ከአላህ ስሞችና ባሕሪያት አንዱ ነው
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8 "
"አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8
1. "አር-ራሕማን"
ሀ.ትርጓሜው፡- የዚህ መለኮታዊ ስም "አር-ራሕማን" ትርጉም፡- እጅግ በጣም ሩኅሩህ ማለት ነው፡፡ ርኅራሄው ፍጥረቱን በመላ ያካለለ ለአማኙም ሆነ ለከሐዲው የተረፈ ነው፡፡ "አር-ራሕማን" የሚለው መለኮታዊ ሰም አላህ ብቻ የሚጠራበት ነው፡፡ ከሱ ውጪ ማንንም በዚህ ስም መጥራት አይፈቀድም፡፡ ከራሕመቱ መገለጫዎችም፡- ባሬያዎቹን ፈጥሮ ለሲሳያቸውም ኃላፊነቱን ራሱ መውሰዱ፣ የመኖሪያ ስፍራቸውን ዱንያን ያለ-ምንም ሽያጭና ኪራይ በነጻ መስጠቱ፣ ነቢያትን ከመሐከላቸው መርጦ፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን አውርዶ ወደ ቅን ጎዳና ማመላከቱና ማገዙ....ከፊሎቹ ናቸው፡፡ የአላህ ራሕመት ለባሪያዎቹ የተስፋ በርን የሚከፍት፤ ወደ መልካም ስራም የሚያነሳሳ፡ እንዲሁም ፍርሐትና ተስፋ መቁረጥን የሚያርቅ ነው፡፡ ስለሆነም ነው ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ የተናገሩት፡-
"ሙእሚን አላህ ለኃጢአተኞች ያዘጋጀውን ቅጣት ታላቅነት ቢረዳ ኖሮ ጀነቱን ተስፋ አያደርግም ነበር፤ ካፊር ደግሞ አላህ ለተመላሽ ባሪያዎቹ የደገሰውን የራሕመቱን ታላቅነት ቢረዳ ከጀነቱ ተስፋ አይቆርጥም ነበር" (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
ይህ የሚያሳየን በራሕመቱ ላይ ብቻ ተደግፈን ኃጢአት ላይ እንዳንወድቅ እና ቅጣቱንም ፈርተን ተስፋ እንዳንቆርጥ ሚዛናዊ መሆን እንዳለብን ነው፡፡ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ ቂያማ እስከሚቆም ድረስ ጌታችን በምድራችን ላይ ያወረደው ራሕመት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን? ከፈለግን ቀጣዩን ነቢያዊ ሐዲሥ እንመልከት፡-
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለ፡- "አላህ ራሕመትን ከፈጠረው በኋላ ወደ መቶ ቦታ ከፈለው፡፡ ከዛም አንድ እጁን ወደ ምድር በማውረድ ዘጠና ዘጠኙን እሱ ዘንድ አኖረ፡፡ በዚህ አንድ ክፋይ ነው ፍጥረታት በመላ የሚተዛዘኑት፡ ፈረስ እነኳ ሳትቀር እግሯን ከልጇ ላይ እንዳትጎዳው በማሰብ የምታነሳው የዚሁ ራሕመት ውጤት ነው" (ቡኻሪይ የዘገበው)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ፡- የቂያም ዕለት መቶውንም የራሕመት ክፍሎች ለአማኝ ባሪያዎቹ እንደሚለግሳቸው ተገልጾአል፡፡ ጌታችን አላህ ከቁጣው ራሕመቱ የቀደመ አምላክ ነው፡፡
ለ. አመጣጡ "አር-ራሕማን" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 57 (ሃምሳ ሰባት) ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለናሙና ያክል፡-
"እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፤ ጌታህን ፈሪ እንደ ኾንክ፣ (አትቅረበኝ) አለች።" ሱረቱ መርየም 18
"የአልረሕማን አንቀጾች በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ፣ ሰጋጆችና አልቃሾች ኾነዉ ይወድቃሉ።" ሱረቱ መርየም 58
"ሃሩንም ከዚያ በፊት በእርግጥ አላቸው፦ ሕዝቦቼ ሆይ! (ይህ) በርሱ የተሞከራችሁበት ብቻ ነው ጌታችሁም አልረሕማን ነው ተከተሉኝም፤ ትእዛዜንም ስሙ።" ሱረቱ ጣሀ 90
ይህ "አር-ራሕማን" የሚለው መለኮታዊ ስም ስምነትን ብቻ ሳይሆን ባሕሪንም ጭምር ያዘለ ነው፡፡ እሱም ጌታችን አላህ የራህመት ባሕሪ ባለቤት መሆኑን ያሳየናል፡፡ ለመለኮታዊ ክብሩ ተገቢ በሆነ መልኩ ከፍጡራን የርኅራሄ ባሕሪ ጋር ምንም ባልተመሳሰለ መልኩ አላህ የራህመት ባለቤት ነው፡፡
"ቢያስተባብሉህም፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ሕዝቦች ላይ አይመለስም» በላቸው፡፡" ሱረቱል አንዓም 147
ችሮታ ማለት እዝነት ቸርነት የሚለውን የሚገልጽ ነው፡፡ ከፍጡራን ጋር ምንም የሚያመሳስለው ነገር የለም፡-
"ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፤ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም" (ሱረቱ-ነሕል 74)፡፡
"…የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው" (ሱረቱ-ሹራ 11)፡፡
"ለርሱም አንድም ብጤ የለውም" (ሱረቱል-ኢኽላስ 4) የሚሉትን ተመልከት፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡- ከዚህ "አር-ራሕማን" ከሚለው መለኮታዊ ስሞች ብዙ ጠቀሚ ነገሮችን እንወስዳለን፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
1. "አር-ራሕማን" የሚል ስም እንዳለው፡- ፈጣሪ አምላካችን አላህ እርሱ "አር-ራሕማን" መሆኑን እንረዳለን፡፡አምነንም እንቀበላለን፡፡
"እርሱ (እመኑበት የምላችሁ) አልረሕማን ነው፤ (እኛ) በርሱ አመንን፤ በርሱም ላይ ተጠጋን፤ ወደ ፊትም በግልጽ መሳሳት ውስጥ የሆነው እርሱ ማን እንደ ሆነ በእርግጥ ታውቃላችሁ በላቸው።" ሱረቱል ሙልክ 29
2. ይህ ስም የ ራሕመት ባሕሪን እንዳቀፈ፡- ጌታችን በርኅራሄና በቸርነቱ የሚታወቅ በዚህም ባሕሪ የሚገለጽ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
"ጌታህም ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው፡፡ ቢሻ ያስወግዳችኋል፤ (ያጠፋችኋል)፡፡ ከሌሎች ሕዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ከበኋላችሁ የሚሻውን ይተካል፡፡" ሱረቱል አንዓም 133
3. ማመስገን እንዳለብን፡- "አር-ራሕማን" የሆነው አምላካችን አላህ ከራህመቱ ስፋት የተነሳ ቀኑን እንድንሰራበትና ሲሳያችንን እንድንፈልግበት ብርሐን፡ ሌሊቱን ደግሞ እንድናርፍበት ጨለማ አድርጎልናል፡፡ በዚህ ራሕመቱም እንድናመሰግነው ይፈልጋል፡፡ አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን፡፡
"ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት፣ አመስገኞችም ልትኾኑ አደረገላችሁ፡፡" ሱረቱል ቀሰስ 73
4. በዚህ ስም እንድንለምነው፡- ጌታችን አላህን ስንለምነውና ስንማጸነው "ያ አላህ" እንደምንለው ሁሉ "ያ ራሕማን" ብለንም መማጸንና መለመን እንችላለን፡፡
"፦አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤(ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ፣(መልካም ነው)፤ ለርሱ መልካም ስሞች አሉትና በላቸው…" ሱረቱል ኢስራእ 110
5. ባርነትን ወደዚህ ስም ማስጠጋትን፡- "አር-ራሕማን" የጌታችን ስም እስከሆነ ድረስ እኛም ባርነታችንን ወደዚህ ስም በማስጠጋት "ዐብዱ-ራሕማን" "አመቱ-ራሕማን" ብለን መሰየም፡ ስም ማውጣት እንችላለን፡፡
"በሰማያትና በምድር ያለዉ ሁሉ (በትንሣኤ ቀን)፣ ለአልረሕማን ባሪያ ኾነዉ የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም።" ሱረቱ መርየም 93
"የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ ሰላም የሚሉት ናቸው።" ሱረቱል ፉርቃን 63
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-"አላህ ዘንድ ከተወደዱት ስሞቻችሁ ውስጥ "ዐብደላህ" እና "አብዱ-ራሕማን" ናቸው" (ሙስሊም 2132)
በዚህ ስም ከተጠሩት የዚህ ኡመት ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ታላቁ ሶሐቢይ "ዐብዱ-ራህማን ኢብኑ ዐውፍ" ነው፡፡ በሒጅራ አቆጣጠር 32ኛው አመት ላይ የሞተ፤ ጀነት ከተበሰሩት አስሩ ሶሓባዎች አንዱ ነው ረዲየላሁ ዐንሁ፡፡

6. ይህን ባህሪ መላበስ እንዳለብን፡- "አር-ራሕማን" የሆነው አምላካችን አላህ በመለኮታዊ ባሕሪው ለባሪያዎቹ ርኅሩህ እንደሆነው እኛም በፍጥረታዊና ደካማ ባሕሪያችን ለመሰል ወንድሞቻችንና ለእንሰሳት ርኅሩህ መሆን እንዳለብን እንማራለን፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-"አዛኞችን አር-ራሕማን ያዝንላቸዋል፡፡ የምድር ነዋሪዎች ሆይ! እዘኑ፤ ከሰማይ በላይ ያለው ያዝንላችኃልና" ( ቲርሚዚ 1924)
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder

አንዱና ብቸኛው "አል ዋሒዱል አሐድ"
በ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
2. "አል-ዋሒድ" (ፍጹም አንድና ብቸኛ)
ሀ. ትርጉም፡- "አል-ዋሒድ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ አንድና ብቸኛ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በህልውናው (በዛቱ) የማይከፋፈል አንድ ጌታ በመሆኑ "አል-ዋሒድ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ዩኒቨርሱን (አጽናፈ ዓለሙን) ሲፈጥር ያለ አጋርና ያለ አማካሪ ብቻውን ያዘጋጀ በመሆኑ "አል-ዋሒድ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በባሕሪያቱና በስሞቹ አምሳያና ሞክሼ የሌለው ብቸኛ አምላክ በመሆኑ "አል-ዋሒድ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ብቻውን የሚመለክና የሚሰገድለት እውነተኛ አምላክ በመሆኑ "አል-ዋሒድ" ተብሎ የሚጠራ ነው፡፡
ለ. አመጣጡ፡- "አል-ዋሒድ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ሀያ አንድ ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 163)፡፡
"እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት፥ ወደኔ የሚወርድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ፤ ነኝ፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፤ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ፣ በላቸው።" (ሱረቱል ከህፍ 110)፡፡
"…እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው።" (ሱረቱ-ዙመር 4)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. ሁለት አለመሆኑን፡- ፈጣሪ አምላካችን አላህ ፍጹም አንድ መሆኑ ሁለት ላለመሆኑ ሌላ መረጃ ነው፡፡ ሁለት አምላክ (የብርሐንና የጨለማ ፈጣሪ የሆኑ) አሉ ብለው የሚያምኑ ሰዎች (መጁሳዎች) የተሳሳቱ እንደሆኑ መረዳት ይቻላል፡-
"አላህ አለ፦ ሁለት አማልክትን አትያዙ፤ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ እኔንም ብቻ ፍሩ።" (ሱረቱ-ነሕል 51)፡፡
2. ሶስት አለመሆኑን፡- ጌታችን አላህ "አል-ዋሒድ" ተብሎ መገለጹ ሶስት ላለመሆኑ መረጃ ነው፡፡ አላህን በአንድነቱና በሶስትነቱ መግለጽ ፍጹም የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ በአንድነት ውስጥ ልይዩ ሶስትነት አልለ ብሎ ያስተማረ አንድም ነቢይ የለም፡፡ አንድ ከሶስት ያንሳል፡ ሶስትም ከአንድ ይበዛል፡፡ አንድ ሶስት መሆን አይችልም፤ ሶስትም አንድ ሊሆን አይችልም፡-
"እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት (የሁን) ቃሉም ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ (አማልክት) ሦስት ናቸው አትበሉም፤ ተከልከሉ ለናንተ የተሻለ ይሆናልና፤ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ለርሱ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው። በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው። መመኪያም በአላህ በቃ።" (ሱረቱ-ኒሳእ 171)፡፡
"እነዚያ አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው (ከሶስቱ አንዱ እሱ ነው) ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ ከአምላክም አንድ አምላክ እንጅ ሌላ የለም፤ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ፣ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል።" (ሱረቱል ማኢዳህ 73)፡፡
3. ከሶስት በላይ አለመሆኑን፡- አምላካችን አላህ "አል-ዋሒድ" በመሆኑ፡ ከአንድ በላይ ብዙ አማልክት የሚያመልኩ ሰዎች የተሳሳቱና ጥመት ላይ ያሉ መሆናቸውን እንረዳለን፡-
"የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይንስ አሸናፊው አንዱ አላህ?" (ሱረቱ ዩሱፍ 39)፡፡
"«በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «አላህ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው፡፡ ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስፈራራበት ወደኔ ተወረደ፡፡ ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላችሁን» በላቸው፡፡ «እኔ አልመሰክርም» በላቸው፡፡ «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 19)፡፡
4. ለሳቸው የወረደ ወሕይ መሆኑን፡- ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ይወርድ የነበረው ወሕይ (መለኮታዊ ራእይ) አምላክ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚለው ነበር ማለት ነው፡-

"(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም። ያ ወደኔ የሚወረደው፣ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን? በላቸው።" (ሱረቱል አንቢያእ 107-108)፡፡
"(እንዲህ) በላቸው፦ እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደርሱም ቀጥ በሉ፤ ምሕረትንም ለምኑት ማለት፣ ወደኔ ይወርድልኛል። ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው።" (ሱረቱ ፉሲለት 6)፡፡
5. ቁርኣን የወረደበት አንዱ ዓላማ መሆኑን፡- ቅዱስ ቁርኣን አንዱ የወረደበት ዓላማ ይህንኑ የአምላክን አንድነት ለማስተማር ነው፡-
"ይህ (ቁርአን) ለሰዎች ገላጭ ነው፤ (ሊመከሩበት) በርሱም ሊስፈራሩበት እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን ሊያውቁበት የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሠጹበት (የተወረደ) ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 52)፡፡
"የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፤ ከነሱ ነዚያን የበደሉትን ሲቀር በሉም ፦ በዚያ ወደኛ በተወረደው፣ ወደናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች ነን።" (ሱረቱል ዐንከቡት 46)፡፡
6. ሰዎች በአንዱ አላህ ማመን እንደሚገባቸው፡- የጣኦት አምልኮን ትተው በአላህ አንድነት ሰዎች እስካላመኑ ድረስ ከክህደት ዓለም ሊላቀቁ አይችሉም፡፡
"በኢብራሂምና በነዚያ ከርሱ ጋር በነበሩት (ምእመናን) መካከል መከተል አለቻችሁ። ለሕዝቦቻቸው፦ እኛ ከናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን በናንተ ካድን፤ በአላህ አንድ ብቻ ሲሆን እስከምታምኑ ድረስ በኛና በናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፤ ባሉ ጊዜ( መልካም መከተል አለቻችሁ)…" (ሱረቱል ሙምተሒናህ 4)፡፡

7. ከኩፍር ጋር ኅብረት እንደሌለው፡- ካፊሮችና ሙሽሪኮች (በአላህ የሚያጋሩ) የአላህ ፍጹማዊ አንድነት ሲወሳ፡ እሱ ብቻውን መመለክ እንዳለበት ሲነገር አይስማማቸውም፡፡ ውስጣቸውን ይረብሸዋል፡፡
"አንድ አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይግገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን? ከውነተኞች ከሆንክ የምታስፈራራብንን (ቅጣት) አምጣብን አሉ።" (ሱረቱል አዕራፍ 70)፡፡
"ቁርአንንም ባነበብክ ጊዜ ባንተና በነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሽግን ግርዶሽ አድርገናል። እንዳያውቁትም በልቦቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን፤ ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርአን ባወሳኸው ጊዜ የሚሸሹሆነው በጀርቦቻቸው ላይ ይዞራሉ።" (ሱረቱል ኢስራእ 46)፡፡
"በል፦ እርሱ አላህ አንድ ነው። አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለርሱም አንድም ብጤ የለውም።" (ሱረቱል ኢኽላስ 1-4)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder
"አንድ አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይግገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን? ከውነተኞች ከሆንክ የምታስፈራራብንን (ቅጣት) አምጣብን አሉ።" (ሱረቱል አዕራፍ 70)፡፡
"ቁርአንንም ባነበብክ ጊዜ ባንተና በነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሽግን ግርዶሽ አድርገናል። እንዳያውቁትም በልቦቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን፤ ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርአን ባወሳኸው ጊዜ የሚሸሹሆነው በጀርቦቻቸው ላይ ይዞራሉ።" (ሱረቱል ኢስራእ 46)፡፡
"በል፦ እርሱ አላህ አንድ ነው። አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለርሱም አንድም ብጤ የለውም።" (ሱረቱል ኢኽላስ 1-4)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder
🌎 ሒዳያ የመወያያ መድረክ (በቴሌግራም) 📚
🍒 የሀይማኖታዊ ንፅፅር ትምህርቶች ይተላለፉበታል
🍒 በእስልምና ዙሪያ ያለዎትን ማንኛውም ጥያቄ በማቅረብ በንፅፅር ኡስታዞች ምላሽ ያገኙበታል።
🍒 እንዲሁም ከሌላ እምነት ተከታይ መምህራን ጋር የሚደረጉ ክርክሮችን ይከታተሉበታል።
https://tttttt.me/joinchat/Ez5a1EF-_IRPsLLoe6dFPg

የአላህ ስሞችና ባሕሪያት
በ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8 "
"አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8
3. "አል-ሐይ" (ፍጹም ሕያው)
ሀ.ትርጉም፡- "አል-ሐይ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፍጹም ሕያው ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በራሱ ሕያው የሆነ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐይ" ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታ አላህ ለሕያውነቱ ጅማሬና ፍጻሜ የሌለው ጥንታዊና ዘላለማዊ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ሞት የማይከተለው፡ እክል የማይገጥመው ጌታ በመሆኑ "አል-ሐይ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡- "አል-ሐይ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አምስት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ " سورة آل عمران 2
"አላህ ከሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም (እሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 2)፡፡
" وَعَنَتِ الْوُجُوهُ لِلْحَيِّ الْقَيُّومِ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا " سورة طه 111
"ፊቶችም ሁሉ፣ ሕያው፣ አስተናባሪ ለሆነው (አላህ )ተዋረዱ፤ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።" (ሱረቱ ጣሀ 111)፡፡
" هُوَ الْحَيُّ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ فَادْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة غافر 65
"እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ፣ ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፣ የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት።" (ሱረቱ ጋፊር 65)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. በራሱ ሕያው መሆኑን፡- አምላካችን አላህ በዛቱ (በህልውናው) ሕያው የሆነ አምላክ ነው፡፡ የሱ ሕያውነት ከሌላ አካል ወይም ምንጭ የተገኘ አይደለም፡፡ ጅማሬ የሌለው ሕያው አምላክ ነው፡-

"ፊቶችም ሁሉ፣ ሕያው፣ አስተናባሪ ለሆነው (አላህ) ተዋረዱ፤ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።" (ሱረቱ ጣሀ 111)፡፡
ከርሱ ውጭ ያለው ፍጥረት ግን ሕያውነቱ የተፈጠረ የሆነ፡ ከሌላ ምንጭ (ከአላህ) የተገኘ፡ ከጊዜ በኋላ የመጣ ጥንታዊነት የሌለው ሕይወት ነው፡-
" الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ " سورة الملك 2
"ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ፣ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፤ እርሱም አሸናፊው መሐሪው ነው።" (ሱረቱል ሙልክ 2)፡፡
2. ዘላለማዊ መሆኑ፡- የጌታ አላህ ሕያውነት ፍጹም ዘላለማዊ ነው፡፡ በሞት አይቋረጥም፡፡ ማብቂያም የለውም፡፡ ሁልጊዜም "አል-ሐይ" ነው፡-
" وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ وَكَفَى بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا " سورة الفرقان 58
"በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፤ ከማመስገንም ጋር አጥራው፤ በባሮቹ ኀጢአቶችም ውስጠ ዐዋቂ በርሱ በቃ።" (ሱረቱል ፉርቃን 58)፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- "የአላህ መልክተኛ ዱዓእ ሲያደርጉ ‹‹አላህ ሆይ! ላንተ ታዘዝኩ፣ ባንተም አመንኩ፣ ባንተ ላይም ተመካሁ፣ ወዳንተም ተመለስኩ፣ ባንተም (ዲን) ተከራከርኩ፣ አላህ ሆይ! ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለምና (በኃጢአቴ ሰበብ) እንዳታሳስተኝ በእልቅናህ እጠበቃለሁ፣ #አንተ_የማትሞት_ህያው_ነህና፡፡ ሰዎችና ጂኒዎች ይሞታሉ›› ይሉ ነበር" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡ ከሱ ውጪ ያለው ሕያው ፍጥረት በጠቅላላ ሕያውነቱ ጊዜያዊ ነው፡፡ በሞት ይቋረጣል፡፡ ዘላለማዊነት የለውም፡-
" كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ * وَيَبْقَى وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ " سورة الرحمن 27-26
"በርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው። የልቅናና የልግሥና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል። (አይጠፋም)።" (ሱረቱ-ራሕማን 26-27)፡፡
" وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ " سورة القصص 88
"ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ" (ሱረቱል ቀሶስ 88)፡፡
" كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ وَنَبْلُوكُمْ بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ " سورة الأنبياء 35
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፤ ወደኛም ትመለሳላችሁ።" (ሱረቱል አንቢያእ 35)፡፡
3. ጉድለት የሌለበት መሆኑ:- የጌታችን ሕያውነት እንከን አልባ ነው፡፡ ጉድለት አይቀርበውም፡፡ እንደ መተኛት፣ መዘንጋት፣ ራስን መሳት የመሳሰሉት የጉድለት ምልክቶች አጠገቡ አይደርሱም፡-
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ... " سورة البقرة 255
"አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም…" (ሱረቱል በቀራህ 255)፡፡
አቢ ሙሳ አል-አሽዐሪይ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገሩን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህ አይተኛም መተኛትም ተገቢው አይደለም…" (ሙስሊም፣ አሕመድ 4/395)፡፡
" وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ " سورة إبراهيم 42
"አላህንም፤ በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው ዓይኖች በርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 42)፡፡
4. ህያው አድራጊ መሆኑን፡- ጌታ አላህ "አል-ሐይ" በመሆኑ፡ ለሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ መገኛ ሰበብ ነው፡፡ ሕያው ማድረግና መግደል የሱ ስልጣን ብቻ ነው፡፡ ከሱ ውጪ ሕይወትን ሊለግስ ወይም ሞትን ሊወስን የሚችል ሌላ አካል የለም፡-
" وَهُوَ الَّذِي أَحْيَاكُمْ

ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ إِنَّ الْإِنْسَانَ لَكَفُورٌ " سورة الحج 66
"እርሱም ያ ሕያው ያደርጋችሁ ነው፣ ከዚያም ይገድላችኃል፣ ከዚያም ሕያው ያደርጋችኃል፤ ሰው በእርግጥ በጣም ከሃዲ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 66)፡፡
" لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ يُحْيِي وَيُمِيتُ رَبُّكُمْ وَرَبُّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ ر سورة الدخان 8
"ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሕያው ያደርጋል፣ ያሞታልም፣ ጌታችሁ፣ የመጀመሪያ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።" (ሱረቱ-ዱኻን 8)፡፡
" لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الحديد 2
"የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።" (ሱረቱል ሐዲድ 2)፡፡
" اللَّهُ الَّذِي خَلَقَكُمْ ثُمَّ رَزَقَكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ هَلْ مِنْ شُرَكَائِكُمْ مَنْ يَفْعَلُ مِنْ ذَلِكُمْ مِنْ شَيْءٍ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الروم 40
"አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚያሞታችሁ፥ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው፤ ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ ከዚኻችሁ አንዳችን የሚሠራ አልለን? ለአላህ ጥራት ይገባው፤ (በርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ።" (ሱረቱ-ሩም 40)፡፡
5. ሙታንንም ህያው አድራጊ መሆኑን፡- ጌታ አላህ "አል-ሐይ" የሆነ ጌታ በመሆኑ፡ ፍጡራንንም ከመቃብራቸው ዳግም ነፍስን በመዝራት ሕያው አድርጎ ይቀሰቅሳቸዋል፡-
" أَمِ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءَ فَاللَّهُ هُوَ الْوَلِيُّ وَهُوَ يُحْيِ الْمَوْتَى وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الشورى 9
"ከርሱ ሌላ ረዳቶችን ያዙን? (ረዳቶች አይደሉም)።አላህም ረዳት እርሱ ብቻ ነው።እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።" (ሱረቱ-ሹራ 9)፡፡ " أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَى أَنْ يُحْيِيَ الْمَوْتَى بَلَى إِنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الأحقاف 33
"ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ እነርሱም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መሆኑን አላስተዋሉምን? (በማስነሳት) ቻይ ነው እነርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና" (ሱረቱል አሕቃፍ 33)፡፡
"أَيَحْسَبُ الْإِنْسَانُ أَنْ يُتْرَكَ سُدًى * أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِنْ مَنِيٍّ يُمْنَى * ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّى * فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنْثَى * أَلَيْسَ ذَلِكَ بِقَادِرٍ عَلَى أَنْ يُحْيِيَ الْمَوْتَى " سورة القيامة 40-36
"ሰው ስድ ሆኖ መትተውን ይጠረጥራልን? የሚፈስስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? ከዚያም የረጋ ደም ሆነ፤ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፤ አስተካከለውም። ከርሱም ሁለት ዓይነቶችን፣ ወንድና ሴትን አደረገ። ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?" (ሱረቱል ቂያማህ 36-40)፡፡

6. ምድርንም ሕያው አድራጊ መሆኑን፡- ፈጣሪ አምላካችን አላህ በባሕሪው "አል-ሐይ" በመሆኑ፡ ምድርንም ከሞተች በኋላ(አረንጓዴዎቿ ረግፈው፡ ተሰነጣጥቃ) በዝናብ አማካይነት ሕያው የሚያደርጋት እርሱ ብቻ ነው፡-
" فَانْظُرْ إِلَى آثَارِ رَحْمَتِ اللَّهِ كَيْفَ يُحْيِ الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا إِنَّ ذَلِكَ لَمُحْيِ الْمَوْتَى وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الروم 50
"ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ሕያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ፈለጎች ተመልከት፤ ይህ (አድራጊ) ሙታንንም በእርግጥ ሕያው አድራጊ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።" (ሱረቱ-ሩም 50)፡፡
"اعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يُحْيِ الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ " سورة الحديد 17
"አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው የሚያደርጋት መኾኑን ዕወቁ፤ ታውቁ ዘንድ አንቀጾችን ለናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ።" (ሱረቱል ሐዲድ 17)፡፡
" وَمِنْ آيَاتِهِ أَنَّكَ تَرَى الْأَرْضَ خَاشِعَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ إِنَّ الَّذِي أَحْيَاهَا لَمُحْيِ الْمَوْتَى إِنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة فصلت 39
"አንተ ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው፤ በርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ (በቡቃያዎችዋ) ትላወሳለች፤ ትነፋለችም፤ ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንን ሕያው አድራጊ ነው፤ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።" (ሱረቱ ፉሲለት 39)፡፡

Forwarded from የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
ጊዜያዊ ጋብቻ/ሙትዓህ/ ምንድን ነው?
ምርጥ ማብራሪያ በኡስታዝ አቡ ዩስራ፤ በዚህ ሊንክ ያገኙታል
http://ethio-islamic.org/%e1%8c%8a%e1%8b%9c%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8c%8b%e1%89%a5%e1%89%bb-%e1%88%99%e1%89%b5%e1%8b%93%e1%88%85-%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8a%90%e1%8b%8d/

ዐሹራእ ደረሰ
በአቡ ሀይደር
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
#ዐሹራእ ምንድነው?
ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አሥረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡
#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው፡-
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አሥረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡
#ለምን ይጾማል?
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡
#ጥቅሙስ ምንድነው?
አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡ ሐዲሡ ዶዒፍ ነው የሚሉም አሉ ወላሁ አዕለም፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡
#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?
የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-
እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡
#መቼ እንጀምር?
የሙሐረም አስረኛው ቀን (ዐሹራእ) የፊታችን ቅዳሜ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ቅዳሜን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡
ለ. ዐርብና ቅዳሜን፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭና ሱንና ነው፡፡
ሐ. ከ ዐርብ-እሁድ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህም በላጩ ነው፡፡
መ. ቅዳሜና እሁድ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ 9ኛውን ቀን ጁምዓህ ለመፆም ያልተመቸው 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል፡፡
አላህ ይወፍቀን፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ዙል–ሒጃና አሥርቱ ቀናቶቹ!!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
እንግዲሕ በአላህ ፈቃድ ካላንደር እንደሚያሳየው ነገ የፊታችን እሁድ የዙል-ሒጃ ወር ይጀምራል፡፡ ዛሬ ዙል–ቂዕዳህ 29 ነው። ዙል-ሒጃ በእስልምና ወር አቆጣጠር አስራ ሁለተኛው (የመጨረሻው) ወር ነው፡፡ በዚህ ወር ውስጥ ካሉት 29/30 ቀናት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ቀናቶች ናቸው፡፡ መከበራቸውን ከሚያመላክቱት ውስጥ:–
ሀ. አላህ የማለባቸው መሆኑ:–
" በጎህ እምላለሁ።በዐሥር ሌሊቶችም።" (ሱረቱል ፈጅር 1-2)።
ታላቅ የሆነው ጌታችን አላህ የሚምለውም ታላቅ በሆነ ነገር ስለሆነ የቀኑን ክብደት ይገልጽልናል፡፡ እነዚህ አሥር ሌሊቶች የተባሉት የዙል-ሒጃ የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት እንደሆኑ አብዝሓኞቹ የቅዱስ ቁርኣን ተንታኞች ይገልጻሉ፡፡
ለ. እኔን አስታውሱባቸው ማለቱ:–
" ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ።" (ሱረቱል-ሐጅ 28)።
" የታወቁ ቀኖች " የተባሉት እነዚሁ አሥርቱ ቀናት እንደሆኑ ሙፈሲሮች ያስረዳሉ፡፡ ታዲያ አላህን በማንኛውም ጊዜ ማውሳትና ማወደስ ከመቻሉ ጋር በነዚህ ቀኖች አወድሱት ብሎ ቀኖቹን ለይቶ መጥቀሱ የተለየ ደረጃና ክብር እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡
ሐ. ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ መሆናቸው:–
ከጃቢር ኢብኒ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈው ሐዲሥ ረሱላችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-" ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጩ (የዙል-ሒጃ) አሥሩ ቀናት ናቸው " (ሶሒሕ አል-ጃሚዑ ሰጊር 1133)፡፡
በዚህ መሰረት እነዚህ አስርት ቀናቶች ልዩ ክብር የሚሰጣቸው ናቸው፡፡
ምን እንስራባቸው?
ዐብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም ሥራ ከዙል-ሒጃ አሥርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" ሶሓባዎችም፡- በአላህ መንገድ ጂሐድ ማድረግም (ጠላትን መታገልም) ቢሆን? ሲሉ፡ እሳቸውም፡- አዎ ጂሐድም ቢሆን! ሰውየው ከነፍሱና ከንብረቱ ጋር በዛው ሳይመለስ የቀረ ካልሆነ በስተቀር አይበልጥም " (ቡኻሪይ)።
ታዲያ ያለምንም የመግቢያ ክፍያ እንዲህ ዐይነት ታላቅ ኤግዚቢሽን ከተዘጋጀልን እኛስ ለመሳተፍ ምን ያህል ወስነናል?፡፡ ጠላታችን ሸይጣን እንዳንጠቀምበት ደፋ ቀና ማለቱ አይቀርምና እኛም አላህን ይዘን እሱን ድል በመምታት ቀኑን እንጠቀምበት፡፡ ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ውስጥ፡-
1. ሐጅና ዑምራህ:–
" ዑምራህ ቀጣዩ አመት ዑምራ እስኪመጣ ድረስ (በመሃል ለተፈጸሙ ጥቃቅን ኃጢአት) ማስተሰረያ ነው፣ ትክክለኛ ሐጅ ደግሞ ከጀነት ውጪ ክፍያ የለውም" (ቡኻሪና ሙስሊም)።
2. ጾም:–
የፈለገ ሙሉውን ዘጠኝ ቀን: ካልሆነም የቻለውን ያክል መጾም ይችላል፡፡ዐብደላ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም ስራ ከዙል-ሒጃ አስርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" በዚህ ሐዲሥ መሠረት ጾም "መልካም ሥራ" የተባለው ሐዲሥ ውስጥ ስለሚካተት በጾሙ የቻለውን ያክል መበርታት ይችላል፡፡
3. አላህን ማውሳት:–

ይህ ቅዱስ አንቀጽ አላህን በነዚህ ቀናት ማውሳት: መዘከር እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ነቢዩ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "በነዚህ ቀናት ውስጥ ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢልለሏህ)፤ተክቢር (አላሁ አክበር)፤ተሕሚድ (አል-ሐምዱ ሊላህ) ማለትን አብዙ" (አህመድ 7/224)
ዐብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁም) ወደ ገበያ በመውጣት በተክቢራ ሲያሞቁት ሰዎቹም እነሱን ተከትለው ተክቢራ ይሉ ነበር (ኢርዋዑል-ገሊል: አልባኒይ 651)።
4. ተውበት ማብዛት:–
"…ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።" (ሱረቱል አሕዛብ 31)።
5. መልካም ሥራዎችን ማብዛት:–
በኢስላም የመልካም ሥራ በሮች ብዙ ናቸው፡፡ ተቆጥረው አይዘለቁም፡፡ ከኛ የሚጠበቀው ስራው ላይ ተሳታፊ መሆን ነው፡፡ ከቤተሰብ ጀምረን እሰከ ሩቅ ሰው ድረስ አቅማችን የቻለውን ያህል በመርዳት ወደ አላህ እንቃረብ፡፡
6. በዒባዳህ መጠናከር:–
ከፈርድ ሶላት ቀጥሎ ያሉትን ሱንና ሶላቶችን ማብዛት፤ቁርኣንን ማንበብና ማዳመጥ፡፡
7. ከሐራም መቆጠብ:–
ከላይ የተጠቀሱት መልካም ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የአላህን ተውፊቅ ያላገኘ ሰው ቢያንስ ከሱ እጅና ምላስ ሌሎች ሰላም እንዲሆኑ እራሱን ማቀብ፡፡እሱም ትልቅ ተውፊቅ ነውና፡፡
አላህ ተጠቃሚ ያርገን
#የኡድሑይያህ እርድ
1/ ኡድሑይያህ ማለት:– በዙል ሒጃህ ወር ከአሥረኛው ቀን አንስቶ እስከ አያመ–ተሽሪቅ (አስራ ሶስተኛው ቀን ድረስ) ወደ አላህ ለመቃረብ ሲባል ከቤት እንሰሳት (ግመል፣ ከብት፣ ፍየል/በግ) አንዳቸውን በመምረጥ የማረድ ስርአት ማለት ነው።
2/ የኡድሑይያህ ስርአት በጣም ጠንካራ ሱንና ከሆኑ የአምልኮ ዘርፎች ይመደባል። የአላህ ቃልም:– "ለጌታህም ስገድ፣ በስሙም እረድ" (አል–ከውሠር 3)። ባለው መሠረት በአላህ ሥም ይታረዳል።
3/ የኡድሑይያህ የእርድ ስርአት ሱንና ነው። ዋጂብ አይደለም። የተወው ሰው በኃጢአት አይከሰስም። ሲታረድም ለአላህ ተብሎና በአላህ ሥም ነው የሚታረደው።
4/ የኡድሑይያህ የእርድ ቀናት ከዒዱ ቀን ሶላት መጠናቀቅ ጀምሮ (የውሙ–ነሕር 10ኛው ቀን ማለት ነው) እስከ አያሙ–ተሽሪቅ የመጨረሻው ቀን (11፣ 12 እና 13ኛው ቀን ፀሀይ መግባት ድረስ) የሚቆይ ይሆናል። በጥቅሉ አራት ቀናት ይኾናል ማለት ነው። 10ኛው ሶላቱል ዒድ የሚሰገድበት ቀን (የውሙ–ነሕር)፣ 11ኛው ቀን፣ 12ኛው ቀን፣ 13ኛው ቀን።
5/ በዋጋ ጠንከር ያለ፣ ስጋው በዛና ሞላ ያለ፣ ከነውር የፀዳ፣ የእርድ አይነት መግዛቱ በላጭ ይኾናል። ኡድሑይያህ የነየተውም አካል: ከእርዱ ላይ እራሱም ሊበላ፣ ቤተሰቡንም ሊያበላ፣ ዘመድና ወዳጆቹንም ሊጋብዝ፣ ለምስኪኖችም ሊያከፋፍል ይወደድለታል።
6/ የሚታረደው የእርድ አይነት ግመል ከሆነ አምስት አመት የሞላው፣ ከብት (በሬ/ላም) ከሆነ ሁለት አመት የሞላው፣ ፍየል ከሆነ አመት የሞላው፣ በግ ከኾነ ስድስት ወር ያለፈው ከኾነ ለእርድ የበቃ ይኾናል።
7/ የእርዱ አይነት እውር ወይም አንካሳ ወይም በሽተኛ ከሆነ አይበቃም። ጆሮው ወይም ጭራው የተቆረጠ፣ ጥርሶቹ በመላ የረገፉ ከኾነ ደግሞ እሱን ለእርድ ማቅረብ የተጠላ ይኾናል።
8/ የዒዱል አድሓን እርድ ለመፈጸም የነየተ የአላህ ባሪያ (ወንድም ሆነ ሴት) ወሩ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ፡- የሰውነት ጸጉሩን መላጨትም ሆነ መቀነስ፣ የእጁንም ሆነ የእግሩን

ጥፍር ማስተካከል፣ ከገላው ላይ የተወሰነ ቆዳንም ቢሆን ቆርጦ ማንሳት አይፈቀድለትም፡፡ ይህ ብይን የሚመለከተው የዒዱን እርድ በራሱ ወጪ ለማረድ የነየተውን ግለሰብ ብቻ ነው፡፡ ቤተሰቦቹን ብይኑ አይመለከታቸውም፡፡
ሰውየው በቀጥታ እራሱም አራጅ ሆነ፡ ወይም በወኪል ቢያሳርድ ኃላፊው እሱ እስከሆነ ድረስ ብይኑ ይመለከተዋል፡፡ ወኪል ሆኖ የሚያርደውን ሰው ግን ብይኑ አይመለከተውም፡፡
ኡሙ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዙል-ሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና አንዳችሁም ኡድሑያን (እርድን) ከነየተ፡ ጸጉሩንና ጥፍሩን (ከመቀነስ) ይቆጠብ" (ሙስሊም 1977)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ ‹‹ከጸጉሩና ከሰውነቱ (ቆዳው) ይቆጠብ›› ይላል፡፡
ስለዚህ ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ የዚል-ቂዕዳህ 29ኛው ቀን ስለሆነ፡ ወሩ በዚያው ሊጠናቀቅም ስለሚችል፡ የመግሪብ አዛን ከተሰማ በኋላ ያለው ምሽት የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ሆኖ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ ወሩ ሠላሳ ከሞላ ደግሞ፡ ከእሁድ መግሪብ በኋላ ወሩ የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናም ለዒዱ እርድን የነየታችሁ ወንድምና እህቶች ሆይ! ከዛሬ መግሪብ አዛን በፊት (የጸጉር፣ የጥፍርና የቆዳ) ጣጣችሁን ጨርሱ፡፡
ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር፡ እርዱን የነየተ ሰው፡ በዙል-ሒጃህ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ ጸጉሩን ወይም ጥፍሩን ቢቀንስ፡ ከፋራው ‹ካሳው› ተውበትና ኢስቲግፋር ብቻ ነው በማለት ዑለሞች ፈትዋ ሰጥተዋል (ኢብኑ ቁዳማህ፡ አል-ሙግኒይ 9/346)፡፡
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder
ሰውየው በቀጥታ እራሱም አራጅ ሆነ፡ ወይም በወኪል ቢያሳርድ ኃላፊው እሱ እስከሆነ ድረስ ብይኑ ይመለከተዋል፡፡ ወኪል ሆኖ የሚያርደውን ሰው ግን ብይኑ አይመለከተውም፡፡
ኡሙ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዙል-ሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና አንዳችሁም ኡድሑያን (እርድን) ከነየተ፡ ጸጉሩንና ጥፍሩን (ከመቀነስ) ይቆጠብ" (ሙስሊም 1977)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ ‹‹ከጸጉሩና ከሰውነቱ (ቆዳው) ይቆጠብ›› ይላል፡፡
ስለዚህ ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ የዚል-ቂዕዳህ 29ኛው ቀን ስለሆነ፡ ወሩ በዚያው ሊጠናቀቅም ስለሚችል፡ የመግሪብ አዛን ከተሰማ በኋላ ያለው ምሽት የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ሆኖ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ ወሩ ሠላሳ ከሞላ ደግሞ፡ ከእሁድ መግሪብ በኋላ ወሩ የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናም ለዒዱ እርድን የነየታችሁ ወንድምና እህቶች ሆይ! ከዛሬ መግሪብ አዛን በፊት (የጸጉር፣ የጥፍርና የቆዳ) ጣጣችሁን ጨርሱ፡፡
ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር፡ እርዱን የነየተ ሰው፡ በዙል-ሒጃህ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ ጸጉሩን ወይም ጥፍሩን ቢቀንስ፡ ከፋራው ‹ካሳው› ተውበትና ኢስቲግፋር ብቻ ነው በማለት ዑለሞች ፈትዋ ሰጥተዋል (ኢብኑ ቁዳማህ፡ አል-ሙግኒይ 9/346)፡፡
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
6 "አል-ዐሊም" " (ሁሉን ዐዋቂ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
ከፈጣሪ አምላካችን አላህ መለኮታዊ ባሕሪያት መካከል አንዱ ‹‹ሁሉን ዐዋቂነት›› ነው፡፡ ከጌታ አላህ ስሞች አንዱ ‹‹አል-ዐሊም›› የሚለው ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ ትርጉሙም፡- ሁሉን ዐዋቂ ማለት ነው፡፡ አላህ ከዚህ በፊት የተፈጸመና የሆነን ነገር፣ አሁን እየተፈጸመና እየሆነ ያለን ነገር፣ ገና ያልተፈጸመና ወደፊት ሊመጣ ያለን ነገር ሁሉ ያውቃል፡፡ ያም ብቻ አይደለም፡፡ የማይሆን ነገር ራሱ የመሆን ዕድል ቢሰጠው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ለዕውቀቱ ምንም ገደብ የለውም፡፡
ጌታ አላህ ከርሱ የሚሸሸግና የሚሰወር አንዳችም አይነት እንቅስቃሴ ስለሌለ "አል-ዐሊም" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በደረቶቻችን ውስጥ በልብ ያሰብነውን፡ በአንደበታችን የምንገልጸውንና በስራ የምንተገብረውን ገና ከመከሰቱ በፊት ቀድሞ ስለሚያውቀው "አል-ዐሊም" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በዕውቀቱ ፍጡራንን በመላ ያካበበ በመሆኑ "አል-ዐሊም" ይባላል፡፡
ሰዎች በዚህ ምድር ላይ በተሰጣቸው ዕውቀት "ዐሊም" ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ (ሱረቱ ዩሱፍ 55.68፣ ፋጢር 28) ፡፡ ነገር ግን የጌታችን አላህ ዕውቀት ፈጽሞ ከፍጡራኑ ጋር እንደማይገናኝ ለመረዳት የተወሰኑ ነጥቦችን እንመልከት፡-
1. ያልተገደበ መሆኑ፡- አምላካችን አላህ ዕውቀቱ ያልተገደበ፣ በጊዜና በቦታ ያልተወሰነ ሁሉንም ያካተተ ያለፈውንና የአሁኑን እንዲሁም መጪውን ነገር ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን፤ ፍጡራን ግን ዕውቀታቸው ውስን፡ በጊዜና በቦታ የተገደበ፡ እየሆነ ካለው ነገር አጠገባቸው ያለውን እንጂ የራቀውን የማያውቁ፣ መጪውን ነገር ፈጽሞ ሊያውቁ የማይችሉ ናቸው፡-
"...يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ..." سورة البقرة 255
"…(ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)…" (ሱረቱል በቀራህ 255)፡፡
" اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا " سورة الطلاق 12
"አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፤ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፤ አላህ በነገር ሁሉ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)።" (ሱረቱ-ጦላቅ 12)፡፡
" وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُمْ مِنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا " سورة الإسراء 85
"ከሩሕም ይጠይቁሃል፤ ሩሕ ከጌታዬ ነገር (በዕውቀቱ የተለየበት) ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።" (ሱረቱል ኢስራእ 85)፡፡
2. መሐይምነት ያልቀደመው መሆኑ፡- አምላካችን አላህ በባሕሪው ጥንትም ዘላለምም ዐዋቂ ጌታ ነው፡፡ ለህልውናው ጅማሬ እንደሌለው እንዲሁ ለዕውቀቱም መነሻ የለውም፡፡ የሱ ዐዋቂነት ካለማወቅ በኋላ የመጣ ሳይሆን ከራሱ ባሕሪይ ጋር አብሮት የነበረ ነው፡፡ የፍጡራን ዕውቀት ግን መነሻቸው ጅህልና ነው፡፡ ማንኛውንም ነገር የምናውቀውና የምንረዳው ካለማወቅ በኋላ ነው፡፡ ዐዋቂ ሆኖ የሚፈጠር የለም፡-
" وَاللَّهُ أَخْرَجَكُمْ مِنْ بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ " سورة النحل 78
"አላህም ከናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፤ ታመስግኑም ዘንድ ለናንተ መስሚያን፣ ማያዎችንም፣ ልቦችንም አደረገላችሁ።" (ሱረቱ-ነሕል 78)፡፡
" الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ * عَلَّمَ الْإِنْسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ " سورة العلق 5-4
"ያ በብዕር ያስተማረ፤ሰውን ያልወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን።" (ሱረቱል ዐለቅ 4-5)፡፡
3. የማይቀያየር መሆኑ፡- ጌታ አላህ ዕውቀቱ ሁሉን ያካበበና መነሻም የሌለው ነው ብለናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ የማይቀያየር ነው እንላለን፡፡ ማለትም፡- መርሳትና መዘንጋት፣ የዕውቀት መጨመርና መቀነስ የመሳሰሉት የመለዋወጥ ባሕሪያት እሱ ዘንድ አይጠጉም፡፡ ፍጡራን ግን ዕውቀታቸው ተለዋዋጭ ነው፡፡ ያውቁት ከነበረው ብዙውን ይረሳሉ፡፡ ሌላ አዳዲስ ዕውቀት ይቀስማሉ፡፡ ወደ እርጅና ዕድሜ ሲሄዱ ደግሞ ምንም ወደ-አለማወቅ ይመለሳሉ፡-
" وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَلِكَ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا " سورة مريم 64
"(ጂብሪል፤ አለ) በጌታህም ትእዛዝ እንጂ አንወርድም፤ በፊታችን ያለው በኋላችንም ያለዉ፣ በዚህም መካከል ያለዉ ሁሉ የርሱ ነው፤ ጌታህም ረሺ አይደለም።" (ሱረቱ መርየም 65)፡፡
" قَالَ فَمَا بَالُ الْقُرُونِ الْأُولَى * قَالَ عِلْمُهَا عِنْدَ رَبِّي فِي كِتَابٍ لَا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنْسَى " سورة طه 52-51
"(ፈርዖንም) የመጀመሪያይቱ ዘመናት ሕዝቦች ሁኔታ ምንድን ነው? አለ። (ሙሳም) ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሃፍ የተመዘገበ ነው፤ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም አለው።" (ሱረቱ ጣሀ 51-52)፡፡
"...وَمِنْكُمْ مَنْ يُتَوَفَّى وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَى أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنْ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْئًا..." سورة الحج 5
"…ከናንተም የሚሞት ሰው አለ፤ ከናንተም ከዕውቀት በኋላ፣ ምንንም እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ…" (ሱረቱል ሐጅ 5)፡፡
4. እሱ አስተማሪ እንጂ ተማሪ አለመሆኑ፡- ጌታ አላህ በራሱ የተብቃቃ የዕውቀት ሁሉ ምንጭና አስተማሪ ነው እንጂ ከፍጡራኑ የሚማር ዕውቀትን የሚቀስም ጌታ አይደለም፡፡ እኛ ግን በራሳችን ያልተብቃቃን አስተማሪ የሚያስተምረን፡ መሪ የሚያስፈልገን ተመሪዎች እንጂ ዐዋቂዎች አይደለንም፡-
" الرَّحْمَنُ * عَلَّمَ الْقُرْآنَ * خَلَقَ الْإِنْسَانَ * عَلَّمَهُ الْبَيَانَ " سورة الرحمن 3-1
"አል-ረሕማን፤ቁርአንን አስተማረ። ሰውን ፈጠረ። መናገርን አስተማረው።" (ሱረቱ-ራሕማን 1-3)፡፡
"...وَأَنْزَلَ اللَّهُ ع

َلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُنْ تَعْلَمُ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا " سورة النساء 113
"…አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፤ የማታውቀዉንም ሁሉ አስተማረህ። የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 113)፡፡
" قُلْ أَتُعَلِّمُونَ اللَّهَ بِدِينِكُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ " سورة الحجرات 16
"አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ ሲኾን አላህን በሃይማኖታችሁ ታስታውቁታላችሁን? በላቸው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።" (ሱረቱል ሑጁራት 16)፡፡
" وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُوحِي إِلَيْهِمْ فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِنْ كُنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ " سورة النحل 43
"ከአንተም በፊት ወደነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤ የማታውቁም ብትሆኑ የዕውቀትን በለቤቶች ጠይቁ።" (ሱረቱ-ነሕል 43)፡፡ ለ. አመጣጡ፡- "አል-ዐሊም" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 188 (አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት) ጊዜ ሲጠቀስ "አል-ዐልላም" የሚለው መለኮታዊ ስም ደግሞ አራት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለአብነት ያህል፡-
" قَالُوا سُبْحَانَكَ لَا عِلْمَ لَنَا إِلَّا مَا عَلَّمْتَنَا إِنَّكَ أَنْتَ الْعَلِيمُ الْحَكِيمُ " سورة البقرة 32
«ጥራት ይገባህ፤ ከአስተማርከን ነገር በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም፡፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (አሉ)፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 32)፡፡
" إِذْ قَالَتِ امْرَأَتُ عِمْرَانَ رَبِّ إِنِّي نَذَرْتُ لَكَ مَا فِي بَطْنِي مُحَرَّرًا فَتَقَبَّلْ مِنِّي إِنَّكَ أَنْتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ " سورة آل عمران 35
"የዒምራን ባለቤት (ሐና)- ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ዉስጥ ያለዉን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲሆን ለአንተ ተሳልኩ፤ ከኔም ተቀበል፤ አንተ ሰሚዉ ዐዋቂዉ ነህና ባለች ጊዜ (አስታውስ)" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 35)፡፡
"يَوْمَ يَجْمَعُ اللَّهُ الرُّسُلَ فَيَقُولُ مَاذَا أُجِبْتُمْ قَالُوا لَا عِلْمَ لَنَا إِنَّكَ أَنْتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ " سورة المائدة 109
"አላህ መልክተኞቹን የሚሰበስብበትንና ምን መልስ ተሰጣችሁ የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፤ ለኛ ምንም ዕውቀት የለንም አንተ ሩቆችን በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህ ይላሉ።" (ሱረቱል ማኢዳህ 109)፡፡
" أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَاهُمْ وَأَنَّ اللَّهَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ " سورة التوبة 78
"አላህ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የሚያውቅ መሆኑን አላህም ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ መሆኑን አያዉቁምን" (ሱረቱ-ተውባህ 78)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት
1. የሩቅን ዐዋቂ እሱ ብቻ መሆኑ፡- ከህዋስ የራቀ ነገር በጠቅላላ ‹‹ገይብ›› ይባላል፡፡ በሌላ አገላለጽ ያለፈው፣የአሁኑና መጪው ድርጊት በጠቅላላ በአላህ ዕውቀት ስር ነው፡፡ የሩቅን በማወቅ ጌታችን ብቸኛ ነው፡-
" وَعِنْدَهُ مَفَاتِحُ الْغَيْبِ لَا يَعْلَمُهَا إِلَّا هُوَ وَيَعْلَمُ مَا فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَمَا تَسْقُطُ مِنْ وَرَقَةٍ إِلَّا يَعْلَمُهَا وَلَا حَبَّةٍ فِي ظُلُمَاتِ الْأَرْضِ وَلَا رَطْبٍ وَلَا يَابِسٍ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُبِينٍ " سورة الأنعام 59
"የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡ በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢኾን እንጅ፡፡ ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በኾነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢኾን እንጅ፡፡" (ሱረቱል አንዓም 59)፡፡
"قُلْ لَا يَعْلَمُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ " سورة النمل 65
"በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅ ምስጢር ማንም አያውቅም፤ ግን አላህ (ያውቀዋል)፤ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም በላቸው።" (ሱረቱ-ነምል 65)፡፡
2. ለባሪያዎቹ እንደሚያሳውቅ፡- ጌታ አላህ የሩቁን ዐዋቂ እሱ ብቻ ስለሆነ ከመልክተኞቹ ለወደደውና ለመረጠው የተወሰነ ነገር ያሳውቃቸዋል፡፡ ይህም ነቢይነታቸው እንዲረጋገጥና አማኞችም በእምነታቸው እንዲጸኑ ነው፡-
" مَا كَانَ اللَّهُ لِيَذَرَ الْمُؤْمِنِينَ عَلَى مَا أَنْتُمْ عَلَيْهِ حَتَّى يَمِيزَ الْخَبِيثَ مِنَ الطَّيِّبِ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُطْلِعَكُمْ عَلَى الْغَيْبِ وَلَكِنَّ اللَّهَ يَجْتَبِي مِنْ رُسُلِهِ مَنْ يَشَاءُ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَإِنْ تُؤْمِنُوا وَتَتَّقُوا فَلَكُمْ أَجْرٌ عَظِيمٌ " سورة آل عمران 179
"አላህ መጥፎዉን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ ምእምናንን እናንተ በርሱ ላይ ባላችሁበት (ሁኔታ) ላይ የሚተዉ አይደለም፤ አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም፤ ግን አላህ ከመልክተኞቹ የሚሻዉን ይመርጣል፤ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ። ብታምኑና ብትጠነቀቁም ለናንተ ታላቅ ምንዳ አላችሁ።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 179)፡፡
" عَالِمُ الْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَى غَيْبِهِ أَحَدًا * إِلَّا مَنِ ارْتَضَى مِنْ رَسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا " سورة الجن 27-26
"(እርሱ) ሩቁን ሚስጢር ዐዋቂ ነው፣ በሚስጢሩ ላይ አንድንም አያሳውቅም። ከመልክተኛ ለወደደው ቢሆን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)፤ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል።" (ሱረቱል ጂን 26-27)፡፡
3. እኛም መለመን እንዳለብን፡- ዕውቀትን መጠየቅ ያለብን ከዐዋቂ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ከዐዋቂዎች ሁሉ በላይ ፍጹም ዐዋቂ ደግሞ አላህ ብቻ ስለሆነ እሱ የሚጠቅመንን ዕውቀትን ይጨምርልን ዘንድ መለመን ይገባናል ማለት ነው፡-
"فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِنْ قَبْلِ أَنْ يُقْضَى إِلَيْكَ وَحْيُهُ وَقُلْ رَبِّ زِدْنِي عِلْمًا " سورة طه 114
"እውነተኛው ንጉስ አላህም(ከሃዲዎች ከሚሉት)ላቀ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፤ ጌታ