ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ይ:ካ: እግዚአብሔር ምስለ ኰልክሙ ቄሱ:-እግዚአብሄር በሁላችሁም
አድሮባችሁ ይኑር ይበል::
#ይ:ሕ: ምስለ መንፈስከ ህዝቡም እንደቃልህ ይደረግልን ይበሉ::
#ይ:ካ: አእኩትዎ ለአምላክነ :-ቄሱ ፈጣርያችንን አመስግኑት ይበል
#ይ:ሕ: ርቱዕ ይደሉ :- ህዝቡም ዕውነት ነው ይገባል ይበሉ
#ይ:ካ: ብነ ሃበ እግዚአብሔር አምላክነ
ህዝቡም በፈጣርያችን በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ::
#መጽሃፍ ከመጽሃፍ ማያያዝ ልማድ ነው: አባቷ ዳዊት ለንጉሰ ሰማይ ወምድር ምስጋና
ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ ብሎ ተናግሮ ነበርና እሱም ለንግስተ ሰማይ ወምድር ምስጋና
ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ አለ አንድም ለአባቷ ለዳዊት የገለጸ መንፈስቅዱስ ምሥጢር
ከምስጢር አያይዞለት ጐሥዐ አለ ወአየድዕ ይላል በልብ መደብ ቁሞ ወአነ አየድዕ ይላል
በቃለ መደብ ቁሞ ልቦናዬ በጎ ነገርን አውጥቶ ተናገረ:: አንድም ልቦናየ ስንቡል
መንፈስቅዱስን ተቀብሎ በጎ ነገርን ገሳ ሐተታ:-በሃገራቸው የተመገቡት ምግብ
ያልተስማማቸው እንደሆነ ዑድ ሰንደል የሚባል ሽቱ አለ ያንን ተመግበው በጎ በጎ ነገር
ገሣው ይላሉና ያጎሥዓኒ እንዲል ትግሬ
#ሐተታ :- ሶስት ግዜ ጐሥዐ ጐሥዐ ጐሥዐ ብሎ መላልሶ ተናገረ ስለምን ቢሉ በንጽሃ ስጋ
በንጽሃ ነፍስ በንጽሃ ልቦና መዓረግ አምሳል አንድም ወጣንያን ማዕከላውያንን ፍጹማን
የሚያመሰግኗት ስለሆነ: አንድም በዚህ አለም በገነት በመንግስሠማያት ያሉ ጻድቃን
የሚያመሰግኗት ስለሆነ: ከዚህስ አስቀድሞ መንግስተ ሰማይ የገባ የለም ብሎ ኋላ
መንግስተ ሰማያት የሚገቡ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ሲለሆነ: አንድም ሊቃውንት
በሚስጥረ ሥላሴ መጀመር ልማዳቸው ነው: ሦስት ግዜ ደጋግሞ መናገሩ የሦስትነት: ቃሉ
አለመለወጡ የአንድነት:ምሳሌ ነው:አንድም ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ
ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ የሚል ነውና ሦስት አርዕስት ተናገረ ለሦስቱም ያመጣል::
4:-ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም:- አባቷ ዳዊት ወአነ አየድዕ ግብርየ ለንጉሥ ብሎ
ነበርና ለዚያ ዋዌ እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው አለ ሐተታ:- መጀመርያ ጐሥዐ
ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ አለ በቅድስና ወበንጽህና ስርጉት
አንቲ የሚል ነውና ለዚያ አርዕስት ነው::
አኮ በአብዝኖ በማብዛት አይደለም : አላ በአውህዶ በማሳነስ ነው እንጂ ሐተታ:-
የእመቤታችን ምስጋና ከምስጋና ቢበዛ እንጂ ያንሳልን? መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን
አይደለችምን ቢሉ እውነት ነው የእመቤታችን ምስጋና ሰማይና ምድር ብራና አብህርት
ቀለም ዕጽው ብርዕ አዕባን መድመድ: መላዕክት ደቂቀ አዳም ጸሃፍት ቢሆኑ ባልተፈጸመም
ነበር:እንደቅድስናዋ እንደንጽህናዋ አይደለም ሲል እንዲህ አለ ከዚያ ሁሉ ቅዱስ ቄርሎስ
የቴዎዶስዮስን እህቶች የአርቃድያ የመሪናን ምስጋናቸውን ተናግሮ ዝውዳሴንዘተናገርነ
ይውህደ እምክብርክን እንዳለ አንድም ንባብን በማብዛት ምሥጢሩን በማሳነስ አይደለም:
ንባቡን በማሳነስ ምሥጢሩን በማብዛት ነው እንጂ::
ወአነ አይድዕ ውዳሴሃ ለድንግል:- እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው ሐተታ:-
ሁለተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ድንግል አኮ
ስፋጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወጹኪ በከመ ተብህለ ካህናት ወሊቃነ ካህናት
ወደሱኪ የሚል ነውና::
አኮ በአንሆ በቃለ ዝንጋዔ:- ዝንጋዔን የሚያመጣ ዝንጋዔን የሚያስከትል ነገርን በማብዛት
አይደለም: ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ: ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ:እንዲሉ ነገር ከበዛ ዘንድ ከምን
ተነስቶ ከዚህ ደረሰ ይባላልና ነው::
አላ በአሕፅሮ:-በማሳጠር በመጠቅለል ነው እንጂ ሲሰበር ይሰንጠር ሲረዝም ይጠር
እንዲሉ:
ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ለድንግል:- የድንልን ገናንነቷን እናገራለው ሐተታ:- ሦስተኛ ጐሥዐ
ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ማርያም ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ
ብሎ የሚያመጣ ነውና: ይህስ አይደለም አርዕስት ተቀዳደመ ለፊተኛው አርቆ ለኋለኛው
አቅርቦ አይሰጥም ብሎ መጽአ ሃቤኪ ቃል ብሎ የሚያመጣ ነውና:: ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ
: ወአነ አይድዕ ቅዳሴሃ : ወአነ አይድዕ ዕበያቲሃ ብሎ ሦስት ጊዜ መላልዞ ተናገረ::
ኦ ማርያም በእንትዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ: ኦ ድንግል አኮ
ዘተአምሪ ርስሃተ የሚል ነውና: አንድም አባቷ ዳዊት ቀደሰ ማህደሮ ልዕል:መሰረታቲሃ
ውስተ አድባር ቅዱሳን እስመ ሓረያ እግዚአብሄር ለጽዮን ብሎ ሦስት ግዜ መላልሶ
አመስግኗታል::
#ወእቀውም ዮም በትህትና ወበ ፍቅር በዛቲ ዕለት ቅድመ ዝንቱ ምስጢር
ግሩም : ዮምና በዛቲ ዕለት አንድ ወገን: ቀድሶ ያቆረበባት ቀን ናት: እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደናቁኝ ልናቃቸው ሳልል በፍቅር በትህትና ጸንቼ ግሩም በሚሆን በስጋው በደሙ ፊት እቆማለው::
#ሐተታ :- ስጋው ደሙን ምስጢር አለው ከአምስቱ አዕማደ ምስጢር አንዱ ምስጢረ ቁርባን ነውና:: አንድም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት በልሳነ ነፍስ ያናግራልና:አንድም ሲለወጥ
አይታይምና: ለበቁትም ሰዎች ስንኳ ከተለወጠ በኋላ ነው እንጂ ሲለወጥ አይታይምና: አንድም የወድያኛውን ምስጢር ይገልጣልና ግሩም አለ: በሚገባ ቢቀበሉት ግሩም ጸጋ ያሰጣልና: በሚገባ ባይቀበሉት ግሩም ፍዳ ያመጣልና: አንድም ግሩማን መላእክት ከበውት ይቆማሉና አንድም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት ግሩም ምስጢርን ይገልጻልና: አንድም የአምላክ ስጋ የአምላክ ደም አይገርም ማን ይገረም: አንድም የሚወደድ ሲል ነው: ኢትርዓይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ እንዲል አንድም ልዩ ሲል ነው: ግሩም ምክሩ እመጓ ለእመ ህያው እንዲል::
ወቅድመ ዝንቱ ማዕድ ወቁርባን ዐ ማእድም ያለው ስጋው ደሙ ነው: #ሐተታ:- ማእድ
አለው ማእድ ስጋዊን ከበው እንዲመገቡት ይህንም አእሩግ ህጻናት ከበው ይቀበሉታልና: አንድም ለማእድ ስጋዊ ሰው እንዲመረጥለት ለዚህም የበቃና ያልበቃ ይመረጥለታልና አንድም ማዕደ ነፍስ ነውና ቁርባን እንዳለፈው: አንድም ማእድ ጻህል ጽዋው ቁርባን ስጋው ደሙ ነው ::
#በአማን ቁርባን ውዕቱ ዘእይክሉ ይጥዐሙ እምኔሁ ግሙናነ መንፈስ ልቦናቸውን ሰውነታቸውን በሃጥያት ያሳደፉ ሰዎች ሊቀበሉት የማይገባቸው መለኮት የተዋሃደው እውነተኛ ቁርባን ነው:
#ሐተታ :- ማን ይከለክላቸዋል ቢሉ ራሳቸው ፈርደው ይከለከላሉና አንድም ቄሱ ይከለክላቸዋልና አንድም እግዚአብሔር በምልዓት በልቡናቸው አድረው ይከለክላቸዋልና: ህዝቡ ያልበቁ ልዑካኑ የበቁ የሆኑ እንደሆነ የህዝቡን ለልዑካኑ ይደርብላቸዋል: ልዑካኑ
ያልበቁ ህዝቡ የበቁ ይሆኑ እንደሆነ የልዑካኑን ለህዝቡ ይደርብላቸዋል ህዝቡም ልዑካኑም ያልበቁም የሆኑ እንደሆነ መልአክ ወስዶ በበርረሃ ለወደቁ ባህታውያን ያቀብላቸዋል: ምግብ ሁኑአቸው የሚኖር ቅሉ ይህ ነው: ያም አያውቅም ይህም አያውቅም ያ እንዳይታበይ ይህ ከቀቢጸ ተስፋ እንዳይደርስ ነው:: አኮ ከመ መስዋእቶሙ ለቀደምት አበው ዘበደመ በግዕ ሐርጌ ወላህም:: በደመ በግዕ በደመ ላህም የቀደሙ ሰዎች ይሰውት እንደነበረ መስዋእት አይደለም: አንድም የቀደሙ ሰዎች በደመ ላህም በደመ በግዕ ይሰዉት እንደነበረ መስዋዕት አይደለም::
#ሐተታ:- ሃርጌን ለበግ የቀጸሉ እንደሆነ ሙክት በላህም የቀጸሉ እንደሆነ ጊድር ማለት ነው::
#አላ እሳት ውዕቱ:: መለኮት የተዋሃደው ቁርባን ነው እንጂ እሳት መለኮት የተዋሃደው ቁርባን ነው እንጂ:እሳት ማህየዊ ለርቱአነ ልብ ለዕለ ይገብሩ ፈቃዶ:: ለና ለ አንድ ወገን እሳትም ብዬ ብላችሁ አንድነቱን ሶስትነቱን አውቀው ህማሙን ሞቱን አምነው ሃጥያታቸውን ለመምህረ ንስሓ ነግረው መምህረ ንስሃ ያዘዘውን ሰርተው በሚገባ ለሚቀበሉ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው::
#ሐተታ:- እሳት በመጠን የሞቁት እንደሆነ የበሉት የጠጡትን ያስማማል: ደዌ ይከፍላል: ይህም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት ይህወተ ስጋ ህይወተ ነፍስ ይሆናል: ደዌ ነፍስ ያርቃልና:: እሳት በላዒ ለአማጽያን ለእለ ይክህዱ ስሞ:: ለና ለ አንድ ወገን ነው እሳት ማህየዊም ብላችሁ ስመ አምላክነቱን ለሚክዱ ሰዎች የሚያቃጥል እሳት ነው::
#ሐተታ:- ስመ አምላክነቱን ከካዱ የማን ስጋ የማን ደም ብለው ይቀበሉታል ቢሉ ስመ ቁርባንነቱን ለሚክዱ ሰዎች::
#ሐተታ:- ስመ ቁርባንነቱንስ ከካዱ ምን ይረባናል ምን ይጠቅመናል ብለው ይቀበሉታል ቢሉ በግብሩ መካድ አለና::ከሃጥያት ሳይነጹ ቢቀበሉት በፍዳ ላይ ፍዳ የሚያመጣ ስለሆነ እሳት ነበልባሉ ከወረደው ፍህሙ ከመረተው ቀርበው ያለመጠን ቢሞቁት ያቃጥላል ይህም በማይገባ ቢቀበሉት ፍዳ ያመጣልና:: ወይእዜኒ ዘበልዖ ለዝንቱ ህብስት: ወዘሰትዮ ለዝንቱ ጽዋ እንዘ እይደልዎ ደይኖ ወመቅሰፍቶ በልዓ ለርእሱ መንሱትኬ ነሢአ ሥጋሁ በድፍረት ወተመጥዎ ደሙ ዘእንበለ ሃፍረት እንዘቦ ላዕሌሁ ነውረ ሃጥያት እንዲል::ከዚህም ስጋውን ከእሳተ ባቢሎን ደሙን ከማየ ግብጽ ምሳሌ አምጥተው ይናገራሉ: እሳተ ባቢሎን ሰልስቱ ደቂቅን ሳይነካ በአፍአ ያሉ የባቢሎንን ሰዎች አቃጥሎአቸዋል ስጋውም ከሃጥያት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከሃጥያት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና ማየ ግብጽ በግብጻውያን ሲለወጥባቸው በእስራኤል አልተለወጠባቸውም ደሙም ከሃጥያት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከሃጥያት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና ዛሬም ቀሳውስት ይህን ምሳሌ ይዘው የበደላችሁትን ሳትክሱ የቀማችሁትን ሳትመልሱ ከሃጡያት ሳትነጹ ሳትበቁ ብትቀበሉት ሥጋው ደሙ በነፍስ በስጋ ያስፈርድባችኋል እያሉ አዋጅ
ይነግሩበታል::
#በአማን እሳት ውዕቱ ዘኢይክሉ ለኪፎቶ እሳታውያን እለ ነደ እሳት እሙንቱ
ኪሩቤል ወሱራፌል ከእሳት ከነፋስ የተፈጠሩ ኪሩቤል ሱራፌል ሊይዙት የማይቻላቸው መለኮት የተዋሃደው እውነተኛ ቁርባን ነው ተፈጥሮዋቸው ከእሳት ከነፋስ ነውና:: ወሶበ ኢያእኮትኮ ለዘፈጠርከ እምነፋስ ወነድ ፈጠረ ህየንቴከ ሰንአ ዘማሬ እማይ ወእመሬት እንዲል::
#ሐተታ:- ከእለተ ሰሉስ አስቀድሞስ ግብር እም ግብር የተፈጠረ ፍጥረት የለም:
የመላእክትም ተፈጥሮ እምሃበ አልቦ ነው: ግብራቸውን ሲያይ እሳት ነፋስ ሃያላን ረቂቃን ፈጣኖች ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው: መላእክትም ሃያላን ረቂቃን ናቸውና: ለተልኮ ይፋጠናሉና: የፈጣሪያቸውን ፈቃድ ይፈጽማሉና::
#ሐተታ:- እሳት ሰብዓ ሰዶምን ደቂቀ ቆሬን አጥፍቷል ነፋስም ብእሲት ዘማን ጥቅመ
ሰናኦርን ሃራ ጰራግሞንን አጥፍቷልና አንድም የባለሟልነት ስማቸው ነው: እገሌ ነደ እሳት ባለሟል ነው እንዲሉ::
#ታሪክ:- ዘኢይክሉ ለኪፎቶ አለ ንጉሱ ዖዝያን ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ይባላል በቀኙ ይቀመጣል: ምነው በቀኜ ትቀመጥብኛለህ ይለዋል ወካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ እንጂ ይለኛል ይለዋል:: ከልብሰ መግስቱ ልብሰ ክህነቱ ይበልጣል ምነው ከኔ የበለጠ ልብስ ትለብሳለህ ይለዋል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ እንጂ ይለኛል ይለዋል:: ፍርዱን ይገስበታል ምነው ፍርዴን ትገስብኛል ይለዋል እምነ መንግስት የአቢ ክህነት እንጂ ይለኛል ይለዋል አድርጎ ቤተ መንግስትም እያረካከሰ ቤተ ክህነትን እያነጋገሰ እየጠቃቀሰ ቢያውከው በዚያም በዚያም ቢሉ ቀንቶበት ከቤተ መንግስትማ ቤተ ክህነት ከበለጠ እኔስ ባባቴ ከቤተ መንግስት ብወለድ በናቴ ከቤተ ክህነት እውለድ የለምን ብሎ ማእጠንተ ወርቁን ይዞ ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ ሊያጥን ገባ: ሲያጥን ጢሱ ቢያርፍበት ከግንባሩ ለምጽ ተቀረጸበት በሻሽ ሸፈነው: ከሻሹ ላይ ወጣበት ለምጻሙን በእስራኤል ስንኳንስ በቤተ መቅደስ በከተማ አያኖሩትምና: እሱን አውጥተው ልጁን አንግሰዋል በዘመኑ የነበረ ነቢይ ኢሣያስ ነው ፈርቶ ሳይገስጸው ቢቀር ለምጽ ወቶበት ሃብተ ትንቢት ተነስቶት 3 አመት ከመንፈቅ ያህል ኖሯል ወእምዝ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉስ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ
ይነብር ዲበ መንበሩ ብሩህ ወነዋህ እንዲል: ዖዚያን በሞተበት ወራት ጌታ በመንበረ ጸባኦት እንዳለ ሆኖ ለኢሳያስ ታየው ያ ታፍረው ታከብረው የነበረው ንጉስ ሞተ አልፈ እኔ ግን እልፈት ውላጤ የለብኝም ሲል ሊያድነው ቢሻ መነ እፌኑ ሃበ ህዝብየ እስራኤል ሁሉ ራሱ ጠበቀ አንገቱን ቀበረ ወደወገኖቼ ወደ እስራኤል በመምህርነት ማንን ልስደድ አለ
#ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ: ኦ ቃለ አክብሮ ቃለ አህስሮ ቃለ አራህርሆ ይሆናል: ቃል አክብሮ ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ ብሎ የሚያመጣው ነው: ቃለ አራህርሆ ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ቃለ አህስሮ ኦ ሃናንያ ኦ አብዳን ሰብአ ገላትያ ነው:: በእንተዝ ያለፈውን አጠፈ እንደገና ብሎ መጽሃፍ ያለፈውንም የሚመጣውንም ማጠፍ
ልማድ ነውና የሚመጣውን አጠፈ እመቤታችን ሆይ እናከብርሻለን እናገንሻለን::
#ሐተታ:- እኛ እሷን የምናከብራት የምናገናት ሆነን አይደለም ክብርሽን ገናንነትሽን እንናገራለን ሲል ነው::
እስመ ወልድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ህይወት ዘበአማን:: እውነተኛውን ምግብ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና ስላስገኘሽልን::
#ሐተታ:- ዘበአማን አለ ከመስዋዕተ ኦሪት ሲለይ ያ ስጋዊ ይህ መንፈሳዊ ያ አፍአዊ ይህ ውሳጣዊ ያ ምድራዊ ይህ ሰማያዊ ነውና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ጥዋት በልቶ ለማታ ማታ በልቶ ለጠዋት ያሻል ይህ ግን በሚገባ ከተቀበሉት በሃጥያት ካላሳደፉት
ህማሙን ሞቱን ለማዘከር ነው እንጂአንድ ግዜ ከተቀበሉት በሌላ ግዜ አያሻምና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ሃሰር ይሆንል ይለወጥል በሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና አንድም የዚህ አለም ምግብ ሞትን ያስከትላል ይህ ግን የዘላለም ህይወት ይሆናል አንድም ከማናዊት
እመቤታችን ስለተገኘ መብልአ ጽድቅ ዘበአማን ውስቴ ህይወት ዘበአማን አለ::
#ይካ ንፍቅ ጸሎተ ቡራኬ
#ይ ዲ ንፍቅ መሐረሙ እግዚኦ
#ይ ካ ለዑልኒ፡፡ ቄሱ ያነሳቸውን፡፡
ወለኲሎሙ፡፡ ያላነሳቸውን አንድም ከእሱ ጋር ያሉ ልእካኑ በቅድስት አሉትን አንድም በቅድስት ያሉትን በዝንቦ ያሉትን አንድም በቆመ ብእሲ ያሉትን በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን ያሉትን አንድም በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን ያሉትን በብህንሳ ያሉትን፡፡ እንድም እጣን ያረገላቸውን መስዋእት
የተሰዋላቸውን፡፡ ወለኲሙ፡፡ ይህ ሁሉ ያልተደረገላቸውን፡፡ #ኦ መስተምህርት አስተምህሪ ኀበ ወልድኪ፡፡ ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ ከልጅሽ ዘንድ አማልን ይበል ከመ ያዕርፍ ነፍሰ ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳተ ዋዌ የቀረው ነው የጳጳሳት የሊቃነ ጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳትን ነፍስ ዕረፍተ ነፈሰን ሰጥቶ ያሳርፈ ዘንድ፡፡
#ቀሳውስት ወዲያቆናት፡፡
ዋዌ የቀረው ነው የቀሳውስትን የዲያቆናትን ነፍስ ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ ቀሳውስተ ወዲያቆናተ ይላል ቀሳውስት ዲያቆናተን ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡
#እለ ያረትዑ ፍኖተ ቃል ዘበአማትን፡፡
ዕውነተኛ ሕገ ወንጌልን የሚያስተምሩ አንድም ፍኖተ ግስ ነው የረትዑ ካልሁ ብሎ አንዲህ አለ እንጂ ወንጌልን የሚያስተም አንድም ፍኖተ ወንጌል፡፡ ቀቃል አካላዊ ቃል ነው፡፡ አካላዊ ቃል ያስተመረው ወንጌልን የሚያስተምሩ፡፡ ነገሥተ ነገሥታቱን፡፡ ወመኳንንት፡፡ ቀኛዝማች ግራዝማቹን፡፡ ወመሳፍንተ፡፡ ደጃዝማቹን፡፡
#ወእለ በሥልጣናት፡፡ ተወራጅ ነገሥታት፡፡ እንደ ሸዋ መርድ አዝማች እንደ ጎጃም ጣፌ ላምነት፡፡
አንድም ወመሳፍንተ፡፡ ተወራጅ ነገሥታት፡፡
ወእለ በሥልጣናት፡፡ ሥሉጣነ ነገር እንደ ጥቁር ከብቴ እንደ ቆብ አሰጥል ኃይሉ ያሉ ናቸው፡፡
ወራኩተ፡፡ ወራዙተን የነዚህ ተወራጅ ናቸው፡፡
#ወደናግለ፡፡ ደናግለ ሥጋ ደናግለ ነፍስን፡፡ ወመነኮሳተ፡፡ መነኮሳትን ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡
#ሐተታ፡፡ መነኮሳት ደናግልም ወራዙትም ካላቸው የገባሉ፡፡ በድንግልና የሚመነኩሱ አግብተውም ነረው ኋላ የሚመነኩሱ አሉና ባዕለ ወነዳየ፡፡ ባለጸጋውን ደኋውን፡፡ ዐቢየ ወንዑሰ፡፡ ታላቁን ታናሹን፡፡ ሐተታ፡፡ የማዕርግ የዕድሜ ነው፡፡ ዕቤተ፡፡
ጎመን ዘሪ ቤ ሠሪ ባል ልጅ የሌት ባለቴቲቱን፡፡ ወዕጓለ ማውታ፡፡ አባት እናት የሚቱበት ድኋውን፡፡ ግዩረ፡፡ ካጣዖት ፊልሶ የመጣውን፡፡ አንድም በድ መትቶበት አንበጣ በልቶበት የሰደውን አንድም የምግባር ቁርጭኝ፡፡
#ወምሰኪነ፡፡ የለት ራት የጣት ቀለበት የሌለውን ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡ አንድም የነዚህን ነፍስ ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡
#ወኲሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን እለ አዕረፋ እማኅበረ ቤተ ክርስቲያን መቅድመ፡፡
ውሎ ውሎ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከመሬት እንዲሉ ከክርስቲያን አንድነት አስቀድሞ የሚቱት የክርስቲያን ወገን የሚሆኑ እነዚህን፡፡ አንድም የእንዚህን ነፍስ እረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ አማልጅን፡፡ አንድም ከክርስቲያን አንድነት ተለይትው የሞቱ የእነዚህ ነፍስ እረፍት ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ ሀተታ፡- ፡፡ ወቅመ ዓለም ሰው እንደ መከር ነው፡፡ መከር እኩሉ ሲዘረዝር እኩሉ ይታጨዳል ሰው እኩሉ ሲወለድ እኩሉ ይሞታል እና፡፡
09 ወፈድፋደሰ በእንተ እለኖሙ ውስተ ዛንቲ መካን፡፡ ይልቁንም በብህንሳ ያረፉትን አስቀድመሽ፡፡ እንቲ ዘበእንቲ አሆሙ አስተበቁኢ ጽፋቀ፡፡
አብዝተሽ መላልሰሽ አማለጂ ወጽፋቅ በዋዔ ቤታ እንዲል ጽሁቀ ይላል ተግተሸ አማለጂን ከመ ያዕርፍ ነፍሶሙ ንሁየ፡፡ ነፍሳቸውን ፈጽሞ ያሳርፍ ዘንድ፡፡ አንድም በጎ እረፍትን ያሳርፍ ዘንድ ተደሞ ታህየ ምንዱባን አንዲል፡፡ #ሀተታ፡- አስቀድሞ ላለበት ሀገር መጸለይ ይገባል አስራት በኩራቱን ይቀበላልና፡፡ ህሱ ሰላማ ለእግዚአብሔር ኦ እግዚኦ ተሳሀል በይበይከ ላእለ ዛቲ ሀገረ አርመኒያ እንዳለ ጎርጎርዮስ፡፡ የእክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ ለሀገሩ ሳይጸልይ ለሌላው እንዳይፀልይ፡፡
#በህበ ኩሉ ዘተሰምዬ መካነ ሰማእት መዋእያን፡፡ በብህንሳ ያሉትን ባማልድ በሌላው አገር ያሉትን ማማለድ እንደምን ይሆንልኛል ትዪኝ እንደሆነ አላውያን ነገስታት አላውያን መኳንንት፡፡ ፍትሰታት አኩያት አጣውእን ድል የነሱ የሰማእታት ስማቸው በተጸራበት ቤተ ክርስቲያንና በታነጸበት ታቦታቸው በተቀረበት ስእታለቸው በታለበት በዚህ ሁሉ፡፡ #ወመካነ ጻድቃን ብሩካን:: ይቀጥላል.......
#ወመካነ ጻድቃን ብሩካን፡፡ በርገመ ጌባል ያልወደቀባቸው ኃጢአተ አዳም የሌለባቸው ንዑህቤየ ብሩካኑ ለአቡየ የተባሉ የጻድቃን ስማቸው የተጠራበት እንዳለፈው በል፡፡
ወመካነ መላእክት ትጉሀን፡፡
ጸሐይ ከመመላለስ ጸሐይ ከመፍሰስ እንዳያቋርጥ ምስጋና የማያቋርጡ የመላእክት ስማቸው በተጠራበት በተ ክርስቲያናቸው በታነጸበት ታቦታቸው በተቀረጸበት ስዕላቸው በተሳበት፡፡ #በህበ ኩሉ መካን በቦታው ሁሉ ርእስት እንቲ፡፡ ገዢ አለቃ ነሽ ወአርሶ ለጴጥሮስ ንነዲል ታሪክ ቤተ ክርሰቲያን ቅሉ መጀመሪያ በፊልጵስዮ የተሰራ በእሷ ሰም ነውና፡፡ ጳውሎስና በርናባስ ፊልጵስዮስ ገብተው አስተማሩ፡፡ ሕዝቡም አመኑ፡፡ ተጠመቁ ካመናችሁ ከተጠመቃችሁ እንግዴህ ወይ ቤተ ፃዖት አትሂዱ አሏቸው የለመድነውንም ከነሳችሁን መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡ አምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ብሎ አዟቸው አረገ፡፡ ሐንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ ከዚያ ወዲህ ነው እሰኪል ድረስ እንደ መጀመሪያው ታሪክ ተርከው፡፡ ምሳሌውንና ጥቀሱነ ጨምረህ ነው፡፡ እንድም ርስት ይላል ርስት ነሽ #ሐተታ፡- ፡፡ ሲሶ ለነጋሽ ሲሶ ለአንጋሽ ሕዝብ ሲሶ ለቀዳሽ ነው
እመቤታችንም በጽሕፈትም በቅርጽም በምስጋንም ሲሶ አላትና፡፡ በጸሐፈት ከላይ አልፋ ወዖ የጌታ ስም፡፡ ሁለተኛ ዮሐንስ ሦስተኛ ምስለ ፍቁር ወልዳ ነው፡፡ ይህ ታቦቱ ታቦተ ማርያም ታቦተ ኢየሱስ ታቦተ ዮሐንስ ቢሆን ነው፡፡ ታቦቱ ሰማዕት ጻድቅ የሆነ እንደ ሆነ አልፋ ወዖ የጌታ ዮሐንስን ዘረፈቀ ውስተ ሕጹ ይለዋልና አሰጠግቶ ታቦቱ ሰማዕትም ሦስተኛ ምስለ ፍቁር ወልዳን፡፡ ባቀራረጽም ከላይ ሥላሴን፡፡ ዝቅ ብሎ እመቤታችንን አንገቷን አቅንቶ ይቀርጻል፡፡ ዝቅ ብሎ ሰማዕትም ጻድቅም ቢሆን ባቤቱን አሰታጥቆ አንገቱን ወይ
አመቤታችን አቅንቶ ይቀርጸል፡፡ እሱ ከሱዋ እሱዋ ከሥላሴ የሚያማልዱን ሰለሆነ በምሰጋናም መጀመሪያ ተአምረ ማርያም ቀጥሎ ጻድቅም ሰማእትም ቢሆን የባለቤቱን ቀጥሎ ተአምረ ኢየሱስ ነውና አንድም ርስተ ሰማይም ርስተ ምድርም የተገኘ ጌታ ከእመቤታችን ሰው ከሆነ በዲህ ነውና፡፡ አንድም የምነቀበለው ስጋው ደሙ ከእሷ የነሳው ነውና፤ አጽመ ርስቴን በላሁ አንዲሉ ፡፡
ወስሉት ስምኪ በህበ እግዚአብሔር፡፡
ስምሽም በእግዚአብሔር በማማለድ ስሉጥ ነው ይህም በአንድ ሰው ታውቋል ታሪክ እጅግ ገንዘቡ የበዛ የተፈው አንድ ባለጸጋ ነበረ ለአዝማሪ ለዘዋሪ እየሰጠ አለቀበት፡፡ አንድም የዚህ ዓለም ገንዘግ ሲሰበሰብ እንጂ ኢጠፋ አይታወቅም እና ህልፈቱ ቅድም አስተርእዮቱ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ ገብሬ በኖሩኩበት ሀገር ተዋርጄ፤ ሰጥቼ በኖርኩበት ሀገር ለምኜ አልኖርም ብሎ ሀገር ጥሎ ቁርበት ጠቅልሎ ሲሄድ ሰይጣን የጨዋ ልጅ መስሎ ከጎዳና ቆይቶ ወዴት ትሄዳህ አለው ከብሬ በኖርኩበት ሀገር ተዋርጄ ሰጥቼ በኖርኩበት ሀገር ለምኜ
አለኖረም ብዬ ነው ሀገር ጥዬ ቁርበት ጠቅልዬ መሄዴ ነው ያዘነ መስሎ ደንጊያውን በምትሀት አስመስሎ ይህን ብሰጥህ አትመለስምን አለው፡፡ ይህንንማ ካገኘሁ ስንኳን ለእሙ ለልጅ ልጄ አይበቃምን ከዚህ በኋላ ሰጠው አንተም ፍቃዴን ፈጽምልኝ አለው ምን ላድርግልህ አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስን ካድልኝ ማእክት ጻድቃን ሰማእታት አያማልዱም በል አለው ካደ አያማልዱም አለ ከተለያዩ በኋላ ነገር ረስቼ ዎየሁን ምእመናን አፍረው አክብረው ስሟን የሚጠሯት ማርያም የምትባል አለች፡፡ ወላዲተ አምላክ መሆኗን ካድልኝ የለማኝ ምርኩዜን ምን ይዞ ይሄዷል ጉዞ እንዲሉ እሷስ አየሆንም አንኪያስ አምጣ ብሎ ወርቅ እስመስሎ የሰጠወን ደንጊያ ተቀብሎ ልብ ራሱን ብሎ ገደለው ወዲያውኑ መላእክተ ጽልምት መጥተው ነፍሱን ከስጋው ለይተው እጅ አድርገዋታል፡፡ መላእክተ ብርሀንም የጌታን ቁርጽ ፍርድ ሳያዩ አይለዩምና እመቤታችን ዘንድ ሄደው ምነው ዝም አልሽ ከስጋዋ የተለየች ባንች ምክንያት አይደለምን አታማልጅምን አሏት፡፡ እሷም መሃር ሊተ ወልድየ ዛቲ ነፍሰ አለችው፡፡ ከልብኑ ይትምሀር፡፡ አባቴን እኔን የባህርይ ህይወቴ መንፈስ ቅዱስን የወዳጆቼ የማእክት የታድቃን የሰማእታት አማላጅነታቸውን የካደ ይማራልን አላት፡፡
#ዘጸውአ ስምኪ ወዘገብረ ተዘካርኪ እምህር ለኪ ያልኸውን ቃል ይታበላልን አለችው፡፡ ያውስ ቢሆን ምግባር ነው እንጂ ሐይማኖት ነውን ከገር ግን ከስጋስ ስጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቼ ሰው መሆኔ ፍቃድሽን ላልፈጽምልሽ ነውን ምሬልሻለሁ እንኪያስ ከማረህልኝ ነፍሱን ከስጋው አዋህደህ አስነሳልኝ ነፍሱም ከስጋው ጋራ አዋህዶ አስነሳላት ለምን ካድህ አለችው ባጣ አላት ያጣ ይለምናል እንጂ ይክዳል አሁንም ከልጄ አማልጄህ አንዲህ ካለ ቦታ ምግብህን አዞልሀልና ሂድ አለችው፡፡ በዚያች ቦታ አንድ ባለጸጋ ነበረ አንዲት መልከ መልካም ልጅ ነበረች ባለጸጋው መጥቶ ልጅህን ስጠኝ ያለው እንደ ሆነ ልጄን በመልክ አትተካከላተም ይለዋል፡፡ መልከ መልካም መጥቶ ስጠኝ የለው እንደ ሆነ ልጄን በገንዘግ አትተካከላትም ይለዋል፡፡ አንዲህ አድረጎ ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ያኖራት ነበር፡፡ በዚያች ቀን እመቤችን ከቤተ ክርሰቲያን እንዲሄድ አድረጋዋለች፡፡ የባጸጋ ጸሎት አጭር ነውና
የሰጠኸኝን አትንሣኝ፡፡ ይህችን አንዲት ቅነተጣት ልጄን ባርክልኝ ብሎ ተቀመጠ ወዲያው ተደሞ መጣበት፡፡ ያም ሰው ጠፈር ጠፈሩን እያየ ሲዞር ከሱ አተገብ ደርሶ ቆመ፡፡ ልጅህንም ከብትህንም ለዚህ ሰው ስጠው አለችው ቀና ቢል አየው፡፡ ከዚህ በኋላ ወስዶ ልጁንም ከበቱንም ሰጥቶት ወድያው ወረፈ፡፡ ስሱም ቆርቦ የእመቤታችን ስሟን ሲጸረ ዝክሯን ሲዘክር በዚህ ጊዜ ያልፋል፡፡ የመይባል መንግሥተ ሰማያትን አውርደሰዋለችና አንዲህ አለ፡፡ ፩ዱ ነዳይ ዘክሕደ ሃማኖተተ ኪያ ከሐደ ቦበ ዐበየ በቅድመ ሰይጣን ዘአስሐቶ አሚነ ኢዘኪ ድንግል ለአድኀኖ ነፍሱ በቁዐቶ እንዘ ሰብሕ ተአምረኪ ወለጸጌኪ ምህረቶ ተንሥአ እምንዋሙ ወእተወ ሰቤቶ አንዳለ ደራሲ፡፡
#ይ ዲ እለ ትነብሩ ተንሥኡ ብቅዳሴ ጊዜ የተቀመጣችሁ ተነሡ፡፡ አሁን በቅዳሴ ጊዜ ከህሙም ከአረጋዊ በቀረ የሚቀመጥ ኑሮ አይደለም፡፡ ከዓራቱ ዝንጋዔ በተዘክሮ ከዓራቱ ሐኬት በአንክሮ ተነሡ ሲል ነው፡
#ይ ካ ንትነሣእ በፍርሃት እግዚአብሔር፡፡ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ምርኩዝ አድገን እንነሣ
ይበል ፊሪሃ እግዚብሔርን በትር ነምፈሳዊት ይላታልና #ሐተታ ዲያቆኑ ቢያዝዝ አይሰሙትምና ቄሱ ንትነሣእ ይላል፡፡
ከመ ናዕብያ ወንወድሰ ለምልእተ ውዳሴ፡፡ ምስጋናን የተመላች እመቤችንን ፈጽመን እናገናት እናመስግናት ዘንድ፡፡
አንዘ ንብል ኦ ምልእተ ጸጋ፡፡
ጸጋ ሰማያዊን ጸጋ ምድራዊን የተመላሽ፡፡
ኦ ሙሐ ፍሥሓ፡ የደስታ መገኛ የምትሆኝ እመቤችን #ሐተታ፡፡ መልአኩ ተፈሥሒ ፍሥሕት ያላት እንደ ነቅዕ እንደ እሰትንፋስ ሳያቋርጽ ሲነገረ ይኖራልና አንድም ጻጋን ፍሥሓን አንድ ወገን አድርጎ የጌታ መገኛ የምትሆኝ እመቤታችን እያልን እናገናት እናከለብት ዘንድሰ እንነሣ ይበል፡፡
#ፈድፋደ ብኪ ግማ ራዕይ ዘየወቢ እምኪሩቤል እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ፡፡
ዐይናቸው ብዙ ከሚሆን ከኪሩቤል፡፡ እለ 6 ከነፈሆሙ ክንፋቸው ስድስት ከሚሆን ከሱራፌል ይልቅ መልከ አለሽ፡፡ አንድም የመወደድ ግርማ የባለሟልነት መልክ አለሽ ፈድፋደ ይላል በዘልሽ መፈራት በአጋንንተ በመናፍቃን በአይሁድ ዘንድ በለሟልነት በሥላሴ ዘንድ ነው፡፡ እለ ብዙኃት አዕይቲሆሙ ያላቸው፡፡ እለ ስድስቱ ከነፊሆሙ ዩላቸው እለ ቡዙሀት አዕይንቲሆሙ ካላቸው ይገባሉ፡፡ #ሐተታ፡- ከነገደ ኪሩቤል ገጸ ላህም ገጸ ብእሲ ከነገ ሱራፌል ገጸ ንስር ገጸ አንበሳን አውጥቶ መንበሩን አሸሟቸዋል፡፡ #እለ ብዙኋት አዕይቲሆሙ አለ ከፊት ከገንራቸው እስ
ከ ጥፍራቸው አኋላ ከራሳቸው እስከ ተረከዛች ድረስ ዐይንን የተመሉ ናቸው፡፡ ይህስ አይደለም እንደብሌ እንደብርጭቆ እያፈብለጨለጨ ለዓይን ባልተመቸም ነበረ ብሎ አልፎ አልፎ ነው እንደ ቀሽመሪ መታጠቂያ እንደሶራ ግምጃ እንደ ነብረ ለምድ እንደ ማር ሰፈፍ አንድም ከአንገታቸው በላይ ነው ይህም እንደ መስታወት እባረቀ ላዓይን አይመችም ብሎ ዓይናቸው ሁለት ነው ሀላፊያት መጻእያት እለተገለጻለቻ እውቀት እላልተከፈለባቸው
እንዲህ አለ፡፡ 6ቱ ክነፈ ሆሙ አለ ኢሳያስ እንዳያቸው ነው፡፡ #ሐተታ፡- እንደ ቅዳሴ ሐወርያት ተርክ
#ይ ዲ ውስተ ጽባሕ ነጽሩ፡፡