የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አይደለም!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ሰሞኑን የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) በተመለከተ፡ ተከታታይ ትምሕርቶችን እየዳሰስን ነው፡፡ በተለይ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢይነትና ከሰብአዊ ፍጥረት ክልል አውጥቶ እሱን አምላካዊ ማንነት ለማላበስ የሚደረገውን ከንቱ ሙከራ ምላሽ እየሰጠንበት ነው፡፡ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢያት ኹሉ በላይ ከፍ ለማድረግ ያግዙናል የሚሏቸውን አንዳንድ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾችንም በማንሳት የአንቀጹን ትክክለኛ መልእክት እና የነሱን የተሳሳተ ግንዛቤ እየተመለከትን ነው፡፡ ዛሬም አላህ ፈቃዱ ከኾነ የምንመለከተው የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ እንዳልነበረ፣ እንዳልኾነና ፈጽሞም ሊኾን እንደማይቸል የሚያስረዱትን ቀጥታና ግልጽ የኾኑ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾችን በመጠቀም ነው፡፡ መልካም ንባብ፡-

ሀ/ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም!

ይህ አንዱና ዋነኛው መረጃችን ነው፡፡ የአላህ ቃል የኾነው ቅዱስ ቁርኣን ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ በግልጽ ይናገራል፡፡ ‹‹ሌላ የለም›› በሚለው ቃል ውስጥ ከአላህ ውጭ የኾነው ፍጥረት ኹሉ ይካተታል፡፡ የመርየም ልጅም ከነዚህ ‹‹ሌላ›› ተብለው ከተጠቀሱት አካላት አንዱ ነው፡፡ እሱ አላህ አይደለምና፡ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም! ከተባለ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አለመኾኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል ማለት ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡163)፡፡

"ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል (ከሓዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን (አስታውቁ በማለት ያወርዳል)፡፡" (ሱረቱ-ነሕል 16፡2)፡፡

"እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡" (ሱረቱ ጣሀ 20፡14)፡፡

ለ/ ዒሳ ጠፊ ነው፡-

ይህ ደግሞ ሌላኛው ማስረጃችን ነው፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ፍጹም ዘላለማዊነትን አልተላበሰም፡፡ ፈጣሪ አምላኩ አላህ በፈለገ ጊዜ ሊያጠፋው ይችላል፡፡ ከዚህ ጥፋት እራሱም ሆነ ሌላው አካል በመተባበር ሊያድነው የሚችል አንድም ኃይል የለም አይኖርምም፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

“እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን፡ እናቱንም፡ በምድር ያለንም ሁሉ #ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማን ነው? በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው የሚሻውን ይፈጥራል አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡” (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡17)፡፡

በዚህ አንቀጽ መሰረት፡ ጌታ አላህ ዒሳንም ሆነ እናቱን እንዲሁም በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለማጥፋት ቢፈልግ፡ ማንም ሊያድናቸው የሚችል እንደሌለ ያስረዳል፡፡ አያይዞም በመቀጠል ‹‹የሚሻውን ይፈጥራል›› በማለት ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ከፍጥረታዊ ማንነት ውጪ የዘለለ ሌላ ነገር እንደሌለው ያስረዳል፡፡ እውነተኛ አምላክ የሆነው አላህ ግን አይጠፋም፡፡ ሁሌም ቀሪ ነው፡፡ ቃሉም የሚለው እንዲህ ነው፡-

“በርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ የእልቅናና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል (አይጠፋም)” (ሱረቱ-ረሕማን 55፡26-27)፡፡

“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ ከርሱ በቀር አምላክ የለም ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው ፍርዱ የርሱ ብቻ ነው ወደርሱም ትመለሳላችሁ” (ሱረቱል ቀሶስ 28፡88)፡፡

ሐ/ ዒሳ ምግብን ይመገብ ነበር፡-

ሰዎች በዚህ ምድር ላይ በሕይወት ለመቆየት ከሚያስፈልጋቸው መሠረታዊ ነገራት አንዱ መብል ነው፡፡ ያለ መብል በሕይወት መቆየት አይችሉም፡፡ ይህም ደካማ ፍጡር መኾናቸውን ያሳያል፡፡ የመርየም ልጅም ከተመጋቢዎቹ አንዱ ነበር፡፡ ታዲያ እንዴት ኾኖ ነው ከአፈር የወጣንና የበቀለን ነገር እንደምግብነት የሚጠቀም አካል የኔ አምላክ ሊኾን የሚችለው? ደግሞስ የበላውና የጠጣው ነገር ተመልሶ በሌላ መልክ (በሽንትና በቆሻሻ) ከሰውነቱ መውጣቱ ይቀራልን? እንግዲያውስ ይህን ስርአት የሚፈጽም አካል አምላኬ ነው ብዬ ልቀበለው? እሱም ደፍሮ አይለኝም!!

“የመርየም ልጅ አል መሲሕ፡ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም እናቱም በጣም እውነተኛ ናት (ሁለቱም) ምግብን #የሚበሉ ነበሩ፡፡ አንቀጾችን ለነርሱ (ለካሀዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት” (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡75)፡፡

እውነተኛው አምላክ አላህ ግን አይበላም፡፡ ባይሆን ፍጡራኑን (ሰውን፣ እንሰሳትን፣ ነፍሳትን፣ በራሪዎችን…) ያበላል እንጂ፡፡ እርሱ መጋቢ እንጂ ተመጋቢ አይደለም! የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

“ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ፡ እርሱ የሚመግብ፣ #የማይመገብም ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን? በላቸው፡፡ እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልሆን ታዘዝኩ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን (ተብያለሁ) በላቸው” (ሱረቱል አንዓም 6፡14)፡፡

“ጋኔንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም #ሊመግቡኝም አልሻም አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኃይል ባለቤት ነው፡፡” (ሱረቱ-ዛሪያት 56-58)፡፡

መ/ ዒሳ ወደፊት ሟች ነው፡-

መሞት የፍጡራን ባሕሪ እንጂ የአምላክ አይደለም፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳም (ዐለይሂ-ሰላም) ፍጡር በመኾኑ ከሞት ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ቂያማ ከመቆሙ በፊት ወደዚህ ምድር በጌታው ፈቃድ ከወረደና ተልእኮውን ከፈጸመ በኋላ እሱም ይሞታል፡፡ ሟች መሆኑን ገና በእናቱ እቅፍ ሳለ በልጅነቱ እንዲህ ተናግሯል፡-

“ሰላምም በኔ ላይ ነው በተወለድኩ ቀን #በምሞትበትም ቀን ህያው ሆኜ በምቀስቀስበት ቀን” (ሱረቱ መርየም 19፡33)፡፡

እውነተኛው ጌታና አምላክ አላህ ግን ፈጽሞ የማይሞት ነው፡፡ ደግሞስ የሞት ፈጣሪና አምላክ እንዴት በፈጠረው ሞት ይያዛል?

“ፊቶችም ሁሉ #ሕያው አስተናባሪ ለሆነው (አላህ) ተዋረዱ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ” (ሱረቱ ጣሀ 20፡111)፡፡

“በዚያም #በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ…” (ሱረቱል ፉርቃን 25፡58)፡፡

ሠ/ የትንሳኤ ቀን ጥያቄና መልስ

ነገ በየውሙል ቂያም (በዕለተ ትንሳኤ) ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) በጌታው ፊት በሰዎቹ ይመሰክርባቸውና ይክዳቸው ዘንድ ይጠየቃል፡፡ አንተ ለሰዎቹ እኔና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርጋችሁ ያዙ ብለህ አስተምረህ ነበርን? ተብሎ ይጠየቃል፡፡ የሱም መልስ፡- በፍፁም! የሚል ይሆናል፡፡ ይህም አምላክ አለመሆኑን ፍንትው አድርጎ ያስረዳል፡-

“አላህም የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሀልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ) ጥራት ይገባህ ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ #አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ አውቀኸዋል በነፍሴ ውስጥ ያለው
👍1
9-11)፡፡
"ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፤እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ወይንንም፤ እርጥብ ሳርንም፤የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)። ለናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)።" (ሱረቱ ዐበሰ 24-32)፡፡
7. አመስጋኝ መሆን እንዳለብን፡- ሲሳይ ሰጪና የሕይወታችን ቋሚ ጠባቂ የሆነው አምላካችን አላህ ከሆነ፡ እኛም በሚሰጠን ሲሳይ ላይ ልናመሰግነው እንደሚገባ እንማራለን፡-
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮች ብሉ፡፡ ለአላህም እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደኾናችሁ አመስግኑ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 172)፡፡
"ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት (በካዕባ) አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥሁ፤ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ (አስቀመጥኳቸው)፤ ከሰዎችም ልቦችን ወደነሱ የሚናፍቁ አድርግ፤ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፤" (ሱረቱ ኢብራሂም 37)፡፡
"አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ፣ የተፈቀደ ንጹሕ ሲሆን ብሉ፤ የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትግገዙት፣ ብትሆኑ አመስግኑ።" (ሱረቱ-ነሕል 114)፡፡
"ለሰበእ (ሰዎች) በመኖሪያቸው በውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሩዋቸው)፤ ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ፤ ለርሱም አመስግኑ፤ ሀገራችሁ ውብ ሀገር ናት፤ (ጌታችሁ) መሐሪ ጌታም ነው፤ (ተባሉ)።" (ሱረቱ ሰበእ 15)፡፡
8. ፈተና እንደሚመጣ፡- አላህ ለባሮቹ የሚሰጠውን ሲሳይ በመቀነስና በማጥበብ እንዲሁም በመጨመርና በማስፋት ሊፈትናቸው እንደሚችልም እናምናለን፡፡ ዓላማውም ሲሳዩ የሰፋላቸው በማመስገን እንዲለግሱ፡ የጠበበባቸው ደግሞ እንዲታገሱ ነው፡-
"ሰዉማ፣ ጌታዉ በሞከረዉ ጊዜ፣ ባከበረዉና ባጣቀመዉም (ጊዜ) ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል። በሞከረዉና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ ጌታዬ አሳነሰኝ ይላል።" (ሱረቱል ፈጅር 15-16)፡፡
"ጌታህ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ እርሱ በባሮቹ ሁኔታ ውስጠ ዐዋቂ ተመልካች ነውና።" (ሱረቱል ኢስራእ 30)፡፡
"አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ፥ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አሉበት።" (ሱረቱ-ሩም 37)፡፡
"በላቸው፦ ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።" (ሱረቱ ሰበእ 36)፡፡ "
"የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መከፈቻዎች የርሱ ናቸው። ሲሳይን ለሚሻ ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ እርሱ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።" (ሱረቱ-ሹራ 12)፡፡
9. ካለን መስጠት እንዳለብን፡- ሲሳያችን ከአላህ ዘንድ መሆኑን ካመንን፡ እርሱም የማያልቅበት ጌታ መሆኑን ከተረዳን እንግዲያውስ በምድር ላይ ለተቸገሩ ሰዎች ልናዝንና ካለንም ነገር ልናካፍላቸው ይገባናል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ ዘንድ ያለው ቢያልቅም ሰጪው ጌታ አያልቅበትምና፡-
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ውስጥ ሽያጭ (መበዠት)፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 254)፡፡
"ለነዚያ ላመኑት ባሮቼ በርሱ ውስጥ ሽያጭና ወዳጂነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ሶላትን በደንቡ ይሰግዳሉ፤ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም በግልጽም ይለግሳሉ፤ (ስገዱ ለግሱም) በላቸው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 31)፡፡
"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና፦ ጌታዬ ሆይ! እንድመሰውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" (ሱረቱል ሙናፊቁን 10)፡፡
"የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድድም፤ አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል።" (ሱረቱ-ጦላቅ 7)፡፡
10. የአማኞች ባሕሪ መሆኑን፡- እውነተኛ ሙእሚኖች ካላቸው ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው፡-
"ፍጹም ምእምናን፣ እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፤ በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸው ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው። እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ፣ ናቸው።" (ሱረቱል አንፋል 2-3)፡፡
"አንቀጾቻችንን የሚያምኑት እነዚያ በርሷ የተገሰጹት ጊዜ ሰጋጆች ኾነው የሚውድቁትና እነሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ብቻ ናቸው። ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፤ ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ።" (ሱረቱ-ሰጅዳህ 15-16)፡፡
11. እሱ የተብቃቃ መሆኑን፡- ጌታችን ፍጡራኑን መጋቢ እንጂ ተመጋቢ ጌታ አይደለም፡-
"«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ #የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው…" (ሱረቱል አንዓም 14)፡፡
"ጋኔንንና ሰውን ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። ከነሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፤ #ሊመግቡኝም አልሻም። አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ፣ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው።" (ሱረቱ-ዛሪያት 56-58)፡፡
12. ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ መሆኑን
"እነዚያም በአላህ ሃይማኖት የተሰደዱ፣ ከዚያም የተገደሉ፣ ወይም የሞቱ፣ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይስጣቸዋል፣ አላህም እርሱ ከስጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 58)፡፡
"ወይስ ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ በላጭ ነው፡፡ እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 72)፡፡
"ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ለርሱም ያጠባል፤ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፤ እርሱም ከሲሳይ ሰጭዎች ሁሉ በላጭ ነው በላቸው።" (ሱረቱ ሰበእ 39)፡፡
"ንግድን ወይንም ዛዛታን ባዩህ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲሆኑ ወደርሷ ይበተናሉ፤ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፤ አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው በላቸው።" (ሱረቱል ጁሙዓህ 11)፡፡
" قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا أَنْزِلْ عَلَيْنَا مَائِدَةً مِنَ السَّمَاءِ تَكُونُ لَنَا عِيدًا لِأَوَّلِنَا وَآخِرِنَا وَآيَةً مِنْكَ وَارْزُقْنَا وَأَنْتَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ " سورة المائدة 114
"የመርየም ልጅ ዒሳ አለ ፦ጌታችን አላህ ሆይ! ለኛ ለመጀመሪያዎቻችንና ለመጨረሻዎቻችን ባዕል (መደሰቻ) የምትሆንን ከአንተም ተአምር የሆነችን ማእድ ከሰማይ በኛ ላይ አውርድ፤ ስጠንም፤ አንተ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነህና።" (ሱረቱል ማኢዳህ 114)፡፡
ያ ረዛቅ! ሐላል የሆነ ሪዝቅን፣ ተቀባይነት ያለው ስራን ወፍቀን፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder