የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
ል፡- "የሙናፊቅ ምልክት ሶስት ናቸው፡- ሲናገር ይዋሻል፣ ቀጠሮ ያፈርሳል፣ ሲታመን ይከዳል" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
8ኛ. ነጌ የቂያም ቀንም ጠቃሚነቱ በእምነታቸውና በስራቸው እውነተኛ ለሆኑ ለአላህ ባሮች ብቻ እንደሆነ ቅዱስ ቁርኣን ያስተምራል፡-
"አላህ ይላል ፦ ይህ እውነተኞችን እውነታቸው የሚጠቅምበት ቀን ነው፤ ለነርሱ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው በውስጣቸው ሁልጊዜ ዘውታሪዎች ሲሆኑ የሚኖሩባቸው ገነቶች አሉዋቸው፤ አላህ ከነሱ ወደደ፤ እነርሱም ከርሱ ወደዱ፤ ይህ ታላቅ ዕድል ነው።" (ሱረቱል ማኢዳህ 5:119)፡፡
"አላህም እውነተኞችን በውነተኛነታቸው ሊመነዳ፣ መናፍቃንንም ቢሻ ሊቀጣ፣ ወይም (ቢመለሱ) በነሱ ላይ ጸጸታቸውን ሊቀበል፥ (ይህን አደረገ)፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" (ሱረቱል አሕዛብ 33:24)፡፡
9ኛ. እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ኢስላም ውሸትን ለቀልድና ሰውን ለማሳቅ ብሎ እንኳ አለመፍቀዱ ነው፡-
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "ወየውለት! ለዚያ ሲናገር ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ ለሚዋሽ ሰው፡ ወየውለት! ወየውለት!" (አቡ-ዳዉድ 4992፣ አሕመድ 20055)፡፡
አቢ ኡማማህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "በጀነት ውስጥ ላለው መሐከለኛ ቤት ውሸትን ለቀልድም እንኳ ቢሆን ለተወ ሰው ተሟጋች ነኝ" (ሶሒሑ ተርጊብ-ወተርሂብ 6/3)፡፡
10ኛ. የታላቁ ሮም ንጉስ የነበረው ሒረቅል አባ ሱፍያንን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢያችሁ በምን ያዛችኋል? ብሎ በጠየቀው ጊዜ እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- "አላህን ብቻውን ተገዙት፡ በርሱም ምንንም አታጋሩ፣ አባቶቻችሁ የሚሉትን ነገር ተዉ፣ ሶላት እንድንሰግድ፣ #እውነትን እንድንናገር፣ ዝምድናን እንድንቀጥል ያዘናል" (ቡኻሪይ)፡፡
ታዲያ ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢስላም ለሃይማኖትህ ስትል ውሸትን መናገር ይፈቅዳል ብሎ ወሬ ማናፈስ የጤና ነውን?
ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ እንግዲያውስ ከላይ መግቢያ ላይ እንደ ርእስ የተጠቀሰው ሐዲሥ መልእክቱ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ስለሚነሳ እስኪ ወደሱ እንመለስ፡-
ሀ. በሰዎች መሐል እርቅ ለመፍጠር፡-
ሰዎች ተጣልተው እርቅ ለመፍጠር የሚፈልግ ሽማግሌ እውነቱን ተናግሮ የጥሉን ግድግዳ ማፍረስ የማይችል ቢሆንና ሌላ አማራጭ ቢጠፋበት፡ ሰላሙን ለማውረድ አስቦ የአንደኛውን ጥፋት መግለጹ የባሰ ጥሉን እንደሚያባብሰው ከተረዳ፡ ዋሽቶ ቢያስታርቃቸው እንደ ኃጢአተኛ አይቆጠርም፡፡ ምክንያቱም ዓላማው የግል ጥቅሙን ለማስጠበቅ፣ ተወዳጅነትን ለማትረፍና ምድራዊ ጥቅሙን ለማግኘት ሳይሆን በሰዎች መሐል እርቅ ለማውረድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተጨባጩ ዓለም ላይ የምናየውና የምንኖረው እውነት ነው፡፡ ባልና ሚስት ተጣልተው ትዳሩ ሊፈርስ ቢቃረብና ጉዳዩን የተረዳ ሽማግሌ የአንዳቸውን ነውር ደብቆ ዋሽቶ ቢያስታርቃቸው ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው? ወይስ እውነቱን አውጥቶ ያፍረጥርጠውና ትዳሩም ይፍረስ፡ ቤተሰቡም ይበተን?
ጉዳዩን የበለጠ ለመረዳት ምሣሌን እንመልከት፡-
ምሣሌ አንድ፡- አንድ ተበዳይ የሆነ ሰው ከበዳዩ ለማምለጥ እየሮጠ ወደ አንድ ግቢ ሲሸሸግ በአይንህ ተመልክተኸዋል፡፡ በዳዩ ሰው ወዳንተ መጥቶ፡- አሁን በዚህ ጋ የሮጠውን ልጅ አይተኸዋል? የት ነው የተሸሸገው? ብሎ ቢጠይቅህ ምን ብለህ ትመልሳለህ? አሁን አንተ ሁለት አጣብቂኝ ነገር ውስጥ ገብተሀል፡፡
1ኛ. አላየሁም ብለህ መዋሸት
2ኛ. አይቼዋለሁ ብለህ የተደበቀበትን ቦታ ማሳየትና ልጁን ማስገደል ወይም ማስመታት
ታዲያ ውሸት ኃጢአት ነው ብለህ ልጁ የተደበቀበትን ቦታ አሳይተህ ማስገደሉ ፍትህ ነው? አእምሮህስ ይቀበለዋል? ወይንስ የተደበቀውን ሰው እንዳላየህ ገልጸህ ልጁን ማዳን? በተለይ ሊገደል የሚፈለገው ሰው የቤተሰብህ አካል ቢሆን ምን ልታደርግ እንደምትችል አስብ፡፡ ‹‹አኸፉ-ደረረይን›› ከሁለት ጉዳቶች፡ ጉዳቱ የተሻለውን መርጦ መጠቀም አግባብነት ያለው ድርጊት ነው፡፡
ምሣሌ ሁለት፡- የህክምና ባለሙያ ነህ እንበል፡፡ አንድን በሽተኛ እያከምኸው ሳለ፡ ህመሙ በጣም እንዳገረሸበትና በከፋ አደጋ ላይ እንዳለ ታውቃለህ፡፡ ይህን ሁኔታ ለበሽተኛው ብትነግረው፡ ምናልባትም መቋቋም አቅቶት የባሰ ህመሙ አገርሽቶበት ይሞታል ብለህ ትሰጋለህ፡፡ እናም ይህ ህመምተኛ፡- ዶክተር! አሁን እንዴት ነኝ? በምን ሁኔታ ላይ ነው የምገኘው? የጤናዬስ ነገር ያስፈራልን? ቢልህስ ያንተ ምላሽ ምንድነው የሚሆነው? ግልጽ ነው፡፡ እሱን ለማጽናናት የተስፋ ቃል እንጂ፡ በጣም አደጋ ላይ ነህ አትለውም፡፡ ይህን ማለትህ በበሽታው ላይ ሌላ በሽታ ማምጣት ነው፡፡
ለ. ባለቤቱን ለማስደሰት፡-
በትዳር ዓለም በባልና ሚስት መሐል የፍቅር ጨዋታዎች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ ታዲያ ባል የባለቤቱን ፍቅር ለመጨመርና በመሐከላቸው መዋደድ እንዲኖር ውሸትን ያዘሉ የጨዋታ ቃላቶች መጠቀም ተፈቅዶለታል፡፡ አንቺ ከዓለማት ሴቶች ሁሉ በላይ ለኔ ውድ ነሽ! እና የመሳሰሉትን፡፡ ምናልባት ምንም ሚስቱን ቢወዳትም፡ እሷ የዚያን ያህል የተወደደች ላትሆን ትችላለች፡፡ በውስጥዋ ደስታን ለመዝራትና ፍቅሩን ለማጠንከር ግን መጠቀም ይችላል፡፡ አንድ ምሣሌ እንመልከት፡-
ባለቤትህ አንተ ቤት ስትገባ እንድትበላና እንድትደሰት ቀኑን ሙሉ ምግብ ሰርታ ለፍታ አዘጋጅታ ጠበቀችህ፡፡ አንተም ወደ ቤት በገባህ ጊዜ የተዘጋጀህልን ምግብ መብላት ጀመርክ፡፡ ግን ምግቡ ላይ ጥፍጥና አላገኘህበትም፡፡ እናም ላንተ ብላ የለፋችው ባለቤትህ ወዳንተ በመምጣት፡ በፍቅር ቋንቋ፡- እንዴት ነው ምግቡ? ብትልህ፡ ምንም አይጣፍጥም! ነው ያንተ መልስ፡ ወይስ መስተካከል ያለበትን ሌላ ቀን እነግራታለሁ ብለህ ለዛሬ ሞራሏን ላለመንካት፡- በጣም አሪፍ ነው የሰራሽው ምግብ፡ ይጣፍጣል ውዷ ባለቤቴ! ነው የምትላት?
ሐ. በጦርነት ጊዜ፡-
ለወረራ የመጣን የጠላት ጦር በማዘናጋትና በማሳሳት ጥቃት ለመፈጸም በፍጥጫው ሌላ አቅጣጫ እንዳለን አድርጎ ማታለል የተፈቀደ ተግባር ነው፡፡ ካልሆነም የት እንዳለህ፡ የጦር ሰራዊቶችህን ብዛትና ቁጥር፡ የታጠቃችሁትን የመሳሪያ አይነት፡ ጦርነቱ መቼ እንደሚጀመር ከጠየቁህ እውነቱን ግለጽላቸውና መጥተው ይጨርሱት፡፡
ወንድምና እህቶች ከላይ እንዳነበብነው ኢስላም ውሸትን ምን ያህል እንዳወገዘና የተጠላ ተግባር እንደሆነ በሰፊው ተመልክተናል፡፡ ውሸተኞችም የማይድኑ መሆኑን አንብበናል፡፡ ለሶስት ምክንያቶች ግን ፡ እሱም ለማኃበረሰቡ ጥቅምና ግልጋሎት ሲባል እንጂ ለግል ጥቅም ታስቦ ባልሆነበት ቦታ ላይ መዋሸት መቻሉን አይተናል፡፡ የኢስላም ጠላቶች ግን፡ አንድም የተሟላ ዲን ስለሌላቸው ፡ ሌላም በጥላቻና መኃይምነት ስሜት በመነሳት እነዚህን ሶስቱን ነጥቦች ብቻ አጉልተውና አጋነው፡- ኢስላም ለሃይማኖትህ ስትል ዋሽ! ብሏል በማለት የሌለውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ ጭራሹኑ ለሃይማኖትህ ስትል መዋሸት በኢስላም ይቻላል ይላሉ፡፡ ይህ ትልቅ ቅጥፈት ነው፡፡ እኔ ለሃይማኖቴና ለጌታዬ አላህ ክብር ስል እንድዋሽ አልተፈቀደልኝም፡፡ ይልቁኑ ይህ ያለው በናንተ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ መጽሐፋችሁ እንዲህ ይላል፡-
‹‹በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኃጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል? ስለ ምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና። የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው።›› (ወደ ሮሜ ሰዎች 3፡7-8)፡፡
ወገኖቻችን ሆይ! ከፍጡራን አምልኮ ወጥታችሁ አንዱንና እውነተኛውን አምላክ አላህን ታመልኩና
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ መኖሩ የተረጋገጠ መሆኑ፡- የፈጣሪ አምላካችን አላህ መኖር ምናባዊ ሳይሆን ፍጹም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ የሱ መኖር scientifical truth ወይም Historical truth ሳይሆን Universal truth (ተፈጥሮአዊ እውነታ) ነው፡፡ የአላህን መኖር ለማረጋገጥ የከርሰ ምድር ጥናት ወይም የጠፈር ምርምር ወይም የታሪክ ማረጋገጫ አያስፈልግም፡፡ ማንም ሰው በተፈጥሮው ያለ-ምንም ሃይማኖታዊ ተጽእኖ አምኖ የሚቀበለውና የሚያድግበት እውነት ነው፡፡ ስለሆነም ጌታ አላህ "አል-ሐቅ" ተብሎ ይጠራል፡-
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنْ كُنْتُمْ فِي رَيْبٍ مِنَ الْبَعْثِ فَإِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ مِنْ نُطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ مِنْ مُضْغَةٍ مُخَلَّقَةٍ وَغَيْرِ مُخَلَّقَةٍ لِنُبَيِّنَ لَكُمْ وَنُقِرُّ فِي الْأَرْحَامِ مَا نَشَاءُ إِلَى أَجَلٍ مُسَمًّى ثُمَّ نُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوا أَشُدَّكُمْ وَمِنْكُمْ مَنْ يُتَوَفَّى وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَى أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنْ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْئًا وَتَرَى الْأَرْضَ هَامِدَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ وَأَنْبَتَتْ مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ * ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِ الْمَوْتَى وَأَنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الحج 6-5
"እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ)፤ እኛም ከዐፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤ የምንሻውንም፣ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ፣ በማህጸን ዉስጥ እናረጋዋለን ከዚያም ሕጻን ሆናችሁ እናወጣችኋለን። ከዚያም ሙሉ ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፣ (እናሳድጋችኋለን)፤ ከናንተም የሚሞት ሰው አለ፤ ከናንተም ከዕውቀት በኋላ፣ ምንንም እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፤ ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ፤ በስዋም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም፤ ውበት ካለው ቦታ ሁሉ ታበቅላለችም። ይህ፣ አላህ እርሱ #መኖሩ-የተረጋገጠ፤ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 5-6)፡፡
"ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ هُوَ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة الحج 62
"ይህ አላህ እርሱ #እውነት በመሆኑ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሽት በመሆኑ አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 62)፡፡
"يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ " سورة النور 25
"በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይመላላቸዋል አላህም እርሱ #መኖሩ-የተረጋገጠ (ሁሉን ነገር) ገላጭ መሆኑን ያውቃሉ።" (ሱረቱ-ኑር 25)፡፡
"ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة لقمان 30
"ይህ፣ አላህ እርሱ #እውነት፣ ከርሱም ሌላ የሚገዙት (ጣዖት)ውሸት በመሆኑና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመኾኑ ነው።" (ሱረቱ ሉቅማን 30)፡፡
2. ንግግሩ እውነት መሆኑን፡- እውነተኛው አምላክ አላህ የሚናገረውም እውነትን ብቻ ነው፡፡ ውሸት እሱ ዘንድ በፍጹም የለም አይታሰብምም፡፡ በንግግርም ከርሱ የበለጠ እውነተኛ የለም፡-
"اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا " سورة النساء 87
"አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 87)፡፡
"وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا " سورة النساء 122
"እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሠሩ፣ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ እናገባዋቸዋለን፤ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንገገርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማን ነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 122)፡፡
"وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَيَوْمَ يَقُولُ كُنْ فَيَكُونُ قَوْلُهُ الْحَقُّ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنْفَخُ فِي الصُّورِ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ " سورة الأنعام 73
"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ #እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 73)፡፡
"وَلَا تَنْفَعُ الشَّفَاعَةُ عِنْدَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ حَتَّى إِذَا فُزِّعَ عَنْ قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ قَالُوا الْحَقَّ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة سبأ 23
"ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ፣ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፤ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠም ጊዜ (ተማላጆቹ) ጌታችሁ ምን አለ? ይላሉ፤ (አማላጆቹ) #እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው ይላሉ።" (ሱረቱ ሰበእ 23)፡፡
3. መጽሐፍቱ እውነት መሆናቸውን፡- ከጌታ አላህ ዘንድ ለሰው ልጆች መመሪያ ይሆኑ ዘንድ የተወረዱት መለኮታዊ መጽሐፍት በእውነት የተሞሉ ሆነው ነው የወረዱት፡፡ የመጽሐፍቱ ባለቤት እውነተኛ ነውና፡-
"كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَأَنْزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ..." سورة البقرة 213
"ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ #በእውነት አወረደ…" (ሱረቱል በቀራህ 213)፡፡
"أُولَئِكَ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الضَّلَالَةَ بِالْهُدَى وَالْعَذَابَ بِالْمَغْفِرَةِ فَمَا أَصْبَرَهُمْ عَلَى النَّارِ * ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ نَزَّلَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِي الْكِتَابِ لَفِي شِقَاقٍ بَعِيدٍ " سورة البقرة 176-175
"እነዚያ ጥመትን በቅንነት ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው፡፡ በእሳት ላይም ምን ታጋሽ አደረጋቸው! ይህ (ቅጣት) አላህ መጽሐፍን #በእውነት ያወረደ በመኾኑ ምክንያት (እና በርሱ በመካዳቸው) ነው፡፡ እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት (ከእውነት) በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ ናቸው" (ሱረቱል በቀራህ 175-176)፡፡
"نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنْزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ " سورة آل عمران 3
"ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፉን (ቁርአንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ #በዉነት አወረደ። ተዉራትንና ኢንጅልንም አውርዷል።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 3)፡፡
4. ንግስናው እውነት መሆኑን፡- አላህ የዩኒቨርሱ አስተናባሪና ብቸኛ ተቆጣጣሪ በመሆኑ እውነተኛ ንጉስ ተብሎ ያጠራል፡፡ የሌላው ምድራዊ ንግስና በግዜና በቦታ የተገደበ ስለሆነ ይጠፋል፡፡ ፍጹም እውነተኛ ንጉስ እሱ ብቻ ነው፡-
"فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِنْ قَبْلِ أَنْ يُقْضَى إِلَيْكَ وَحْيُهُ وَقُلْ رَبِّ زِدْنِي عِلْمًا " سورة طه 114
"እውነተኛው ንጉስ አላህም (ከሃዲዎች ከሚሉት) ላቀ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፤ ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ በል።" (ሱረቱ ጣሀ 114)፡፡
"أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ * فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ " سورة المؤمنون 116-115
"«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን) የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 115-116)፡፡
"وَيَوْمَ تَشَقَّقُ السَّمَاءُ بِالْغَمَامِ وَنُزِّلَ الْمَلَائِكَةُ تَنْزِيلًا * الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَنِ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا " سورة الفرقان 26-25
"በሰማይም በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መወረድን የሚወርዱበትን ቀን (አስታውስ)። እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልረሕማን ብቻ ነው፤ በከሐዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው።" (ሱረቱል ፉርቃን 25-26)፡፡
5. ነቢያችንም የእውነት ነቢይ መሆናቸውን፡- ነቢዩ ሙሐመድ(ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ከእውነተኛው አምላክ ከአላህ ዘንድ የተላኩ በመሆናቸው፡ የሳቸውም ነቢይነት የእውነት መሆኑን እንረዳለን፡-
"إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَا تُسْأَلُ عَنْ أَصْحَابِ الْجَحِيمِ " سورة البقرة 119
"እኛ አብሳሪና አስፈራሪ ኾነህ #በውነት ላክንህ፡፡ ከእሳትም ጓዶች አትጠየቅም፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 119)፡፡
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِنْ رَبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَكُمْ وَإِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا " سورة النساء 170
"እላንተ ሰዎች ሆይ! መልክተኛው #እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ እመኑም ለናንተ የተሻለ (ይሆናል) ብትክዱም አትጎዱትም፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 170)፡፡
" إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ * وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُو آلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَجْنُونٍ * بَلْ جَاءَ بِالْحَقِّ وَصَدَّقَ الْمُرْسَلِينَ " سورة الصافات 37-35
"እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ በነሩ። እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተዉ ነን? ይሉም ነበር። አይደለም እዉነቱን (ሃይማኖት) አመጣ። መልክተኞቹንም እዉነተኛነታቸዉን አረጋገጠ።" (ሱረቱ-ሷፍፋት 35-37)፡፡
6. ኢስላም እውነት መሆኑ፡- አላህ ለሰዎች የወደደው ብቸኛው ሃይማኖት ኢስላም ምንጩ ከሱ ዘንድ የመጣ በመሆኑ እውነተኛ ሃይማኖት ነው፡-
"هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ " سورة التوبة 33
"እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛዉን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነዉ።" (ሱረቱ-ተውባህ 33)፡፡
"هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَكَفَى بِاللَّهِ شَهِيدًا " سورة الفتح 28
"እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በውነተኛ ሃይማኖት፣ በውነተኛ ሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው።" (ሱረቱል ፈትሕ 28)፡፡
"هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ " سورة الصف 9
"እርሱ ያ አጋፋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ (መጽሐፍ