፩ ሃይማኖት
8.92K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
"ኦርቶዶክስ መሆን እፈልጋለሁ!"

@And_Hymanot

ሚጢጢዬዋ ሰባኪ ቦታው ሐዋሳ ነው። ባለፈው ወር ከአንድም ኹለት ጊዜ ወደ ሐዋሳ ለአገልግሎት ሔጄ ነበር። ኹሌም ወደ ሐዋሳ ስሔድ አንድ አስገራሚ ነገርን መስማትን ጆሮዬ ለምዷል። ከመልመድም አልፎ ይናፍቅ ጀምሯል። ለዚያም ነው አሁን ከሐዋሳ በ25 ደቂቃ መንገድ ርቀት ተጎራብታ ወደ ምትገኘው ሻሸመኔ እየሔድኩ ይህ ታሪክ የታወሰኝ። ለነገሩ ሻሸመኔም ብዙ ታሪክ የተሠራባት ቦታ ስለሆነች ለአንድ አዲስ ድንቃይ ታሪክ ጆሮዬ ሳይቋምጥ አይቀርም።
የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መዋዕለ
ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አለው። በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ኦርቶዶክሳውያንም ሆኑ የሌሎች አብያተ እምነት አማኞች ይማሩበታል።
ሕፃናቱ ሰኞ ጠዋት ሲገናኙ ታዲያ የቅዳሜና እሑድ ውሏቸውን እየተሻሙ ለጓደኞቻቸው ይተርካሉ። አንዱ ከአንዷ እምቦቀቅላ አፍ ነጥቆ ያወራል፤ ሌላኛዋም እንዲሁ። ዘወትር ሰኞ
ከሚተርኩት ቁምነገር መካከል ታዲያ "እኔ ትላንት ቆረብኩ" የሚለው የማይቀር ነበር። አንዷ ይህን ካለች 'እኔም' 'እኔም' የሚሉ ቀልጣፋና ኮልታፋ ኦርቶዶክሳውያን አፎች ያጅቧታል። ቁርባንን የማያውቁ ሌሎች ኮልታፎች ግራ ይገባቸዋል። ቁርባንን ከማያውቁ
ኮልታፋ አፎች አንዱ የሚጡ ነው።
ሚጡ ከፕሮቴስታንት ወላጆች ተገኝታ በእናትና አባቷ ምርጫ ፕሮቴስታንት የኾነች እምቦቀቅላ ናት። ዘወትር ሰኞ ኦርቶዶክሳውያን ጓደኞቿ
መቁረባቸውን በነገሯት ቁጥር ታዲያ ትቆጭ ኖሯል። አንድ ቀን ሰኞ አንዲት ሚጢጢ የክፍል ጓደኛዋ ከእናትና አባቷ ጋር አስቀድሳ መቁረቧንና በሰንበት ትምህርት ቤት የተማረችውን በመዝሙር እያጀበች ስታወራና የውሎዋን ቅድስና በመንገር እንቁልልጭ ስትል የሚጡ የመቁረብ ፍላጎት ከአቅሟ በላይ ሆነ።
አንገቷን ቀለስ አድርጋ የሥረኛው ከንፈሯን እንደ ማኩረፍ ባለ መለማመጥ አሞጥሙጣ ዐይኗን በተቻለ መጠን በምስኪን አተያይ አሠልጥናና ዕምባዋም ቀሮ ወደ ቆረበችው ጓደኛዋ ሔደችና
"በናትሽ እ... እኔንም እ... እ.. አቁርቢኝ" ብላ ግጥም አድርጋ ሳመቻት። ጓደኛዋ ግን "አንቺ መቁረብ አትችዪም" አለች።
"ለምን?" በሚጡ ግራ ዐይን የሞላው ዕንባ የመሬት ስበት መኖሩን አረጋገጠ።
"አንቺ ኦርቶዶክስ አይደለሽማ..."
"መቁረብ እፈልጋለሁ" ሚጡ ሊያለቅስ አምስት ጉዳይ በሆነው ድምጸት አሞሸች። ጓደኞቿ ሳቁ፤ "መቁረብ እፈልጋለሁ" ክፍሉ በሳቅ ተሞላ።
ሚጡም ሳቃቸው የዐይን ሚጥሚጣ ሆነባት፤ እንባዋ ጎረፈ፤ በሳቅ የታጀበ የልቅሶ ወላፈን 'ሚስ' ባረፈደችበት ክፍል ውስጥ ተቀጣጠለ። የሚጡ ልቅሶ ካንጀት ነበርና ከሳቁ ድምቀት
ይልቅ መጉላት ጀመረ። ጓደኞቿ መሳቅ ትተው ማባበል ጀመሩ። ከልብ መሻት የፈለቀች አንዲት ልቅሶ የእልፎችን ሳቅ አሸነፈች። ተቆጣጠረቻቸው። በልቅሶ የተጨመቀው ዐይን ያወጣው ዕንባ በሳቅ የተጨመቁ ዐይኖች ያፈለቁትን ዕንባ ዋጣቸው፤ የተገኘን ውኃ ኹሉ
በጉልበቱ የዝናብ እንደሚያስመስል እንደ ደራሽ ጎርፍ በሳቅ የተገኘው ዕንባ ኹሉ በሚጡ ዕንባ ጉልበት እንደዚያ ኾነ...
"መቁረብ እፈልጋለሁ" አሁን ሳቅ የለም - ማባበል ብቻ እንጂ። 'አይዞሽ በቃ' እያሉ ከልብ የሚያባብሉ ከንፈሮች ጉንጮቿ ላይም ያርፉ ነበር። ሚጡ ቤት ስትገባ እንደውዳሴ ማርያም ቀኑን ሙሉ ስትደግመው የነበረውን ሐረግ
ደገመችው፦ "መቁረብ እፈልጋለሁ"
ወላጆቿ ግራ ገባቸው። ቀልድም መሰላቸው። ለማረሳሳትም ሞከሩ። ሚጡ ግን ያነሣሣት መንፈስ ቅዱስ ነውና ዝም ልትል አንደበቷ
አልታዘዘላትም። "መቁረብ እፈልጋለሁ!"
አንደበቷ ብቻ ሳይሆን አካሏ በሙሉ በዚህ ፍላጎቷ ተቃኘ። ዐይኗ በዕንባ መቁረብን ለመነ። ጆሮዋ ሌላ ነገር መስማትን ናቀ፤ አፎች ኹሉ
'እናቆርብሻለን' የሚል የምሥራችን
እንዲዘምሩም ተመኘ። እግሯ ቤተ ክርስቲያን እንጂ የትም የማይሔድ ኾነ። አፍንጫዋ የጸሎት፣ የምልጃ ዕጣንን መዓዛ እንጂ ሌላ ሽታ ከረፋው። እጇ ከቆረበች በኋላ ነጠላዋን አፈፍ
አድርጎ ጸበል እስክትጠጣ አፏ ላይ ሊጫን ፣ አፏን ሊሸፍን ጓጓ - ጓደኞቿ እንደነገሯት - እንደዚያ። አንገቷ ካለ ክር መራቆቱ አሳፈረው። ግንባሯ መስቀል መሳለምን፣ ከንፈሯ ሥዕለ ማርያምን መሳምን ተመኙ። ጸጉሯ በሻሽ ተሸፍኖ፣ ትከሻዋም ነጠላ ተጣፍቶለት መዝሙር
ማጥናትና ሰኞ ስትመጣ ከጓደኞቿ ጋር መዘመር የዘወትር ኅልሟ ሆነ። የሰውነት አካሏ ባጠቃላይ ኦርቶዶክሳዊነትን ሻተ፤ ጌታ የለኮሰው፣ ሐዋርያት ያቀጣጠሉት የሃይማኖት እሳት በማዕከለ ሰብእናዋ ተንቦገቦገ። (ሉቃ. 12፡49)። የሚጡ ኹለመና እንዲህ አለ፦ "መቁረብ እፈልጋለሁ፣ ኦርቶዶክስ መሆን
እፈልጋለሁ!" ይህ የሚጡ ልምምጥ ቃል ብቻ አይደለም
- በዕንባ የተለወሰ ንጹህ ጩኸት እንጂ። ንግግር ብቻ አይደለም - ከደመና በላይ የሚወጣ ልመና እንጂ። ዝርው ድምጽ ብቻ አይደለም
- ሳይበተን የሚያርግ ጸሎት እንጂ።
...እናም ወደላይ ወጣ። ከፍ ከፍ አለና ራማን አንኳኳ። ቅዱስ ገብርኤልም አስተናገደው። የሚጡ ሰሞንኛ ውትወታ ግራ ያጋባቸው ወላጆቿ ከእሑዶች በአንዱ ሚጡን ይዘው ወደ ገዳሙ ሰንበት ትምህርት ቤት መጡ። ሚጡ
ዛሬ ነፍሷን አታውቅም። በወላጆቿ ተይዛ ልክ እንደጓደኞቿ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጣች። ኹሉነገሯ ጥርስ ሆኗል። ሰኞ ደርሶ ትምህርት ቤት የምታወራው፣ የምትፈጥረው የትረካ ድባብ
በሰንበቱ ታያት። ወላጆቿ የሆነውን ኹሉ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ መምህራን ነግረው "እባካችሁ ሚጡ እንድትቆርብ አድርጉልን" አሉ። ሚጡም "መቁረብ እፈልጋለው!" አለች በጥዑም
አንደበቷ። መምህራኑ ግን አንድ ሰው ለመቁረብ የሚያስፈልገውን ትምህርት መማር እንደሚቀድምና ወላጆቿም በቁርባን ጊዜ በመቅደስ መቆየት እንደማይችሉ አስረዷቸው።
ሚጡም የዚያኑ ቀን እንደማትቆርብ ተረዳችው። አንድ ነገር ግን ገብቷታል - ኦርቶዶክስ ካልሆነች በገዳሙ መቁረብ እንደማትችል። ስለዚህ ድምጿን ከፍ አድርጋ "ኦርቶዶክስ መሆን እፈልጋለሁ" አለች። ወላጆቿ ደንግጠው ተያዩ። በድምጿ ውስጥ ያለው ቆራጥነት እናትና
አባቷን ለመተው እንኳን ደግማ የማታስብ አስመስሏታል።
መምህራኑ ሚጡንም ወላጆቿንም አረጋግተው ክትትላቸውን ቀጠሉ። የደብሩ ካህናትም ጉዳዩን ሥራቸው አደረጉት። ከዕለታት ለሚጡ በተቀደሰች አንዲት እሑድ
እንዲህ ኾነ....
የሚጡ ወላጆች ከመምህራኑ እንደተነገራቸው ቅዳሴ ሳይጀመር በሌሊት የገዳሙ ግቢ ውስጥ
ተገኙ። መምህራኑ እየመሯቸው ወደ ክርስትና ቤት ሔዱ....
ከቆይታ በኋላ ወጥተው ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ። ሚጡ የአንድ ሰውን እጅ ይዛ የቤተ መቅደሱ በር ጋር ደረሱ። እንደተማረችው ጫማዋን አውልቃ ተሳለመች፤ ወደ ውስጥ ገባች። አብረዋት ያሉትም ገቡ። ወላጆቿም
ከመግባት አልተከለከሉም። "ፃዑ ንዑሰ ክርስቲያን" ተባለ። ወላጆቿ ግን
አልወጡም። ልዑካኑ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ይዘው ከመቅደስ በክብር ወደ ቅድስቱ ተገለጡ። እንደተለመደው ብዙ ቆራቢያን ተሰለፉ። ሚጡም ሰልፉን ከሠሩት ተነሣህያን ጋር
በመኾን ከበረች። ከትምህርት ቤት ጓደኞቿ መካከል በወላጆቻቸው
ታጅበውሊቆርቡ የተሰለፉም አሉ። ዛሬ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚጡ ተበለጡ። በርግጥ ሚጡ በልጅነት ጥምቀት ከብራ፣ በምሥጢረ ሜሮን መንፈስ ቅዱስን ተቀብላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመቁረብ መቅረቧ ነው። ጓደኞቿ ግን
ደጋግመው በሥጋ ወደሙ ከብረዋል። ግን ኹሉም ብቻቸውን ናቸው።
ሚጡ ሥጋ ወደሙን ተቀብላ በነጠላዋ አፏን ሸፍና ስትመለስ በጓደኞቿ ላይ ብልጫዋ ተገለጠ። ኹለት ረጃጅም ሰዎች ከኋላዋ እርሷን ተከትለው ተጠምቀውና ቆርበው አፋቸውን
ይዘው ተከተሏት - እናትና አባቷ። የጓደኞቿ ወላጆች ልጆቻቸውን
"ኦርቶዶክስ መሆን እፈልጋለሁ!"
....Cont
- እናትና አባቷ። የጓደኞቿ ወላጆች ልጆቻቸውን አቆረቡ። የእርሷ ወላጆች ግን እርሷን ቆርበው አቆረቡ። ለካስ "ኦርቶዶክስ መሆን እፈልጋለሁ - መቁረብ እፈልጋለሁ"
የሚለው ንግግር ወደ ወላጆቿም ተጋብቶ ኖሯል
- ይኸው በልጃቸው ተሰብከው ከልጃቸው ጋር ከበሩ - በምድርም በሰማይም ደስታ ሆነ። አንዳንድ ጊዜ ልጅም ለእናቷ ምጥን ታስተምራለች። ሚጡ ለእናትና አባቷ ምጥ
የሆነባቸውን ኦርቶዶክሳዊነት አስተማረች።
በቀጣዩ ቀን ሰኞ ሚጡ ትምህርት ቤት ስትሔድ ምን ብላ ገድሏን እንደምትተርክ ብንሰማ... አቤት...
አፎች ኹሉ ጆሮ ኾነው ሲያዳምጧት፣
በተቃራኒው የእርሷ ኹለመና አፍ ሲሆን... "እየውላችሁ.... እ.... እ..." ስትል በተራዋ ሌሎችን ስታጓጓ....
አቤት..... መቼስ እግዚአብሔር በጥበቡ እንደጠራት ከነቤተሰቧ ይጠብቅልን፣ ያጽናልን እንጂ ምን ይባላል! የሚጡን ዕንባ ያበሰ ቅዱስ ገብርኤል የእኛንም
ዕንባ በምልጃው ያብስልን!
©ዘሕሊና
@And_Hymanot
@And_Hymanot
የጌታችን የክብሩን መጠን የተረዳ ሰው ማደሪያው የሆነችውን እናቱን ይወዳል እንኳን የወለደችው ቀርቶ
የለበሰውን ልብስ አክብሮ ነክቶ ይፈወሳል ያረገውን ጫማ ልፈታ አይገባኝም ይላል ክብር ለድንግል
ማርያምይሁን
ተአምረ ማርያም ላይ ከተሃድሶ መናፍቃን ጥያቄዎች አንዱ

☞ ጥያቄ. ነፍሳትን በበላው በበላኤ ሰብ ታሪክ ላይ።
☞ መልስ፦ የብላዔ ሰብዕ 78 ነፍስ አጥፍቶ መማሩ በማቴ10:42
"በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ዉሃ ቢጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም" በሚለው አምላካዊ ቃል መሰረት ነው::
ተአምረ ማርያም እንደሚነግረን ስምዖን የተባለው ይህ ሰው ብዙ ነፍስ ካጠፋ በሗላ ንስሓ ገባ ተጸጸተ ልክ በቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ::
በወንጌሉ መሰረት ለድሀ ከደቀመዛሙርት ሁሉ ከፍጥረት
ሁሉ በከበረችው በእመቤታችን ስም ቀዝቃዛ ዉሀ ለድሀ አጠጣ:: እመቤታችም በወንጌሉ መሰረት ማርለኝ አለችው ማረላት:: በቀኝ የተሰቀለ ከብላዔ ሰብዕ (ከዚህ ሰብ በላ) የበለጠ ይሥራ አይሥራ እኛ አናዉቅም::
ቃል ኪዳን ሲሰጥ ክርስቶስ ገደብ አላስቀመጠም (ይህንን ያህል
የገደለ አልምርም የሚል የለ)::
በደቀ መዝሙር ስም ያጠጣ አለ እንጂ:: ስለዚህ የወንበዴውን መዳንም እየተጠራጠሩ በወንጌል አምናለሁ ማለት አይቻልም:: በወንጌል ተጽፎ ነው እንጂ በቀኝ የተሰቀለው ታሪክ በተአምረ
ማርያም ቢጻፍ ኖሮ አይቀበሉትም ነበር::
በመጨረሻም መናፍቃን ከተለያዩ ገድላት፣ድርሳናት፣ተአምራት በመጥቀስ ምዕመንን ለማሰናከል ይኳትናሉና።
በተቻለ መጠን አይታለሉላቸው። ምንም እንኳን ገድሉ ተአምሩ ለማመን ከባድ ቢሆንም ክርስቲያኖች ነንና ከዚህም በላይ እንደሚደረግ እንወቅ!
ጌታ ያለውም ይህንኑ ነው።በእኔ የሚያምን ከዚህ በላይ ያደርጋል
ተብሎ ተፅፋልና!!!..... ሌሎች ጥያቄዎችን እንመለስበታለን ይቆየን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
አባ ሊባኖስ ገዳም
ኤርትራ
የአባታችን በረከት ይደርብን
❤️አሜን👍
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 31 አጀንዳዎችን በማጽደቅ
መወያየቱን ቀጥሏል
• ከተደጋጋሚ ጥሪ በኋላ በምልዓተ ጉባኤው የተገኙትን ብፁዕ
አቡነ ኤዎስጣቴዎስን በይቅርታ ተቀብሏል፤የሀገረ ስብከት ምደባ
ይሰጣቸዋል፤
• የአእላፋት ድምፅ የካህናትና የምእመናን ተናሥኦት ኅብረት
ተወካዮች፣በመሪ ዕቅድ ትግበራና የምእመናነ ከፍተኛ ተሳትፎ
የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥ እንቅስቃሴያቸውን
ቀርበው እንደሚያስረዱ ይጠበቃል፤
***
ከትላንት በስቲያ የተጀመረውና ሦስተኛ ቀኑን የያዘው፣ የቅዱስ
ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ 31 አጀንዳዎችን በማጽደቅ ስብሰባውን
ቀጥሏል፤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን የመክፈቻ
ንግግር ካደመጠ በኋላ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ
መንፈሳዊ ጉባኤ 37ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የአቋም
መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ላይ በመወያየት አጽድቋል፡፡
ከ27 ዓመታት በኋላ በተመለሰው ሲኖዶሳዊ አንድነት፣ የአህጉረ
ስብከት ድልደላ እና የብፁዓን አባቶች ምደባ ማካሔድን
በተመለከተ በአጀንዳ ተ.ቁ(3) በመያዝ፣ የድልደላና ምደባ
ምክረ ሐሳቦችን ተቀብሏል፤ ጉዳዩን አደራጅተው ለምልዓተ
ጉባኤው የሚያቀርቡ የብፁዓን አባቶች ኮሚቴም ሠይሟል፤
በድልደላው፣ ከሀገር ውስጥም ኾነ ከውጭ በተደራራቢነት
የተያዙት አህጉረ ስብከት ተነጣጥለው ምደባ
እንደሚካሔድባቸው፤አዲስና ተጨማሪ የአህጉረ ስብከት
አደረጃጀትም እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡
ከቀረቡትም ምክረ ሐሳቦች ውስጥ፤ ከሀገር ውስጥ
በተደራራቢነት የተያዙ 8 አህጉረ ስብከት ራሳቸውን ችለው
ብፁዓን አባቶች እንዲመደቡባቸው፤ የሰሜን አሜሪካ አህጉረ
ስብከት ለ9፣ የካናዳ ሀገረ ስብከት ለ3፣ የአውሮጳ አህጉረ
ስብከት ለ4፣ የአፍሪቃ አህጉረ ስብከት ለ3፣ የአውስትራልያ ሀገረ
ስብከት ለ3 ተከፍለው ብፁዓን አባቶች እንዲመደቡባቸው
የሚጠይቀው ይገኝበታል፡፡
በአሁኑ ምልዓተ ጉባኤ የተገኙት የቀድሞው የካሊፎርኒያ ሀገረ
ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ከ2003 ዓ.ም.
ጀምሮ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ በተላለፉላቸው ተደጋጋሚ
ጥሪዎች መሠረት ያልቀረቡበትን ምክንያትና በአንዳንድ ወገኖች
ስለሚነሡባቸው ክሦችም ተጠይቀዋል፡፡ ክሦቹን
በተመለከተ፣“ግለሰቦች ስማቸውን ለማጥፋት የሸረቡት ሤራ
ነው፤” በማለት አስረድተዋል፡፡ ከፍተኛ ትምህርታቸውን
እየተከታተሉ እንደነበርና ለመመለስ የማይችሉበት ኹኔታ
እንዳጋጠማቸው የጠቀሱት ብፁዕነታቸው፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን
ይቅርታ ጠይቀዋል፤ የሀገረ ስብከት ምደባ እንዲሰጣቸውም
አመልክተዋል፡፡ ይቅርታቸውን የተቀበለው ምልዓተ ጉባኤው፣
በቃል ያስረዱትን በጽሑፍ ሲያቀርቡ ምደባው እንዲሰጣቸው
ተስማምቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው፣ በትላንት የቀትር በፊት ውሎው፣ በተ.ቁ(11)
አጀንዳው፥ አቤቱታ ስለቀረቡባቸው አህጉረ ስብከት ማለትም፦
• የሻሻመኔ ምእመናን የሀገረ ስብከት ጥያቄ፣
• የምሥራቅ ጎጃም ካህናትና ምእመናን በሊቀ ጳጳሱ ላይ
ስላቀረቡት አቤቱታ፣
• የአዊ ዞን ምእመናን በብፁዕ አባ ቶማስ ላይ ስላቀረቡት
አቤቱታ፤
• የደቡብ እና ሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት፣
• የካፋ፣ የምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት፣
• የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ
ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ምእመናን አቤቱታዎች ላይ
መወያየት ጀምሯል፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን ሊቀ ጳጳሱ
ብፁዕ አባ ማርቆስ እንዲነሡላቸው ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ
ሲያቀርቡ የቆዩትን አቤቱታዎችና ራሳቸውም ምልዓተ ጉባኤውን
መጠየቃቸውን ተከትሎ ከሀገረ ስብከቱ እንዲነሡ ወስኗል፡፡
ችግሩ በአፋጣኝ ሳይፈታ ዓመታትን በማስቆጠሩና በሀገረ ስብከቱ
ምእመናን መካከል ልዩነት በመፍጠሩ አንድነቱን ለመጠበቅ
የሚያስችሉ የስብከተ ወንጌልና አስተዳደራዊ ሥራዎች
እንዲከናወኑ ምልዓተ ጉባኤው አሳስቧል፡፡ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ
ስብከት ሥር ያለውና በሀገረ ስብከት ራስን የመቻል ጥያቄ
ያቀረቡት የምዕራብ አርሲ(የሻሸመኔ) ምእመናን የዓመታት
አቤቱታ፣ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም ባቀረቡት
የመፍትሔ ሐሳብ እልባት ይሰጠዋል፤ተብሏል፡፡
ከምልዓተ ጉባኤው ሌሎች ዐበይት አጀንዳዎች መካከል፡-
• ስለ ቤተ ክርስቲያን መሪ ዕቅድ እና ኹለንተናዊ ጉዳዮች
የተካሔደው ጥናት፣
• ሀገራዊ ሰላምና ዓለም አቀፍ የስብከተ ወንጌል ሥምሪትን
በተመለከተ፣
• በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ዝርዝር ደንብ እንዲወጣላቸው ስለተባሉ
ጉዳዮች፣
• የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ኅብረት ተወካዮች፡-
በመሪ ዕቅድ ትግበራና ከፍተኛ የምእመናን ተሳትፎ የቤተ
ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥን በተመለከተ ስላቀረቡት ጥያቄ፤
• የፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ሀገር አቀፍ ሪፖርት፣
• የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያ በተመለከተ፣
• የላሊበላ አብያተ መቃድስ፣ የአኵስም ሙዝየም እና
የኢየሩሳሌም ገዳማት ችግሮች፣
• ከኤርትራ ኦርቶዶክስ የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገረ
ስብከት ስለተጻፈ ደብዳቤ፣
• ስለ አእምሯዊ ንብረት ሀብት የቀረበ ጥናት፣
• ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግርንና አዲስ አበባን በተመለከተ፣
• እነ አባ ገዳ ተሾመ ያቀረቡት አቤቱታ፣
• የውጭ ጉዳይ መምሪያ በውስጥና በውጭ እንዲደራጅ
ስለማድረግ፣
• የቤተ ክርስቲያኒቱን የትምህርት ተቋማት በተመለከተ፣
• የሰላም እና አንድነት ጉባኤ አደረጃጀት፣
• የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ እና የአባቶች ማረፊያ
ሕንፃ ግንባታ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡
ምንጭ ፡- ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
#ዜና #ዘኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ዕለታዊ
ቅዱስ ሲኖዶስ ገራሚ ገራሚ ውሳኔዎች ማሳለፉን ቀጥሏል። በትላንትናው ዕለት ካሥተላለፋቸው ውሳኔዎችም
#1ኛ ) በትላንትና እለት የዘገብነውን የሻሸመኔ ምዕመናን ፦ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያመቻቸው ያቀረቡትን የአዲስ አህጉረ ስብከት መቋቋም ፥ ተወያይቶ አፅድቆላቿል ። አዲሱ
የሻሸመኔ ሐገረ ስብከትም የምዕራብ አርሲ ሐገረ ስብከት ተብሎ
ተሰይሟል ። ሊቀ ጳጳስም በዚሁ ምልአተ ጉባኤ ይሾምለታል ።
#2ኛ ) የአዊ ምዕመናን እንባ መድኃኔአለም ያየው ይመስላል ።
ከአባ ማርቆስ ቀጥሎ ሁለተኛው ባለ ቅባት አባ ቶማስ በምዕመናኑ ላይ ያደረሱት የአስተዳደር በደል በአስቸኳይ
እንዲጣራ ኮሚቴ ተቋቁሟል ። ቀጣዩ ተነሺ እንደሚሆኑ ይጠበቃል ።
#3ኛ ) የከፋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጽኡ አቡነ ሕዝቅኤል ስራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ፥ ከባድ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቿል ።
# 4ኛ ) የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከትን ለመንፈሳዊ አገልግሎት እና ለሐብት ቁጥጥር በሚያመች መልኩ ለ4 አህጉረ ስብከቶች የመክፈሉን ጉዳይ ተወያይቶ ውሳኔ ሊሰጥበት ቀጠሮ
አስቀምጧል ።
#5ኛ ) ባለፈው ሳምንት እንደገለጽነው በመላው ሐገሪቱ ሰላም ለማስጠበቅ ፥ ብጥብጥን ለማስወገድ ፥ የብጽአን አባቶች
#የሰላም #ሐዋሪያዊ #ተልዕኮ በቡድን በቡድን ሆኖ ስምሪት ለማድረግ ከስምምነት ተደርሷል ።
#6ኛ ) በምዕራብ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት በታላቁ የአሰቦት ገዳም "የኦነግ " ታጣቂዎች ነን ባዮች በመነኮሳት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ተጠቁሟል ። የኦሮሚያ እና የፌደራል.መንግስት ባስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቁ ።
#7ኛ ) የኢየሩሳሌም የዴር ሱልጣን ገዳም ፥ በግብጽ መነኮሳት
የማይገባቸውን እርስት የመጠየቅ ብጥብጥ ፥ የእስራኤል ፖሊስ
ጣልቃ ገብቶ ፥ ቀሳጢያንን የግብጽ መነኮሳት ማሰሩ። እርሱንም ተከትሎ የCoptic ቤተክርስቲያን ተጽኖ ለመፍጠር ዘመቻ መጀመሯ ።

#በቀጣይ #ቀናት #ውሎ
#1ኛ ) ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት ለማናጋት
ዘረኝነትን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለማስገባት ለሚፈልጉ ቡድኖች የማያዳግም መልስ ይሰጣል ተብሎ ይጠብቃል
#2ኛ ) በቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና በጣና ገዳማት ላይ በተጋረጠው አደጋ ዙሪያ አስቸኳይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል
#3ኛ ) የኢየሩሳሌምን የቅድስት ቤተክርስቲያን እርስቶች በሚገባ የሚያስጠብቅ የማያዳግም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኢትዮጵያ እና የኤርትራ

✢~በታሪክ አጋጣሚ የተለያዩ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ከ27 አመታት በኋላ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር እንዲተዳደሩ ፥ ከኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ ቀርበ ።
✢ ~ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ
በሶስት ፓትሪያኮች ልትመራ ትችላለች ።
✢ ~ ለ27 አመታት በታሪክ አጋጣሚ ፥ በተለያዩ ሲኖዶሶች ተከፋፍላ የቆየችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ፥ የመጀመሪያውን ወሳኝ አንድነት ከፈጠረች በኋላ ቀጣዩ አንድነት ከኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ጋር ለመፈጸም እንደታሰበ ብጽኡ ወቅዱስ ፓትሪያክ አቡነ
ማቲያስ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ።
✢ ~ ብጽኡ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በንግግራቸው "ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን በታሪክ ና በሐይማኖት አንድ ህዝቦች ናቸው ብለዋል : አክለውም ለኢትዮጵያዊያን
ከኤርትራውያን በላይ ቅርብ ወንድም ለኤርትራውያንም ከኢትዮጵያውያን በላይ የሚቀርባቸው ወንድም የለም ብለዋል።"
✢~ በመጨረሻም ለኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እህት ቤተክርስቲያን የአንድነት ሲኖዶሳዊ አስተዳዳር ለመፍጠር ጥሪ
አቅርበዋል ።
✢ ~ ከኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ በወርሃ
ሐምሌ 2010 ዓም የአንድነት እና የትብብር ጥሪ መቅረቡ
አይዘነጋም ።
✢~ የኤርትራ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያክ ከግብጽ የማርቆስ መንበር ወደ ቀደመ ማንነቱ የአቡነ ተክለኃይማኖት
መንበር ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያስደምም ውሳኔዎቹ ታጅቦ ቀጥሏል!
ጥቅምት 16/2011 ዓም
¶ ከእንግዲህ ሚስጥር ያላቸውን የቅድስት የቤተክርስቲያንን
የመዝሙር እቃዎች ከመርካቶ እየሸመቱ መለፋደድ አከተመ።
¶ ቅዱስ ሲኖዶስ ትላንት በቀጠለው ጉባኤው "የቅድስት ቤተክርስቲያንን ንዋየ ቅድሳት እና የመዝሙር እቃዎች
የባለቤትነትን መብት ከእንግዲህ በኋላ አስከብራለው " ብሏል።
¶ በትላንትናው እለት በቀጠለው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፥ አጀንዳ ተራ ቁጥር 14 ላይ በተቀመጠው ርዕስ ማለትም በቅድስት ቤተክርስቲያኒቱ ንዋየ ቅድሳትና የመዝሙር እቃዎች ዙሪያ ተወያይቶ በቅርብ ቀናት ባለሙያ አስመድቦ በብሔራዊ ስነ አይምሯዊ ተቋም የባለቤትነት መብት (Patent Right ) እቀበላለው ብሏል ።
¶ ከዛ በኋላማ የ ተሃድሶ መናፍቅን እና መናፍቃን በማያገባቸው
ንብረቶቻችን ላይ መለፋደዳቸውን በህግ ያቆማሉ ።
እነ አዝማሪት ዘርፍሺዋም ወደ ለመዱት ፒያኗቸው እና ጃዛቸው ይመለሳሉ ማለት ነው ።
የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ፀበሉ ፥
አናፍርም ተምክህታችን ነው መስቀሉ ።
Share Share Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot
'በሐዲስ ኪዳን ውግዘት
የሚባል የለም!' ለምትሉት፦
by Zemaryam zeleke
@And_Haymanot
✞ "...ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።" [1ኛቆሮ.5፥5] ማለት ምን ማለት ነው?
❖ "መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።" [1ኛቆሮ.5፥5]
ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት /መጥውዎ ለሰይጣን/(1ኛጢሞ.1፥20) ማለት፦ በተጨባጭ ኑፋቄ የተገኘበትን ሰው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሲያወግዙት አድሮበት የነበረ መንፈስ ቅዱስ ይለየዋል፥ መንፈስ ቅዱስም ከተለየው ማኅደር ያለኀዳሪ አያድርም ሰይጣን
ያድርበታልና ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት(መጥውዎ ለሰይጣን)አለ።
"ለሥጋው ጥፋት..." ከመ ይሥርዎ ሥጋሁ ሲል በሥጋው ያጠፋው ዘንድ ማለት ነው። "መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ፦ ወትድኃን መንፈሱ በዕለተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲል ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን በዕለተ ሞት በዕለተ ምጽአት ነፍሱ ትድን ዘንድ ማለት ነው። ይኼም ማለት ከሞተ ኃጢአቱን አይሠራውምና ኃጢአቱንም ካልሠራው ፍዳው ይቀርለታልና። አንድም በሱ ጥፋት የሌላው ነፍስ ትድን ዘንድ የእነረዓይትን (የኔፍሊሞች) ጥፋት ለእነኖኅ ለፈውሰ ነፍሶሙ ሥጋሆሙ(ለነፍስ ለሥጋቸው ፈውስ እንደሆነች) እንዳለ ኄኖክ።

❖ "ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር
ተሰብስበን፥..." [1ኛ ቆሮ. 5፥4-5]
"በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ አንገሊገክሙ በስመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።" የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ዳኛ አድርጋችሁ። "መንፈሴም" ወምስለ መንፈስየ ሲል ክታቤን ይዛችሁ
ማለቱ ነው።."ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን" ምስለ
ኃይለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲል ደግሞ ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሰብስባችሁ ማለቱ ነው።
"ለሰይጣን እንዲሰጥ፦ መጥውዎ ለሰይጣን" ማለት ለቀኖናው አሳልፋችሁ ስጡት ሲል ነው።

ቀኖናውን ሰይጣን አለው፥ በዚያ ወራት ሰይጣን መከራ የሚያጸናበት ስለኾነ።
"የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።" ገላ.5፥12 ርቱዕ ይንትጉ እለ የሐውኩክሙ፦ አገባብስ የሚያውኳችሁ(በክህደት፥ በጥርጣሬ) ሰዎች ከአንድነት ሊወጡ ይገባል ሲል ነው። "...በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥..." [1ኛቆሮ.11፥24] ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወልደ ማርያም ሥግው መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ "ነሥአ
ኅብስተ አኰተ(እንጀራን(ዳቦን) አንሥቶ አመሰገነ) ሲል፦ ዳቦ አንሥቶ አባቱን አመሰገነ። ያንተ ሞት የዓለሙ ድኅነት፤
ያንተ ኃሣር የዓለሙ ክብር ይኹን ያልህ ብሎ አባቱን አመሰገነ ማለት ነው።

አንድም ሞቱን አመሰገነ፤ ብዙ ነቢያት ጻድቃን ቢሞቱ የነዚያ ሞት ዓለሙን አላዳነም የኔ ሞት ግን ዓለሙን አዳነ ብሎ ሞቱን አመሰገነ ማለት ነው።
አንድም መሥዋዕትነቱን አመሰገነ፤ ብዙ አልሕምት (ላሞች)፥ ብዙ አባግዕ(በጎች) ቢሠዉ የነዚያ መሥዋዕትነት
ለዓለም ጥቅም አልኾነም፤ የኔ መሥዋዕትነት ግን ለዓለሙ
ጥቅም ኾነ ብሎ መሥዋዕትነቱን አመሰገነ።
❖ "እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤" [1ኛቆሮ.11፥29]
✞ ሥጋውን ደሙን በመብል በመጠጥ ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለምን ነው ቢሉ መብል መጠጥ ያፋቅራል፤ ሥጋው
ደሙም ያፋቅራልና፤ አንድም የቀረው ከብት በአፍአ ይቀራል የበሉት የጠጡት ይዋሐዳል፤ በዚህ ምክንያት ተዋሕጃችሁ
እኖራለሁ ሲል ነው። ያውስ ቢኾን በስንዴ በወይን ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለምን ነው ቢሉ፦ ትንቢቱ ምሳሌው ሊፈጸም።
፠ ትንቢት እምፍሬ ሥርናይ ወወይን ወቅብዕ በዝኀ/ከስንዴ ፍሬና
ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ/ (መዝ.4፥7)።
ቀዳሜ ሕይወቱ ለሰብእ እክል ወማይ ወይን ወሥርናይ/ የሰው የፈቃዱ መጀመሪያ ውኃ እሳት ብረት ጨው እህል ስንዴ ማር ወተት የወይን ዘለላ ደም ዘይት ልብስ ነው/ ያለው ነው
(ሲራክ 39፥26።)
፠ ምሳሌም መልከ ጼዴቅ በስንዴ በወይን ያስታኩት ነበርና
ትንቢቱን አውቆ ተናግሯል፤ ምሳሌውንም እንጂ አውቆ አስደርጓል ፍጻሜው እንደምን ነው ቢሉ ስንዴ ስብ ይመስላል፤
ወይንም ደም ይመስላልና፤ በመሰለ ነገር ለመስጠት ስንዴ ልባም ሴት የያዘችው እንደኾነ ነውር የሌለበት የማይለወጥ
ይኾናል ነውር የሌለበት የማትለወጥ ሕግ ሠራሁላችሁ ሲል። ወይንም የጣሉት እንደኾነ ኃይል እየነሣ ይሔዳል፤ ኃይል የምትኾን ሕግ ሠራሁላችሁ ሲል።

❖ "ተወዳጆች ሆይ፥ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቁጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤..." ሮሜ 12፥19 ወኢትትበቀሉ ለሊክሙ(እናንተ
እንበቀላለን አትበሉ)፤ አኀዊነ አኅልፍዋ ለመዓት(ወንድሞቻችን ቂምን አርቋት)። እንደ ዋርካ። ዋርካ በቡቃያነቷ ሳለች አንድ ብላቴና ነቅሎ ይጥላታል። ካደገች ከገነነች በኋላ ግን ብዙ ሰው፥ ብዙ ምሳር፥ ብዙ መጫኛ ታስፈልጋለች። ቂምም የዋለች ያደረች እንደኾነ ከቀቲል(ከመግደል) ታደርሳለች፤ ከቀቲልም ካደረሰች ፍዳዋ ይጸናልና።
አንድም ክህደትን ከናንተ አርቋት መዓተ አርዮስ እንዲል።
❖ "የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤..." [1ኛቆሮ.3፥19] ዘይእኅዞሙ ለጠቢባን ትምይንቶሙ/እርሱ ጥበበኞችን
በተንኰላቸው የሚይዝ/(ኢዮብ 5፥12-15) ማለት ፈላስፎችን
ከዕውቀት የሚገታቸው እናውቃለን ማለታቸው ነው ብሏልና። (ታሪክ) እንደ አንድ ፈላስፋ መምህር ውዳሴ ከንቱ ሽቶ ሙስና (መቃብር ፈርቶ) አርድእቶቹን ልጆቼ የሞትሁ እንደኾነ ሥጋዬን
አትቅበሩት አርዳችሁ ብሉት ጥበብ ይገለጥላችኋል አላቸው፤.ጥበብማ የሚገለጥልን ከኾነ እስኪሞት ምን ያጠባብቀናል ብለው አርደው ተቀራምተው ቀምሰውታልና እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ አለ።
❖ "ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና።"[1ኛ ቆሮ. 3፥20]
ዳግመኛ ጠቢባን ነን የሚሉ ሰዎች ጥበባቸው ከንቱ እንደ ኾነ እግዚአብሔር ያውቃል ብሎ መጽሐፍ እንደተናገረ። (ታሪክ) እንዳንድ ፈላስፋ በፍልስፍና ሲዞር ዕፀ ሕይወትን አገኘ ከሀገር
የኾነ እንደኾነ ከሰው ይተርፋል ብሎ በሸክላ ዘፍዝፎ ተሸክሞ ወደ በረሀ ሲሔድ ጌታ ምቀኝነት አይወድምና መልአክ ከላዩ ላይ ሰበረበት በኲል አካሉ ሲፈስ በኲሌታ አካሉ ሳይፈስበት ቀረ
የፈሰሰበት አካሉ ሕያው ኾኖ ያልፈሰሰበት አካሉ ሸቶ ተልቶ
በኃሣር የሚኖር ኾኗል። (ዜና እስክንድር)

☞ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ በ Youtube በተለያዩ ርዕሶች
የሚሰጣቸውን መንፈሳዊ ትምህርቶችን Audio በሚከተለው
አድራሻ ይከታተሉ። https://www.youtube.com/channel/UCyW5pGARAaJt4HMNmtZsYGQ/videos?
view_as=subscriber
☞ Join @And_Haymanot
እኔ እና እሱ.....
@And_Haymanot
እኔ ለእግዚአብሔር የአምልኮ ስግደት ለቅዱሳኑ ደግሞ የክብር ስግደት እፈፅማለሁ! አንድ ሰው የሚከተለው ጥቅስ ጠቅሶ ስግደት መፈፀም ያለበት
ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ምስጋናም እንዲሁ ብለኝ መንፈስ ቅዱስ እንደገለጠልኝ እንደሚከተለው እመልስለት ነበር። እሱና እኔ

እሱ=> እኔ ሕያው ነኝ ይላል ጌታ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይምበረከካል ምላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ
ተጽፏልና። ሮሜ 14:11
ስለዚህ ስግደትና ምስጋና ለጌታ ብቻ ነው የሚገባው።
እኔ=> የሮሜ መልእክትን የፃፈው ማን ነው?
እሱ=> እሱ የምያውቅ ከሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ብሎ ይመልሳል።
እኔ=> ታድያ ቅዱስ ጳውሎስ ስግደት መፈፀም ያለበት ለጌታ ብቻ መሆኑን እያወቀ የወህኒ ቤት ጠባቂ ተደፍቶ ስሰግድለት ለምን ዝም አለው? ስግደት ለጌታ ብቻ ነውና ተነስ ለምን አላለውም? ሐዋ 16:29 ያንብቡት!
እሱ=> እሱ ምን ይለኝ እንደነበር እግዚአብሔር ይወቀው እኔ ግን ጥያቄየን እቀጥላለሁ።
እኔ=> በብሉይ ኪዳን በየቦታው ሰዎች ከእግዚአብሔር ውጭ ለፍጡራኖቹ ማለት ለቅዱሳን መላእክትና ቅዱሳን ሰዎች ሲሰግዱ የምናየው ለምንድነው? ዘፍ 19፡1 ኢያ 5:14 2 ነገ1:13 ዳን 2:46 ያ ስግደት ለእርሱ ብቻ የሚገባው ጌታ ያኔ ስላልነበረ ነውን? እንድያውም በአንተ አተረጓጎም ከእኔ በቀር ለሌላ አማልክት አትስገድ(ዘፀ 20) ሲል ለቅዱሳን መላእክትና ለቅዱሳን ሰዎች
ከሆነ ሰዎች ለቅዱሳን ተደፍተው ለምን ሰገዱ? ስግደታቸው በእግዚአብሔር ፍት ያልተወደደና ያልተፈቀደ ከነበረስ እስራኤላዊያን አሮን ላቆመላቸው ጣኦት በሰገዱ ግዜ የተቀሰፉ ሲሆን ለቅዱሳን ስሰግዱ እንኳን ሊቀስፋቸው ምንም
አልተናገራቸውም። ታድያ ለምን? ዘፀ 32:1-32 ከእኔ ውጭ ለማንም አትስገዱ ባለበት በብሉይ ዘመን ከእርሱ
ውጭ ለቅዱሳን ስግደት ከተፈፀመ እንደሱ ብሎ ባልተናገረበት በሐዲስ ኪዳን ስግደት ለቅዱሳን እንዴት አይገባም?? እንደሱ ሲል በብሉይ የተናገረው ቃሉ ለዘላለም የሚሰራ ሕያው መሆኑን ዘንግቼ አይደለሁም ይልቅ በብሉይ እና በሐዲስ እያልክ
ለያይተህ የምትቀበል ካንተ ጋራ እያወራሁ ስለሆነ ነው እንጂ።
እንዳንተ ስንፍና ብሄድ ግን በሐዲስ ኪዳን ከእኔ በቀር ለሌላ አትስገዱ ስላላለ ለድመት ብንሰግድም ችግር የለውም ቢል ልክ ነኝ። ባንተ ቋንቋ መናገሬ ነው። ግን ሎቱ ስብሐት ለእርሱ
የአምልኮ ለቅዱሳኑ ደግሞ የክብር ስግደት ከመፈፀም ውጭ ለማንም አልሰግድም።
እሱ=> እሱ በብሉይ ስግደት ይፈፀም ነበር በሐዲስ ግን አይፈቀድም እንዳይለኝ አስቀድሜ በሐድስ እንደተፈቀደ ስላሳየሁት(ሐዋ 16:29) ምን ይለኝ እንደነበረ አላውቅም።
መሄጃ ቢያጣ ኦህ ይቅርታ በቁርአን አልተፈቀደም ማለቴን ነው እንኳ ቢለኝ ዲያብሎስ ለአደም ባለመስገዱ መቀጣቱን ለመንገር ብዙ አይከብድም። ሱራት አል በቀራህ (2) የቀረን የምስጋና ጉዳይ ነው። እሱ መጀመርያ ላይ እንዳየነው ቃሉ <<ምላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ
ተፅፏልና>> ስለምል ምላስ ያለው ሁሉ ከእግዚአብሔር ውጭ ማንንም ማመስገን የለበትም ባይ ነው።
እኔ=> እንደምታወቀው <ምላስ ሁሉ> ሲል <ትውልድ ሁሉ> ማለቱ ነው። ለሁሉ ግልፅ የሆነ ነገር ስለሆነ አላማው ሌላ
ካልሆነ በስተቀር አይደለም ይለኛል ብየ አልጠብቅም። ታዲያ መፅሐፍ ቅዱስ ትውልድ ሁሉ ለማርያም ብፅዕት ይላታል
የሚለው ቃል አላነበብክምን ።
<< እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይለኛል። ሉቃ
1:48>>
እና መፅሐፍ ተሳስቷል ማለት ነው? ሐሰት
ወይስ ቅዱስ ሉቃስ ተሳስቶት ይሆን? ሐሰት
ሉቃስማ የፃፈው በመንፈስ ቅዱስ እንጂ ከራሱ አይደለም። ሐዋ 1:14 ሥራ 2
እንደሱ እንዳትል መፅሐፉ ቅዱስ ነው ብለህ ተሸክመኸዋል ከእነርሱ አንዱ የሉቃስ ነው። እለው ነበር እናንተም መንፈስ ቅዱስ በገለጠላችሁ መጠን ምን ትሉት እንደነበር በኮሜንት ያስቀምጡለት!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን ሓሰበላ ኣለማ ዘጉንዳጉንዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Channel photo updated
"ከሰማይ መስቀል፣ ጽዋ...መውረዱን በቅዱሳት ገድላት መገለጹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለምን???
@And_Haymanot
✞ ፩. የንዋያተ ቅድሳት መውረድ፤
እንደ ገድለ ቅዱስ ላሊበላና ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ባሉ ገድላት ላይ ከሰማይ መስቀል፣ ጽዋ...መውረዱ ተገልጧል።
አብርሃም በፍጹም ሃይማኖት መታዘዙን ይገልጥ ዘንድ አንድ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ እግዚአብሔር ሲፈትነው እርሱም "እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃለሁ።" ያለኝን ዘነጋውን? ወይንስ ተወው? ብሎ ሳይጠራጠር ልጁን ይዞ በቀረበ ጊዜ
እግዚአብሔር ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ የታሰረ ነጭ በግ እንደወረደለት ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ዘፍ.22፥3-19።
በሰማይ በግ የሚያረባ ኑሮ ነውን? በጭራሽ!! በአምላካዊ ተኣምር የተገኘ እንጂ። ለሙሴም እግዚአብሔር ሁለት ጽላቶችን የሰጠው ጸፍጸፍ(ሰሌዳ) ሰማዩን ከየት አምጥቶት ነው? ቢባል
በአምላካዊ ተኣምር መገኘቱን ከመግለጥ ያለፈ በምርምር
አይደረስበትም። ዘጸ.32፥1-16። ለእስራኤል ዘሥጋ የወረዳው መናም ይህንኑ አሳባችን ያስረግጣል። ዘጸ.16።
✞ አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር እሱ ባወቀ ለእሥራኤል ዘሥጋ ከሰማይ ሥጋ ማውረዱን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል/ዘኁ.11፥1-34/። በሰማይ ቄራ ኖሮ ነው? በማኅበር የተደራጁ ሥጋ አራጅ ማኅበራት በሰማይ አሉ?
❖ ከሰማይ ሰው የሚበላውን ያውም ከአይሁድ ሰንበት/ ከቅዳሜ/ በቀር በየቀኑ ትኩስ፥ ትኩስ ሥጋ ከሰማይ እንደዝናብ ያዘነበ አምላካችንን ከየት አመጣኸው? ሳንል አምነን በፍጹም
ምስጋና ከተቀበልን ብርሃናዊ ቅዱስ መስቀል፥ ጽዋ...ከሰማይ ቢወርድ ከየት አመጣኸው? ልታደርገው አትችልም ሊለው የሚደፍር ማነው???
ከሰማይ ስለወረደው መስቀልና ጽዋ የሚጠይቁ ቢኖሩ ለነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ከሰማይ እንጎቻና በማሰሮ ውኃ
ያወረደለትን እግዚአብሔር/1ኛነገ.12፥6/ በትክክለኛ እምነት ሆነው በጸሎት ቢጠይቁት ይገልጥላቸዋል።
እነዚህን ለመሰሉ ነገሮች ሁሉ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን "ከግብር አምላካዊ ተገኙ።" ትላለች። ይህም ስለ ጽላቶቹ "... ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸባቸው
የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።" ዘጸ.32፥16 የሚለውን መሠረት
ያደረገ ነው።

✞ ፪. የሰንበት መናገር፤
❖ በድርሳነ ሰንበትና በቅዳሴ አትናቴዎስ እንዲሁ በሰዓታቱ ላይ ሰንበተ ክርስቲያን እንደምትናገር መገለጹ አንዳንድ ሰዎችን
ያሳስባቸዋል ። ሰንበት አካል የላት/እጅ፣ እግር፣ አፍ፣ ...የላት/ እንዴት? የሚል ጥያቄ የሚፈጥርባቸውም አልጠፉም።
በመጀመሪያ እንደ ሰንበት ያሉ ረቂቃን አካላትን በሰውኛ ዘይቤ መግለጽ በጥንት መጻሕፍት ዘንድ የተለመደ ነው።
(Personification) ይሉታል። በአይሁድ ጥንታዊ መጽሐፍ በታልሙድ "ረቢ ሐኒና በሰንበት ዋዜማ ፀሐይ በምትገባበት ጊዜ እንዲህ አለ፤ ኑ ንግሥት ሰንበትን እንቀበላት ዘንድ እንሂድ፤ ሙሽራዬ ሆይ ነይ ሙሽራዬ ሆይ ነይ።" እንደሚል ተመዝግቧል
[The Babylonian Talmud, seder mooed sabath II,
London 1938, P.588]።
ከሥነ ፍጥረት ምሥጢር አንጻር ስንመለከተው ደግሞ ዕለታት የሁለት ፍጥረታት አንድነት ናቸው። የጨለማና የብርሃን። ጨለማና ብርሃን ሁለትነታቸው ሳይቀር በአንድነት ቀን ወይንም
ዕለት ይባላል። ስለዚህ ስለ ሰንበት መናገር ማለት የእነዚህን የሁለቱን አንድነት መናገር ማለት ነው። ይህም የነፍስን ነባቢነት ከሥጋዊ ብልት(ከሰውነት ክፍል) ከአፍ ከምላስ ጋር ተዋሕዶ እንደሚገለጠው ያለ ነው። ይህም ተዋሕዷቸውን ለመናገር
እንጂ ግዘፍ አካል አላቸው ለማለት አይደለም። ፍጥረት እስከ ሆኑ ድረስ ደግሞ ለፈጣሪያቸው ይናገራሉ መልስም ይሰጣሉ። እኛ ለምን አልሰማናቸውም ሌላ ጥያቄ ነው። ፍጡር ለፈጣሪው
የማይመልስ ከሆነ ችግሩ የፍጥረቱ ሳይሆን የፈጣሪ ነው ወደ ማለት ጥልቅ ክህደት ውስጥ ያስገባል። ሎቱ ስብሐት(ለእርሱ ክብር ይግባው)ና ፈጣሪያቸው እንዳያውቁት አድርጎ ፈጥሯቸዋል ያሰኛል።
ለእርሱ ክብር ምስጋና ይግባውና እርሱ የፈጠረው ሁሉ ምሉዕ ስለሆነ "መልካም እንደሆነ አየ፤" ተብሎ ተገልጿል።
ዘፍ.1፥1-22። ስለዚህ ሰንበት ልትመሰክር ትችላለች። ቋንቋው
ግን በልሳነ ሰብእ(በሰው ቋንቋ) ላይሆን ይችላል። ጌታችን በተሰቀለበት ዕለት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ መሬትና መቃብር የመሰከሩት በሰው ቋንቋ ሳይሆን ለሰው በታወቀ በተረዳ ተኣምር
እንደሆነው ሁሉ የሰንበትም እንደዚሁ ይሆናል። በቅዱስ መጽሐፍ መሬትና ውኃ ፍጥረታትን እንዲያወጡ ሲታዘዙ ሰምተው ፈጽመዋል። የሰውን ጆሮ የመሰለ ጆሮ ግን አልነበራቸውም።
ከእርሱ ለሚወጣው ቃል ስለ ፈቃዱም የሚታዘዙና የሚመልሱ ሆነው ለራሳቸው በሚስማማ ጸጋ ከብረው ተፈጥረዋልና። ቅዱስ ዳዊትም "አቤቱ ውኆች አይተውህ ፈሩ።" /መዝ.76፥6/ ያለው
አምላካቸውን ዐውቀው መታዘዛቸውን ለመናገር እንጂ የሰውን የመሰለ ዓይነ ሥጋ አላቸው ለማለት እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ከዚህ አንጻር ሰንበት ትናገራለች።
"ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።" መዝ.113፥3 ሲል ባሕር የምታይበት እንደ ሰው ዓይን አላት? የዮርዳኖስ ወንዝስ ወደ ኋላው የተመለሰው እንደ እኛ እግር
ኖሮት ነው? "መልሶም። እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች
ይጮኻሉ አላቸው።" ሉቃ. 19፥40። መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የቢታንያ ድንጋዮች እንደሚጮኹ ሲናገር ድንጋዮች እንደ ሰው ልሳን፥ አፍ አላቸው ማለቱ ነውን? ለእኛ ለፍጡራን ድንጋይ
ግዑዝ በድን አካል ቢሆንም ለፈጣሬ ዓለማት ለቅድስት ሥላሴ ግን እሱ ባወቀ እንዲናገሩ ያረጋቸዋል፥ ሥራም ያሰራቸዋል።

✞ አካል ስለሌላት አትናገርም ማለት አካል ሳይኖራት እንዴት አከበራት ብሎ እግዚአብሔርን እንደ መተቸት ይሆናል።
"እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።" ተብሎ
ተጽፏልና። ዘፍ. 2፥3።
፠ በአጠቃላይ ገድላትን በሚገባ ለመረዳትና በገድልና በትሩፋት
የኖሩትን አበውና እማትን/እናቶችን/ ሃይማኖትና ምግባር መያዝ፤ በመንገዳቸውም መጓዝ ተገቢ ነው። ያለበለዚያ የይመስለኛል እምነት መድረሻው ክህደት፤ የክህደትም መደምደምያው ሞት ነው።
by ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
\\\አይናችን ነሽ ማርያም///
አይናችን ነሽ ማርያም አንችን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሃሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ!!!
አዝ፡፡፡
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
ባሽዋላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
አዝ፡፡፡፡
ገብተሻል ላትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነው ባንችነው የጠፋው ተገኝቶ
አዝ፡፡፡፡፡
ወይኑንያፈራሽው የወይን ሐረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሸን በቀራኒዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
አዝ፡፡፡፡፡
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ፀዋሪተ ፍሬ ያዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
አዝ፡፡፡
ከሃገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
ባደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጂ
ለፃድቃን አይደለም ለሃጣን አማልጂ
አሜን ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን
ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጥቅምት 20/2011 ዓም
¶ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ የተሃድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ በቸልተኝነት የሚመለከቱ አንድ አንድ አህጉረ ስብከቶችን አስጠነቀቀ ።
¶ በተሃድሶ መናፍቃን የተዘረፉ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሐብት ንብረቶች በሙሉ በህግ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
¶ ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው ከያዛቸው አጀንዳው አንዱ በሆነው ፥ በተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ዙሪያ የሰመረ ውይይት በማድረግ ይህንን የተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በውስጥም በውጭም ያሉ አህጉረ ስብከቶች ፥ በቸልተኝነት የሚመለከቱ
ካሉ ፥ አበክረው በጉዳዩ ዙሪያ እንዲሰሩ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል ።
¶ # እነዚህን መናፍቃን ማሽሞንሞኑ ይብቃ ! ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ በአህጉረ ስብከት ደረጃ እስከ አጥቢያ
አብያተክርስቲያናት ድረስ የፀረ ተሃድሶ መናፍቃን መኃቀፍ ያላወቀሩ አንድአንድ አህጉረስብከቶች ባስቸኳይ አቋቁመው
እንዲሰሩና አስቀድመው ያቋቋሙ ደግሞ ያለመዘናጋት ጠንክረው እንዲሰሩ ከስምምነት ላይ ደርሷል ።
¶ በዚሁ አጋጣሚ የተሃድሶ መናፍቃን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሙዳይ 12 million ብር ዘርፈው በዱከም(Dukem ) ከተማ ፥ባለቤትነቱ የአቶ በጋሻው እና የአቶ
አሰግድ በመሆን ለምንፍቅና አገልግሎታቸው በEconomy
ረገድ እንዲደግፋቸው ያቋቋሙትን Koyla (ቆይላ ) የህትመት ፋብሪካ ለባለቤቷ ለቤተክርስትያን በህግ ያስመልሳል ተብሎ ይጠበቃል ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ጥያቄ፡- "አባትና እናት የትውልድም ቁጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።" ዕብ.7፥3-5።

ይህን ገጸ ንባብ በማንበብ ብቻ በመያዝ መልከ ጼዴቅ ሰው አይደለምን? ሰው ከሆነ ለምን እናትና አባት የሉትም ይላል? ከአባታችን ከአዳምና ከእናታችን ከሔዋን በቀር ከእናት አባት ያልተገኘ ፍጡር ሰው አለ? ወዘተ...የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
❖ "አባትና እናት.." አልቦ ዘዘከረ ሎቱ አበ ወኢእመ የሚለው ለመልከ ጼዴቅ እገሌ አባቱ እገሊት እናቱ ብሎ የተናገረለት መጽሐፍ የለም ሲል ነው።
"...የትውልድም ቁጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፥..." ወአልቦ ጥንት ለመዋዕሊሁ ወኢማኅለቅት ለሕይወቱ ሲል ደግሞ በዚህ ቀን ተወለደ በዚህ ቀን ሞተ ብሎ የተናገረለት መጽሐፍ የለም ማለቱ ነው፤ ምነው በስንክሳር ተጽፎ የለምን ቢሉ በሌዋውያን መጽሐፍ ስላልተጻፈ እንዲህ አለ።

መጻሕፍተ መነኰሳት ሁለተኛ መጽሐፍ "ፊልክስዩስ" ላይ ክፍል 2፤ ተስእሎ 17፤ ገጽ 39 ላይ "አባትና እናት...የሉትም" የሚለውን ገጸ ንባብ ይዘው 'መልከ ጼዴቅ ወልደ እግዚአብሔር ራሱ ነው' ላሉት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ፦ የነገደ ካም ትውልዳቸው ነገዳቸው በኦሪት ባይጻፍ ነው እንጂ እናት አባት አሉት። ሐሴል ሳሌምን፤ ሳሌም ሜልኪን፤ ሜልኪ ደግሞ ሜልኪንና መልከ ጼዴቅን ይወልዳል፤ እናታቸው ሰሊማ ትባላለች። አባታቸው ጣዖት ያመልክ ነበርና መልከ ጼዴቅን ጠርቶ ከበጎቹ መርጠህ ለጣዖት የምንሰዋው በግ አምጣልኝ አለው፤ አባቴ ይኸ ጣዖት ምን ይረባናል አለው፤ እምቢ ብለህ እንደሆነ አንተን እሰዋሀለሁ ብሎ ያዘው። እናቱ ትወደው ነበርና ባይሆን በዕፃ(ጣ) ይሁን እንጂ ልጄን አትሠዋብኝ አለችው፤ ዕፃ ቢጥል በታላቁ ወጣበት፤ ሊሠዋው ይዞት ሄደ። እናቱ አይታ ወንድምህን ሲወስድብህ ዝም ትላለህን አለችው፤ ወደ ጌታ ቢያመለክት ከሰማይ እሳት ወርዶ አባቱንም ወንድሙንም በልቷቸው እርሱ ብቻ ቀረ። ከዚህ በኋላ ወደ ዮርዳኖስ መጥቷል ብሎ ነግርዋቸዋልና እንዲህ አለ። ይላል።

❖ "አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።" ዮሐ.8፥56 ትርጓሜው፦ አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር አበ ብዙኃን አባታችን አብርሃምን ዮርዳኖስን ተሻግረህ ሒድ ምሳሌውን ታያለህ አለው። ዮርዳኖስን ተሻግሮ ቢሔድ መልከ ጼዴቅ ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት ይዞ ተቀብሎታል፤ ምሳሌ ነው። መልከ ጼዴቅ የጌታ፤ የቀሳውስትም ይሉታል፤ አብርሃም የምእመናን፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት፤ ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት የሥጋው የደሙ ምሳሌ። ወባረኮሂ(መልከ ጼዴቅ አብርሃምን ባረከው፤ አብርሃም ቡሩኩ ለእግዚአብሔር ብሎ)።

❖ "...ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።" ዕብ.7፥3-5 ማለት፦ የወልደ እግዚአብሔር ክህነት በመልከ ጼዴቅ ክህነት አምሳል ጸንቶ ለዘለዓለሙ ይኖራል። ጌታ መልከ ጼዴቅን በምን ይመስለዋልና አምሳሊሁ(ተመስሎ) አለ ቢሉ መልከ ጼዴቅ በስንዴ በወይን ያስታኩት ነበር፤ እሱም ሥጋውን ደሙን በስንዴ በወይን ሰጥቶናልና፤ መልከ ጼዴቅ ሹመቱን ከእገሌ ተሾመው አይባልም ከእግዚአብሔር ተሾሞታል፤ እሱንም(ጌታችንም) ሤሞ አቡሁ ይለዋልና፤ የመልከ ጼዴቅ ሹመት ለእገሌ አለፈ አይባልም፤ የጌታም ሹመት ለእገሌ አለፈ አይባልምና።
"የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው። " ዕብ. 7፥2 ሲል የመጀመሪያ የስሙ ትርጓሜ መልከ ጼዴቅ ማለት ንጉሠ ጽድቅ ማለት ነው። የኹለተኛው ስሙ ትርጓሜ ንጉሠ ሳሌም ማለት ንጉሠ ሰላም ማለት ነው። የሀገሩ ሰዎች ሔደው ንገሥልን ብለውታል፤ ያስጠበቀኝን(አጽመ አዳምን) ትቼ አይኾንም ብሏቸዋል። እንዲህ ግን ስለኾነ ቢከራከሩ እውነት ይፈርድላቸው ነበርና ንጉሠ ጽድቅ፤ ቢጣሉ ያስታርቃቸው ነበርና ንጉሠ ሰላም አለው። ይህን ለምን አነሳው ቢባል በትሩፋቱ ያጸደቀን/ያከበረን/ ንጉሠ ጽድቅ(የእውነት ንጉሥ)፥ በደሙ ያስታረቀን ንጉሠ ሰላም(የሰላም ንጉሥ) መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለማለት ነው።
by ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ለቅዱሳን መስገድን ያስተማረው እግዚአብሔር ነው፡፡
@And_Haymanot
መጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ ለቅዱሳን መስገድ አንደሚገባ ያስረዳል፡፡ በዘፍ. 27፡29 “አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን
የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።” ብሎ ልጁን ያዕቆብን የባረከው ይሥሐቅ ነበር፡፡ ይህን ምርቃት ማግኘት የነበረበት የያዕቆብ ታላቅና በኩር የነበረው ኤሳው ቢሆንም ያዕቆብ በእናቱ ብልኃት
ታግዞ ተመረቀ፡፡ ይሥሐቅን እንዲህ ብሎ እንዲመርቅ ያደረገው እግዚአብሔር አምላክም የአብርሃም ፣ የይሥሐቅና የኤሳው አምላክ በመባል ፋንታ የአብርሃም ፣ የይሥሐቅና የያዕቆብ
አምላክ ተባለ፡፡ አምላካችንን ሙሴ ማነህ ብሎ በጠየቀው ጊዜም ራሱን ሲገልፅ እርሱ ራሱን ለአብርሃም ለይሥሐቅና
ለያዕቆብ የሚገለጥና ምድረ ርስትንም ሊሰጣቸው ቃል እንደገባ ለሙሴ ገልፆለታል፡፡ ስለዚህ በይሥሐቅ አንደበት አድሮ ያዕቆብን የመረቀው እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህንን የሚጠራጠሩ ቢኖሩ
እንኳን የይሥሐቅን ምርቃት የፈጸመው /እንዲደርስ ያደረገው/ እግዚአብሔር ነው፡፡ ታዲያ አምላካችን ለቅዱሳን የሚገባን ስግደት የሚቃወም ቢሆን ይሥሐቅን “ሕዝብም ይስገዱልህ”
ብሎ ሲመርቅ አይገሥጸውም ነበርን? ባይገሥጸው እንኳን “ልጆች ይስገዱልህ” ብሎ የመረቀ ይሥሐቅን ምርቃቱን
ባለመፈጸም /እንዲደርስ ባለማድረግ/ ቃሉ ልክ እንዳልሆነ አያሳይም ነበርን? ደግሞስ ለፍጡር በሚገባ መስገድ ስሕተት ቢሆን ከብዙ ዘመን በኋላ ያዕቆብ ከነቤተሰቡ ለኤሳው በመስገድ
የአባቱን የይሥሐቅን “ስሕተት” ይደግመው ነበርን? ከዘፍ.37-41 ድረስ የፃድቁን የዮሴፍን ታሪክ እናገኛለን፡፡ በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ለዮሴፍ እንደሚሰገድለት የሚተነብይ
ሕልም አሳየው፡፡ “እኔ ያለምሑትን ሕልም ስሙ፡ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናሥር ነበርና፤ እነሆም የእኔ ነዶም ቀጥ
ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከበው እነሆ ለኔ ነዶ ሰገዱ” /ዘፍ.37፡7/፡፡ ወንድሞቹ ከሕልሙ የተነሣ እንደሚሰግዱለት ተረድተው ወንድማቸው ዮሴፍን ይበልጥ
ጠሉት፡፡ ለቅዱሳን አንሰግድም ብለው ቅዱሳንን የማያከብሩ ሰዎች በትዕቢት ራሳቸውን ከቅዱሳን በላይ በማድረግ፣
ወንድማቸውን ዝቅ ያደረጉትን የዮሴፍን ወንድሞች ይመስላሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህንን እንዲረዱት ዮሴፍ ነዶ በተባሉት በወንድሞቹ ብቻ ተሰግዶለት የሚቀር ሳይሆን በሌሎች ፍጥረታትም ዘንድ እንደሚከብር ሲገልፅላቸው ዮሴፍን ሌላ ሕልም ዐሳየው፡፡ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፣ እነሆ
ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” / ዘፍ.37፡9/፡፡
እግዚአብሔር ተናግሮ ነገር አይቀርምና ወንድሞቹ እንዳይሰግዱለት፣ እንዳይገዙለት ሽተው ሊገድሉት ቢሞክሩም፣ ጉድጓድ ውስጥ ቢጥሉትም፣ ለነጋድያን ቢሸጡትም በሀገራቸው ሊፈጽሙት የከበዳቸውን ሐቅ ርሐብና ድርቅ ሲመጣ በባዕድ
ምድር በግብፅ ሊያደርጉት ግድ ሆኖ ወንድሞቹ ለዮሴፍ መስገዳቸው አልቀረም፡፡ “የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በግምባራቸው በምድር ላይ ሰገዱለት” /ዘፍ.42፡6/፡፡

ለቅዱሳን አንሰግድም የሚሉ ሰዎች ምንም እንኳን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሊያጠፉት ሽተው ቢሰርዙና ቢደልዙትም፣ በቀላል አማርኛ በሚል ፈሊጥ ቃሉን ቢዘነጥሉትም፣ ጥቅስን ዘንጥሎ በመጣል ጉድጓድ ውስጥ ቢጥሉትም፣ አውጥተው ለሥጋዊ
ስሜትና ለዓለም ክህደት ቢሸጡትም ርሐበ ነፍስ ድርቀተ መንፈስ ሲመጣ በሀገራቸው፣ በሕይወተ ሥጋቸው ያላደረጉትን እውነትን በሲዖል እንኳን ለማድረግ መጓጓታቸው አይቀርም፡፡
“የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ” እንዳለ ኢሳይያስ /ኢሳ.60፡14/፡፡ በምድር ምጽዋት የነፈገውን አልአዛርን በሲዖል በአብርሃም አማላጅነት እንደለመነው ነዌ፡፡ /ሉቃ.16፡20-31/፡፡ ጳዎሎስንና ሲላስን ለመሰሉ ቅዱሳን ለእናንተ የሚገባው ስግደት ሳይሆን መታሠር ነው ብለው ደብድበው ካሠሯቸው ሰዎች መኃል
አንዱ የሆነው የእሥር ቤቱ ጠባቂ በእሥር ቤቱ ውስጥ በነጳውሎስ ዝማሬ ምክንያት ከደረሰው ታላቅ መናወጽ በኋላ
ከሥራቸው ተደፍቶ ሰገደላቸው፡፡ “ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ” /ሐዋ.16፡29/ እንዲል ግብረ ሐዋርያት፡፡ የቅዱሳኑን ዝማሬ ሰምቶ እሥር ቤቱን አናውጾ ጠባቂውን እንዲሰግድ
ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?

☞እግዚአብሔር ቃል በቃል ለቅዱሳን ስግደት እንደሚገባ የተናገረበት ቦታን ለሚሻ ደግሞ እነሆ፡~ በራእየ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ላይ ሁለት የቤተክርስቲያን ጠባቂዎችን እናገኛለን፡፡ አንደኛው በሰርዴስ የሚገኘው
መልአክ /ጠባቂ/ ሲሆን አንደኛው ደግሞ የፊልድልፍያ ቤተክርስቲያን መልአክ /ጠባቂ/ ነው፡፡ የሰርዴሱ ጠባቂ ሥራው በአምላክ ፊት ፍጹም ያልሆነና በቁሙም ሞተሀል የተባለ ሲሆን እንዲነቃና ንስሐ እንዲገባ አግዚአብሔር አዟል፡፡ እንዲህ ካላደረገ ግን እንደሚፈርድበት “እመጣብሃለሁ” ሲል ነግሮታል፡፡ የፊልድልፍያው መልአክ /ጠባቂ/ ግን በእግዚአብሔር ፊት
የተወደደና ቅዱስ ነበርና እግዚአብሔር እንዲህ አለው “ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ፤ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ትንሽ ቢሆን ቃሌን
ጠብቀሃልና ስሜንም አልካድህምና፡፡ እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ
አደርጋቸዋለሁ” /ራእ.3፡8-9/፡፡
ለቅዱሳን ስግደት አይገባም የሚሉ ምንኛ ያልታደሉ ናቸው? “የተከፈተ በር ሰጥቼሀለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም” የተባለላቸውን ቅዱሳንን የሚመሰገኑበትን የጸጋ በር ሊዘጉ
የሚሮጡ ምንኛ ምስኪኖች ናቸው? “እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር” የተባሉ ክርስቲያን ሳይሆኑ ክርስቲያን ነን የሚሉ ነገር ግን
የሚዋሹ ምንኛ አሳዛኝ ናቸው? እነሆ ክርስቲያን ሳይሆኑ ክርስቲያን ነኝ በሚል ቅዠት ቅዱሳንን የማይወዱ የሰይጣን
ማኅበር አባላት መባላቸው እንዴት የሚደንቅ ነው? እንደ ቅዱሳን ሁሉ እንዲሠጣቸው ተፈጥረው እነርሱ ራሳቸው ተላልፈው መሠጠታቸውና ባይወዱም እንኳን በቅዱሳን እግር ፊት
መስገዳቸው የማይቀር መሆኑ እንዴት ግሩም ነው? በተዐብዮ ራሳቸውን እኔም እንደ እገሌ ቅዱስ ነኝ የሚሉ ዘባቾች ቅዱሳንን በትሕትናቸውና አንዱ ለአንዱ በመስገዳቸው የሚወድ እግዚአብሔር “እንዴት እንደወደድሁህ ያውቁ ዘንድ
አደርጋቸዋለሁ” ብሎ ለቅዱሳን ቃል መግባቱ እንዴት ያለ ምሥጢር ነው?
ይቆየን።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን?" ቅዱስ ኤፍሬም
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ፡፡ እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን እንዲህም እንላለን☞Open
ጥያቄ፡- በጥምቀት ጊዜ ወልድ እየተጠመቀ ባለበት ሰዓት አብ የምወደው ልጄ ይኽ ነው ሲል ወልድ እታች እየተጠመቀ ከሆነ አብ በምን ቃልነት ተናገረ?? ወልድ የአብ ቃሉ
ከሆነ...
@And_Haymanot
መልስ፦ ጥያቄው በቀጥታ የአካልን ትርጉም የሚያመጣ ነው።.. አካልና ባሕርይን ትርጉማቸውን በትክክል መረዳት ለምሥጢረ ሥላሴና ለሥጋዌ በጣም አስፈላጊ ነው።
*አካል ማለት "ቀዋሚ"፣ "እኔ ነኝ ባይ" ተብሎ ተተርጉሟል።..
*አብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ማወቂያቸው፣ ወልድ የአብና
የመንፈስ ቅዱስ መናገሪያ ቃላቸው፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የአብና የወልድ ሕይወታቸው መሆኑ የታወቀ የተረዳ ነው።.. በመሆኑም ክርስቶስ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ፡ አብ በሰማይ ሆኖ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" አለ።.. ይህን ያለው አብ በወልድ ቃልነት ነው። ቢሆንም ግን "በሰማይ ሆነህ የምወደው ልጄ ይህ ነው ያልከው ማን ነኝ ትላለህ?" ብለን ብንጠይቅ "እኔ ነኝ"(እኔ
ነኝ ባይ እንዳልነው) የሚመልስን እግዚአብሔር አብ ነው .. ምክንያቱም በህልውናው በሚኖር በወልድ ቃልነት ቢናገረውም ("ቢናገረውም" እንኳ ስንል እርሱን እያመለከትን ነው) ተናጋሪነት
የተለየ አካልነት (እኔነት) ስለሆነ አብ ነው እንላለን ... ይህ የህልውናቸውን ብቻ ስንናገር ነው።.. ሌላው ቀላል አመክንዮ
ደግሞ ".. የምወደው ልጄ" ማለቱ እርሱ አባት (አብ) እንደሆነ በዚያውም ማስረዳቱ ነው።
* ነገረ ድኅነት ላይ።.. ሥላሴ ዓለምን አድነዋል ተብሎ በደንብ ይነገራል። እንደውም ስለ አብ መጽሐፈ ኪዳን ዘሠርክ "..ወበሞተ ወልድከ ቤዘውከ ወዘተገድፈ ኀሠሥከ.." ማለትም
"በልጅህ ሞት አዳንህ። የጠፋውን ፈለግህ።" ተብሎ ተነግሯል። ማዳን (አድኅኖት) የሥላሴ ቢሆንም መሰቀል ግን ለወልድ ብቻ የሚነገር ነው። በተለየ አካሉ ያደረገው ነውና።.. "የተሠቀልከው
እኔ ነኝ ባይ ማን ነህ?" ብንል.. ወልድ መሆኑ ላይ እንደርሳለንና።.. ማዳን ግን ሥልጣናዊ ነው።.. ስለሆነም አብም
አዳነ፡ ወልድ አዳነ፡ መንፈስ ቅዱስ አዳነ ይባላል።... *ሌላ ማንጸሪያ ልጨምር፡- ነገረ ትንሣኤ። ጌታን ማስነሳት የሥልጣን (የኃይል) ሥራ ነው ስልሆነም ምንም ምሥጢር ሳይፋለስ "አብ አስነሳው" ተብሏል፤ "መንፈስ ቅዱስ አስነሳው"
ተብሏል፤ እሱ ራሱ "በሥልጣኑ ተነሣ" ይባላል።.. ሥልጣናቸው አንዲት ናትና ምንም እንግዳ አይሆንም።.. ከሙታን ስለመነሣት ሲነገር ግን "ወልድ ተነስቷል" ይባላል እንጂ ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ ይህ አይነገርም። ምክንያቱስ? ከሙታን ተለይቶ መነሳት ልክ እንደ ልደትና ስቅለት "የተለየ አካል" ሥራ ነውና።
by zemaryam zeleke
@And_Haymanot
@And_Haymanot