የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አይደለም!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ሰሞኑን የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) በተመለከተ፡ ተከታታይ ትምሕርቶችን እየዳሰስን ነው፡፡ በተለይ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢይነትና ከሰብአዊ ፍጥረት ክልል አውጥቶ እሱን አምላካዊ ማንነት ለማላበስ የሚደረገውን ከንቱ ሙከራ ምላሽ እየሰጠንበት ነው፡፡ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢያት ኹሉ በላይ ከፍ ለማድረግ ያግዙናል የሚሏቸውን አንዳንድ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾችንም በማንሳት የአንቀጹን ትክክለኛ መልእክት እና የነሱን የተሳሳተ ግንዛቤ እየተመለከትን ነው፡፡ ዛሬም አላህ ፈቃዱ ከኾነ የምንመለከተው የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ እንዳልነበረ፣ እንዳልኾነና ፈጽሞም ሊኾን እንደማይቸል የሚያስረዱትን ቀጥታና ግልጽ የኾኑ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾችን በመጠቀም ነው፡፡ መልካም ንባብ፡-

ሀ/ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም!

ይህ አንዱና ዋነኛው መረጃችን ነው፡፡ የአላህ ቃል የኾነው ቅዱስ ቁርኣን ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ በግልጽ ይናገራል፡፡ ‹‹ሌላ የለም›› በሚለው ቃል ውስጥ ከአላህ ውጭ የኾነው ፍጥረት ኹሉ ይካተታል፡፡ የመርየም ልጅም ከነዚህ ‹‹ሌላ›› ተብለው ከተጠቀሱት አካላት አንዱ ነው፡፡ እሱ አላህ አይደለምና፡ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም! ከተባለ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አለመኾኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል ማለት ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡163)፡፡

"ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል (ከሓዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን (አስታውቁ በማለት ያወርዳል)፡፡" (ሱረቱ-ነሕል 16፡2)፡፡

"እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡" (ሱረቱ ጣሀ 20፡14)፡፡

ለ/ ዒሳ ጠፊ ነው፡-

ይህ ደግሞ ሌላኛው ማስረጃችን ነው፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ፍጹም ዘላለማዊነትን አልተላበሰም፡፡ ፈጣሪ አምላኩ አላህ በፈለገ ጊዜ ሊያጠፋው ይችላል፡፡ ከዚህ ጥፋት እራሱም ሆነ ሌላው አካል በመተባበር ሊያድነው የሚችል አንድም ኃይል የለም አይኖርምም፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

“እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን፡ እናቱንም፡ በምድር ያለንም ሁሉ #ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማን ነው? በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው የሚሻውን ይፈጥራል አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡” (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡17)፡፡

በዚህ አንቀጽ መሰረት፡ ጌታ አላህ ዒሳንም ሆነ እናቱን እንዲሁም በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለማጥፋት ቢፈልግ፡ ማንም ሊያድናቸው የሚችል እንደሌለ ያስረዳል፡፡ አያይዞም በመቀጠል ‹‹የሚሻውን ይፈጥራል›› በማለት ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ከፍጥረታዊ ማንነት ውጪ የዘለለ ሌላ ነገር እንደሌለው ያስረዳል፡፡ እውነተኛ አምላክ የሆነው አላህ ግን አይጠፋም፡፡ ሁሌም ቀሪ ነው፡፡ ቃሉም የሚለው እንዲህ ነው፡-

“በርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ የእልቅናና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል (አይጠፋም)” (ሱረቱ-ረሕማን 55፡26-27)፡፡

“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ ከርሱ በቀር አምላክ የለም ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው ፍርዱ የርሱ ብቻ ነው ወደርሱም ትመለሳላችሁ” (ሱረቱል ቀሶስ 28፡88)፡፡

ሐ/ ዒሳ ምግብን ይመገብ ነበር፡-

ሰዎች በዚህ ምድር ላይ በሕይወት ለመቆየት ከሚያስፈልጋቸው መሠረታዊ ነገራት አንዱ መብል ነው፡፡ ያለ መብል በሕይወት መቆየት አይችሉም፡፡ ይህም ደካማ ፍጡር መኾናቸውን ያሳያል፡፡ የመርየም ልጅም ከተመጋቢዎቹ አንዱ ነበር፡፡ ታዲያ እንዴት ኾኖ ነው ከአፈር የወጣንና የበቀለን ነገር እንደምግብነት የሚጠቀም አካል የኔ አምላክ ሊኾን የሚችለው? ደግሞስ የበላውና የጠጣው ነገር ተመልሶ በሌላ መልክ (በሽንትና በቆሻሻ) ከሰውነቱ መውጣቱ ይቀራልን? እንግዲያውስ ይህን ስርአት የሚፈጽም አካል አምላኬ ነው ብዬ ልቀበለው? እሱም ደፍሮ አይለኝም!!

“የመርየም ልጅ አል መሲሕ፡ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም እናቱም በጣም እውነተኛ ናት (ሁለቱም) ምግብን #የሚበሉ ነበሩ፡፡ አንቀጾችን ለነርሱ (ለካሀዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት” (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡75)፡፡

እውነተኛው አምላክ አላህ ግን አይበላም፡፡ ባይሆን ፍጡራኑን (ሰውን፣ እንሰሳትን፣ ነፍሳትን፣ በራሪዎችን…) ያበላል እንጂ፡፡ እርሱ መጋቢ እንጂ ተመጋቢ አይደለም! የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

“ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ፡ እርሱ የሚመግብ፣ #የማይመገብም ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን? በላቸው፡፡ እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልሆን ታዘዝኩ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን (ተብያለሁ) በላቸው” (ሱረቱል አንዓም 6፡14)፡፡

“ጋኔንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም #ሊመግቡኝም አልሻም አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኃይል ባለቤት ነው፡፡” (ሱረቱ-ዛሪያት 56-58)፡፡

መ/ ዒሳ ወደፊት ሟች ነው፡-

መሞት የፍጡራን ባሕሪ እንጂ የአምላክ አይደለም፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳም (ዐለይሂ-ሰላም) ፍጡር በመኾኑ ከሞት ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ቂያማ ከመቆሙ በፊት ወደዚህ ምድር በጌታው ፈቃድ ከወረደና ተልእኮውን ከፈጸመ በኋላ እሱም ይሞታል፡፡ ሟች መሆኑን ገና በእናቱ እቅፍ ሳለ በልጅነቱ እንዲህ ተናግሯል፡-

“ሰላምም በኔ ላይ ነው በተወለድኩ ቀን #በምሞትበትም ቀን ህያው ሆኜ በምቀስቀስበት ቀን” (ሱረቱ መርየም 19፡33)፡፡

እውነተኛው ጌታና አምላክ አላህ ግን ፈጽሞ የማይሞት ነው፡፡ ደግሞስ የሞት ፈጣሪና አምላክ እንዴት በፈጠረው ሞት ይያዛል?

“ፊቶችም ሁሉ #ሕያው አስተናባሪ ለሆነው (አላህ) ተዋረዱ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ” (ሱረቱ ጣሀ 20፡111)፡፡

“በዚያም #በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ…” (ሱረቱል ፉርቃን 25፡58)፡፡

ሠ/ የትንሳኤ ቀን ጥያቄና መልስ

ነገ በየውሙል ቂያም (በዕለተ ትንሳኤ) ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) በጌታው ፊት በሰዎቹ ይመሰክርባቸውና ይክዳቸው ዘንድ ይጠየቃል፡፡ አንተ ለሰዎቹ እኔና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርጋችሁ ያዙ ብለህ አስተምረህ ነበርን? ተብሎ ይጠየቃል፡፡ የሱም መልስ፡- በፍፁም! የሚል ይሆናል፡፡ ይህም አምላክ አለመሆኑን ፍንትው አድርጎ ያስረዳል፡-

“አላህም የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሀልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ) ጥራት ይገባህ ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ #አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ አውቀኸዋል በነፍሴ ውስጥ ያለው
👍1