነበር። በመርሀ ግብሩ ላይ የተለያዩ የዕምነት ድርጅቶች የበዓል
አከባበር፣ የጸሎትና የመዝሙር ሥርዓትና ሌሎችንም ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ከቀረቡ በኋላ የመርሀ ግብሩ መሪ
በመጨረሻ እንዲህ ነው ያለው፡- “now let us see the real Christianity” ማለትም “አሁን እውነተኛውን የክርስትና
ሃይማኖት እንመልከት” በሚል መሸጋገሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የበዓል አከባበር ስነ-ሥርዓት ማስተላለፍ ጀመረ። ካህናት አባቶች ወረብ ሲያቀርቡ፣ የቅዳሴውን ሥርዓት፣ መዝሙሩ ሲዘመር፤ ጧፉ እየበራ ወንጌሉ ሲነበብ፣ እጣኑ እየጤሰ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲቀርብ......
ሁሉንም በየተራ ማቅረብ ጀመረ። እናም እነርሱ ማለት ምዕራባውያን ስለ ዕምነት ጉዳይ እውነት የሆነውን ነገር ፍለጋ
ፊታቸውን ወደ እኛ ባዞሩበት ወቅት እኛ ደግሞ እውነተኛውን ማንነታችንን ባንጥልና የአጉል ባህል ተገዢዎች ባንሆን ብሎም በአምልኮ ጣኦታቸው ተሳታፊዎች ባንሆን መልካም ነው።
መልካም ነው ብቻም ሳይሆን መንፈሳዊና ሞራላዊ ግዴታዎችም አሉብን።
በእርግጥ እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች የግሎባላይዜሽን ጎርፍ ጠራርጎ የወሰደን ስለሆንንና ‹‹በጣም ስልጡኖችና ዘመናውያንም›› ስለሆንን ይህ ምን ማለት እንደሆነ ላይገባን
ይችላል፤ እንዲገባንም አንፈልግም፡፡
የሴቶቻችን እርቃን መሄድ፣ አካሎቻቸውን መነቀስና መበሳት፣ የወንዶች አለባበስና ፀጉር አቆራረጥ… እነዚህና ሌሎቹም ነገሮች በዘመናዊነት ሰበብ የመጡብን የዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውጤቶች
ናቸው፡፡ በግል አዳኝ ‹‹ኢየሱሴ›› ስም ብዙኃኑን ሕዝባችንን ፈጣሪውን አስክደው አምላክ የለሽ አደረጉትና ለግሎባላይዜሽናቸው የተመቸ ዝርው ትውልድ ፈጠሩ፡፡ አሁንማ ጭራሽ ለይቶላቸው ‹‹church of Satan›› በማለት ‹የሰይጣን ቤተክርስቲያን› ከፍተው አባሎቻቸው በሆኑ ‹‹ታዋቂ የሂፖፕ›› አቀንቃኞቻቸው አማካኝነት የአባላቶቻቸውን ቁጥር ለመጨመር
እኛም ሀገር ብቅ ብለውልናል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት እንደግለሰብ ነፃነት አድርጋችሁ ካልተቀበላችሁ እርዳታ አንሰጣችሁምም ተባልን፡፡ እሺ እነዚህና ሌሎቹም አስከፊ ኃጢአቶቻቸውን
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እንድንቀበል ቢያስገድዱንም
ቢያንስ እኛ በራሳችን ጊዜ ለምን የራሳችንን ባሕል ድምጥማጡን
በማጥፋት የእነርሱን ባሕል እንከተላለን? የዘመናዊነት መገለጫው የራስን ባሕልና እምነት በሌሎች መተካት ሆነ
እንዴ? ድሮ ቅኝ ቅዛት ተገዝተን ቢሆን ኖሮ ምንድን ነበር የምናጣው? ቀላል ነው መልሱ፡- የራስ ማንነት፣ እምነት፣ ባሕል፣ታሪክ…አይኖረንም ነበር፡፡ አሁን ታዲያ በዘመናዊው ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት ምክንያት እነዚህን ነገሮች አላጣናቸውም ይሆን?

🙏 እንዲያው በመድኃኔዓለም! እባካችሁ ከፊት ለፊታችን በታላቅ ጉጉትና ተስፋ የምንጠብቀውን ከድቅድቅ ጨለማ ወጥተን ብርሃን ያገኘንበትን የአማኑኤልን የልደት በዓል የገናን ዛፍ በመጠቀም ከነጮቹ ባዕድና ጣኦት አምልኮ ጋር አንቀላቅለው፡፡ ልደቱን ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደሚገባው አድርጋ ታከብረዋለችና እኛም ልጆቿ እንደሚገባው መጠን ልደቱን እናክብር፡፡ የገና ዛፍ የባዕድ አምልኮ መገለጫ ነው፡፡ ማህቶተ ቤተክርስቲያን ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ምንድን ነበር
ያለው! ‹‹ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
የእግዚአብሔርን ታቦት በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማነው?
2ኛ ቆሮ 6፡14-16፡፡ “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ” 2ኛ ቆሮ 13፡5፡፡ ተዘጋጀ በጀማል ሀሰን ዓሊ (ስመ ጥምቀቱ ገብረሥላሴ) የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በሃይማኖታችንና በኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን ያፅናን አሜን።
(የጽሑፉ ምንጮች፡- አናቆጸ ሲኦል በብርሃኑ ጐበና፤ ሐመር 5ኛ
ዓመት ቁ1፣ 1989 ዓ.ም
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ውርጃ


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ

ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን?

ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ግብር እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። ✞

ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገፅ 53
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የኔ አባት…. ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት

@And_Haymanot

(ያንብቡ ለሌሎች ያጋሩ)

👉 የኔ አባት ብዙ ጊዜ ሳዮት የሰንበት ትምህርት ቤት ነገር የገባዎት አልመሰለኝም... መቼስ ከርሶ ባላውቅም ጥቂት ልበልዎት.. አደራ ያስተውሉኝ!

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… እኛ ልጆችዎ ሰው የሆንበት ሥፍራ ነው። ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… በፍቅር ወድቀን፣ በፍቅር ተነሥተን፣ በፍቅር ተርበን፣ በፍቅር በልተን፣ በፍቅር ተጣልተን፣ በፍቅር ታርቀን፣ በፍቅር ተኮራርፈን ፣ በፍቅር ተጨዋውተን፣ በፍቅር አልቅሰን፣ በፍቅር ስቀን፣ በፍቅር ኮርኩመን፣ በፍቅር ተኮርኩመን፣ በፍቅር ተፎካክረን፣ በፍቅር ተሸናንፈን፣ በፍቅር ተምረን፣ በፍቅር ተተራርበን፣ በፍቅር አጥፍተን፣ በፍቀር ታርመን እኛነታችን የተሠራበት ቦታ ነው፡፡ አባቴ ይሙቱ! … እኔ በርሶ ምዬ አልዋሽም፡፡

❖ ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… በፍቅር ባሪያ የሆንበት፣ በፍቅርም ገዢ የሆንበት ቦታ ነው፡፡ አሽከርም ንጉሥም ሆነንበታል፤ አባቴ አሽከርና ንጉሥ በአንድ ጊዜ ሆነው ያውቃሉ? በፍቅር ባሪያም ገዢም ሆነውስ ያውቃሉ? በእውነት እንደዛ ከሆኑስ እርሶም ሰንበት ተማሪ ኖት ማለት ነው፡፡ ነቃሁቦት፤ ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት ልጅ ሳለን ሥራ አመራርን ያጠናንበት፣ የሕዝብ አስተዳደርን የተማርንበት ፣ በተለያየ ሙያ ስብጥር የተሰባጠርንበት፣ ለአረንጓዴ ልማት አትክልትን የተከልንበት፣ በሀገር ፍቅር የነደድንበት፣ በዕቅበተ እምነት የበለጸግንበት፣ በበጎ አድራጎት ስለ ወገን ማሰብን ያየንበት፣ ለሀገር ጥሩ ዜጋ መሆንን የቀሰምንበት ቦታ ነው፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… ካለዘር ክፍፍል የተፋቀርንበት፣ እገሌ ከዚህ ነው እገሌም ከዚያ ነው ያልተባለበት ሰሜንና ደቡብ፣ ምዕራብና ምስራቅ የሌለው ቦታ ነው፡፡ ሰንበት ተማሪ ሲሆኑ አባቴ… ብሔሮ ክርስትና፣ ቋንቋዎ ፍቅር ፣ ሀገርዎ በሰማይ ፣ ንጉሦ ክርስቶስ ይሆናል፡፡

✞ እመቤቴን! የኔ አባት… መቼስ ከእርሶ አናውቅም፣ እንደርሶ ሊቅም አይደለንም፣ ብሉዩን ከሐዲሱ ፣ ሊቃውንቱን ከመነኮሳቱም አናመሰጥር ይሆናል፤ ሰንበት ተማሪ ሲኮን ግን አባቴ… በሐዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን ያለው እንደ እሳት የሚንቀለቀል ፍቅረ ቤተ ክርስቲያን በውስጥዎ ይነዳል፡፡ ቤተ ክርቲያን ስትነካ አካሎ እንደተቆረጠ ያንገበግቦታል፤ ትምህርትዎን ሥራዎን እርግፍ አድርገው መፍትሔ ለመስጠት ይሮጣሉ፤…. ብቻ አባቴ ሰንበት ትምህርት ቤት የቅንዐተ ቤተ ክርስቲያን እሳት የሚንቦገቦግባት ምድጃ ናት፡፡
🔷 አባቴ… ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት፣ እርሶ የሚወዷቸው ትልቁ መምህር የተማሩበት ቦታ ነው፤ እርሶ የሚያከብሯቸው ትልቁ ሊቅም ማስተማርን የጀመሩበት ቦታ ነው፤ ያኔ ተኮለታትፈው ባያስተምሩን ኖሮ ዛሬ እርሶን የመሰለ አባት በተገኙበት ጉባኤ ለማስተማር መንፈሳዊ ልምድ አይኖራቸውም ነበር፡፡ እኛ አሜን ባንላቸው ኖሮ ዛሬ በሺ የሚቆጠር ምእመን አሜን አይላቸውም ነበር፡፡ ድንግልን! በዚህ ቅንጣት አልጠራጠርም፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የሆኑ ተኩላዎች እንደጉድ የሚፈሩት ቦታ ነው፤ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች አሉበታ፤ አባቴ… ሰንበት ትምህርት ቤት እንደ ጳውሎስና እንደ ሲላስ ሲያገለግሉ የሚታሠሩበት ቦታ ነው፤ ያኔ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች የእግዚአብሔር ቅዱሳንን ነገር እየጠመዘዙ ከነገሥታት ጋር እንደሚያጣሉና በምድራዊ ፍርድ ቤት እንደሚገትሩ… በሰንበት ትምህርት ቤትም እንዲሁ ነው፤ ለሃይማኖት ሲቆረቆሩ የፓርቲ አባል የመንግሥት ጠላት ተደርገው ይከሰሳሉ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዘረፍ ሲቃወሙ በዓለማዊ ፍርድ ቤት አሸብረዋል ተብለው ይገተራሉ፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት ወንድምዎ በኃጢአት ሲወድቅ እንደእነ ቅዱስ መቃርዮስ የወንድሞን ነውር ለመሸፈን ቅርጫት የሚደፉበት ቦታም ነው፡፡ በየቦታው ሲናቁና ሲባረሩም በፍቅር ተመክረው የሚመለሱበት ገዳም ነው፡፡ በወጣትነት ብዙ እያጠፉ በብዙ የሚማሩበት ቦታም ነው፡፡

አባቴ… እውነተኛ ወንድሞች አሉዎት? በሐዘንዎ ጊዜ ሳይለዮት ከልብ የሚያስተዛዝኖት፣ ማስተዛዘን ብቻም ሳይሆን በመንፈስ የሚያጸኑዎት… ወንድሞች አሎት? አብረው ውለው አብረው አድረው… እንግዳን አስተናግደው፣ ዕቃ አጥበው የሚያግዙዎትስ እኅቶች አሉዎት? በደስታዎ ጊዜ ከእርስዎ ጋር አብረው ከልብ የሚደሰቱ፣ ድግሶን ድግሳቸው አድርገው የሚንደፋደፉ ወዳጆች አሉዎት? እኚህ ከሌሉዎት የኔ አባት አንድ ነገር ጎሎታል ማለት ነው… ሰንበት ተማሪነት አልነካካዎትም ማለት ነው፡፡

💮 ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት አንድነትና ኅብረት አካል ነሥቶ የሚያዩበት ቦታ፤ አባቴ ይሙቱ እውነቴን ነው፡፡ አንድነትና ንጹህ ፍቅር በስምንተኛው ሺ ገዝፎ የሚታይበት ገነት ነው ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡ ለዛ ነው እኮ አባቴ… ሰነፍ ሆነን እንኳን እንደ ብርቱ የምንታየው፣ ምንም ሳንደክምበት እንኳን አገልግሎታችንና ሐሳባችን የሚሞላው… ምንም ሳናውቅ እንኳን ከአዋቂዎች በላይ የምናገለግለው… አባቴ ይሙቱ… ይኸው በርሶ ምያለሁ… ይሄ ሁሉ ስለአንድነታችንና ስለፍቅራችን ነው፡፡ እንጂማ እኛ አኮ ባዶ ነን…፤ ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የኔ አባት… ባዶ ሳሉ ምሉዕ የሚሆኑባት ሥፍራ ነች፡፡

ስለዚህ አባቴ… ቢቻሎ እርሶም ሰንበት ተማሪ ይሁኑ፤ አባል ሆነው ይቀላቀሉን፤ ካልተቻሎም አባል የሚሆኑትን አይከልክሉ፡፡ ቢቻልዎት ሰንበት ትምህርት ቤትን ከልቦ ይደግፉ፤ ባለዎት ነገር ሁሉ ያበርቱ፡፡ ካልቻሉም አደራ አገልግሎቱን ከሚያደናቅፉት ፣ አባላትን ከሚያንገላቱት ጎን አይሁኑ፡፡ ቢቻልዎት ስለሰንበት ትምህርት ቤት መልካምነት ያውሩ፤ ባይቻልዎትም ዝም ይበሉ እንጂ ልጆችዎን አይሙ፡፡
ቢቻልዎት በጸሎትዎ ሰንበት ትምህርት ቤትን ያስቡ፤ ባይቻልዎትም ቢያንስ አይርገሙ፡፡

(በዲ/ን ሕሊና በለጠ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የነብያት ትንቢታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ


"በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ







@And_Haymanot
" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)

" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)

" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6


ጌ ታ ች ን

አ ም ላ ካ ች ን

መ ዳ ኒ ታ ች ን





ክርስቶስ
የእናታችን
የቅድስት
ድንግል
ማሪያም


አ ማ ኑ ኤ ል

በቸርነቱ






የሰላም
የደስታ
የፍቅር
የበረከት
የአንድነት

በዓል
ይሁንልን
አሜን!!!
አሜን!!!
አሜን!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ያለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የሚያርግ
ጸሎት እንደሌለ ያውቃሉ?

@And_Haymanot

ብዙ የተሐድሶ መናፍቃን ያለ እመቤታችን አማላጅነት የሚያርግ ጸሎት እንደሌለ ማመን ሲከብዳቸው ይስተዋላል፡፡ አንዳንዶቹ ያለ እመቤታችን አማላጅነት የሚያርግ ጸሎት የለም የሚለው
የሆነ አባት በሆነ ግዜ የተናገረው በቅዱሳት መጻሕፍት ያልተመዘገበ አድርገው ይናገራሉ፡፡
የዚህ ዓለም ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ጸጋ ርቋቸው፤በመንፈስ ድህነት ውስጥ ሲማቅቁ የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሀብቱ ተራቁቶ ነዳይ ሆኖ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን በቀጥታ ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ መቀበል ሲያቅታቸው፤ በመንፈሳዊነት በበለጸገችው፤ ጸጋን በተመላች
በእመቤታችን በኩል እግዚአብሔር አንድያ ልጁ ሰጠ፤ ዓለምም
ከእመቤታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አገኘ፡፡ ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ(St. Augustine) "The world being
unworthy to receive the Son of God directly from the hands of the Father, he gave his Son to Mary for the world to receive him from her." እንዲል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ(Saint John Eudes) እንደተናገረው "ለኢየሱስ ክርስቶስ እናት ፍቅር የሌለው ሰው እውነተኛ ክርስቲያን አይደለም- A man is no true Christian if he has no devotion to the Mother of Jesus Christ."
እንዳለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር እጥብ፣ ጥርግ፤ ሙልጭ አድርገው ከልባቸው ያወጡ መናፍቃን ዳሩ ግን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሐሰተኞች ናቸው፡፡ ስለ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ስናነሳ የግድ ስለ እመቤታችን ማንሳት ይጠይቃል፡፡

ነገረ ማርያም የነገረ ሥጋዌ መቅድም ነውና፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን ሰው ሲሆን በእመቤታችን በኩል ብቻ ነውና፡፡ ለዚህም አይደል! ቅዱስ ሊውስ(Saint Louis Marie de Montfort) "The Son of God became man for our salvation but only in Mary and through Mary." በማለት
የተናገረው፡፡ እንዳውም ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የውጭ
ሀገር ሊቃውንትም ስለ እመቤታችን ግልጽ ባለ መልኩ ከተናገሩት መካከል ቅዱስ ጀርማነስ ዘቁስጥንጥንያ(Saint
Germanus of Constantinople) ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲናገር "ድንግል ሆይ ያለ አንቺ ከክፉ ሁሉ ማንም ማምለጥ አይችልም፤ ድንግል እናት ሆይ! ማንም ምሕረት ቢያገኝ ባንቺ በኩል ነው፤ ምልዕተ ጸጋ፣ ምልዕተ ክብር;
- "There is no one, O Most Holy Mary, who can know God except through thee, no one who can be saved or redeemed but through thee, O Mother of God, no one who can be delivered from dangers but through thee, O Virgin Mother,
no one who obtains mercy but through thee, O Filled- Will – All – Grace!" ብሏል፡፡

እንዳውም ሊቁ ቅዱስ አንሴለም የተባለ አንድ ሊቀ ጳጳስ (Saint Anselm, Archbishop & Doctor of the Church) የተባለ አባት "ያለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ውዴታና ጥበቃ አንዲት ነፍስ አትድንም፡፡" ብሏል፡፡ "It is impossible to save one’s soul without devotion to
Mary and without her protection." ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ኬሊዶነስ ለተባለ ቄስ በላከው መልእክቱ ላይ (St. Gregory Nazinzen,Letter to Cledonius the priest) ደግሞ ማንም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ የማይላት ያ ሰው ስለ ነገረ
እግዚአብሔርም ባእድ ነው ሲል ተናግሯል፡፡ "If anyone does not believe that Holy Mary is the Mother of God, such a one is a stranger to the Godhead."
በመጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ላይም ሰራኤ ካህን መሥዋዕቱን፣ዕጣኑን፣ ማኅቶቱን(መብራቱን) ና አገልጋዮቹን ሲባርክ ያለውን ክፍል ያለውን ሲተረጉም "አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንበሌኪ
ማርያም ዘየዓርግ ሉዓሌ- እመቤቴ ማርያም ሆይ ምንም ዓይነት ጸሎትም ሆነ ልመና ያለ አንቺ አማላጅነት አያርግም፡፡" አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው የጠቀሱትን በማንሳት ያለ እመቤታችን አማላጅነት የሚያርግ ጸሎትም ሆነ ልመና የለም ይላል፡፡

ይኼ ማለት አንድ ኦርቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ክርስቲያን በጸሎቱ የእመቤታችን አማላጅነት በማቃለል ቢጸልይ ጸሎቱ ግዱፉ(የተተወ) ይሆናል፤ ስለሆነም አይድንም ማለት ነው፡፡ ያለ
እመቤታችን አማላጅነት ሲልኮ እመቤታችን አማላጅ ናት፤ እግዚአብሔር ደግሞ ተማላጅ ነው ማለት ነው፡፡ የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት፤ አማላጅነት በአጠቃላይ ነገረ ማርያም
ደግሞ ዶግማ እንጂ ቀኖና አይደለም፡፡ የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት፤ አማላጅነት ወዘተ …በማመን እግዚአብሔርን ቢለምን እመቤታችን ለፍጡራን ሁሉ ለማማለድ የፈጠነች ናትና ትራዳዋለች፡፡ ጸሎቱም ዉኩፍ(ተቀባይነት ያለው) ይሆናል፤
አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔርም ጻሕቀ ልቡናውን
(የልቡናውን መሻት) ይፈጽምለታል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ(St. Basil the Great) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ዘንድ ስላላት ድንቅ
ተሰሚነት ሲናገር "O sinner, be not discouraged, but have recourse to Mary in all you necessities. Call her to your assistance, for such is the divine Will that she should help in every kind of necessity."
ለዚህም አይደል ኢትዮጵያውያን መጋብያነ ምሥጢር ሊቃውንተ
ቤተ ክርስቲያን "የእናት ልመና አንገት አያስቀልስ፤ ፊት አያስመልስ" የሚሉት?!!
by Zemaryam zeleke
@And_Haymanot
@And_Haymanot
መሠረተ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ዘአሣሣ:
†††አውጣኝ አውጣኝ†††


በብፁዕ አቡነ ሰላማ /የቀድሞ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/

@Meserete_Yared_Asasa

በአንድ ዱር ጫካ ውስጥ አንበሳ በጣም ተርቦ አቤቱ ፈጣሪዬ የእለት ምግቤን ስጠኝ አብላኝ አብላኝ እያለ ይፀልያል ዱክላም ተራራው ጫፍ ላይ ሆኖ አንበሳውን አይቶ በመፍራት አቤቱ ፈጣሪዬ ከዚህ ጩኸት አውጣኝ አውጣኝ እያለ እየፀለየ ሁለቱም ይሮጣሉ አንበሳው አብላኝ ዱክላው አውጣኝ በማለት ሲሣደዱ በመሐል ጠግቦ የተኛን ዓሣማ አንበሳው ያገኘዋል አንበሳውም ተመስገን ጌታዬ ብሎ ያን አሣማ በላው ይባላል።

@Meserete_Yared_Asasa

❖ እንግዲህ ከዚህ ምሣሌ ልንወስድ የሚገባን አንበሣም አብላኝ ብሎ ፀሎት በማድረሱ ምግቡን እንዳገኘና ዱኩላም አውጣኝ ብሎ በማለቱ ፀልዮ ከፈተና እንደወጣ እንመለከታለን ነገር ግን ፀሎት ሣያደርግ እንደበላ ጠግቦ የተኛው ዓሣማ እንደተበላ ተገንዝበናል እኛም ዛሬ እንደዚህ ዓሣማ በሰይጣን ዲያብሎስ ከመዋጣችን አስቀድሞ ብርቱ ፀሎት ያስፈልገናል።

#አውጣኝ_ያለው_ወጣ_አብላኝ_ያለው_በላ
#ተኝቶ_ያለው_ዓሣማ_ተበላ

ምንጭ፦ የአቡነ ሰላማ መጽሐፈ ታሪክ ከነትምህርታቸው ገጽ 50-51

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
"ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል፡፡"
# አባ_ጽጌ_ድንግል

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
ኢያቄም ወሐና እናት አባትሽ
ቤተ እግዚአብሔር ወስደው ስዕለት የሰጡሽ
መና ከሰማያት የወረደልሽ
ፍጹም ድንግል የሆንሽ ማርያም አንቺ ነሽ
ኦ /፬/ እመ ክርስቶስ ማርያም አንቺ ነሽ
ኦ /፬/ ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ

@Meserete_Yared_Asasa

እንኳን ለበዓታ ማርያም ወርሃዊ በዓል አደረሰን!!! አደረሳችው!!!

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
በሳውላ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 35 ፕሮቴስታንት የነበሩ የሕግ ታራሚዎች ተዋሕዶን ተቀብለው ሥርዓተ ጥምቀታቸው በቅዱስ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል ተፈፆሞላቸዋል።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
#update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየምን ዛሬ  አስመረቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅርሶችን ጠብቃና ተንከባክባ እዚህ አድርሳለች ብለዋል። አሁን ያለው ትውልድ ተንከባክቦ የመጠበቅና ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለበት ሲሉም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን ዳሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ በበኩላቸው፥ ሙዝየሙን ለማዘመንና ወደ ዲጅታል ላይብረሪ ለማሳደግ በቀጣይ እንደሚሰራ ገልፀዋል። በሐመረ ኖኅ ሙዚየም ውስጥ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የታሪክ ጉዞና የገዳማት ታሪክ በከፊል የሚያሳዩ እንዲሁም በርካታ ንዋየ ቅድሳት፣ መጽሀፍት፣ አልባሳትና የተለያዩ ረጅም እድሜን ያስቆጠሩ መገልገያ ቁሳቁሶች ይገኛሉ።

Via FBC

@And_Haymanot
@And_Haymanot
ወጣቶች ጥምቀትን ለማድመቅ ያላቸው ዝግጅት እጅግ ያስደስታል

በእውነት እግዚአብሔር ጉልበታቸውን ይባርከው
🙏🙏አሜን🙏🙏
"በዓለ ጥምቀት"
@And_Haymanot
ክፍል ፩
☞1. ትርጉም

ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒ፣ በግእዝ አስተርእዮ፣ በአማርኛ
መገለጥ ፡ይባላል። ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው። በምሥጢረ ትርጉሙ ግን ጥምቀት ከሰባቱ ምጥጢራተ ቤተ
ክርስቲያን /ጥምቀት፣ ሜሮን፣ ቁርባን፣ ንስሐ፣ ክህነት፣ ተክሊለና ቀንዲል/ አንዱና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ላይ “… ሰው ከውኃና
ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም”ብሎ እንደተናገረው ከውኃና ከመንፈስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት፣ መንግሥተ ሰማያት
የምንገባበት፣ ኃጢአታችን የሚደመሰስበትና ድኅነትን
የምናገኝበት ዐቢይ ምሥጢር ነው። ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ አምኖ ለሚቀበለው ሰው ሁሉ ለኃጢአት መደምሰሻ፣ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት ለመቀበልና
የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የተሰጠ ልዩ የሕይወት መንገድ ነው።

☞2. አመጣጥ

የምሥጢረ ጥምቀት መሥራቹ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን ከጌታችን ጥምቀት በፊት
አይሁድ ለመንጻትና ለኃጢአት ሥርየት /ይቅርታ/ የሚጠመቁት ጥምቀት ነበራቸው። ይኸውም እግዚአብሔር በረድኤት በሚገለጥባቸው የተቀደሱ ዕለታትና ቦታዎች ሁሉ ሰውነትንና
ልብስን ማጠብ፣ የእግዚአብሔር ቤት መገልገያ የሆኑ ዕቃዎችን ሁሉ ማጠብ ማንጻት ሥርዓትና ልምድ ነበር። የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት አሠራር ነበር። ወደ ቤተ እግዚአብሔርም
ከመቅረባቸውና ለተቀደሰው አገልግሎት ከመግባታቸው አስቀድመው እግሮቻቸውንና እጆቸቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው፡ ሰውነታቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው።
ሰውነታቸውን ከአፍአዊ /ከውጫዊ/ እድፍ በማጠብና ንጹሕ በማድረግ በባሕርዩ ንጹሕና ቅዱስ በሆነው አምላክ ፊት ውስጣዊ ሕይወትን ንጹሕ አድርጎ የመቅረብን ሥርዓትና ምሥጢር የሚያመለክት ልማድ ነበር፦ “አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛቸው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ፣
ሙሴም አሮንና ልጆቹን አቀረበ። በውኃም አጠባቸው” /ዘዳ 29፡
4፤ ዘሌ 8፡6/። ዮሐንስ በዮርዳኖስ በኢየሩሳሌም ይሁዳ አውራጃዎች ከጌታ
ቀደም ብሎ ተልኮ “መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፣ ልጅነት በእምትና በጥምቀት ልትሰጠ ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፣ ከኃጢአትና ከበደል ተመለሱ” እያለ ለኃጢአት ሥርየት ለንስሐ ያጠምቅ ነበር። ብዙ ሰዎችም ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ከሱ ይጠመቁ ነበር። በብሉየ ኪዳን ዘመን በርከት ያሉ የጥምቀት
ምሳሌዎችን እናገኛለን። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን ለመመልከት፦

✞ 1ኛ) አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ መልከ ጼዴቅ መሄዱ የጥምቀት ምሳሌ ነው። አብርሃም የምዕመናን፣ መልከ ጼዴቅም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌዎች ናቸው። /ዘፍ 14፡17/
✞ 2ኛ) ኢዮብ በዮርዳኖስ ተጠምቆ ከደዌው ተፈውሷል። ይህም ምእመናን ተጠምቀው ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ የመፈወሳቸው / ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ/ የመዳናቸው ምሳሌ ነው።
✞ 3ኛ) ንዕማን ሶርያዊ ተጠምቆ ከለምጹ ድኗል። /2ኛ ነገ 5፡14/። ይኸውኛውም ምእመናን ተጠምቀው ከመርገመ ሥጋ
ከመርገመ ነፍስ የመዳናቸው ምሳሌ ነው።
✞ 4ኛ) የኖኅ መርከብ የጥምቀት ምሳሌ ነው። /ዘፍ 6፡13/። ይህንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጥሮስ “ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቆየ ጊዜ ደግሞ አልታዘዙም። ይህም ውኃ
ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል። የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፣ ለእግዚአብሔር የበጎ ኅሊና ልማድ ነው
እንጂ።” ሲል ተርጉሞታል። /1ኛ ጴጥ 3፡20/
✞ 5ኛ) እሥራኤል በደመና ተጋርደው ቀይ ባሕርን መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ነው። /ዘፀ 13፡21/ ። ይኽንንም ሓዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ። ሁሉም
ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ” ሲል ተርጉሞታል። /1ቆሮ 10፡2/
✞ 6ኛ) አብርሃም ሕግ ሆኖ የተሰጠው ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነው። አብርሃም ካረጀ በኋላ ቢገረዝም ልጆቹ ግን በተወለዱ በስምንተኛው ቀን እንዲገረዙ እግዚአበሔር አዝዞ ነበር። /ዘፍ 17፡9/። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእጅ ባልተደረገ
መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ” ሲል ተርጉሞታል። /ቆላ 1፡11/። እንግዲህ ጥምቀት የግዝረት
ምሳሌ በመሆኑ በኦሪቱ ዘምን ቀን ተወስኖ ሕፃናቱ ይገረዙ እንደ ነበረ በአዲስ ኪዳንም ተወስኖ ሕፃናት ወንዶች በተወለዱ በአርባኛው ቀን፣ ሴቶቹ ደግሞ በተወለዱ በስማንያኛው ቀን
ይጠመቃሉ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም፣
በዘመነ ሉቃስ፣ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ኬሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡ /ፍት ነገ አንቀጽ 19፤ ዲድስቅ 29፤ ተረፈ ቄርሰሎስ/ በተጠመቀ ጊዜ 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር። /ሉቃ 3፡23/
ለመሆኑ ጌታችን ለምን በ30 ዓመቱ ተጠመቀ? በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር
ተልዕኮና መንፈሳዊ አገልግሎት ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር። እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ለማድ
አልነበረም። የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ፣ ተልእኮአቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ
የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው። /ዘኁ 4፡3፤ 1ኛ ዜና መዋ. 23፡24፤ ዕዝ 3፡8፤ 1ኛ ጢሞ 3፡6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር። ዮሐንስ መጥምቅም
የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው።
ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40 ቀን ተሰጥቶት ያስወሰደውን ልጅነቱን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር የአዳም ልጆችን
የዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስሕተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው። ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ለይ በማረፉ አብ በደመና
“ይህ ልጄ ነው” ብሎ ሲመሰክርለት የምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል። /ማቴ 3፡16/
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትህትና ከገሊላ ወደ ዮረዳኖስ መጣ። ይህንንም ያደረገልን አብነት
ሊሆነን ነው። ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን “መጥተህ አጥምቀኝ” ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ተነጎዲያ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን “መጥታችሁ አጥምቁን” ባሉ ነበር። ስለዚህ እንዲህ
እንዳይሆን ነው ጌታችን “ጌታ” ሲሆን በባሪያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት
እጅ ተጠመቁ ሲል ነው። ቅደስ ዮሐንስ ጌታችን በእርሱ እጅ ለመጠመቅ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ “እኔ ባሪያህ በአንተ በጌታዬ እጅ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጂ አንተ በእኔ በባሪያህ እጅ
ትጠመቅ ዘንድ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?” አለው። ጌታችንም
መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፣ እንግዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና /ትንቢተ ነቢያትን እንዲህ ልንፈጽም ያስፈልጋል/”
አለው። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን አጠመቀው። በዚህም “መጥምቀ መለኮት” ተብሎ የቅዱስ ዮሐንስ ገናንነቱ ይነገራል፣...👇👇👇
👆👆👆በዓለ ጥምቀት...
ጌታችንም በባርያው እጅ በመጠመቁ ፍፁም
ትኅትናው ይነገርለታል። ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም። ምክንያቱም እርሱ እከብር አይል ክቡር፣ እጸድቅ አይል ጻድቅ
ነውና። ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን ምን እያለ እንደሚያጠምቅ አልገባውም
ነበር፡ በዚህም ምከንያት ጌታችንን “ጌታ ሆይ ሌላውን በአንተ ስም በባሕርይ አባትህ በአብ ስም፣ በባሕርይ ሕይወትህ በመንፈስ ቅዱሰ ስም አጠምቃለሁ። አንተንስ የማጠምቀው
በማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። ጌታችንም “ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ እግዚኦ፣ አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከጼዴቅ፣ የቡሩክ አብ ልጅ ቡሩክ ወልድ ብርሃንን የምትገልጥ ይቅር በለን። እንደ መልከጼዴቅ ክህነት አንተ
ለዘለዓለም ካህን ነህ” እያልክ አጥምቀኝ ብሎታል። ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ ምሥጢረ ሥላሴ ተገልጧል። መንፈስ
ቅዱስ በተለየ አካሉ በርግብ አምሳል ወረደ፤ አብም በተለየ አካሉ በደመና ሆኖ በማዕከለ ዮርዳኖስ የቆመውን ኢየሱስ
ክርስቶስን መለኮትን ከሥጋ ሳይለያይ አንድ አድርጎ “የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” አለ። ምክንያቱም በተለየ አካሉ ሰው ሆኖ በዮርዳኖስ የቆመው ኢየሲስ ክርስቶስ በተዋሕዶ አንድ
አካል አንድ ባሕርይ ሆኖአልና። ተገልጦ የማያውቅ ምሥጢር ተገልጧል። የመንግሥተ ሰማያት በር ይከፈትላችኋል ማለት ነው።

ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው? ይቆየን ...
በዓለ ጥምቀት
ክፍል ፪
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው?
@And_Haymanot
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች፣ ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው። ጌታ ጥምቀቱን ዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ
ነው፦ “ባሕር አይታ ሸሸች፣ ዮርዳኖስም ወደ ኋላዋ ተመለሰች፣ አንተስ ዮርዳኖእስ ወደ ኋላ የተመለስኸው ምን ሆነሃል? አቤቱ ውኈች ዐዩህ፤ ዐይተውም ፈሩህ /ጥልቆችም ተነዋወጡ፤ ውኈችም ጮሁ” /መዝ 113/114፡3-4፣ 76፡16/
ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ አንደሚገናኘ በግዝረትና በቁልፊት /በመገዘርና ባለመገዘር/ ተለያይተው የነበሩ ሕዝበና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታ
ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገለጽ ትርጉም አለው፡፤ እሥራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል። ያመኑ የተጠመቁ ምእመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን
ይወርሳሉ። /ዮሐ 21፡15/ ከላይ የቀረቡት ታሪኮች ለመረዳት እንደምንችለው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በዮሐንስ እጅ ነው። ለምን?
ቅዱስ ዮሐንስ በኃጢአት የተዳደፉት ሁሉ ንስሐ ገብተው የተዘጋጀላቸውን መንግሥት ወራሾች ይሆኑ ዘንድ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያለ ሲሰብክ ነበር። ይህ
“መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፤ ልጅነት ደግሞ በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና ከኃጢአት ተለይታችሁ፣ ከበደል ርቃችሁ
ቅረቡ” ማለት ነው። በነቢያት እንደተነገረውም “ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ድምጹን አሰምቶ ሰብኳል። ምሥጢሩንም በመጣ ጊዜ ተራራውና
ኮረበታው ተንዶ፣ ጎድጓዳው ተመልቶ፣ ሥሩ ተነቅሎ፣ ደንጊያው ተለቅሞ ለፈረስ ለሰረገላ እንዲመች ተደልድሎ እንደሚቆይ ሁሉ እናንተም የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችሁን ከኃጢአታችሁ ንጹሕ አድርጋችሁ ጠብቁ ማለት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ ከንስሐው ስበከት በተጨማሪም ዘመን የማይቆጠርለት ሲሆን ሥጋን በመለበሱ ዘመን ተቆጥሮለት ከእርሱ በኋላ ስድስት ወር ዘግይቶ ስለሚመጣው ስለ ኢየሱስ
ክርስቶስ ማንነትም ሰብኳል፦“እኔስ ለንስሐ በውኃ አተምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው። አውድማውንም ስንዴውንም በጎተረው ይከታል፤ ፈጽሞ ያጠራል፤
ሰንዴወንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። /ማቴ 3፡11፤ ዮሐ 1፡26/
“እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ። ሙሽራዪቱ ያለችው.እርሱ ሙሽራ ነው። ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው
ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል፡ እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል፡ ከላየ የሚመጣው ከሁሉ በላየ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው፣ የምድርንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው… አባት /አብ/ልጁን /ወልድን/ ይወዳል፡፤ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን
የእግዚአብሔር ቁጣ በርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም” /ዮሐ 3፡28/።
በዚህ ስብከቱና ምስክርነቱ የተነሣ ጌታ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። ከዚህም ጋር ጌታ ዮሐንስ ወዳለበት ኺዶ ተጠመቀ እንጂ ዮሐንስ ወደእርሱ እንዲመጣ አላደረገም። ይህም በዚህ ዓለም
ሀብት ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ሁሉ ካህናትን በየቤታችን እየመጣችሁ አጥምቁን የማለት ልምድ እንዳይኖር ሥርዓት.መወሰኑንና ጌታ መምህረ ትሕትና መሆኑን የሚያመለክት ነው።

☞ 3. የበዓሉ አከባበር

ይህ የዓለም መድኃኒት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት መታሰቢያ በዓል በመላው ዓለም በክርስቲያኖች ይከበራል። በዓሉ የሚከበርበት መሠረታዊ መልአክት ተመሳሳይ ቢሆንም የአከባበሩ ይዘት ፣ ሥርዓትና ትውፊት እንደየሀገሩ ባሕልና እንደየአብያተ ክርስቲያናቱ እምነትና
ሥረዓት የተለያየ መልክ አለው። የጥምቀት በዓል በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመታት ዑደት ከሚከበሩት ዐበይት በዓላት አንዱ ነው።
በአዳምና ሔዋን ሰብአዊ ተፈጥሮ አንድ ለሆነው ሰው ሁሉ ድኅንነተ የሰውን ሥጋ ዋሕዶ በተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ
ደም የታነጸችው አሐቲ ቤተ ክርስቲያን በሰዎች የተለያየ አመለካከትና የእምነት ትርጉም ዛሬ በየአህጉሩና በየጎጡ
ተከፋፈላ በብዙ ስሞች ብትጠራም የጥንተ ክረስትናውን መሠረት ሳትለቅ፣ ከቀደምት አበው በተላለፈወ እምነትና ሥርዓት ጸንታ የመትጓዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
የጥቀትን በዓል የምታስበውና የምታከብረው በሌሎቸ ዘንድ በማንኛውም ቤተ ክርስቲያን በማይታይ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትውፊትና ሥርዓት ነው፡፤ በተለይ ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ፣ ዮሐንስ ጌታን ሊያጠምቅ ወደ ዮርዳኖስ
እንደወረዱ ቤተ ክርስቲያን ታቦቷን ከመንበሯ አውጥታ ወደ ውኃ
ምንጮች /ወንዞች/ በመሄድ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓት ታከብራለች። ተከታዮቿ ምእመናንም /ሕዝበ ክርስቲያኑም/ ከታቦታቱ ጋር በየአካባቢአቸው አብረው በመውጣት ለዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን እምነት፣ ፍቅርና አክብሮት
በጋለ መንፈስ እየገለጡ በዓሉን በደማቅ ሥነ ሥርዓት ያከብራሉ፡፤ ለኢትዮጰያ ቤተ ክርስቲያን ልዩ የሆነውን ይህን ሥነ
በዓል ለመመልከት ከዓለም ዙሪያ የሚሰበሰቡ ሀገር ጎብኚዎች
ብዙዎች ናቸው።
ሐመር ፲፩ኛ ዓመት፣ ቁ. ፮፤ ጥር - የካቲት ፲፱፻፺፮ ዓ.ም.

መልካም የጥምቀት በዓል።
@And_Haymanot
@And_Haymanot