"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡
ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል፡፡ እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት
ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
@And_Haymanot

☞~በኢያሪኮ ከኤልሳዕ ምንጭ ዋናውን መንገድ ወደ ቀኝ በመተው በግራ በኩል ባለው ጐዳና በመጓዝ ቆሮንቶስ ተራራ ሥር ተራራውን በእግር ተጉዘው ያገኙታል። ይህም ጌታችን መድኅን አለም ክርስቶስ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት የጾመበት ሥፍራ #ገዳመ_ቆሮንቶስ ነው።
☞~በእዚህ ላይ ሆኖ የኢያሪኮን ከተማ ልምላሜ፣ የዮርዳኖስን ወንዝ ሸለቆ፣ የአሞን ተራራ የተባለውን አርቆ አሻግሮ ለማየት ይቻላል። ጌታ በቆሮንቶስ ተራራ የተፈተነበትን በእግረ ሥጋ ረግጦ፣ በዓይን ዓይቶ ምስክር ለመሆን እንዲያበቃን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot

ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሐ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር
... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሐ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሐ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን?
የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡
አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡
ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሐ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው?
ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡
እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሐ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡
"ሕማማት" ከተሰኘው ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ የተወሰደ

ከቅዱስ ያሬድ መዝሙር
ለቤተክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ።
ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው።
ለርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተትን የቻለ።
የበደለውም በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ።
አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ።
@And_Haymanot
ለቤተክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ።
ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው።
ለርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተትን የቻለ።
የበደለውም በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ።
አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ።
@And_Haymanot
እምነትህን በሥራ አሳይ
@And_Haymanot
ያዕ 2፥14-26
14 ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
15 ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥
16 ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
18 ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
20 አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?
21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
23 መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
25 እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - እንደ አስተማሪ
@And_Haymanot
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከሌሎች ቅዱሳን አባቶች ልዩ የሚያደርገው አንዱ ነገር፥ ሃይማኖትን ከምግባር ጋራ አዋሕዶ ማስተማሩ ነው - ተዋሕዶ ! የተረጎማቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ስንመለከታቸው መጀመሪያ ኃይለ ቃሉን ይተረጉማል፤ ቀጥሎም ያ ኃይለ ቃል ወደ መሬት እንዴት ማውረድ (መተግበር) እንደሚገባ ያስተምራል፡፡ እንደ ምሳሌ ብንወስድ የዕብራውያን መልእክትን ሲተረጉም ወደ አማርኛ ሲመለስ ድርሳንና ተግሣፅ ተብሎ በኹለት መጽሐፍ የቀረበ ቢኾንም አንድ ወጥ መጽሐፍ ነው፡፡ ድርሳን አንድና ተግሣፅ አንድ ተብለው የተጠቀሱት አንድ ወጥ ድርሳን (ክፍለ ትምህርት) ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል፣ በኦሪት ዘፍጥረት እንደ ተመለከታችሁት ማለት ነው፡፡
እንደዚህ ማስተማሩም ክርስቲያኖች በነገረ ሃይማኖቱ ትምህርት የተራቀቁ በምግባር ግን የጎደሉ እንዳይኾኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰምተው ብዙ የሚናገሩ እግዚአብሔርን ግን የማያውቁት እንዳይኾኑ ይጠብቃቸዋል፡፡
የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ዋና ዓላማውም ይህ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ብዙ መራቀቅ ሳይኾን እግዚአብሔርን በገቢር ማወቅ ! ስለ ጸሎት ብዙ ማወቅ ሳይኾን በተግባር መጸለይ ! ስለ ጾም እጅግ ብዙ ቅጾች ያሏቸውን መጻሕፍት መጻፍ ሳይኾን እንደ ዓቅም በአግባቡ መጾም !
ይህን ካለ መገንዘብ የተነሣ ብዙ ሰዎች ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እንደ ምግባር ሰባኪ ብቻ አድረገው ይመለከቱታል፡፡ ነገር ግን ከላይ እንደ ጠቀስነው የቅዱስ ዮሐንስ ዋና አሳብ፥ አንድ ክርስቲያን በተግባር ክርስትናን የሚኖር ከኾነ በትምህርት ብዛት እግዚአብሔርን ከሚያውቀው በላይ በዚያ በኑሮው ውስጥ እግዚአብሔርን ወይም አጠቃላይ ነገረ ሃይማኖቱን እንዲያውቀው ማድረግ ነው፡፡ ስለ ፍቅር ብዙ ከማወቅ ይልቅ ፍቅርን በተግባር ኑሮ እንዲቀምሰው ማድረግ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ይበልጥ ድኅነቱን እንዲፈጽም የሚያደርገውም ይህ ነውና፡፡
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ

“ሰው ሆይ ! በዚህ ዓለም መጻተኛ ኾነህ ትኖር ዘንድ እያዘዝሁህ ሳለ፥ አንተ ግን የትውልድ ሀገርህን ጠቅሰህ የምትታበየው ስለ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር ! “ይህ ዓለም ለአንተ እንደማይገባ አስበህ እንድትንቀው ስነግርህ አንተ ግን ስለ ትውልድ ቀዬህ የምትመካው ስለ ምንድን ነው?” እነዚህ ነገሮች ፈጽመው የተናቁ ናቸውና፤ በክርስቲያኖች ዘንድስ ይቅርና በግሪክ ፈላስፎች ዘንድም ቢኾን የተናቁ የተጠቁ ናቸውና፥ “ውጹአን” ተብለውም ይጠራሉና፥ ዝቅ ያለ ግምትም ይሰጣቸዋልና፡፡
@ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ፱፥፯
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ፱፥፯
@And_Haymanot
@And_Haymanot
“ወዳጄ ሆይ! የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብኻልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርኻል፡፡ የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮኻልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለኽ፡፡ የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮኻልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምኅረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለኽ፡፡ ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞኻልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለኽ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ልል ዘሊል ብትኾን ይኽን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትኾናለኽ፡፡ ቆሽሸኻልን? እንኪያስ ወደዚኹ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርኻለኹ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለኽ፡፡”
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✅ "ፀንሳ ተገኘች" ✅
@And_Haymanot
[ማቴዎስ ሆይ !] እባክህ ንገረኝ ልደቱ እንዴት ነበር? “እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ” (ማቴ.1፡18)፡፡ “ድንግል” አላለም፤ “እናቱ” እንጂ፡፡ ይኸውም ትምህርቱን በቀላሉ ይቀበሉት ዘንድ ነው፡፡ በመኾኑም ጥቂት ነገር ሰጥቶ ሰማዒውን እንዲህ ካሰናዳውና መሠረት ካስቀመጠ በኋላ፥ ቀጥሎ ያለውን ኃይለ ቃል በመናገር ደግሞ፡- “ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች” በማለት እንዲደነቅ ያደርገዋል፡፡ “ወደ ሙሽራው (ወደ ዮሴፍ) ቤት ከመምጣትዋ በፊት ፀንሳ ተገኘች” አላለም፤ አስቀድማ እዚያ ነበረችና፡፡ በጥንቱ የአይሁድ ባሕል ባሎች እጮኞቻቸውን አስቀድመው በቤታቸው ውስጥ የመጠበቅ ልማድ ነበራቸው፤ አሁንም ይህ ልማድ እንደ ተፈጸመ አንድ ሰው መገንዘብ ይችላል፡፡ [“ሎጥም ወንድን ያላወቁ ኹለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጉአቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። … ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም። ተነሡ፤ ከዚህ ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው” እንዲል] በዚሁ ልማድ መሠረት የሎጥ የወንድ ልጆቹ እጮኞችም በቤቱ ይኖሩ ነበር (ዘፍ.19፡8፣14)፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም በዮሴፍ ቤት ትኖር የነበረችው በዚህ ባሕል ነው፡፡ [ምሥጢሩ ግን ያገለግላት ዘንድና ከላይ እንደ ተገለጠው ከአጋንንትና ከአይሁድ ፅንሱን ለመሰወር ነው፡፡]
ለዮሴፍ ከመታጨትዋ በፊት አለመፅነስዋስ ለምንድን ነው? ቀደም ብዬ እንደ ተናገርሁት፡-
☞ እስከ ጊዜው ጊዜ ሥራው [ከሰይጣን] ይሰወር ዘንድ ስላለው፣
☞ [ላቲ ስብሐትና] ቅድስት ድንግል ማርያም “ከዝሙት ፀንሳ ተገኘች” ተብሎ በድንጋይ እንዳትወገር [ከአይሁድ] ለመጠበቅ ነው፡፡
ከሌሎች ሕገ ኦሪትን እንጠብቃለን ከሚሉት ሰዎች ይልቅ [“ከሌላ ሰው ጋር ዝሙት ፈጽማ ተገኘች” ብሎ] እጅግ ሊቀና ይችል የነበረው ጻድቁ ዮሴፍ በፍጹም ለሌሎች ሳይገልጣት ወይም ሳያዋርዳት እንዲያውም ፀንሳ ከተገኘች በኋላ ከተቀበላትና ካገለገላት፥ ፀንሳ የተገኘችው በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደ ኾነ አስቀድሞ ተነግሮትና እርሱም አምኖ ተቀብሎት ባይኾን ኖሮ በቤቱ እንዲቀበላትና በሚያስፈልጋት ነገር ኹሉ ሊያገለግላት አይችል እንደ ነበረ በጣም ግልፅ ነው፡፡ በመኾኑም ወንጌላዊው፡- “ፀንሳ ‘ተገኘች’” ማለቱ ይህን ድንቅ፣ ከሕገ ተፈጥሮ [ከጋብቻ] አፍአ የኾነውን ሥራ፣ በልብ ከመታሰብና ከመመርመር ውጭ መኾኑን፣ ከዚህ በፊትም ከዚህ በኋላም መቼም ቢኾን መች ያልታየና የማይታይ መኾኑን በግልፅ የሚያስረዳ ነው፡፡
ስለዚህ [እመን ታመንም እንጂ] ከተጻፈልህ ነገር አልፈህ አትመርምር፡፡ ከተባለውና ከተነገረው ነገር አልፈህ ምንም አትሻ፡፡ “ድንግል በድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ፀንሳ የተገኘችው እንዴት ነው?” ብለህም አትጠይቅ፡፡ በዘር በሩካቤ የሚገኝ ፅንስ እንኳን እንዴት ፅንስ እንደሚፈጠር ማወቅ የማይቻለን ከኾነ መንፈስ ቅዱስ ተአምራትን ሲያደርግ’ማ እንደ ምን ማወቅ ይቻለናል? ወንጌላዊውም እንዳታስጨንቀውና እነዚህን ነገሮች አዘውትረህ በመጠየቅ እንዳታውከው ብሎ አስቦ የተከናወነው ነገር ተአምር እንደ ኾነ ነገረህ፤ እንዲህ አድርጎም ራሱን ነጻ አደረገ፡፡ “የተከናውነው ነገር በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከመኾኑ በቀር ከዚህ ውጭ ምንም ምን የማውቀው ነገር የለም” አለህ፡፡
@ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን 4፥5