የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
በአላህ_ማመን_ክፍል_1_በ_By_Dai_Sadiq_Mo.m4a
12.9 MB
በአላህ ማመን ክፍል 1
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/gGro8y

Join us➤ t.me/abuhyder
በአላህ_ማመን_ክፍል_2_By_Dai_Sadiq_Moha.m4a
9.1 MB
በአላህ ማመን ክፍል 2
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/4ACq4L

Join us➤ t.me/abuhyder
24. "አል-ገኒይ" (በራሱ የተብቃቃ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ገኒይ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- በራሱ የተብቃቃ ሐብታም ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ በራሱ የተብቃቃ የምሉእ ባሕሪያት ባለቤት በመሆኑ "አል-ገኒይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ከፍጡራኑ ምንም ነገር የማይፈልግና የማያስፈልገው አምላክ በመሆኑ "አል-ገኒይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ባሪያዎቹን ከችሮታው በመለገስ የሚያብቃቃ (ሐብታም የሚያደርግ) በመሆኑ "አል-ገኒይ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ የለመኑትን ሁሉ እንደ-ፍላጎታቸው ቢሰጥ ምንም የማይጎድልበት አምላክ በመሆኑ "አል-ገኒይ" ተብሎ ይጠራል፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ገኒይ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አስራ ስምንት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-
"قَوْلٌ مَعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِنْ صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ " سورة البقرة 263
"መልካም ንግግርና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም #ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 263)፡፡
"وَرَبُّكَ الْغَنِيُّ ذُو الرَّحْمَةِ إِنْ يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَسْتَخْلِفْ مِنْ بَعْدِكُمْ مَا يَشَاءُ كَمَا أَنْشَأَكُمْ مِنْ ذُرِّيَّةِ قَوْمٍ آخَرِينَ " سورة الأنعام 133
"ጌታህም #ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው፡፡ ቢሻ ያስወግዳችኋል፤ (ያጠፋችኋል)፡፡ ከሌሎች ሕዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ከበኋላችሁ የሚሻውን ይተካል፡፡" (ሱረቱል አንዓም 133)፡፡
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة فاطر 15
"እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁልጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 15)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ ከኛ የተብቃቃ መሆኑን፡- የኛ አምልኮና ታዛዥነት ጠቀሜታው ለኛው እንጂ ለአላህ አይደለም፡፡ አላህ ስላመለክነው የሚጠቀመው ስለከዳነው የሚቀርበት ነገር የለም፡፡ ጥቅምና ጉዳቱ ለኛው ነውና፡-
"فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَنْ دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ " سورة آل عمران 97
"በዉስጡ ግልጽ የሆኑ ታምራቶች፥ የኢብራሂም መቆሚያ አለ የገባዉም ሰዉ ጸጥተኛ ይሆናል፤ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጐብኘት ግዴታ አለባቸዉ፤ የካደም ሰዉ አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 97)፡፡
"وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَلَقَدْ وَصَّيْنَا الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ وَإِيَّاكُمْ أَنِ اتَّقُوا اللَّهَ وَإِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَكَانَ اللَّهُ غَنِيًّا حَمِيدًا " سورة النساء 131
"በሰማያት ያለውና በምድርም ያለው ሁሉ የአላህ ነው። እነዚያንም ከበፊታችሁ መጽሐፍን የተሰጡትን፣ እናንተንም አላህን ፍሩ፣ በማለት በእርግጥ አዘዝን፤ ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ (አትጎዱትም)፤ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 131)፡፡
"وَقَالَ مُوسَى إِنْ تَكْفُرُوا أَنْتُمْ وَمَنْ فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا فَإِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ حَمِيدٌ " سورة إبراهيم 8
"ሙሳም አለ፦ እናንተም በምድር ላይ ያለውም ሁሉ በመላ ብትክዱ፤ አላህ በርግጥ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 8)፡፡
"وَمَنْ جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ " سورة العنكبوت 6
"የታገለ ሰውም የሚታገለው ለነፍሱ ነው፤ አላህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና።" (ሱረቱል ዐንከቡት 6)፡፡
2. ልጅ እንደማያስፈልገው፡- አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የሱ ንብረት ነው፡፡ ዘላለማዊ ሕያው ጌታ በመሆኑም የተብቃቃ ነው፡፡ የማይሞት በመሆኑም ወራሽ ልጅ አያስፈልገውም፡፡ ሁሉን ቻይ አምላክ በመሆኑም ይደክማልና ጉልበት የሚሆነው ልጅ ይኑረው አይባልም (ተዓለላሁ ዐን-ዛሊከ ዑሉወን ከቢራ)፡-
"قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا سُبْحَانَهُ هُوَ الْغَنِيُّ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ إِنْ عِنْدَكُمْ مِنْ سُلْطَانٍ بِهَذَا أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ " سورة يونس 68
"«አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ (ከሚሉት) ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን" (ሱረቱ ዩኑስ 68)፡፡
"لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة الحج 64
"በሰማያት ውስጥ ያለውና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 64)፡፡
"لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة لقمان 26
"በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው።" (ሱረቱ ሉቅማን 26)፡፡
3. ሐብትን እንደሚሰጥ፡- ጌታ አላህ በራሱ የተብቃቃ "አል-ገኒይ" እንደመሆኑ ባሮቹንም ከለመኑትና ከጸጋው ከተማጸኑት እንደሚያብቃቃቸው መረዳት ይቻላል፡-
"وَلْيَسْتَعْفِفِ الَّذِينَ لَا يَجِدُونَ نِكَاحًا حَتَّى يُغْنِيَهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ... " سورة النور 33
"እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠበቁ…" (ሱረቱ-ኑር 33)፡፡
"وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنْثَى * مِنْ نُطْفَةٍ إِذَا تُمْنَى * وَأَنَّ عَلَيْهِ النَّشْأَةَ الْأُخْرَى * وَأَنَّهُ هُوَ أَغْنَى وَأَقْنَى " سورة النجم 48-45
"እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድና ሴትን ፈጠረ። ከፍትወት ጠብታ (በማኅፀን ውስጥ) በምትፈስስ ጊዜ፤ የኋለኛይቱም ማስነሳት በርሱ ላይ ነው። እነሆ እርሱም አከበረ፤ ጥሪተኛም አደረገ።" (ሱረቱ-ነጅም 45-48)፡፡
"أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًا فَآوَى * وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَى * وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَى " سورة الضحى 8-6
"የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)።የሳትክም ሆነህ አገኘህ፤ መራህም። ድኻም ሆነህ አገኘህ፤ አከበረህም።" (ሱረቱ-ዱሓ 6-8)፡፡
4. ከሱ ውጭ ያለው ሁሉ ድኃ መሆኑን፡- እውነተኛ ሐብታም አላህ ብቻ ነው፡፡ በራሱ የተብቃቃ ጌታ በመሆኑ፡፡ የሌላው ግን አንጻራዊ ነው፡፡ የአንዱ የሐብት መጠን ከሌላው አንጻር በሚለው መስፈሪያ ነው ሐብታምና ድኃ ተብለው የሚከፋፈሉት፡፡ ሁሉም ግን አላህ ዘንድ ድኃዎች ናቸው፡፡ ከአላህ መብቃቃትና ሌላውንም ማብቃቃት ስለማይችሉ፡-
"وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَبِيًّا * إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنْكَ شَيْئًا " سورة إبراهيم 42-41
" እኛ ምድርን፣ በርሷም ላይ ያለውን ሁሉ እኛ እንወርሳለን፤ ወደኛም ይመለሳሉ። በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምንም አዉሳ፤ እርሱ በጣም እውነተኛ ነቢይ ነበርና። " (ሱረቱ መርየም 41-42)፡፡
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ " سورة فاطر 15
"እላንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁልጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 15)፡፡
አምላካችን አላህ ሆይ! አንተ በችሮታህ ካንተ ውጭ ካለው ነገር ሁሉ አብቃቃን፡፡ የሰው ፊት ከመጠበቅም አድነን አሚን፡፡ ይቀጥላል፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
25. "አል-ፈታሕ" (ፈራጅ፣ከፋች)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡- "አል-ፈታሕ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፈራጅ፣ ከፋች ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ ለምእመናን ባሮቹ የድልን በር የሚከፍትና የሚረዳ በመሆኑ "አል-ፈታሕ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ለፍጡራኑ የራሕመትን በር የሚከፍትና የሚለግስ በመሆኑ "አል-ፈታሕ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በፍጡራኑ መካከል በፍትሕ የሚዳኝና የሚፈርድ በመሆኑ "አል-ፈታሕ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡- "አል-ፈታሕ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡፡
"قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ " سورة سبأ 26
"ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፤ ከዚያም በመካከላችን በውነት #ይፈርዳል፤ እርሱም #በትክክል_ፈራጁ ዐዋቂው ነው በላቸው።" (ሱረቱ ሰበእ 26)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ "አል-ፈታሕ" በመሆኑ ለባሪያዎቹ የሚከፍተውን ሲሳይ ማንም ሊያጠፋውም ወይም ሊያጎድለው አይችልም፡-
"مَا يَفْتَحِ اللَّهُ لِلنَّاسِ مِنْ رَحْمَةٍ فَلَا مُمْسِكَ لَهَا وَمَا يُمْسِكْ فَلَا مُرْسِلَ لَهُ مِنْ بَعْدِهِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة فاطر 2
"አላህ ለሰዎች ከችሮታ #የሚከፍታት ለርሷ ምንም አጋጅ የላትም፤ የሚያግደውም ከርሱ በኋላ ለርሱ ምንም ለቃቂ የለውም፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 2)
2. አላህ "አል-ፈታሕ" በመሆኑ በባሪያዎቹ መካከል ለማንም ሳያዳላ ማንንም ሳይበድል በዚህ በዱንያ፡ የቂያም ዕለትም በፍትህ ይፈርዳል፡-
"قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ " سورة سبأ 26
"ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፤ ከዚያም በመካከላችን በውነት #ይፈርዳል፤ እርሱም #በትክክል_ፈራጁ ዐዋቂው ነው በላቸው።" (ሱረቱ ሰበእ 26)፡፡
"قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوْمِي كَذَّبُونِ * فَافْتَحْ بَيْنِي وَبَيْنَهُمْ فَتْحًا وَنَجِّنِي وَمَنْ مَعِيَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ " سورة الشعراء 118-117
"(እርሱም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ አስተባበሉኝ፡፡ «በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) #ፍርድን_ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን፡፡»" (ሱረቱ-ሹዐራእ 117-118)፡፡
"قَدِ افْتَرَيْنَا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِي مِلَّتِكُمْ بَعْدَ إِذْ نَجَّانَا اللَّهُ مِنْهَا وَمَا يَكُونُ لَنَا أَنْ نَعُودَ فِيهَا إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّنَا وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا افْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِالْحَقِّ وَأَنْتَ خَيْرُ الْفَاتِحِينَ " سورة الأعراف 89
"አላህ ከርሷ ካአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፤ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለኛ ወደርሷ ልንመለስ አይገባንም፤ ጌታችን እውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ በአላህ ላይ ተጠጋን፤ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፤ አንተም #ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ (አለ)።" (ሱረቱል አዕራፍ 89)፡፡
3. ጌታችን "አል-ፈታሕ" በመሆኑ ወደ አላህ ቤት (መስጂድ) ስንገባ የራሕመት በሮቹን እንዲከፍትልን ‹‹አልላሁመ-ኢፍተሕ-ሊ አብዋበ ፈድሊክ›› በማለት ልንለምነው ይገባል፡-
عَنْ أَبِى حُمَيْدٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم « إِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمُ الْمَسْجِدَ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ افْتَحْ لِى أَبْوَابَ رَحْمَتِكَ. وَإِذَا خَرَجَ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّى أَسْأَلُكَ مِنْ فَضْلِكَ » رواه مسلم.
አቢ ሑመይድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አንዳችሁ መስጂድ በገባ ጊዜ፡- ‹‹አላህ ሆይ! የእዝነት በሮችን (ሰበቦችን) ክፈትልኝ›› ሲወጣ ደግሞ፡- ‹‹አላህ ሆይ! ከትሩፋቶችህ እንድትለግሰኝ እለምንሀለሁ›› ይበል" (ሙስሊም 1685)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
26. "አል-ወሓብ" (ለጋሽ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ወሓብ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ለጋሽ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ ያለ ልዋጭ የሚሰጥ፣ ሳይለመንም የሚለግስ፣ ያለ-መጠንም የሚያከብር ጌታ በመሆኑ "አል-ወሓብ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡- "አል-ወሓብ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ሶስት ጊዜ ተጠቅሷል፡-
"رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ رَحْمَةً إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ " سورة آل عمران 8
"(እነሱም ይላሉ) ፦ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፤ ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለኛ ስጠን፤ አንተ በጣም ለጋስ ነህና።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 8)፡፡
"أَمْ عِنْدَهُمْ خَزَائِنُ رَحْمَةِ رَبِّكَ الْعَزِيزِ الْوَهَّابِ " سورة ص 9
"ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?" (ሱረቱ ሷድ 9)፡፡
"قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَهَبْ لِي مُلْكًا لَا يَنْبَغِي لِأَحَدٍ مِنْ بَعْدِي إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ " سورة ص 35
"«ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ማር፡፡ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህና» አለ፡፡" (ሱረቱ ሷድ 35)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አምላካችን አላህ ችሮታው ሰፊ፡ ልግስናው የላቀ ጌታ በመሆኑ ራሕመትን እንዲለግሰን መለመን እንዳለብን እንማራለን፡-
"رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ رَحْمَةً إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ " سورة آل عمران 8
"(እነሱም ይላሉ) ፦ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፤ ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለኛ ስጠን፤ አንተ በጣም ለጋስ ነህና።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 8)፡፡
2. ልጅ በማጣት የተቸገረ ሰው ያለ-መታከት አላህን እንዲለግሰው መለመን እንዳለበት እንማራለን፡፡ አላህ ለሚፈልገው ልጅን ይሰጣልና፡-
"لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ يَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ الذُّكُورَ * أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا وَيَجْعَلُ مَنْ يَشَاءُ عَقِيمًا إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ " سورة الشورى 50-49
"የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፤ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፤ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል። ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል። የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፤ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና።" (ሱረቱ-ሹራ 49-50)፡፡
"هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُ قَالَ رَبِّ هَبْ لِي مِنْ لَدُنْكَ ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً إِنَّكَ سَمِيعُ الدُّعَاءِ * فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَى مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِنَ الصَّالِحِينَ " سورة آل عمران 39-38
"እዚያ ዘንድ ዘከርያ ጌታዉን ለመነ- ጌታዬ ሆይ ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ፤ አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና አለ። እርሱም በጸሎት ማድረሻዉ ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠራችዉ። አላህ በየሕያ ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም፣ ከደጋጐቹ ነቢይም ሲሆን ያበስርሃል፤ በማለት፥ (መላእክት ጠራችዉ)" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 38-39)፡፡
"وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَى رَبِّي سَيَهْدِينِ * رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ * فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلَامٍ حَلِيمٍ " سورة الصافات 100-99
"አለም፡- እኔ ወደ ጌታዬ ኺያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡ ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው" (ሱረቱ-ሷፍፋት 99-100)፡፡
"وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ نِعْمَ الْعَبْدُ إِنَّهُ أَوَّابٌ " سورة ص 30
"ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! (ሱለይማን)፣ እርሱ መላሳ ነው፡፡" (ሱረቱ ሷድ 30)፡፡
"وَاذْكُرْ عَبْدَنَا أَيُّوبَ إِذْ نَادَى رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الشَّيْطَانُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ * ارْكُضْ بِرِجْلِكَ هَذَا مُغْتَسَلٌ بَارِدٌ وَشَرَابٌ * وَوَهَبْنَا لَهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُمْ مَعَهُمْ رَحْمَةً مِنَّا وَذِكْرَى لِأُولِي الْأَلْبَابِ * وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثًا فَاضْرِبْ بِهِ وَلَا تَحْنَثْ إِنَّا وَجَدْنَاهُ صَابِرًا نِعْمَ الْعَبْدُ إِنَّهُ أَوَّابٌ " سورة ص 44-41
"ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው (ተባለ)፡፡ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለ-አእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡" (ሱረቱ ሷድ 41-44)፡፡
3. ጥበብም እንዲሁ የሚገኘው ከአላህ ዘንድ መሆኑን እንማራለን፡-
"قَالَ فَعَلْتُهَا إِذًا وَأَنَا مِنَ الضَّالِّينَ * فَفَرَرْتُ مِنْكُمْ لَمَّا خِفْتُكُمْ فَوَهَبَ لِي رَبِّي حُكْمًا وَجَعَلَنِي مِنَ الْمُرْسَلِينَ " سورة الشعراء 21-20
"(ሙሳም) አለ፦ ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ሆኜ ሠራኋት። በፈራኋችሁም ጊዜ ከእንናተ ሸሸሁ፡፡ ጌታየም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ፡፡ ከመልክተኞቹም አደረገኝ፡፡" (ሱረቱ-ሹዐራእ 20-21)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
ተዓምራትና ፈውስ
የንጽጽር ዳዒዎች
🎯ተዓምራትና ፈውስ

ሙሉ ትምህርቱ

🎤 ተናጋሪዎች

- ኡስታዝ አቡ ሀይደር
- ወሒድ ዑመር
- የሕያ ኢብኑ ኑህ
- ዑስማን ሙሀመድ

@Hidayaislam
27. "አል-ሙእሚን" (ለባሪያዎቹ ታማኝ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉሙ፡-
"አል-ሙእሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ለባሪያዎቹ ታማኝ ማለት ነው፡፡ አምላካችን አላህ ለምእመናን ባሪያዎቹ ታማኝና ጸጥታን ሰጪ የሆነ ጌታ በመሆኑ "አል-ሙእሚን" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ ለባሪያዎቹ የገባውን ቃል-ኪዳን የሚፈፅምና የሚሞላ በመሆኑ "አል-ሙእሚን" ተብሎ ይጠራል፡፡
ለ . አመጣጡ፡-
"አል-ሙእሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-
"هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23
"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. እሱን እያመለኩ ምንም ሳያጋሩበት በሱ የታመኑ ባሪያዎቹን በደኅነነቱ ከለላ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ወደ ቅኑ ጎዳናም ይመራቸዋል፡-
"الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ أُولَئِكَ لَهُمُ الْأَمْنُ وَهُمْ مُهْتَدُونَ " سورة الأنعام 82
"እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነሱም የተመሩ ናቸው" (ሱረቱል አንዓም 82)፡፡
2. አላህ ለባሪያዎቹ ታማኝ ጌታ በመሆኑ ማንንም የማይበድል መሆኑን፡-
"إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ وَإِنْ تَكُ حَسَنَةً يُضَاعِفْهَا وَيُؤْتِ مِنْ لَدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا " سورة النساء 40
"አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበደልም፤ መልካም ሥራ ብትኾንም ይደራርባታል፤ ከርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል።" (ሱረቱ ኒሳእ 40)፡፡
"إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَكِنَّ النَّاسَ أَنْفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ " سورة يونس 44
"አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 44)፡፡
"وَوُضِعَ الْكِتَابُ فَتَرَى الْمُجْرِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَا وَيْلَتَنَا مَالِ هَذَا الْكِتَابِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةً وَلَا كَبِيرَةً إِلَّا أَحْصَاهَا وَوَجَدُوا مَا عَمِلُوا حَاضِرًا وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا " سورة الكهف 49
"(ለሰው ሁሉ) መጽሐፉም ይቀርባል፤ ወዲያውም ከሐዲዎችን፥ በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ፤ ዋ ጥፋታችን! ለዚህ መጽሐፍ፥ (ከሥራ) ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው? ይላሉም፤ የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቀራቢ ሆኖ ያገኙታል፤ ጌታህም አንድንም አይበድልም" (ሱረቱል ከህፍ 49)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
28. "አል-ሙሀይሚን"
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ሙሀይሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- የበላይ ተቆጣጣሪ እና ጠባቂ ማለት ነው፡፡ ፈጣሪ አምላካችን አላህ በፍጡራኑ ጉዳይ ፍጹም የበላይ ተቆጣጣሪ ነው፡፡ በንግስናው ስር ከሱ የሚሸሸግ ምንም ነገር የለም፡፡ ዛሬ በምድራችን የአምባገነኖች በደል በዝቶ እውነተኞች ደማቸው ያለ-አግባብ ፈስሶ ብንመለከትና ጌታችንም ያለ ምንም ምድራዊ ቅጣት ዝም ቢላቸው፡ እሱ ለሚያውቀውና ለሚፈልገው ጥበብ ቢፈልገው እንጂ ከግዛቱ መውጣት ችለው አይደለም፡፡ ይሄን እውነታ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡-
"አላህንም፤ በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው ዓይኖች በርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 42)፡፡
እርሱ ጌታ አላህ ዓለማትን በእውቀቱና በራሕመቱ የከበበ ነው፡፡ ፍጥረታቱን በመላ በችሎታው ስር ያደረገ ነው፡፡ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል፡፡ የፈለገውን ነገር "ሁን" ካለው ይሆናል፡፡
"ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም (ማስገኘት) በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 116)፡፡
"ጌታዬ ሆይ! ሰዉ ያልነካኝ ስሆን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፤ ነገሩ እንደዚህሽ ነዉ፤ አላህ የሚሻዉን የፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ሁን ይለዋል ወድያዉኑም ይሆናል፥ አላት።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 47)፡፡
"አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ፥ እንደ አዳም ብጤ ነዉ፤ ከዐፈር ፈጠረዉ፤ ከዚያም ለርሱ (ሰዉ) ሁን አለዉ ሆነም" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 59)፡፡
"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ እውነት ነው…." (ሱረቱል አንዓም 73)፡፡
"ለማንኛውም ነገር (መሆኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለርሱ ሁን ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።" (ሱረቱ-ነሕል 40)፡፡
"ነገሩም አንዳች ባሻ ጊዜ ሁን ማለት ነው ወዲያው ይሆናልም።" (ሱረቱ ያሲን 82)፡፡
"እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ፣ የሚያሞትም ነው፤ አንዳችን ነገር ባሻም ጊዜ የሚለው ሁን ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።" (ሱረቱ ጋፊር 68)፡፡
እንዲሁም ይህ "አል-ሙሀይሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም ተመልካች የሚልም ትርጉም አለው፡፡ የባሪያዎቹን ንግግርና ስራ ተመልካችና አዋቂ ጌታ በመሆኑ በእውነት ይመሰክራል ይፈርድባቸውማል፡-
"እነዚያ ያመኑ፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ፡ አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና።" (ሱረቱል ሓጅ 17)፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ሙሀይሚን" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-
"هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23
"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡
የጌታችን ቃል የሆነው ቅዱስ ቁርኣንም ከሱ በፊት የነበሩትን ቀደምት መለኮታዊ መጽሓፍት የሚቆጣጠርና ስለነሱም የሚመሰክር በመሆኑ "ሙሀይሚን" የሚል የባሕሪ ስም ተሰጥቶታል፡-
"وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ... " سورة المائدة 48
"ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲሆን በውነት አወረድን…" (ሱረቱል ማኢዳህ 48)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
በነቢያት_ማመን_ክፍል_5_Dai_Sadiq_Mohamm.m4a
Belief In Angels
የዕምነት ማዕዘናት ክፍል 6
በመላዕክት ማመንክፍል 1
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/Mi2Hkg

Join us➤ t.me/abuhyder
29. "አል-ቁዱስ" (እንከን አልባ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
የዚህ መለኮታዊ ስም "አል-ቁዱስ" ትርጉም፡- ከነውር የጸዳ የምሉዕ ባሕሪያት ባለቤት ማለት ነው፡፡
ለ. አመጣጡ "አል-ቁዱስ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል፡-
"هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23
"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡
"يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ الْمَلِكِ الْقُدُّوسِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ " سورة الجمعة 1
"በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ ቅዱስ አሸናፊ ጥበበኛ ለሆነው ያሞግሳል።" (ሱረቱል ጁሙዓህ 1)፡፡
وعند مسلم من حديث عائشة رضي الله عنها أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان يقول في ركوعه وسجوده : ( سُبُّوحٌ قُدُّوسٌ رَبُّ المَلاَئِكَةِ وَالرُّوحِ.(
አዒሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- የአላህ መልክተኛ በሩኩዕ ላይ ሁነው፡- "ሱቡሕ፣ቁዱስ፣ረቡል መላኢከቲ ወር-ሩሕ" ይሉ ነበር፡፡ (ሙስሊም)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
-ጌታችን ከጉድለት የጠራ ንጹህ በመሆኑ፡ እኛ የሱ ባሮች የሆነው፡ እሱን ‹ሱብቡሕ፣ ቁዱስ› እያልን ልናጠራውና ልንዘክረው እንደሚገባ እንማራለን፡-
"وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَنْ يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ " سورة البقرة 30
"(ሙሐመድ ሆይ) ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ፤ እነርሱም) «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ (አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 30)፡፡
የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሩኩዓቸው ላይ ሁነው ከሚሉት ዚክር አንዱ፡- ‹‹ሱብቡሑ፣ ቁዱሱ፣ ረቡል-መላኢከቲ ወር-ሩሕ›› የሚለው ነው (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder