የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
1. በዚህ መልካም ስራቸው ወደ አላህ በመቃረብ ከቸርነት ማዕዱ (ጀነትን) እንዲያቋድሳቸውና
2. በምድራዊ ህይወታቸው ላጠፉት ጥፋት ምሕረቱን እንዲለግሳቸው በመሻት ነው፡፡
"إِنَّ الَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنْفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَارَةً لَنْ تَبُورَ * لِيُوَفِّيَهُمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدَهُمْ مِنْ فَضْلِهِ إِنَّهُ غَفُورٌ شَكُورٌ " سورة فاطر 30-29
"እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ, ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ፣ በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ። ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው፣ ከችሮታቸውም ሊጨምርላቸው፣ (ተስፋ ያደርጋሉ)፤ እርሱ በጣም መሐሪ አመስጋኝ ነውና።" (ሱረቱ ፋጢር 29-30)፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
-"አል-ገፉር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 91 ጊዜ ተጠቅሷል፡-
"تَكَادُ السَّمَاوَاتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْ فَوْقِهِنَّ وَالْمَلَائِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِمَنْ فِي الْأَرْضِ أَلَا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ " سورة الشورى 5
"(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፤ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፤ ንቁ አላህ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነው።" (ሱረቱ-ሹራ 5)፡፡
"إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ * إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ * وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ " سورة البروج 14-12
"የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው። እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም። እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው።" (ሱረቱል ቡሩጅ 12-14)፡፡
-"አል-ገፍፋር" የሚለው መለኮታዊ ስም ደግሞ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 5 ጊዜ ተጠቅሷል፡-
"خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ يُكَوِّرُ اللَّيْلَ عَلَى النَّهَارِ وَيُكَوِّرُ النَّهَارَ عَلَى اللَّيْلِ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِي لِأَجَلٍ مُسَمًّى أَلَا هُوَ الْعَزِيزُ الْغَفَّارُ " سورة الزمر 5
"ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ሌሊትንም በቀን ላይ ይጠቀልላል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፤ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፤ ንቁ እርሱ አሸናፊው መሐሪው ነው።" (ሱረቱ-ዙመር 5)፡፡
"رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا الْعَزِيزُ الْغَفَّارُ " سورة ص 66
«የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡» (ሱረቱ ሷድ 66)፡፡
-"አል-ጋፊር" የሚለው መለኮታዊ ስም ደግሞ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 1 ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-
"غَافِرِ الذَّنْبِ وَقَابِلِ التَّوْبِ شَدِيدِ الْعِقَابِ ذِي الطَّوْلِ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ إِلَيْهِ الْمَصِيرُ " سورة غافر 3
"ኀጢአትን መሐሪ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣. ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከሆነው (አላህ የወረደ ነው)፤ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው።" (ሱረቱ ጋፊር 3)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. እሱ ጌታችን አላህ ፡- "አል-ገፍፋር" መሐሪ መሆኑን እና በነዚህ ስሞችም የሚጠራ አምላክ መሆኑን እንረዳለን፡-
"نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ * وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الْأَلِيمُ " سورة الحجر 50-49
"ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡ ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡" (ሱረቱል ሒጅር 49-50)፡፡
"وَإِنِّي لَغَفَّارٌ لِمَنْ تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا ثُمَّ اهْتَدَى " سورة طه 82
"እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም መልካምንም ለሰራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው፣ በእርግጥ መሐሪ ነኝ።" (ሱረቱ ጣሀ 82)፡፡
"يَا مُوسَى إِنَّهُ أَنَا اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ * وَأَلْقِ عَصَاكَ فَلَمَّا رَآهَا تَهْتَزُّ كَأَنَّهَا جَانٌّ وَلَّى مُدْبِرًا وَلَمْ يُعَقِّبْ يَا مُوسَى لَا تَخَفْ إِنِّي لَا يَخَافُ لَدَيَّ الْمُرْسَلُونَ * إِلَّا مَنْ ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسْنًا بَعْدَ سُوءٍ فَإِنِّي غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة النمل 11-9
"ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ነኝ። በትርህንም ጣል (ተባለ ጣለም)፤ እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ፊቱን ዞሮ ሸሸ፤ አልተመለሰምም፤ ሙሳ ሆይ! አትፍራ፤ እኔ መልክተኞቹ እኔ ዘንድ አይፈሩምና፤ ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሐሪ አዛኝ ነኝ፤" (ሱረቱ-ነምል 9-11)፡፡
2. ከሱ ውጭ የሚምር እንደሌለ:- ጌታችን አላህ ብቻውን "መሐሪ" ነው፡፡ ከርሱ ውጭ ማንም ኃጢአትን ሊምር የሚችል የለም፡፡
"وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَنْ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَى مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ " سورة آل عمران 135
"ለነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ፥ ወይም ነፍሶቻቸዉን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታዉሱና ለኀጢአቶቻቸዉ ምሕረትን የሚለምኑ ለሆኑት፣ ከአላህም ሌላ ኅጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፤ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያዉቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት (ተደግሳለች)።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 135)፡፡
"وَمَا يَذْكُرُونَ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ هُوَ أَهْلُ التَّقْوَى وَأَهْلُ الْمَغْفِرَةِ " سورة المدثر 56
"አላህ ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፤ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው።" (ሱረቱል ሙደሢር 56)፡፡
وعند البخاري من حديث أَبِي بَكْرٍ الصديق رضي الله عنه أنه قال للنبي صلى الله عليه وسلم: " عَلِّمْنِي دُعَاءً أَدْعُو بِهِ فِي صَلاَتِي قَالَ): قُلِ اللهمَّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي ظُلمًا كَثِيرًا وَلاَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلاَّ أَنْتَ ، فَاغْفِرْ لِي مَغْفِرَةً مِنْ عِنْدِكَ ، وَارْحَمْنِي إِنَّكَ أَنْتَ الغَفُورُ الرَّحِيمُ (
አቡ-በክር ሲዲቅ (ረዲየ
👍1
ላሁ ዐንሁ) የአላህ ነቢይን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አላቸው፡- "በሶላቴ ውስጥ ሆኜ አላህን የምለምንበት ዱዓ አስተምሩኝ፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹አላህ ሆይ! እኔ ነፍሴን በጣም ብዙ በድያታለሁ፡ ካንተ በስተቀር ወንጀልን የሚምር የለምና፡ ካንተ ዘንድ የሆነ ምሕረትን ለግሰኝ፡ አንተ መሐሪና አዛኝ ነህና እዘንልኝም›› በል አሉት" (ቡኻሪይ)፡፡
3. የትኛውንም ወንጀል የሚምር እንደሆነ:- የጌታችን ምሕረት ለፍጥረቱ በመላ ነው፡፡ እሱ የማይምረው ኃጢአት የለም፡-
"الَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ إِلَّا اللَّمَمَ إِنَّ رَبَّكَ وَاسِعُ الْمَغْفِرَةِ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنْشَأَكُمْ مِنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنْتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ فَلَا تُزَكُّوا أَنْفُسَكُمْ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اتَّقَى " سورة النجم 52
"(እነርሱ) እነዚያ የኃጢያትን ታላላቆችና አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን ትናንሾቹ (የሚማሩ ናቸው)። ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፤ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ፣ እርሱ በናንተ (ሁነታ) ዐዋቂ ነው። ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው።" (ሱረቱ-ነጅም 52)፡፡
"قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَى أَنْفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ " سورة الزمر 53
"በላቸው፦ እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነውና።" (ሱረቱ-ዙመር 53)፡፡
"وَمَنْ يَعْمَلْ سُوءًا أَوْ يَظْلِمْ نَفْسَهُ ثُمَّ يَسْتَغْفِرِ اللَّهَ يَجِدِ اللَّهَ غَفُورًا رَحِيمًا " سورة النساء 110
"መጥፎም የሚሠራ ሰው ወይንም ነፍሱን የሚበድል ከዚያም (ተጸጽቶ) አላህን ምሕረት የሚለምን አላህን መሐሪ አዛኝ ሆኖ ያገኘዋል።" (ሱረቱ-ኒሳእ 110)፡፡
4. ከለመንነው የሚምረን መሆኑን:- ሁላችንም ኃጢአተኞች ነንና ወደ አላህ ብንመለስ እሱ ይምረናል፡-
…"وَظَنَّ دَاوُودُ أَنَّمَا فَتَنَّاهُ فَاسْتَغْفَرَ رَبَّهُ وَخَرَّ رَاكِعًا وَأَنَابَ * فَغَفَرْنَا لَهُ ذَلِكَ وَإِنَّ لَهُ عِنْدَنَا لَزُلْفَى وَحُسْنَ مَآبٍ " سورة ص 25-24
"…ዳውድም የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፡፡ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፡፡ በመጸጸት ተመለሰም፡፡ይህን ነገርም ለርሱ ማርነው፡፡ ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ (ክብር) መልካም መመለሻም አለው፡፡" (ሱረቱ ሷድ 24-25)፡፡
"يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّهِ تَوْبَةً نَصُوحًا عَسَى رَبُّكُمْ أَنْ يُكَفِّرَ عَنْكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ يَوْمَ لَا يُخْزِي اللَّهُ النَّبِيَّ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ نُورُهُمْ يَسْعَى بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَتْمِمْ لَنَا نُورَنَا وَاغْفِرْ لَنَا إِنَّكَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة التحريم 8
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፤ ጌታችሁ ከናንተ ኀጢአቶቻችሁን ሊሠርይላችሁ፣ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ይከጅላልና፤ አላህ ነቢዩን እነዚያንም ከርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት ቀን ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲሆን ጌታችን ሆይ! ብርሀናችንን ሙላልን፤ ለኛ ምሕረትም አድርግልን፤ አንተ ቤገሩ ሁሉ ቻይ ነህና ይላሉ።" (ሱረቱ-ተሕሪም 8)፡፡
5. ከአቅም በላይ በሆነ ነገር አላህ መሐሪ መሆኑን፡- አላህ ያዘዘንን በአግባቡ ከተገበርን፡ የከለከለንንም ከተጠነቀቅን፡ ነገር ግን በረሐብ ምክንያት ሐላል ምግብ አጥተን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር መጥቶ ህይወትን ከሞት አደጋ ለማትረፍ ብለን ሐራም የነበሩ ምግቦችን (የአላህ ስም ያልተወሳባቸው እርዶች፣ ሳይታረዱ የሞቱ…) ብንበላ እርሱ መሐሪ መሆኑን እንረዳለን፡-
"إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنْزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة البقرة 173
"በናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የእሪያ ሥጋንም፣ በእርሱም (ማረድ) ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይኾን (ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 173)፡፡
…"فَمَنِ اضْطُرَّ فِي مَخْمَصَةٍ غَيْرَ مُتَجَانِفٍ لِإِثْمٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة المائدة 3
"…በረኃብ ወቅት ወደኃጢያት ያዘነበለ ሳይሆን (እርም የሆኑትን ለመብላት) የተገደደ ሰውም (ይብላ) አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" (ሱረቱል ማኢዳህ 3)::
"إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنْزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة النحل 115
"በናንተ ላይ እርም ያደረገው፣ በክትንና ደምን፣ የአሳማንም ሥጋ፣ ያንንም (በመታረድ ጊዜ) በርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፤ አመጠኛም ወሰን አላፊም ሳይሆን (ለመብላት) የተገደደ ሰው (ይፈቀድለታል)፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" (ሱረቱ-ነሕል 115)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
የዕምነት_ማዕዘናት_በ_By_Dai_Sadiq_Mohammed_com.mp3
53.9 MB
የዕምነት ማዕዘናት
(ሙቅተዳየቱል ኢማን ነዋቂዱል ኢማን)
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/9eS3D7

Join us➤ t.me/abuhyder
ኢስላም_ብቸኛው_መለኮታዊ_ሀይማኖት__ክፍል_01__በኡስታዝ_አቡ_ሀይደር.mp3
5.3 MB
ኢስላም ብቸኛው መለኮታዊ ኃይማኖት!
(አዲስ ሙሃደራ)
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/SRjV3E

Join us➤ t.me/abuhyder
Forwarded from ንፅፅር
@ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

የምስራች ...
.
በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የተዘጋጀው ተከታታይ ፓምፍሌት የመጀመሪያ ክፍል ተጠናቆ ህትመት ውስጥ የገባ ሲሆን በቅርቡ ይለቀቃል። ፓምፍሌቱ ሙሉ ለሙሉ በነፃ የሚበተን ሲሆን ከአዲስ አበባ ጀምሮ ክፍለ ሀገር ድረስ ተደራሽ እንዲሆን ታስቧል። በመሆኑም ፓምፍሌቱን

በንግድ ቦታችሁ ለደንበኞቻችሁ በስጦታ መልክ መስጠት የምትፈልጉ ነጋዴዎች

በመስሪያ ቤታችሁ ለወዳጅ ለዘመድ ጎደኛ መስጠት ለምትፈልጉ የመንግስት ሰራተኞች

በየቦታው እየተንቀሳቀሳችሁ ዳዕዋ የምታደርጉና ይህንን ፓምፍሌት ማደል የምትፈልጉ ዱአቶች
.
.
.
.
ፓምፍሌቱ ሲለቀቅ በምናስቀምጠው አድራሻ በመመዝገብ በነፃ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
_
Fb.com/Hidayaislamiccenter1
T.me/hidayaislam
21. "አል-ዋሲዕ" (ችሮታው ሰፊ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ዋሲዕ" ሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ችሮታው ሰፊ ማት ነው፡፡ ጌታ አላህ እዝነቱ የሰፋ ሁሉንም ባሮቹን ያካተተና ለኃጢአኞች በሙሉ የበቃ በመሆኑ "አል-ዋሲዕ" ይባላል፡፡ አምላካችን አላህ ስጦታው ሰፊ የማያልቅበት ሁሉንም ማብቃቃት የሚችል በመሆኑ "አል-ዋሲዕ" ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታ አላህ በዕውቀቱ ሙሉ የሆነ ከሱ የሚሸሸግ ምንም ነገር የሌለ በመሆኑ "አል-ዋሲዕ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ዋሲዕ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ዘጠኝ ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
"وَلِلَّهِ الْمَشْرِقُ وَالْمَغْرِبُ فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا فَثَمَّ وَجْهُ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ وَاسِعٌ عَلِيمٌ " سورة البقرة 115
"ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው (ፊቶቻችሁን) ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 115)፡፡
"وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ اللَّهَ قَدْ بَعَثَ لَكُمْ طَالُوتَ مَلِكًا قَالُوا أَنَّى يَكُونُ لَهُ الْمُلْكُ عَلَيْنَا وَنَحْنُ أَحَقُّ بِالْمُلْكِ مِنْهُ وَلَمْ يُؤْتَ سَعَةً مِنَ الْمَالِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمِ وَاللَّهُ يُؤْتِي مُلْكَهُ مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ " سورة البقرة 247
"ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «አላህ ጧሉትን (ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ» አላቸው፡፡ (እነርሱም)፡- «እኛ ከእርሱ ይልቅ በንግሥና ተገቢዎች ስንኾን ከሀብትም ስፋትን ያልተሰጠ ሲኾን ለእርሱ በኛ ላይ እንዴት ንግሥና ይኖረዋል?» አሉ፡፡ (ነቢያቸውም)፡-«አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፡፡ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት፡፡ አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 247)፡፡
"الَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ إِلَّا اللَّمَمَ إِنَّ رَبَّكَ وَاسِعُ الْمَغْفِرَةِ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنْشَأَكُمْ مِنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنْتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ فَلَا تُزَكُّوا أَنْفُسَكُمْ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اتَّقَى " سورة النجم 32
"(እነርሱ) እነዚያ የኃጢያትን ታላላቆችና አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው። ጌታህ #ምሕረተ_ሰፊ ነውና፤ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ፣ እርሱ በናንተ (ሁነታ) ዐዋቂ ነው። ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው።" (ሱረቱ-ነጅም 32)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. ምሕረቱና እዝነቱ ሰፊ መሆኑን፡- ጌታ አላህ ከቁጣው ትእግስቱ የቀደመ፣ ከቅጣቱ ምሕረቱ የሰፋ አምላክ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ ምሕረቱም ለሁሉም ባሮቹ የተዳረሰና ፍጥረቱን በሙሉ ያካበበ ነው፡-
"الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ " سورة غافر 7
"እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት፣ እነዚያም በዙሪያው ያሉት፣ በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤በርሱም ያምናሉ፤ ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ #በእዝነትና_በዕውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለነዚያ ለተጸጸቱት፣ መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፣ እያሉ ለነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ።" (ሱረቱ ጋፊር 7)፡፡
"الَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ إِلَّا اللَّمَمَ إِنَّ رَبَّكَ وَاسِعُ الْمَغْفِرَةِ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنْشَأَكُمْ مِنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنْتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ فَلَا تُزَكُّوا أَنْفُسَكُمْ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اتَّقَى " سورة النجم 32
"(እነርሱ) እነዚያ የኃጢያትን ታላላቆችና አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው። ጌታህ #ምሕረተ_ሰፊ ነውና፤ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ፣ እርሱ በናንተ (ሁነታ) ዐዋቂ ነው። ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው።" (ሱረቱ-ነጅም 32)፡፡
"وَلِلَّهِ الْمَشْرِقُ وَالْمَغْرِبُ فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا فَثَمَّ وَجْهُ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ وَاسِعٌ عَلِيمٌ " سورة البقرة 115
"ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው (ፊቶቻችሁን) ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 115)፡፡
በዚህም ምክንያት ሁላችንም ሰፊ ከሆነው ራሕመቱ ምሕረትን እናገኝ ዘንድ በመቻኮል ተስፋ ሳንቆርጥ እንለምነው፡-
"قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَى أَنْفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ " سورة الزمر 53
"በላቸው፦ እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነውና።" (ሱረቱ-ዙመር 53)፡፡
2. ዕውቀቱ የሰፋ መሆኑን፡- ጌታ አላህ በዕውቀቱ ሙሉ የሆነ አምላክ ነው፡፡ ከሱ እውቀት ሊሸሸግ የሚችል የዓለማችን ንጥረ-ነገር የለም፡፡ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በዕውቀቱ ስር የተጠቃለሉ ናቸው፡፡ ዕውቀቱ ሰፊና ሁሉን ያካተተ ነው፡-
"وَحَاجَّهُ قَوْمُهُ قَالَ أَتُحَاجُّونِّي فِي اللَّهِ وَقَدْ هَدَانِ وَلَا أَخَافُ مَا تُشْرِكُونَ بِهِ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ رَبِّي شَيْئًا وَسِعَ رَبِّي كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ " سورة الأنعام 80
"ወገኖቹም ተከራከሩት፡፡ «በአላህ (አንድነት) በእርግጥ የመራኝ ሲኾን ትከራከሩኛላችሁን በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም፡፡ ግን ጌታዬ ነገርን ቢሻ (ያገኘኛል)፡፡ ጌታዬም ነገሩን ሁሉ #ዕውቀቱ_ሰፋ፡፡ አትገነዘቡምን» አላቸው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 80)፡፡
"قَدِ افْتَرَيْنَا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِي مِلَّتِكُمْ بَعْدَ إِذْ نَجَّانَا اللَّهُ مِنْهَا وَمَا يَكُونُ لَنَا أَنْ نَعُودَ فِيهَا إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّنَا وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا افْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِالْحَقِّ وَأَنْتَ خَيْرُ الْفَاتِحِينَ " سورة الأعراف 89
"አላህ ከርሷ ካአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፤ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለኛ ወደርሷ ልንመለስ አይገባንም፤ ጌታችን #ዕውቀቱ_ሁሉን_ነገር_ሰፋ፣ በአላህ ላይ ተጠጋን፤ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፤ አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ (አለ)።" (ሱረቱል አዕራፍ 89)፡፡
"إِنَّمَا إِلَهُكُمُ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ وَسِعَ كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا " سورة طه 98
"ጌታችሁ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ የሆነው አላህ ብቻ ነው፤ ዕውቀቱ ነገርን ሁሉ አዳረሰ።" (ሱረቱ ጣሀ 98)፡፡
በዚህም ምክንያት ሁላችንም አላህ በዕውቀት ላይ ዕውቀትን እንዲጨምርልን እንማጸነው፡-
"فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِنْ قَبْلِ أَنْ يُقْضَى إِلَيْكَ وَحْيُهُ وَقُلْ رَبِّ زِدْنِي عِلْمًا " سورة طه 114
"እውነተኛው ንጉስ አላህም(ከሃዲዎች ከሚሉት)ላቀ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፤ ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ በል።" (ሱረቱ ጣሀ 114)፡፡
3. ስጦታው ሰፊ መሆኑን፡- ጌታ አላህ ብቻውን ሲሳይ ሰጪ መጋቢና የዓለሙ አስተዳዳሪ ነው፡፡ ፍጡራኑን ከፈጠራቸው በኋላ፡ ለኑሮአችሁ ራሳችሁን ቻሉ! ብሎ አልተዋቸውም፡፡ ይልቁኑ ኃላፊነቱን እራሱ በመውሰድ ሊረዝቃቸው (ሲሳይን ሊሰጥ) ቃል ገባ (ሱረቱ ሁድ 6)፡፡ ለባሪያዎቹ የፈለጉትን ያህል ቢሰጥና ቢለግስ ችሮታው የማያልቅበት የሰፊ ሪዝቅ ባለቤት ነው፡-
"وَأَنْكِحُوا الْأَيَامَى مِنْكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ إِنْ يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ " سورة النور 32
"ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፤ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻቹሁም ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን (አጋቡ)፤ ድሆች ቢሆኑ፤ አላህም ከችሮታው ያከብራቸዋል፤ አላህም #ስጦታ_ሰፊ ዓዋቂ ነው።" (ሱረቱ-ኑር 32)፡፡
"وَلَنْ تَسْتَطِيعُوا أَنْ تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ وَإِنْ تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَحِيمًا * وَإِنْ يَتَفَرَّقَا يُغْنِ اللَّهُ كُلًّا مِنْ سَعَتِهِ وَكَانَ اللَّهُ وَاسِعًا حَكِيمًا " سورة النساء 130-129
"በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም። እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዝዘንበልን ሁሉ አትዝዘንብሉ፤ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሐሪ አዛኝ ነው። ቢለያዩም አላህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል።አላህም ችሮታው ሰፊ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 129-130)፡፡
"وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ اللَّهَ قَدْ بَعَثَ لَكُمْ طَالُوتَ مَلِكًا قَالُوا أَنَّى يَكُونُ لَهُ الْمُلْكُ عَلَيْنَا وَنَحْنُ أَحَقُّ بِالْمُلْكِ مِنْهُ وَلَمْ يُؤْتَ سَعَةً مِنَ الْمَالِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمِ وَاللَّهُ يُؤْتِي مُلْكَهُ مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ " سورة البقرة 247
"ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «አላህ ጧሉትን (ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ» አላቸው፡፡ (እነርሱም)፡- «እኛ ከእርሱ ይልቅ በንግሥና ተገቢዎች ስንኾን ከሀብትም ስፋትን ያልተሰጠ ሲኾን ለእርሱ በኛ ላይ እንዴት ንግሥና ይኖረዋል?» አሉ፡፡ (ነቢያቸውም)፡-«አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፡፡ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት፡፡ አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 247)፡፡
በዚህም ሰበብ አላህ ሪዝቃችንን እንዲያሰፋልን እንለምነው፡-
"قُلْ إِنَّ رَبِّي يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَنْ يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ وَيَقْدِرُ لَهُ وَمَا أَنْفَقْتُمْ مِنْ شَيْءٍ فَهُوَ يُخْلِفُهُ وَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ " سورة السبأ 39
"፦ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ለርሱም ያጠባል፤ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፤ እርሱም ከሲሳይ ሰጭዎች ሁሉ በላጭ ነው በላቸው።" (ሱረቱ-ሰበእ 39)፡፡
4. ምድሩ ሰፊ መሆኑን፡- ችሮታው ሰፊ የሆነው አምላካችን አላህ ለባሪያዎቹ መኖሪያነት የፈጠራት ምድሩም እጅግ ሰፊ ናት፡፡ የትም ቦታ ብንሰደድ አላህን ለማምለክ የምትመች ሰፊ ግዛት ነች፡-
"إِنَّ الَّذِينَ تَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ ظَالِمِي أَنْفُسِهِمْ قَالُوا فِيمَ كُنْتُمْ قَالُوا كُنَّا مُسْتَضْعَفِينَ فِي الْأَرْضِ قَالُوا أَلَمْ تَكُنْ أَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةً فَتُهَاجِرُوا فِيهَا فَأُولَئِكَ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ وَسَاءَتْ مَصِيرًا " سورة النساء 97
"እነዚያ (ለእምነት ባለመሰደድ) ነፍሶቻቸውን በዳዮች ሆነው መላእክት (በበድር) የገደሉዋቸው፣ (መላእክት ለነርሱ) በምን ነገር ላይ ነበራችሁ? አሏቸው፤ በምድር ውስጥ ደካሞች ነበርን አሉ፤ የአላህ ምድር ትሰደዱባት ዘንድ ሰፊ አልነበረችምን? አሉዋቸው፤ እነዚያም መኖሪያቸው ገሃነም ናት፤ በመመለሻነትም ከፋች!" (ሱረቱ-ኒሳእ 97)፡፡
"يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ أَرْضِي وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ " سورة العنكبوت 56
"እላንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፤ እኔንም ብቻ ተገዙኝ።" (ሱረቱል ዐንከቡት 56)፡፡
"قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُمْ بِغَيْرِ حِسَابٍ " سورة الزمر 10
"(ጌታችሁ) እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፤ ለነዚያ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት፣ መልካም ምንዳ አላቸው። የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ፣ ተሰደዱ)፤ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሠጡት ያለ ግምት ነው፤ (ይላል) በላቸው።" (ሱረቱ-ዙመር 10)፡፡
አምላካችን አላህ ሆይ! በዱንያ የዕውቀት፡ የኢማንና የሪዝቅ ስፋትን፣ በቀብር ምቾትን፣ በአኼራ ጀነትን ወፍቀን፡፡ አልላሁምመ አሚን፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
ኢስላም_ብቸኛው_መለኮታዊ_ሀይማኖት_03_በኡስታዝ_አቡ_ሀይደር.mp3
1.7 MB
ኢስላም ብቸኛው መለኮታዊ ኃይማኖት!
(አዲስ ሙሃደራ) ክፍል 3
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/G4DApG

Join us➤ t.me/abuhyder
22. "አት-ተዋብ" (ለባሮቹ ተመላሽ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አት-ተዋብ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ተመላሽ ማለት ነው፡፡ አላሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ ለባሮቹ ተመላሽ ጌታ በመሆኑ "አት-ተዋብ" ይባላል፡፡ ጌታችን አላህ የባሮቹን ተውበት በምሕረት የሚቀበል ጌታ በመሆኑ "አት-ተዋብ" ተብሎ ይጠራል፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አት-ተዋብ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርአን ውስጥ አስራ አንድ ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
"أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ هُوَ يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَأْخُذُ الصَّدَقَاتِ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ " سورة التوبة 104
"አላህ እርሱ ከባሮቹ ንስሐን የሚቀበል፣ ምጽዋቶችንም የሚወስድ መሆኑን አላህም እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ መሆኑን አያዉቁምን?" (ሱረቱ-ተውባህ 104)፡፡
"وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ وَأَنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ حَكِيمٌ " سورة النور 10
"በናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ፤ አላህም ጸጸትን ተቀባይ ጥበበኛ ባልሆነ ኖሮ (ውሸታሙን ይገልጸው ነበር)።" (ሱረቱ-ኑር 10)፡፡
"فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا " سورة النصر 3
"ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ምሕረትንም ለምነው እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና" (ሱረቱ-ነስር 3)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምህርት፡-
1. አላህ ተመላሽ መሆኑን፡- ጌታ አላህ ኃጢአት ለሰሩ ባሪያዎቹ ተመላሽ ነው፡፡ ለጥፋታቸው ይቅርታ በማድረግ ኃጢአታቸውን ይሰርዘዋል፡፡ ከፈለገም ደግሞ ወደ ሐሰናት ይቀይረዋል፡-
"إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنْزَلْنَا مِنَ الْبَيِّنَاتِ وَالْهُدَى مِنْ بَعْدِ مَا بَيَّنَّاهُ لِلنَّاسِ فِي الْكِتَابِ أُولَئِكَ يَلْعَنُهُمُ اللَّهُ وَيَلْعَنُهُمُ اللَّاعِنُونَ * إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ " سورة البقرة 160-159
"እነዚያ ከአንቀጾችና ከቅን መምሪያ ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፉ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁ፤ እነዚያ አላህ ይረግማቸዋል፤ ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል፡፡ እነዚያ (ከመደበቅ) የተጸጸቱና (ሥራቸውን) ያሳመሩም (የደበቁትን) የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በነሱ ላይ (ጸጸታቸውን) እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 159-160)፡፡
"فَمَنْ تَابَ مِنْ بَعْدِ ظُلْمِهِ وَأَصْلَحَ فَإِنَّ اللَّهَ يَتُوبُ عَلَيْهِ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة المائدة 39
"ከመበደሉም በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ አላህ ጸጸቱን ከርሱ ይቀበለዋል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" (ሱረቱል ማኢዳህ 39)፡፡
"أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ هُوَ يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَأْخُذُ الصَّدَقَاتِ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ " سورة التوبة 104
"አላህ እርሱ ከባሮቹ ንስሐን የሚቀበል፣ ምጽዋቶችንም የሚወስድ መሆኑን አላህም እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ መሆኑን አያዉቁምን?" (ሱረቱ-ተውባህ 104)፡፡
2. እኛም በጸጸት መመለስ እንዳለብን፡- ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን፡፡ የኃጢአቱ አይነትና መጠን ይለያይ እንጂ ከስህተት የሚጸዳ አንድም ሰው የለም፡፡ ፍጹም ምሉእነት የአላህ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች በሰሩት ጥፋት አላህ ወዲያውኑ በቅጣት ቢይዛቸው ኖሮ በምድር ወለል ላይ አንድም ሰው አይኖርም ነበር፡-
"وَلَوْ يُؤَاخِذُ اللَّهُ النَّاسَ بِمَا كَسَبُوا مَا تَرَكَ عَلَى ظَهْرِهَا مِنْ دَابَّةٍ وَلَكِنْ يُؤَخِّرُهُمْ إِلَى أَجَلٍ مُسَمًّى فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِعِبَادِهِ بَصِيرًا " سورة فاطر 45
"አላህም ሰዎችን በሰሩት ኀጢያት ቢይዝ ኖሮ በወለሏ (በምድር) ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ ባልተወ ነበር፤ግን እተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል፤ ጊዜያቸውም በመታ ወቅት (በኀጢያታቸው ይቀጣቸዋል)፤ አላህ በባሮቹ ሁኔታ ተመልካች ነውና።" (ሱረቱ ፋጢር 45)፡፡
ይህ በመሆኑም ሁላችንም ጊዜው ሳያልፍ ተውበት በማድረግ ወደ አላህ እንመለስ፡-
"إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِنْ قَرِيبٍ فَأُولَئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا " سورة النساء 17
"ፀፀትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለነዚያ ኀጢአትን በስሕተት ለሚሠሩና ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው። እነዚያንም አላህ በነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል። አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 17)፡፡
"وَأَنِ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ يُمَتِّعْكُمْ مَتَاعًا حَسَنًا إِلَى أَجَلٍ مُسَمًّى وَيُؤْتِ كُلَّ ذِي فَضْلٍ فَضْلَهُ وَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ كَبِيرٍ " سورة هود 3
"ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፤ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፤ እስከ ተወሰነም ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና፤ የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል፤ ብትሸሹም እኔ በናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።" (ሱረቱ ሁድ 3)፡፡
"يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّهِ تَوْبَةً نَصُوحًا عَسَى رَبُّكُمْ أَنْ يُكَفِّرَ عَنْكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ يَوْمَ لَا يُخْزِي اللَّهُ النَّبِيَّ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ نُورُهُمْ يَسْعَى بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا أَتْمِمْ لَنَا نُورَنَا وَاغْفِرْ لَنَا إِنَّكَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة التحريم 8
"እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፤ ጌታችሁ ከናንተ ኀጢአቶቻችሁን ሊሠርይላችሁ፣ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ይከጅላልና፤ አላህ ነቢዩን እነዚያንም ከርሱ ጋር ያመኑትንበማያሳፍርበት ቀን ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲሆን ጌታችን ሆ! ብርሀናችንን ሙላልን፤ ለኛ ምሕረትም አድርግልን፤ አንተ ቤገሩ ሁሉ ቻይ ነህና ይላሉ።" (ሱረቱ-ተሕሪም 8)፡፡
3. ከተመደበው ሰዓት ውጪ ተቀባይነት እንደሌለው፡- አላህ የባሮቹን ተውበት በነፍስ-ወከፍ ጣእረ ሞት (ገርገራ) ከመግባቱ በፊት፡ በጅምላ ደግሞ ጸሐይ ከመግቢያዋ በኩል ተመልሳ እስከምትወጣ ድረስ ይቀበላል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ጣእረ-ሞት ውስጥ ገብቶ ከዱንያ ተሰናብቶ ወደ አኼራ እንደሚሸጋገር ባረጋገጠ ጊዜ ተውበት ቢገባ ዋጋ የለውም፡፡
"وَلَيْسَتِ التَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ حَتَّى إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ إِنِّي تُبْتُ الْآنَ وَلَا الَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ أُولَئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمً ر سورة النساء 18
"ጸጸትንም መቀበል ለነዚያ ኃጢያቶችን ለሚሠሩ፣ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እኔ አሁን ተጸጸትኩ ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከኃዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለችም። እነዚያ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አዘጋጅተናል።" (ሱረቱ-ኒሳእ 18)፡፡
"إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ ثُمَّ ازْدَادُوا كُفْرًا لَنْ تُقْبَلَ تَوْبَتُهُمْ وَأُولَئِكَ هُمُ الضَّالُّونَ " سورة آل عمران 90
"እነዚያ ከእምነታቸዉ በኋላ የካዱ፣ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ፣ ጸጸታቸዉ ፈጽሞ ተቀባይ የላትም፥ እነዚያም የተሳሳቱ እነርሱ ናቸዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 90)፡፡
"وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إ
ِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ وَجُنُودُهُ بَغْيًا وَعَدْوًا حَتَّى إِذَا أَدْرَكَهُ الْغَرَقُ قَالَ آمَنْتُ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا الَّذِي آمَنَتْ بِهِ بَنُو إِسْرَائِيلَ وَأَنَا مِنَ الْمُسْلِمِينَ * آلْآنَ وَقَدْ عَصَيْتَ قَبْلُ وَكُنْتَ مِنَ الْمُفْسِدِينَ " سورة يونس 91-90
"የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ፡፡ ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ)" (ሱረቱ ዩኑስ 90-91)፡፡
4. ስልጣኑ የሱ ብቻ መሆኑን፡- አላህ እንትናን ማረው፡ እንትናን ግን አትማረው ማለት በፉጹም አይቻልም፡፡ እሱ ከባሮቹ መካከል የፈለገውን ተውበቱን ሊቀበልና ሊምረው የፈለገውን ደግሞ ሊቀጣ መብቱ አለው፡-
"لَيْسَ لَكَ مِنَ الْأَمْرِ شَيْءٌ أَوْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ أَوْ يُعَذِّبَهُمْ فَإِنَّهُمْ ظَالِمُونَ " سورة آل عمران 128
"(አላህ) በነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸዉና እስኪቀጣቸዉ ድረስ፣ ላንተ ከነገሩ ምንም የለህም።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 128)፡፡
"قَاتِلُوهُمْ يُعَذِّبْهُمُ اللَّهُ بِأَيْدِيكُمْ وَيُخْزِهِمْ وَيَنْصُرْكُمْ عَلَيْهِمْ وَيَشْفِ صُدُورَ قَوْمٍ مُؤْمِنِينَ * وَيُذْهِبْ غَيْظَ قُلُوبِهِمْ وَيَتُوبُ اللَّهُ عَلَى مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ " سورة التوبة 15-14
"ተጋደሉዋቸዉ፤ አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል፤ ያዋርዳቸዋልም፤ በነሱም ላይ ይረዳችኋል፤ የምእምናን ሕዝቦችንም ልቦች ያሽራል። የልቦቻችሁንም ቁጭት ያስወግዳል፤ አላህም ከሚሻው ሰዉ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ-ተውባህ 14-15)፡፡
"لِيَجْزِيَ اللَّهُ الصَّادِقِينَ بِصِدْقِهِمْ وَيُعَذِّبَ الْمُنَافِقِينَ إِنْ شَاءَ أَوْ يَتُوبَ عَلَيْهِمْ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَحِيمًا " سورة الأحزاب 24
"አላህም እውነተኞችን በውነተኛነታቸው ሊመነዳ፣ መናፍቃንንም ቢሻ ሊቀጣ፣ ወይም (ቢመለሱ) በነሱ ላይ ጸጸታቸውን ሊቀበል፥ (ይህን አደረገ)፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" (ሱረቱል አሕዛብ 24)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
23. "አል-ሐሚድ" (ፍጹም ተመስጋኝ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ሐሚድ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፍጹም ተመስጋኝ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በህልናውም ሆነ በባሕሪው በራሱ የተብቃቃ የምሉእ ባሕሪ ባለቤት በመሆኑ "አል-ሐሚድ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ለባሮቹ ሊቆጠር የማይችልን ጸጋ በመለገስ አምሳያ የሌለው በመሆኑ "አል-ሐሚድ" ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታ አላህ ሁሌም ካመሰገኑትና ከተማጸኑት ከጸጋው የሚጨምር አምላክ በመሆኑ "አል-ሐሚድ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ሐሚድ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አስራ ሰባት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለናሙና ያህል፡-
"وَهُدُوا إِلَى الطَّيِّبِ مِنَ الْقَوْلِ وَهُدُوا إِلَى صِرَاطِ الْحَمِيدِ " سورة الحج 24
"ከንግግርም ወደ መልካሙ ተመሩ፤ ወደ ምስጉኑም መንገድ ተመሩ።" (ሱረቱል ሐጅ 24)፡፡
"وَلَقَدْ آتَيْنَا لُقْمَانَ الْحِكْمَةَ أَنِ اشْكُرْ لِلَّهِ وَمَنْ يَشْكُرْ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٌ " سورة لقمان 12
"ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፤ (አልነውም)፦ አላህን አመስግን፤ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው፤ የካደም ሰው፣ (በራሱ ላይ ነው)፤ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነውና።" (ሱረቱ ሉቅማን 12)፡፡
"وَهُوَ الَّذِي يُنَزِّلُ الْغَيْثَ مِنْ بَعْدِ مَا قَنَطُوا وَيَنْشُرُ رَحْمَتَهُ وَهُوَ الْوَلِيُّ الْحَمِيدُ " سورة الشورى 28
"እርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናምን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው፤እርሱም ረዳቱ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ-ሹራ 28)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አምላካችን አላህ ያለ-ምንም ገደብ ምስጋና የሚገባው መሆኑ፡- ዓለማቱን በጠቅላላ ብቻውን ፈጥሮ (አል-አንዓም 103)፣ ለእያንዳንዱ ነገር የሚያስፈልገውን ነገር ብቻውን ሰጥቶና አሟልቶ (ጣሀ 50)፣ አማኝ ባሪያዎቹን ደግሞ ዘላለማዊ ሕይወትን በጸጋ ጀነቶች ሊያኖራቸው ቃል ገብቶ (ዩኑስ 9) ሳለ እንዴትስ አይመስገን? ለጸጋው ገደብ እንደሌለው ሁላ ለመመስገኑም ገደብ የለውም፡፡ ማንኛውም አይነት የምስጋና መገለጫዎች ሁሉ የሚግገቡት ለሱ ነውና፡፡ የዓለማት ጌታ በመሆኑ ብቻ ምስጋና ይገባዋል፡-
"الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة الفاتحة 2
"ምስጋና ለአላህ ይገባው የአለማት ጌታ ለሆነው" (ሱረቱል ፋቲሓህ 2)፡፡
"فَقُطِعَ دَابِرُ الْقَوْمِ الَّذِينَ ظَلَمُوا وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة الأنعام 45
"የእነዚያም የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ፡፡ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይገባው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 45)፡፡
"إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ يَهْدِيهِمْ رَبُّهُمْ بِإِيمَانِهِمْ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ * دَعْوَاهُمْ فِيهَا سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَامٌ وَآخِرُ دَعْوَاهُمْ أَنِ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة يونس 10-9
"እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፡፡ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 10)፡፡
ነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ከሩኩዕ ሲነሱ እንዲህ ይሉ ነበር፡- ‹‹ረበና ወለከል-ሐምድ ሚልአ-ሰማዋቲ ወሚልአል-አርዲ ወሚልአ ማበይነሁማ ወሚልአ ማሺእተ ሚን-ሸይኢን በዕዱ››
(ጌታችን አላህ ሆይ! ሰማያትና ምድርን በመሐከላቸው ያለውንም ነገር የሞላ ምስጋና ላንተ የተገባ ነው…) (ሙስሊም)፡፡
እንዲሁም በሌሊቱ ክፍል ለሶላት ሲነሱ ፡- ‹‹አልላሁመ ለከል ሐምድ አንተ ኑሩ-ሰማዋቲ ወል-አርድ፣ ወለከል ሐምድ አንተ ቀዩሙ-ሰማዋቲ ወል-አርድ፣ ወለከል ሐምድ አንተ ረቡ-ሰማዋቲ ወል-አርድ ወመን ፊሂነ›› ይሉ ነበር፡፡
ትርጉሙም፡- (አላህ ሆይ! አንተ የሰማያትና የምድር ብርሐናቸው በመሆንህ ምስጋና ላንተ ነው!፣ አላህ ሆይ! አንተ የሰማያትና የምድር አስተናባሪቸው (ጠባቂያቸው) በመሆንህ ምስጋና ላንተ የተገባ ነው፣ አንተ የሰማያትና የምድር በመሐከላቸው ላለው ሁሉ ጌታ በመሆንህ ምስጋና ላንተ ነው›› ማለት ነው፡፡
2. አላህ የተብቃቃ በመሆኑ ምስጋና ለርሱ የተገባ ነው፡- አላህ ከዓለማት ምንም አይፈልግም፡፡ እሱ ከፍጡራኑ የተብቃቃ ጌታ ነው፡፡ ዓለም ግን ከአላህ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ሊመሰገን ይገባዋል፡-
"وَقَالَ مُوسَى إِنْ تَكْفُرُوا أَنْتُمْ وَمَنْ فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا فَإِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ حَمِيدٌ " سورة إبراهيم 8
"ሙሳም አለ፦ እናንተም በምድር ላይ ያለውም ሁሉ በመላ ብትክዱ፤ አላህ በርግጥ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 8)፡፡
"وَلَقَدْ آتَيْنَا لُقْمَانَ الْحِكْمَةَ أَنِ اشْكُرْ لِلَّهِ وَمَنْ يَشْكُرْ فَإِنَّمَا يَشْكُرُ لِنَفْسِهِ وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٌ " سورة لقمان 12
"ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፤ (አልነውም)፦ አላህን አመስግን፤ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው፤ የካደም ሰው፣ (በራሱ ላይ ነው)፤ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነውና።" (ሱረቱ ሉቅማን 12)፡፡
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة فاطر 15
"እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁልጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 15)፡፡
3. በዚህ በዱንያ ነጌም በአኼራ ምስጋና ለአላህ ብቻ የተገባ ነው፡-
"وَهُوَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَهُ الْحَمْدُ فِي الْأُولَى وَالْآخِرَةِ وَلَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ " سورة القصص 70
"እርሱም አላህ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ምስጋና በመጀመሪያይቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡" (ሱረቱል ቀሶስ 70)፡፡
"الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَلَهُ الْحَمْدُ فِي الْآخِرَةِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ " سورة سبأ 1
"ምስጋና ለዚያ በሰማያትም ያለ፣ በምድርም ያለ ሁሉ፣ የርሱ ለሆነው ለአላህ ይገባው፤ በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ለርሱ ብቻ ነው፤ እርሱም ብልሃተኛው ውስጠ ዐዋቂው ነው።" (ሱረቱ ሰበእ 1)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhayder
Join us➤ t.me/abuhyder