የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
በመላእክት ማመን
ክፍል አስራ ስድስት
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
7/ የመላእክት ሞት፡-
ለዛሬ አላህ ፈቃዱ ከሆነ የምንነጋገረው ‹‹መላእክት ይሞታሉ ወይስ አይሞቱም?›› የሚለውን ነጥብ ነው ኢንሻአላህ፡፡
ሀ/ ፈጣሪ አምላካችን አላህ ከመለኮታዊ ስሞቹ መካከል አንዱ ‹‹አል-ሐይ›› የሚል ነው፡፡ የዚህም መለኮታዊ ስም ቀጥተኛ ትርጓሜ፡- ፍጹም ህያው ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በራሱ ሕያው የሆነ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐይ" ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታ አላህ ለሕያውነቱ ጅማሬና ፍጻሜ የሌለው ጥንታዊና ዘላለማዊ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ሞት የማይከተለው፡ እክል የማይገጥመው ጌታ በመሆኑ "አል-ሐይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ህያው ለተሰኙ ፍጥረታት በጠቅላላ ህይወትን ለጋስና የህይወት ሁሉ ምንጭ በመሆኑ "አል-ሐይ" ተብሎ ይጠራል፡፡
ከሱ ውጭ ያለው በጠቅላላ ሙት ነው፡፡ ካልነበረበት ዓለም፡ ወደ መኖር የመጣውና የተሸጋገረው በአላህ ህያው አድራጊነትና ፈጣሪነት እንጂ፡ በራሱ አይደለምና፡፡
ከሱ ውጭ ያለው በጠቅላላ ሙት ነው፡፡ ምክንያቱም ከተወሰነ ምድራዊ ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ሞት ይመለሳልና፡፡ ማንም በባህሪው ፍጹም ጥንታዊነትን እንዳልተላበሰው ሁሉ፡ ያለ ሞትም ፍጹም ዘላለማዊነትን መላበስ አይችልምና፡፡
ከሱ ውጭ ያለው በጠቅላላ ሙት ነው፡፡ ምክንያቱም ከሙታን ዓለም ዳግም ነፍስ በመዝራት ህያው አድርጎ የሚቀሰቅሰው ጌታው አላህ እንጂ፡ የራሱ ችሎታና ኃይል አይደለምና፡፡ የኛ ህያውነት ፍጥረታዊና ጊዜያዊ ስጦታ ሲሆን፡ የጌታችን ፍጹም ህያዊነት ጥንታዊና ዘላለማዊ የሆነ የራሱ ባህሪ ነው፡፡

ለ/ መላእክት ይሞታሉ ወይ? በሚለው ጉዳይ ላይ አብዝኃኞቹ የኢስላም ሊቃውንት አዎ! ይሞታሉ የሚለውን አቋም ሲይዙ፡ ከፊሎቹ ደግሞ (ኢብኑ ሐዝም፣ የተወሰኑ የተፍሲር ሊቃውንት) አይሞቱም የሚል ነው፡፡ ከመረጃ አንጻር ይሞታሉ የሚሉት ሊቃውንቶች ማስረጃቸው ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ የተሻለውም ምልከታ እሱ እንደሆነ ሌሎች ዑለማዎች ጠቁመዋል፡፡ መላእክት ሟች ለመሆናቸው የቀረቡትም ማስረጃዎች ቀጣዮቹ ናቸው፡-
" وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَمَنْ فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَنْ شَاءَ اللَّهُ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَى فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنْظُرُونَ " سورة الزمر68
"በቀንዱም ይነፍፋል፤ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡርና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ፣ አላህ የሻው ሲቀር #በድንጋጤ_ይሞታል፤ ከዚያም በርሱ ሌላ (መነፋት) ይነፋል፤ ወዲያውም እነርሱ (የሚሠራባቸውን) የሚጠባበቁ ሆነው ቋሚዎች ይሆናሉ።" (ሱረቱ-ዙመር 39፡68)፡፡
በዚህ አንቀጽ ውስጥ ‹‹በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር›› የሚለው መላእክትን የሚወክል ገለጻ ነው፡፡ እነሱ የሰማይ ነዋሪዎች ናቸውና፡፡ በቀንዱ በተነፋ ጊዜ እነሱም በድንጋጤ መሞታቸው እንደማይቀር የሚጠቁም ነው፡፡
‹‹አላህ የሻው ሲቀር›› የሚለው ላይ እነማንን ነው? በሚለው ዙሪያ የተፍሲር ምሁራኖች ዘንድ የሀሳብ ልዩነት አልለ፡፡ ከፊሎቹ፡- ጂብሪል፣ ሚካኢል፣ ኢስራፊል፣ መለኩል መውት (ዐለይሂሙ-ሰላም) ናቸው ሲሉ፡ ከፊሎቹ ደግሞ፡- በተጨማሪም የዐርሽ ተሸካሚዎችን ያስገባሉ፡፡ ሌሎቹ ሶስተኞቹ ደግሞ፡- የጀነት ሑረል-ዒኖች እና ሰማእታት ‹ሹሀዳእ› ናቸው የሚሉ አልሉ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
የሆነው ሆኖ፡ እነዚህ በአላህ መሻት ‹የተነጠሉት› መላእክትም ቢሆኑ በመጀመሪያው መነፋት ላይ ባይሞቱም፡ ከሁለተኛው መነፋት በፊት እንደሚሞቱ ምሁራኖቹ ይገልጻሉ፡፡
" وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ " سورة القصص 88
"ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር #ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ" (ሱረቱል ቀሶስ 28፡88)፡፡
በዚህ አንቀጽ ስር ‹‹ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው›› የሚለው ኃይለ-ቃል፡ መላእክትንም ያጠቃልላል፡፡ ከአላህ በቀር ያለው ሁሉ ጠፊ መሆኑ ከተነገረ፡ መላእክትም ሟች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ የማይጠፋውና የማይሞተው፡ ሁሌም ህያው የሚሆነው ጌታ አላህ ብቻ ነውና!፡-
" وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ وَكَفَى بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا " سورة الفرقان 58
"በዚያም #በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፤ ከማመስገንም ጋር አጥራው፤ በባሮቹ ኀጢአቶችም ውስጠ ዐዋቂ በርሱ በቃ።" (ሱረቱል ፉርቃን 25፡58)፡፡
" وَعَنَتِ الْوُجُوهُ لِلْحَيِّ الْقَيُّومِ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا " سورة طه 111
"ፊቶችም ሁሉ፣ #ሕያው፣ አስተናባሪ ለሆነው (አላህ )ተዋረዱ፤ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።" (ሱረቱ ጣሀ 20፡111)፡፡
" هُوَ الْحَيُّ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ فَادْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة غافر 65
"እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) #ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ፣ ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፣ የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት።" (ሱረቱ ጋፊር 40፡65)፡፡
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ..." سورة البقرة 255
"አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ #ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም…" (ሱረቱል በቀራህ 2፡255
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ " سورو آل عمران 2
"አላህ ከሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም (እሱ) #ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነዉ።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡2)፡፡
ሙሐመድ ዐብድ-ረኡፍ አል-መንናዊይ (952-1031 ሂጅ.) ረሒመሁላህ፡ መላእክት የሚሞቱ ለመሆናቸው የዑለሞች የሀሳብ ስምምነት ‹ኢጅማዕ› እንዳለበት እንዲህ ይገልጻሉ፡-
وأما الملائكة فيموتون بالنص والإجماع ويتولى قبض أرواحهم ملك الموت ويموت ملك الموت بلا ملك الموت. فيض القدير 562/3.
‹‹መላእክትማ በነስ (በቁርኣን ማስረጃ) እንዲሁም በኢጅማዕ (የኢስላም ሊቃውንት ስምምነት) ሟች መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ ሩሐቸውንም በመውሰድ መለኩል መውት ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ በመጨረሻም መለኩል መውትም ያለ ሌላ መልአከ ሞት (በአላህ ትእዛዝ ብቻ) ይሞታል›› (ፈይዱል-ቀዲር 3/562)፡፡
ወላሁ አዕለሙ ቢል-ሐቅ!!
ይቀጥላል
የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አይደለም!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ሰሞኑን የመርየምን ልጅ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) በተመለከተ፡ ተከታታይ ትምሕርቶችን እየዳሰስን ነው፡፡ በተለይ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢይነትና ከሰብአዊ ፍጥረት ክልል አውጥቶ እሱን አምላካዊ ማንነት ለማላበስ የሚደረገውን ከንቱ ሙከራ ምላሽ እየሰጠንበት ነው፡፡ ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከነቢያት ኹሉ በላይ ከፍ ለማድረግ ያግዙናል የሚሏቸውን አንዳንድ ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾችንም በማንሳት የአንቀጹን ትክክለኛ መልእክት እና የነሱን የተሳሳተ ግንዛቤ እየተመለከትን ነው፡፡ ዛሬም አላህ ፈቃዱ ከኾነ የምንመለከተው የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ እንዳልነበረ፣ እንዳልኾነና ፈጽሞም ሊኾን እንደማይቸል የሚያስረዱትን ቀጥታና ግልጽ የኾኑ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾችን በመጠቀም ነው፡፡ መልካም ንባብ፡-

ሀ/ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም!

ይህ አንዱና ዋነኛው መረጃችን ነው፡፡ የአላህ ቃል የኾነው ቅዱስ ቁርኣን ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ በግልጽ ይናገራል፡፡ ‹‹ሌላ የለም›› በሚለው ቃል ውስጥ ከአላህ ውጭ የኾነው ፍጥረት ኹሉ ይካተታል፡፡ የመርየም ልጅም ከነዚህ ‹‹ሌላ›› ተብለው ከተጠቀሱት አካላት አንዱ ነው፡፡ እሱ አላህ አይደለምና፡ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም! ከተባለ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አምላክ አለመኾኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል ማለት ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡163)፡፡

"ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል (ከሓዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን (አስታውቁ በማለት ያወርዳል)፡፡" (ሱረቱ-ነሕል 16፡2)፡፡

"እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡" (ሱረቱ ጣሀ 20፡14)፡፡

ለ/ ዒሳ ጠፊ ነው፡-

ይህ ደግሞ ሌላኛው ማስረጃችን ነው፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ፍጹም ዘላለማዊነትን አልተላበሰም፡፡ ፈጣሪ አምላኩ አላህ በፈለገ ጊዜ ሊያጠፋው ይችላል፡፡ ከዚህ ጥፋት እራሱም ሆነ ሌላው አካል በመተባበር ሊያድነው የሚችል አንድም ኃይል የለም አይኖርምም፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

“እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን፡ እናቱንም፡ በምድር ያለንም ሁሉ #ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማን ነው? በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው የሚሻውን ይፈጥራል አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡” (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡17)፡፡

በዚህ አንቀጽ መሰረት፡ ጌታ አላህ ዒሳንም ሆነ እናቱን እንዲሁም በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለማጥፋት ቢፈልግ፡ ማንም ሊያድናቸው የሚችል እንደሌለ ያስረዳል፡፡ አያይዞም በመቀጠል ‹‹የሚሻውን ይፈጥራል›› በማለት ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ከፍጥረታዊ ማንነት ውጪ የዘለለ ሌላ ነገር እንደሌለው ያስረዳል፡፡ እውነተኛ አምላክ የሆነው አላህ ግን አይጠፋም፡፡ ሁሌም ቀሪ ነው፡፡ ቃሉም የሚለው እንዲህ ነው፡-

“በርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ የእልቅናና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል (አይጠፋም)” (ሱረቱ-ረሕማን 55፡26-27)፡፡

“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትገዛ ከርሱ በቀር አምላክ የለም ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው ፍርዱ የርሱ ብቻ ነው ወደርሱም ትመለሳላችሁ” (ሱረቱል ቀሶስ 28፡88)፡፡

ሐ/ ዒሳ ምግብን ይመገብ ነበር፡-

ሰዎች በዚህ ምድር ላይ በሕይወት ለመቆየት ከሚያስፈልጋቸው መሠረታዊ ነገራት አንዱ መብል ነው፡፡ ያለ መብል በሕይወት መቆየት አይችሉም፡፡ ይህም ደካማ ፍጡር መኾናቸውን ያሳያል፡፡ የመርየም ልጅም ከተመጋቢዎቹ አንዱ ነበር፡፡ ታዲያ እንዴት ኾኖ ነው ከአፈር የወጣንና የበቀለን ነገር እንደምግብነት የሚጠቀም አካል የኔ አምላክ ሊኾን የሚችለው? ደግሞስ የበላውና የጠጣው ነገር ተመልሶ በሌላ መልክ (በሽንትና በቆሻሻ) ከሰውነቱ መውጣቱ ይቀራልን? እንግዲያውስ ይህን ስርአት የሚፈጽም አካል አምላኬ ነው ብዬ ልቀበለው? እሱም ደፍሮ አይለኝም!!

“የመርየም ልጅ አል መሲሕ፡ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም እናቱም በጣም እውነተኛ ናት (ሁለቱም) ምግብን #የሚበሉ ነበሩ፡፡ አንቀጾችን ለነርሱ (ለካሀዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት” (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡75)፡፡

እውነተኛው አምላክ አላህ ግን አይበላም፡፡ ባይሆን ፍጡራኑን (ሰውን፣ እንሰሳትን፣ ነፍሳትን፣ በራሪዎችን…) ያበላል እንጂ፡፡ እርሱ መጋቢ እንጂ ተመጋቢ አይደለም! የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

“ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ፡ እርሱ የሚመግብ፣ #የማይመገብም ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን? በላቸው፡፡ እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልሆን ታዘዝኩ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን (ተብያለሁ) በላቸው” (ሱረቱል አንዓም 6፡14)፡፡

“ጋኔንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም #ሊመግቡኝም አልሻም አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኃይል ባለቤት ነው፡፡” (ሱረቱ-ዛሪያት 56-58)፡፡

መ/ ዒሳ ወደፊት ሟች ነው፡-

መሞት የፍጡራን ባሕሪ እንጂ የአምላክ አይደለም፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳም (ዐለይሂ-ሰላም) ፍጡር በመኾኑ ከሞት ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ቂያማ ከመቆሙ በፊት ወደዚህ ምድር በጌታው ፈቃድ ከወረደና ተልእኮውን ከፈጸመ በኋላ እሱም ይሞታል፡፡ ሟች መሆኑን ገና በእናቱ እቅፍ ሳለ በልጅነቱ እንዲህ ተናግሯል፡-

“ሰላምም በኔ ላይ ነው በተወለድኩ ቀን #በምሞትበትም ቀን ህያው ሆኜ በምቀስቀስበት ቀን” (ሱረቱ መርየም 19፡33)፡፡

እውነተኛው ጌታና አምላክ አላህ ግን ፈጽሞ የማይሞት ነው፡፡ ደግሞስ የሞት ፈጣሪና አምላክ እንዴት በፈጠረው ሞት ይያዛል?

“ፊቶችም ሁሉ #ሕያው አስተናባሪ ለሆነው (አላህ) ተዋረዱ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ” (ሱረቱ ጣሀ 20፡111)፡፡

“በዚያም #በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ…” (ሱረቱል ፉርቃን 25፡58)፡፡

ሠ/ የትንሳኤ ቀን ጥያቄና መልስ

ነገ በየውሙል ቂያም (በዕለተ ትንሳኤ) ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) በጌታው ፊት በሰዎቹ ይመሰክርባቸውና ይክዳቸው ዘንድ ይጠየቃል፡፡ አንተ ለሰዎቹ እኔና እናቴን ከአላህ ሌላ አምላክ አድርጋችሁ ያዙ ብለህ አስተምረህ ነበርን? ተብሎ ይጠየቃል፡፡ የሱም መልስ፡- በፍፁም! የሚል ይሆናል፡፡ ይህም አምላክ አለመሆኑን ፍንትው አድርጎ ያስረዳል፡-

“አላህም የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብለሀልን? በሚለው ጊዜ (አስታውስ) ጥራት ይገባህ ለኔ ተገቢዬ ያልሆነን ነገር ማለት ለኔ #አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደሆነም በእርግጥ አውቀኸዋል በነፍሴ ውስጥ ያለው
👍1