፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዓሉን የሰላም የበረከት የበጎነት የፍቅር ያድርግልን
@And_Haymanot
መልካም በዓል
✞ ✞ ✞ ፩ ሃይማኖት ✞ ✞ ✞ ✞
@And_Haymanot
ሰላም ተወዳጆች እንደምን ቆያችሁ እንኳን ለዚህች ልዩ የትንሳኤ ቀን በሰላም አደረሳችሁ እያልን በ Data connection መዘጋት ምክንያት ብንርቅም እግዚአብሔር ፈቅዶ ተመልሰናልና
በተለመደው መልኩ ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ከመረጃ ጋር ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡ እናንተም ቢያንስ ለምታውቋቸው አምስት ሰዎች ይህን በማጋራት ሌሎችን የማዳን ስራ አብረን እንስራ እንላለን፡፡
እግዚአብሔር ይርዳን
✞ ✞ ✞ ✞ ፩ ጌታ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
✞ ✞ ✞ ፩ ሃይማኖት ✞ ✞ ✞ ✞
✞ ✞ ፩ ጥምቀት ኤፌ4:5 ✞ ✞ ✞
✞ ✞ @And_Haymanot ✞ ✞ ✞
{{{{{J}{{{{O}}}}}{I}}}}}}{N}}}}}}
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ምስጢር)
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
ከወቅታዊ መረጃ ጋር የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ሃይማኖት"👈
ይህን ለሌሎች በማጋራት የቤተክርስቲያናችንን ትምህርት የማዳረስ ሃላፊነታችንን እንወጣ
👉 @And_Haymanot 👈
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን ✞
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
✞✞ @And_Haymanot ✞ ✞
✞✞ @And_Haymanot ✞ ✞
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
✞መልካም የትንሳኤ በዓል✞
🙏1
ጠንቋይ ወደ መልካም ነገሮች ሊመራ ይችላል??? ???

@And_Haymanot

ጥያቄ፦ በሁለት አጋጣሚዎች አንድ ተመሳሳይ ነገር ከ 2 ባልንጀሮቼ ሰማሁ:: ነገሩ እንዲህ ነው አንዱ ባልንጀራዬ
የመድኃኔ ዓለምን ዝክር የሚያዘክረው በጠንቈይ ታዞ መሆኑን ነገረኝ እየተገረምኩ ሳለ አንዱ ደግሞ ወደ አንድ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አዘውትሮ ለበዓለ ንግሥ የሚሔደው በጠንቈይ ታዞ እንደሆነ ሲነግረኝ ግራ መጋባት ውስጥ ገባሁ:: በእውኑ ጠንቋይ ወደ መልካም ነገሮች
ሊመራን ይችላል? ክፉና ደግ የሚባልስ ጥንቆላ አለ?
@And_Haymanot
መልስ:-ጥንቆላ በእግዚአብሔር የተወገዘ የኃጢአት ሥራ ነው:: ስለዚህ የእግዚአብሔር ወገኖች ከዚህ ተግባር ጋር ሊተባበሩ አይችሉም:: አስቀድሞ በመጽሐፍ ቅዱስ "ሟርተኛም ሞራ ገላጭም አስማተኛም መተተኛም
በድግምት የሚጠነቁልም መናፍስትንም የሚጠራ ጠንቈይም ሙታን ሳቢም በወፍም የሚያሟርት በአንተ ዘንድ አይገኝ፤ ይህንን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው:: ... አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሁን::" ዘዳ. 18፥11 ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔርን የሚያምኑ ወገኖች ሁሉ ከዚህ አጸያፊ ተግባር ጋር ሊተባበሩ አይችሉም:: ሰይጣን ማታለያን
ለማድረግ የሚያስችል ማስመያዎች የመሥራት ኃይል እንዳለው በፈርዖን ጠንቈዮች ሥራ መረዳት ይቻላል::
"ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብጽም ጠንቈዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ እባቦችም ሆኑ::"
ዘጸ.7፥10 እንደ ተባለ የሚያስደንቅን ነገርም ሊያደርጉ ይችላሉ:: ነገር ግን በእውነተኛው በእግዚአብሔር ኃይልና
ጥበብ ፊት ግን ሐሰተኛነታቸው ግልጥ ይሆናል:: የአሮን በትር የፈርዖንን ጠንቈዮች በትራቸውን ውጣለችና፤
ስለዚህ ተግባሩ የሐሰትና የወደቀውን የሰይጣንን የማታለያ ኃይል መሠረት ያደረገ ነው:: ሐዋርያትም የጥንቆላ ሥራ
ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚያወጣ የኃጢአት ሥራ መሆኑን በግልጽ አስተምረዋል:: ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ
መልእክቱ ይህንኑ ጠቅሶ አስተምሯል/ገላ.5፥20/:: በሐዋርያት ትምህርት ያመኑ ጠንቈዮችና አስጠንቈዮች ከክፉ ሥራቸው ተመልሰዋል:: "ብዙዎች አስማተኞችም መጽሐፎቻቸውን እየሰበሰቡ እያመጡ በሕዝቡ ሁሉ ፊት
በእሳት ያቃጥሉ ነበር::" /የሐዋ.19፥19/:: ጥንቆላ በጥቅሉ የተወገዘ ተግባር እንጂ ክፉና ደግ የሚባል ገጽታ
ያለው አይደለም:: ከላይ እንደተጠቀሰው ዓይነት ማደባለቅ ግን በሰይጣናዊ ዓለም ውስጥ ሊኖር ይችላል:: ይህ ግን የሰይጣን ዓላማው በጎ ስለሆነ ወይም ሰዎች መልካም እንዲሠሩ ስለሚያስብ አይደለም:: ሰይጣን በጎ የሚመስሉ ነገሮችን ለክፉ ዓለማው ማቀባበያ
ሊያደርጋቸው ይችላል:: ይህንን ሀገራችን ሰዎች አባባል 'ሰይጣን ላመሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል' ይባላል::
ሰይጣን መልካምን ቃል መናገሩ በራሱ ዓላማና ማንነቱን በጎ ሊያደርገው አይችልም:: ለዚህም ነው ጌታችንና
ቅዱሳኑ ሰይጣን መልካም የሚመስል ቃል ሲናገር ቢሰሙትም ዝም እንዲል የገሰጹት:: ጌታችን "የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ አንተ ማን እንደሆንህ
አውቄሀለሁ" ያለውን ክፉ ጋኔን "ዝም በልና ከእርሱ ውጣ" አለው እንጂ መልካም የሚመስል ቃል ስለተናገረ ብዙ
እንዲናዘዝ አልተፈቀደለትም /ማር.1፥25/:: በተመሳሳይ ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዮስ አካባቢ የነበረችው የምዋርተኝነት መንፈስ ያደረባት ሴት "እነዚህ ሰዎች
የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የሕይወትን መንገድ ያስተምሩአችኋል" እያለች ስትጮኽ "መንፈስ ርኩስ ከእርሷ እንድትወጣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ" አለው እንጂ መልካም የሚመስል ቃል ስለተናገረ ብዙ እንዲናገር ሰዎችም እርሱን እንዲሰሙት
ተመላልሰውም እንዲጠይቁት አላሰናበተውም:: በአንጻሩ ጋኔን የክርስቶስን ጌትነት በመናገሩ፤ የሐዋርያትንም እውነተኛ ምስክርነት ለሰዎች በማውራቱ የክርስቶስ ጌትነት
የሐዋርያቱም እውነተኛ አገልጋይነት ሊጎድል የሚችል አይደለም:: በተመሳሳይ የፈርዖን ጠንቈዮችም ሊያሸንፉት ስላልቻሉት የሙሴ አምላክ የእግዚአብሔርን ኃይል ታላቅነት በፈርዖን ፊት በግልጽ በመመስከራቸው መልካም
ጠንቈዮች ሊያስብላቸው አይችልም:: ጠንቈዮቹም ፈርዖንን "ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው" ብለውት
ነበርና:: ስለዚህ የጠንቈይ መንፈስም መድኃኔዓለምን አዝክር፤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን ተሳለም፤
ለሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ስእለት አግባ፤ የሥላሴን ጠበል ተጠመቅ ቢል ለክርስቲያኖች የሚገርመው አይሆንም::
አስቀድመን ሥራውን እናውቃለንና:: ዋናው ቁም ነገር ሰይጣን እነዚህን ነገሮች ስለምን ያደርጋቸዋል የሚለው
ነው:: ሰይጣን ቤተ ክርስቲያን እንድንሳለም ወይም ዝክር እንድናዘክር በጥንቆላ መንገድ የሚነግረን የነፍሳችን
ድኅነት ገዶት አይደለም::
@And_Haymanot
1ኛ. በአምልኮ አመንዝራነት
ውስጥ ነፍሳትን ለመዝፈቅ ስለሚፈልግ ነው:: ይህም እግዚአብሔርን እንደሚያስቀና ያውቃልና በብርቱ ቅጣት
ሰዎችን እንዲያጠፋቸው ከመፈለጉ የተነሣ ነው:: ሰዎች እግዚአብሔርን በማምለክ ውስጥ ሌሎች አማልክትን ሌላ ተጨማሪ የሕይወታቸው ገዢ በማድረግ የአምልኮ ደባል ወይም አመንዝራነትን መፈጸም እንደማይገባ ነቢያትም ሐዋርያትም አስተምረዋል:: ኢያሱ እስራኤልን አምልኮተ ባዕዳንን ከአምልኮተ እግዚአብሔር ጋር አደባልቀው በሕይወት ጉዞ ውስጥ መጽናት እንደማይችሉ ሲያሳስብ
እንዲህ ብሎ ነበር:: "እግዚአብሔርን ታመልኩ ዘንድ ባትወዱ ግን አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው
ያላችሁባቸውን የአሞራያውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆነ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ፤ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና::" /ኢያ.24፥15/:: ነቢዩም እንዲህ ይላል "እስራኤል ሆይ ከአምላክህ ርቀህ አመንዝረሀል እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ"/ሆሴ.9፥1/::
ጥንቆላ ጣዖት አምልኮ ነው:: እግዚአብሔርን አመልካለሁ እያሉ መልሶ ደግሞ ወደ ጠንቈይ ቤት መሔድ አመንዝራነት ነው:: ስለዚህ ሰዎች
አውቀውም ሳያውቁም ወደ ጠንቈይ ቤት እየሔዱ መልሰው ደግሞ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲሔዱ በዚህ የከፋና እግዚአብሔርን በሚያስቆጣ በደል ውስጥ መውደቃቸውን መረዳት አለባቸው:: ሰይጣን ይህንን ምክርም ሲሰጣቸው በዚሁ በደል እንዲፀኑ እያደረጋቸው መሆኑን መረዳት አለባቸው::
@And_Haymanot
2ኛ.ልባቸው ለሚያነክሱ አስጠንቈዮች ማታለያ ነው:: አንዳንዶች የጥንቆላ ሥራ ኃጢአት መሆኑን ልባቸው እየነገራቸው ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጥንቆላ ሲሔዱ 'እዚህም እግዚአብሔር
አለ' የሚል ሐሳብ እንዲያድርባቸውና ተረጋግተው በርኩሰቱ እንዲጸኑ ለማድረግም ነው:: እንደዚህ ያሉ ሰዎች በዚህ ሐሳብ ተታለው ሌሎችንም ሊጋብዙ ድፍረት ሊያገኙ ይችላሉ:: ለዚህም ነው የቤተ ክርስቲያን ጉልላት
የሚመስል ቤተ ጣዖት አየን የሚሉ ሰዎች የምንሰማው፣ ለዚህም ነው ቅዱሳት ሥዕላትን በየበሮቻቸው ላይ
ሰቅለዋል ሲሉ የምንሰማው፤ ለዚህም ነው ጫማ አስወልቀው ያስገባሉ፤ እዚያም ጠበል አለ ሲሉ የምንሰማው:: ሁልጊዜ የመምጣት ሐሳብ ለማሳደር፤
በዚህም እግዚአብሔር የሚወደው በጐ ሐሳብ አለ ለማስበል ጥረት ማድረጋቸውን መረዳት ይገባል:: በሌላም በኩል የእግዚአብሔርን ክብር የራሱ የማድረግ የቀደመ የሰይጣን ሐሳብ ነው::
@And_Haymanot
3ኛ.በሌላም በኩል ሰዎች በርኩሰት ውስጥ ሆነው ወደ እግዚአብሔር የመቅረብን ድፍረት ለማለማመድ ነው:: በተቀደሰው ሥፍራ የርኩሰትን ተግባር
🙏1
...እንዲፈጽሙ፤ የተቀደሱ የእግዚአብሔርን
ምስጢራት በረከሰና በአመንዝራነት ሕይወት ውስጥ ሆነው እንዲቀበሉ በበደል ላይ በደልን ደርበው እንዲፈጽሙ
ለማደፋፈር ነው:: በአጠቃላይ ጥንቆላ ከጥንትም ማሳቻ ሆኖ የኖረ ሰይጣናዊ ተግባር ነው:: ጥንቆላ ለራስ ለቤተሰብና ከዚያም አልፎ ለአካባቢ ጠንቅ ነው:: ጥንቆላ ለነፍስም ለሥጋም የማይበጅ ተግባር ነው:: መዘዙም ለቤተሰቦቻችን እየተረፈ ለዘመናት የሃይማኖትን ምሥጢራት የመረዳትን አቅም በተቀደሰ ሕይወት በንጽሕና ለመኖር እንቅፋት የሚፈጥር ከዚያም ለመላቀቅ ተጋድሎን
የሚጠይቅ በመሆኑ ቢያንስ ለልጆቻችንና ለሀገራችን ሰላም ስንል ቆርጠን ለመጣል መረባረብ ይገባናል::
"የእናትህ የኤልዜባል ግልሙትናዋና መተቱ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?" እንዲል /2ኛ.ነገ.9፥22/:: ሰይጣን በጥንቆላ
መንገድ የነፍስና የሥጋችንን ሰላም ሊያናጋ በሚያደርገው የማሳት ሥራው ላይ እንንቃ እንላለን::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በገድለ ክርስቶስ ሠምራ እንዲሁም በተአምረ ማርያም ላይ ለሚነሱ የተሐድሶ መናፍቃን የተሠጠ ምላሽ
@And_Haymanot
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
Share
የአበው ኃይማኖት አትታደስም፡፡
@And_Haymanot
#ፈገግ ብላችሁ ተማሩበት ሰው በተለያየ ነገር ይማራል አይደል ነገሩ
😁😁😁😁😁😁😁😁😁😁
ትላንት አንድ ቀጭን ድምፅ ያለው ወዳጃችን ፍየል ገዛ፡፡ ፍየሏ ስትጮህ የሰው ስም የምትጠራ ነው የምትመስለው፡፡
“በቀለ!” የምትል፡፡ ደግሞም እንደዛ ነው የምትለው፡፡ ቤቱ ወስዶ አሰራት፡፡ መጮህ ጀመረች፡፡ በቀጭን ድምጿ፡፡
“በቀለ! በቀለ! በቀለ!”
በሩ ተንኳኳ፡፡ ባለ ፍየል ጓደኛችን በሩን ከፈተ፡፡ ጎረቤቱ አቶ በቀለ ከደጅ
ቆመው፡-
“አቤት ! ጠራኸኝ??”
በቀጭን ድምፁ ፤ “ኧረ እኔ አልጠራሁዎትም” አለ፡፡ እንዳልጠራቸው በመኃላ
አረጋገጠ፡፡
እንዲህ እያሉ ሄዱ፣ “የማርያም ብቅል እየፈጨሁ ነው!”

ለካ ፍየሏ ናት በቀጭን ድመምጿ በቀለ ያለችው!😄

@And_Haymanot
የሚጠራን ሁሉ ትክክለኛ ሰው አይደለም እና ዛሬ ላይ እኛም ትክክለኛውን #የቤተክርስቲያንን_ድምፅ_እንድንለይ_ያስፈልጋል እንሰሳም(ተኩላ) በሰው ድምፅ ይጣራል ሰው ደግሞ እውነትን ሊሸፍን ይችላል፡፡ ወንድሜ እንዲሁም እህቴ እኛም ለቤተክርስቲያን እናስፈልጋታለንና ዛሬውኑ ጥሪዋን ሰምተን እንነሳ ብሎም እናሰማ ሌሎቹማ የእናት ጡት ነካሽ ሆነውባታል እባክህ/ሽ አለውልሽ እንበላት

.
.
.
ተነሳ ወገን ተነሳ
ዶግማችን እንዳይረሳ
ቀኖናው እንዳይረሳ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞ አቤቱ የእኔ አገልግሎት ለአንተ የሚያስፈልግህ አይደለም፡ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል፡፡ ✞
/ ቅድስ አባ ላርሳንዮስ/
@And_Haymanot
@And_Hayamnot
«የሰማዩ ጌታ የምድሩ ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን
የሚፈቱን ተፈቱልን»
@And_Haymanot
ተወዳጆች ይህን ሊንክ በመጫን የተሐድሶ መናፍቃን የሚጠይቋቸው ጥያቄ ምላሾችን አግኙባቸው አዲስ ቻናል ነውና ተቀላቀሉት
@Konobyos
@Konobyos
ዘፈን ለምን ይከለከላል?

@And_Haymanot

ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው
ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር ነው
ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሐጢአት ነው፡፡
ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡
ዘፈን ወደ ዝሙትና ወደ ክፉ ሀጢአት የሚመራ ምንጭ ነው
ዘፋኝ በመሆንህ ዕውቀትና መንፈሳዊ ጥንካሬ የሌላቸው ሰዎች ሊሰናከሉብህ ስለሚችሉ
** ዘፈን ለመንፈሳዊ ነገር ሁሉ ያለንን ፍቅርና ትጋት እንዲባረድ ያደርጋል፡፡

. . . ዘፋኝነት የተከለከለበትን ምክንያት በግድ ማወቅ አለብኝ ለምን ትላለህ? ምክንያቱን ማወቅህ አያፀድቅህም አለማወቅህም አያስኮንንህም፡፡ ነገር ግን ዘፋኝ ብትሆን ትጠየቅበታለህ፡፡ ባትዘፍን ደግሞ ታዛዥ ተብለህ በእግዚአብሔር ዘንድ ትመሰገነበታለህ፡፡ ስለዚህ የሚመለከትህን ለምን አታደርግም? …

. . . ዘፈን ለምን እንደተከለከለ መዘርዘሩ ምስጢሩን እንደሚያጠበው መገለጹ ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ይሕ እንዳለ ሆኖ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት የዘፈንን ጎጂ ገጽታ ማሳየት ይገባል፡፡

››› ሀ. ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡ ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንን ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13፥21 አትዝፈኑ ማለት የአጋንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን ተረዳ፡፡ ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ . . . እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› 1መቃ 36፡27-28 የዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለውን አጋንንትን ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጎራ መሰለፋቸው ነው፡፡ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቅ አይንህ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለህ መርምር፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛው ም እንደሆነ ማስተዋል ሞክር፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተህ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
@And_Haymanot
››› ለ. ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የሰስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡ በዘመናችን የሐጢያት ተግባራት በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ አንበሳ ምግቡ ሥጋ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንበሳ ሳር እንዲበላ ማድረግ እንደማያቻል ሁሉ ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡
@And_Haymanot
››› ሐ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሀጥያት ነው፡፡ ገላ 5፡21 ስለዚህ ዘፈን መዝፈን በመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ይከለከላል፡፡ ክርስትያኖች በመንፈሳዊ ሀሳብ መመላለስ እንጂ እንደ ዘፈን ያለውን ስጋዊ ስራ መስራት የለባቸውም፡፡ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ተብሏልና፡፡ ገላ 5፡16

››› መ. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡ ሐመር መጽሔት ይህን ሲያስረዳ ‹‹ዛሬ የአለም ሕዝብ የሚያዘወትረውን ዘፈን ሐዋርያት በትምህርታቸው ደጋግመውና አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ይላል (ሐመር 2ኛ ዓመት ቁ 4 ገጽ 27) በእርግጥም ሐዋርያት በዲድስቅልያ ‹‹አትኩኑ ዘፋንያነ››፤ ‹‹ዘፋኝ አትሁኑ›› ብለዋል፡፡ ዲድስ አን7 ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ብሏል፡፡ ሮሜ 13፡13 ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡›› ይለናል 1ኛ ጴጥ 4፡3
በላይኛው አንቀጽ በሰፈረው የሮም ክታቡ ቅዱስ ጳውሎስ ዘፋኘነትን ከዝሙትና ከስካር ጋር አስተካክሎ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ጴጥ 2፡13-15
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑጽንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ መመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ2፡13-15
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ ‹‹ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል፡፡›› ይለናል፡፡ መጽ ሐዊ አን50 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን አንተው ዘንድ ‹‹ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ›› በማለት የማፀናል ተግ ዘዮሐ አፈ 28
ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ በዘፈን ፀንተው የሞኖሩ ይፈረድባቸዋል›› በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን፡፡ መጽ ሐዊ አን 12 ይህ የሐዊ ቃል ሐዋርያው ‹‹የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› ማለት በምን ይለያያሉ?
@And_Haymanot
››› ሠ. ዘፈን በራሱ ኃጢአትና የሥጋ ፍሬ ከመሆኑም ባሻገር በዜማው በግጥሙና ከእርሱ ጋር በተጓዳኝ ባሉ ነገሮች ማለትም በስካር ፣ በዳንስ፣ በጭፈራ በእስክስታና በአጠቃላይ ውዝዋዜን በመሳሰሉ አጋሮቹ በመታገዝ ወደ ዝሙትና ወደ ክፉ ሀጢአት የሚመራ ምንጭ ነው::>> ተብሏልና፡፡ እንዲያውም ‹‹ኃጢአት በሰዎች ልቡና ለመንገስ ሲመጣ ከሚያቀርብልን እጅ መንሻዎች አንዱ ዘፈን ነው፡፡›› ሐመር 2ኛ ዓመት ቁ4 ገጽ27

የዘፈን ኃይል የሚገፋፋው ወደ ዝሙት ብቻ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሥጋዊ ስሜት እንዲያይልና ወደ ውጭ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡ ዘፈን በውስጥህ የሚገኘውን አንድ ዓይነት ሥጋዊ ምሪት ሊያበረታታ ወይም ሊያጠፋን ይችላል፡፡ ብታዝን ሆድ እንዲብስህ ያደርጋል ስትደሰት ደግሞ ደስታህን ያለ መጠን ሊያጋንነው ይችላል፡፡ ሌላው ቀርቶ አረማመድህን እንኳን ሊቀይረው እንደሚችል አትዘንጋ፡፡ ለምሳሌ፡- ዘፈን መጠጥን በልክህ እንዳትጠጣ መኪናህንም በፍጥነት እንድትነዳ ወይም እንድ
👍1🙏1
ን የጭካኔ ተግባር ያለ አንዳች ርኅራሄ እንድትፈጽም ሊገፋፋህ ይችላል፡፡ በአንዳንድ አገሮች በጣት የሚቆጠሩ ዘፋኞችን የተመረጠ ዘፈን እየሰሙ መኪና ማሽከርከር እስከመከልከል መድረሱ ከላይ ለተጠቀሰው ሐሳብ ምስክር ይሆናል፡፡
@And_Haymanot
››› ረ. ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ዘፈን በአንተ ላይ ምንም ዓይነት ጫና እንደማያደርስብህ ይሰማህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንተ ከብዙዎች ሰዎች የተለየ ማንነት እንደሌለህ ዕወቅ፡፡ ያነተ ዘፋኝነት ሌሎች ሰዎችን እንደሚያሰናክል ተረዳ፡፡ ስለዚህ ዘፋኝ በመሆንህ ዕውቀትና መንፈሳዊ ጥንካሬ የሌላቸው ሰዎች ሊሰናከሉብህ ስለሚችሉ ስለ ሌሎች ሰዎችም ብለህ አለመዝፈን ጠቃሚ ነው፡፡ እንዲህ ከተጠነቀቅህ ‹‹መሰናክልን ለሚያመጣው ለዚያ ሰው ወዮለት!›› በሚለው የአምላክ ቃል ከመውቀስ ትድናለህ፡፡ ማቴ18፡7

››› ሰ. ዘፈን ስሜትን በመግዛት ሱስ ወደመሆን ይለወጣል፡፡ ወደ ሱስነት መለወጡም ሱስ ከሚሆኑ ከሌሎች ነገሮች ማለትም እንደ ጫት ሲጋራ መጠጥና ከመሳሰሉት የማይተናነስ ነው፡፡ ይህንንም አንድ ግዜ ከገቡ በኀላ ለማጣት በሚዳክሩ ሰዎች መረዳት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ዘፈን ራስን ከመግዛት ይልቅ ስሜትን በመንካት የስሜት ተገዢነትን ያዳብራል፡፡
ብዙዎች ስለ ዘፈን የሚከራከሩት የዘፈን መልካምነት ከሀይማኖታቸው መልካምነት በልጦ ስለታያቸው ሳይሆን ዘፈን ሱስ እስከመሆን ደርሶ ስለገዛቸውና የገንዘብም ምንጫቸው ስለሆነ ነው፡፡ የዘፈን ሱሰኛ መሆን በህይወታችን ውስጥ ማከናወን ያለብንን ብዙ መሠረታዊ ጉዳዮች ቸል እንድንላቸው ሊያደርገን የችላል፡፡ በዚህ ምክንያት እኛ ክርስትያኖች ዘፈንና ዘፋኝነት በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ አንፈቅድም፡፡
@And_Haymanot
››› ሸ. ዘፈን መንፈሳነት ይፈልጋል፡፡ ለጸሎት ፣ ለመዝሙር እና ለምስጋና፣ ለመንፈሳዊ ነገር ሁሉ ያለንን ፍቅርና ትጋት እንዲባረድ ያደርጋል፡፡ ከዚሕም በላይ ለበጎ ነገር ያለንን ጊዜ በሙሉ ይሻማል፡፡ ለዚህም በቤታችን ያለ የቴፕ ማጫወቻ በቀን ለምን ያህል ሰዓት ሲጮህ ይውላል ? ከዚያም ውስጥ መንፈሳዊ ነገሮችን የምንሰማበት ጊዜ ቢሰላ ምን ያህሉን እጅ ይይዛል? ብሎ መጠየቅ ብቻ በቂ ነው፡፡

››› ቀ. ዘፈን መንፈሳዊነትን የሚገፋው ጊዜ በመሻማት ብቻ አይደለም፡፡ ሥጋዊ ስሜቶችን በማበረታትና ለመንፈሳዊ ነገር አንዲቀዘቅዝ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ የዘፈን ተገዢዎች ብዙ ጊዜ ወደ ስጋ ፍቃድ ያዘነብላለሉ፡፡
በቀላሉ ለመግለጽ አንዳንድ የቤተ ክርሰትያን ወጣቶች የጸሎት የጸሎት ሰአት እስኪፈፀም ተሰላችተው ከደጅ ይቆሙና ለመዘመር ብቻ ሲሉ ወደ አዳራሽ ይገባሉ፡፡ ይህም ሆኖ በመዝሙር ሰዐት ደግሞ ክንስሐ መዝሙር ይልቅ የቸብቸቦ መዝሙርን ይመርጣና ከበሮ ለመምታት ይሽቀዳደማሉ፡፡ ይህም የዘፈን እርሾ ብባቸው መኖሩን ይጠቁማል፡፡
ቀሪውን ከመጽሐፉ እንዲያነቡ እንጋብዛለን

ምንጭ፡-ሕይወተ ወራዙት ክፍል ሁለት
በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ
ኅዳር 1999 ፣ አ.አ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሰላም ተወዳጆች ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው በተለያዩ አካላት ለሚጠይቁት መልሥ ነው
የኃልዮ ሀጢአት ምንድነው?
ካህኑ የኃጢአት ማሠርያ እግዚአብሔር ይፍታህ ካለ ለምን የንስሃ አባት አሥፈለገ?
እመቤታችን የአለም ቤዛ አትባልም ለሚሉ የተሠጠ መልሥ
@Konobyos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥንተ አብሶ እና ምልዓተ ኃጢአት ልዩነቱን ያውቁ ኖሯል?
@Konobyos
በዲ/ን ቴዎድሮስ
@And_Haymanot
@Konobyos
❖ "ለሚያምን(ለማመን) ይኼ የሚጸን(የሚከብድ) ነገር አይደለም/ To believe this is no doubtful matter/." [ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary)].
@Konobyos
@And_Haymanot
በዲ/ን ቴዎድሮስ

የተሐድሶ መናፍቃን የፍልሰታ ጾምን በእጅጉ ይተቹታል:: በቅርቡ ትዛታው ሳሙኤልን ዕርገተ ማርያምን ሲነቅፍም ሲሰማ በውኑ ዝም ካልን ስለ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተገቢው ያልተረዱትን አባግኣ ክርስቶስ(የክርስቶስ በጎች) ክርስቲያኖችን እንዳያስት ጥቂት ማለቱ አስፈልጓል። የተሐድሶ መናፍቃን ሐዋርያዊ ውርርስ የሌለው እንግዳ ትምህርት እንደሆነም ይናገራሉ:: ሲያልፍም እመቤታችን አርጋለች ማለት ስሕተትም ነው ይሉና፤ ይህንንም ያስተማረው በ 16ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ነው ይላሉ:: ያው አርሲሳን(መናፍቃን) ማሰብ የሚችሉትንና የሚያቁትን ብቻ እንጂ የእምነትና የእውቀት ባሕር ውስጥ መዋኘት ስለማይወዱም ስለማይችሉም ዘመናቸው ባለማወቅ በድንዙዝነት ይገፉታል:: ለመሆኑ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት (Assumption of Mary) ትምህርት በኢትዮጵያ ሊቃውንት ብቻ የታወቀ ነው? የድንግል ማርያምን ዕርገትን በስፋት የሚያትተው ጥንታዊ መጽሐፍ በ (C.400) የተጻፈው ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary(c.400) የተባለ መጽሐፍ ነው:: መጽሐፉ የሚጀምረው የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ስለ ክብርት ወላዲተ አምላክ ዕረፍት የሰጠውን ምስክርነት(The Account of St. John the Theologian of the Falling Asleep of the Holy Mother of God). በማስረዳት ይጀምራል:: ተወዳጆች ሆይ! ይኼ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ሊቃውንት የጻፉት መጽሐፍ አለመሆኑና የተሐድሶ መናፍቃን እንደሚሉት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሳይሆን የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ እናት አባቱ፤ አያት ቅድመ አያት ሳይታሰቡ የተጻፈ ደገኛ ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ፍልሰት(ዕርገት) በስፋት የሚያትት በልሳነ አፍርንጅ(በእንግሊዘኛ) ልሳን የተጻፈ ጥንታዊ መጽሐፍ ነው:: [መቼስ እኛ በግዕዝ ከተጻፈው በእንግሊዘኛ የተጻፈ ፈረንጅ ያረጋገጠውን መቀበል እንደሚቀናን ይታወቃል! የልሳን ቀላዋጭ ከሆንን ከረምን!!] ዳግመኛም ይኼ ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary) የተባለው መጽሐፍ ፍልሰታ ለማርያም(The Passing of Mary) ብሎ በሁለት የላቲን ቅጅዎችን ማለትም First Latin Form & Second Latin Form በማለት ፍልሰታዋን ያትታል:: በቀዳማዊው የላቲን ገለጻ(First Latin Form) የሚጀምረው ስለ ብፅዕት ድንግል ማርያም ፍልሰት ነገር(Concerning the Passing of the Blessed Virgin Mary) በማለት ይጀምርና; ሐዋርያው ቶማስ እመቤታችን ስታርፍ እሱ በሕንድ እንደነበረና እመቤታችንም ባረፈች በሦስተኛ ቀን ስታርግ እሱም በደመና ተጭኖ ሲመጣ እንዳገኛትና ባርካው ሰበኗን እንደሰጠችው ይገልጻል:: እንዲህ በማለት Then the blessed Thomas told them how he was singing mass in India - he still had on his sacerdotal robes. He, not knowing the word of God, had been brought to the Mount of Oliver, and saw the most holy body of the blessed Mary going up into heaven, and prayed her to give him a blessing. She heard his prayer, and threw him her girdle which she had about her. ለሚያምን ይኼ የሚከብድ ነገር አይደለምም(To believe this is no doubtful matter) ይላል:: በመጨረሻም የእመቤታችን ዕርገት በዓለሙ ሁሉ እንደሚከበርም ይገልጻል(And her, whose assumption is at this day venerated and worshipped throughout the whole world). ሁለተኛው የላቲኑ ቅጂ(Second Latin Form) ደግሞ Here Begins the Passing of the Blessed Virgin Mary ብሎ ይጀምርና ክፉዎች አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋዋን እናቃጥለው እንዳሉም ይናገራል(Jews saying, let us burn her body with fire). በመጨረሻም ቅዱሳን ሐዋርያት ሱባዔ ይዘው እመቤታችንም እንደተገለጽላቸው እነርሱም ሐሴት እንዳደረጉ(The apostles then, having entered the house, found Mary, and saluted her, saying: Blessed are you by the Lord, who has made heaven & earth) ና ይህን ሁሉ ያደረገ ልዑል እግዚአብሔርንም እንዳመሰገኑ በመግለጽ ጽሑፉን ያሳርጋል(And the apostles being taken up in the clouds, returned each into the place allotted for his preaching, telling the great things of God, and praising our Lord Jesus Christ, who lives and reigns with the Father and the Holy Spirit, in perfect unity, and in one substance of Godhed, for ever and ever. Amen. [Ante- Nicene Fathers, Vol.8; Assumption of Mary (C. 400)]. ታዲያ የእመቤታችን ፍልሰት(ዕርገት) ልብ ወለድ ፈጠራ ነውን? የኢትዮጵያ ሊቃውንትስ ከዚህ የተለየ ምን አስተማሩን? ወይስ እያንዳንዷ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምሕሮ በአፍርንጅ(በእንግሊዘኛ) የተጻፈ ማስረጃ የግድ ያስፈልግ ይሆን? ጾመ ፍልሰታ ወደ ጽድቅ ሕይወት የምንፈልስበትን ፍልሰተ ልቡና ያድርግልን፤ አሜን::
@Konobyos
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@Konobyos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለዘማሪ ትዝታው ሳሙኤል የተሰጠ ምላሽ
@Konobyos
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
👉ፋሲካ ማለት ምን ማለት ነው?
👉ድንግል ማርያም የአዳም ፋሲካው ለምን ተባለች?
👉የአዳም ደስታው ድንግል ማርያም
👉 መገዛትና ማምለክ ያለው ልዩነት
ሌሎች ምላሾችን ለማግኘት
@Konobyos
@And_Haymanot
በስጋዊ ጥበብ ለማወቅ ቢቃጣ
የእምነት መነጽሩን ይዞ ስላልመጣ/2×/
አንዳንዱ በክህደት አንዳንዱ በስህተት
ፈጣሪውን አጣ/2×/....
~~~~~~~~~~
@And_Haymanot
👍ለጠፉት ልቦናን ያድልልን 👍
“ድኅነሃል ወይ ፤ Are you saved?

@And_Haymanot
የብዙዎች ጥያቄ ነው ፤ በየ አውቶቢስ ማቆሚያው … የምንጠየቀው ጥያቄ ነው “ድኅነሃል ወይ ?፤ Are you saved ?” .. አንድ ኦርቶዶክስ ግን ይህን ጥያቄ አዎ ድኛለሁ ብሎ ሳይሆን መመለስ ያለበት “ድኅነቴን እየፈፀምኩ ነው” [I’m perfecting my salivation] (ፊል 2፡12) በማለት ነው፡፡ ድኅነት አምኛለሁ ብሎ መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ከማመን በኋላ ያሉትን ነገሮች መፈጸምም ጭምር ነው [ለማመንማ አጋንንትም ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል ተብሎ እንደተጻፈ]፡፡ ለምሳሌ ከማመን ..መጠመቅ ትወለዳለች.. ከመጠመቅ ደሞ አዲስ ፍጥረትነት ይወለዳል …በአዲሱ አቁማዳ ደሞ አዲሱን ወይን (የጌታን ሥጋና ደም) መቀበልን እንረከባለን… በዚህ እለት እለት እየበረታን ስንሄድ ድኅነታችንን እየፈጸምን ከዚህ ዓለም እስክንሰናበት ና በእረፍተ ሥጋ በኩል ወደ አዲሲቷ ዓለም እስክንሄድ ድረስ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ድኅነት አምነው ሚተዉት ብቻ ሳይሆን አምነው ሚፈጽሙት እግዚአብሔርንም በጸጋ ወደ መምሰል የሚታደግበት እጹብ ድንቅ ህይወት ነው፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanott
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ገድል_ያወጣል_ከገደል
የገድላት ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም በገድላት ዙርያ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን የምንዳስስበት ተከታታይ ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ
ክፍል ፩
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@Konobyos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ገድል_ያወጣል_ከገደል
ክፍል ፪
@And_Haymanot
ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ

በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@Konobyos
@And_Haymanot