፩ ሃይማኖት
8.97K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
#መልአካይ_ሰይጣን ~ ሰባሪ ዜና

@And_Haymanot

👉 "ኦርቶዶክስ" የሚለው ስም የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ነው!!!!!

√Share √Share √Share

«ውሉደ ብርሃን የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ራሱን ሲጠራ የነበረው የውጉዙ አሰግድ ሣህሉ (?) የተሐድሶ መናፍቃን ቡድን ያሰበውን ያህል በጎችን ከበረት ማውጣት ስላልቻለ ስሙን «ቃለ ዐዋዲ ዘኦርቶዶክስ የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ቀይሮ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ነኝ በማለት ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ይህ በእምነታችን ኃጢአት፣ በባህላችን ነውር፣ በሕጋችንም ወንጀል የሆነ ቅጥፈት ነው። መንግስትም የሌላን ቤተ እምነት ስም በመጠቀምህ ፍቃድ አልሰጥም ማለት እየቻለ "ተቃዋሚ ካለ ሰኞ ሐምሌ 29 3:00 ሰዓት በሰላም ምኒስቴር የሃይማኖት ድርጅቶችና ማሕበራት ምዝገባ ዳይሪክቶሬት ይቅረብ" ብሎ የማርያም መንገድ የሰጠ ይመስላል።
ሰይጣን ሰዎችን ሲያታልል መልአክን እንጂ ራሱን መስሎ አይደለም። የራሱን ኃይልና ብርታት በመግለጥ፣ ከመልአክነት ይልቅ ሰይጣናዊነት እንደሚልቅ በማስረጃ በማስረገጥ አይቀርብም። ስለ ራሱ የሚያቀርበው ነገር የሌለው ባዶ ነውና፣ ሌላን መምሰል እንጂ ራስን መሆን አይሆንለትምና መልአክ-መሳይ (መልአካይ) ሆኖ ይቅበዘበዛል። ተሐድሶዎችም እንዲሁ በመብከን ተሐድሶነታቸውን ሳይሆን ኦርቶዶክስ-መሳይነታቸውን ሊነግሩን ሽሩገድ ይላሉ። 2 ቀናት ብቻ ቀርተውናል! ይህ የብሔርህ አልያም የፖለቲካ ወሬ አይደለም፣ የእውነትም የእምነትም ጉዳይ ነው! ይህንን መልዕክት በውስጥ መስመር ለመምህራን፣ ለሕግ ባለሞያዎች፣ ለባለሥልጣናትና ለብጹዓን አባቶች በማካፈልና በመላክ በቤ/ክ ጉዳይ ለውጥ እንፍጠር! ዳይ ወደ ስራ [©Binyam ZeChristos ሐምለ 26 - 2011]

፪ኛ ቆሮ ፲፩

26 “ብዙ ጊዜ በመንገድ ኼድኹ፤ በወንዝ ፍርኃት፥ በወንበዴዎች ፍርኃት፥ በወገኔ በኩል ፍርኃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርኃት፥ በከተማ ፍርኃት፥ በምድረ በዳ ፍርኃት፥ በባሕር ፍርኃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርኃት ነበረብኝ፤
27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርኹ።
28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ዐሳብ ነው።”


@And_Haymanot
@And_Haymanot