የአላህ ስሞችና ባሕሪያት
በ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى " سورة طه 8 "
"አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም ለርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት።" ሱረቱ ጣሃ 8
3. "አል-ሐይ" (ፍጹም ሕያው)
ሀ.ትርጉም፡- "አል-ሐይ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፍጹም ሕያው ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በራሱ ሕያው የሆነ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐይ" ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታ አላህ ለሕያውነቱ ጅማሬና ፍጻሜ የሌለው ጥንታዊና ዘላለማዊ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ሞት የማይከተለው፡ እክል የማይገጥመው ጌታ በመሆኑ "አል-ሐይ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡- "አል-ሐይ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አምስት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ " سورة آل عمران 2
"አላህ ከሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም (እሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 2)፡፡
" وَعَنَتِ الْوُجُوهُ لِلْحَيِّ الْقَيُّومِ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا " سورة طه 111
"ፊቶችም ሁሉ፣ ሕያው፣ አስተናባሪ ለሆነው (አላህ )ተዋረዱ፤ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።" (ሱረቱ ጣሀ 111)፡፡
" هُوَ الْحَيُّ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ فَادْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة غافر 65
"እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ፣ ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፣ የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት።" (ሱረቱ ጋፊር 65)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. በራሱ ሕያው መሆኑን፡- አምላካችን አላህ በዛቱ (በህልውናው) ሕያው የሆነ አምላክ ነው፡፡ የሱ ሕያውነት ከሌላ አካል ወይም ምንጭ የተገኘ አይደለም፡፡ ጅማሬ የሌለው ሕያው አምላክ ነው፡-

"ፊቶችም ሁሉ፣ ሕያው፣ አስተናባሪ ለሆነው (አላህ) ተዋረዱ፤ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።" (ሱረቱ ጣሀ 111)፡፡
ከርሱ ውጭ ያለው ፍጥረት ግን ሕያውነቱ የተፈጠረ የሆነ፡ ከሌላ ምንጭ (ከአላህ) የተገኘ፡ ከጊዜ በኋላ የመጣ ጥንታዊነት የሌለው ሕይወት ነው፡-
" الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ " سورة الملك 2
"ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ፣ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፤ እርሱም አሸናፊው መሐሪው ነው።" (ሱረቱል ሙልክ 2)፡፡
2. ዘላለማዊ መሆኑ፡- የጌታ አላህ ሕያውነት ፍጹም ዘላለማዊ ነው፡፡ በሞት አይቋረጥም፡፡ ማብቂያም የለውም፡፡ ሁልጊዜም "አል-ሐይ" ነው፡-
" وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ وَكَفَى بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا " سورة الفرقان 58
"በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፤ ከማመስገንም ጋር አጥራው፤ በባሮቹ ኀጢአቶችም ውስጠ ዐዋቂ በርሱ በቃ።" (ሱረቱል ፉርቃን 58)፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- "የአላህ መልክተኛ ዱዓእ ሲያደርጉ ‹‹አላህ ሆይ! ላንተ ታዘዝኩ፣ ባንተም አመንኩ፣ ባንተ ላይም ተመካሁ፣ ወዳንተም ተመለስኩ፣ ባንተም (ዲን) ተከራከርኩ፣ አላህ ሆይ! ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለምና (በኃጢአቴ ሰበብ) እንዳታሳስተኝ በእልቅናህ እጠበቃለሁ፣ #አንተ_የማትሞት_ህያው_ነህና፡፡ ሰዎችና ጂኒዎች ይሞታሉ›› ይሉ ነበር" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡ ከሱ ውጪ ያለው ሕያው ፍጥረት በጠቅላላ ሕያውነቱ ጊዜያዊ ነው፡፡ በሞት ይቋረጣል፡፡ ዘላለማዊነት የለውም፡-
" كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ * وَيَبْقَى وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ " سورة الرحمن 27-26
"በርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው። የልቅናና የልግሥና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል። (አይጠፋም)።" (ሱረቱ-ራሕማን 26-27)፡፡
" وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ " سورة القصص 88
"ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ" (ሱረቱል ቀሶስ 88)፡፡
" كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ وَنَبْلُوكُمْ بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ " سورة الأنبياء 35
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፤ ወደኛም ትመለሳላችሁ።" (ሱረቱል አንቢያእ 35)፡፡
3. ጉድለት የሌለበት መሆኑ:- የጌታችን ሕያውነት እንከን አልባ ነው፡፡ ጉድለት አይቀርበውም፡፡ እንደ መተኛት፣ መዘንጋት፣ ራስን መሳት የመሳሰሉት የጉድለት ምልክቶች አጠገቡ አይደርሱም፡-
" اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ... " سورة البقرة 255
"አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም…" (ሱረቱል በቀራህ 255)፡፡
አቢ ሙሳ አል-አሽዐሪይ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገሩን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህ አይተኛም መተኛትም ተገቢው አይደለም…" (ሙስሊም፣ አሕመድ 4/395)፡፡
" وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ " سورة إبراهيم 42
"አላህንም፤ በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው ዓይኖች በርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 42)፡፡
4. ህያው አድራጊ መሆኑን፡- ጌታ አላህ "አል-ሐይ" በመሆኑ፡ ለሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ መገኛ ሰበብ ነው፡፡ ሕያው ማድረግና መግደል የሱ ስልጣን ብቻ ነው፡፡ ከሱ ውጪ ሕይወትን ሊለግስ ወይም ሞትን ሊወስን የሚችል ሌላ አካል የለም፡-
" وَهُوَ الَّذِي أَحْيَاكُمْ