ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
እንኩዋን ለጌታችን ቅዱስ #ዕፀ_መስቀል የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል +"+
የዕፀዋት ሁሉ ንጉሣቸው የሚሆን ቅዱስ ዕፀ መስቀል
ለእኛም #ኃይላችን: #ቤዛችን: #መዳኛችን: #የድል_
ምልክታችን ነው:: መስቀል #በደመ_ክርስቶስ ተቀድሷልና
አንክሮ: ስግደት ክብርና ምስጋና በፀጋ ይገባዋል::
#ቅዱስ_መስቀለ_ክርስቶስ ላለፉት 2,000 ዓመታት ብዙ
ተአምራትን ሠርቷል:: ከእነዚህ መካከልም አንዱን በዚህ
ዕለት እናዘክራለን:: ታሪኩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው
ቢሉ:- በ400 ዓ/ም አካባቢ በግብፅ #አባ_ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ
ሳለ: #ቅዱስ_ቄርሎስም በሊቀ ዲቁና ሲያገለግል ሳለ
በእስክንድርያ ከተማ 2 ደሃ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የቀን
ሠራተኞች በመሆናቸው ከዕለት ምግብ አይተርፋቸውም
ነበር::
ከ2ቱ አንዱ ፍጹም አማኝ ሲሆን ሌላኛው ግን ተጠራጣሪ
ነበር:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- በከተማዋ ብዙ ሃብታም አይሁድ
ነበሩና እነሱን እየተመለከተ ነው:: ለእርሱ #ክርስትና ማለት
ገንዘብ መስሎታልና ዘወትር "ለምን ክርስቶስን እያመለክን ድሃ
እንሆናለን?" እያለ ያማርር ነበር::
"ያዛቆነ ሰይጣን . . . " እንደሚባለው አንድ ቀን ባልጀራውን "ለምን ክርስቶስን አንክደውም? (ሎቱ ስብሐት!) እርሱን ከማምለክ የተረፈን ድህነት ብቻ ነው" አለው:: ባልንጀራው ሊመክረው ሞከረ:-
"እግዚአብሔር አምላከ-ነዳያን ነው:: ቅዱሳን #ነቢያት :
#ሐዋርያት : #ጻድቃን: #ሰማዕታትም በሥጋዊ ሃብት ነዳያን
ነበሩ" ብሎ ቢለውም ሰይጣን ሠልጥኖበታልና
አልሰማውም:: ያ ስሑት ደሃ ወዲያው ወጥቶ ወደ ማሕበረ አይሁድ ሔደ::
እነርሱ በቁጥር ብዙ ሁነው በአንድነት ይኖሩ ነበር::
"ሥራ ቅጠሩኝ" አላቸው:: "በእምነት አትመስለንምና
አይሆንም" አሉት:: ያን ጊዜ ለአለቃቸው ( #ፈለስኪኖስ)
"አንተ ሥራ ቅጠረኝ እንጂ እኔ ክርስቶስን እክዳለሁ" (ሎቱ
ስብሐት!) አለው::
ወዲያው የከተማው ሕዝብ ተጠርቶ: በጉባኤ መካከል
ሊያስክዱት ተዘጋጁ:: በፍጥነትም #መስቀል: ጦር: ሐሞት
አዘጋጁ:: ስዕለ ስቅለቱንም አመጡ:: ያን ደሃ ከሃዲም
"በል-ክርስቶስ ሆይ! ካድኩህ ብለህ ምራቅህን ትፋበት:
ሐሞቱን አፍስበት: በጦርም ውጋው" (ሎቱ ስብሐት!)
አሉት::
ያ ልቡ የደነቆረ መስቀለ ክርስቶስ ላይ ተፋ:: ሐሞትም
አፈሰሰበት:: በመጨረሻ በጦር ሲወጋው ግን ድንቅ ተአምር
ተገለጠ:: በጦር ከተወጋው ከመስቀሉ ጐን ብዙ ደም
ፈሰሰ:: ለረዥም ሰዓትም አላቁዋረጠም:: በዚህች ሰዓት
በአካባቢው የነበሩ ሁሉም አይሁድ በግንባራቸው ተደፍተው
ለክርስቶስና ቅዱስ መስቀሉ ሰገዱ::
ሁሉም በአንድነት "#ክርስቶስ_የአብርሃም_አምላክ_ነው
:: #መድኃኒትም_ነው " ሲሉ እየጮሁ ተናገሩ:: ባለማወቅ
ስላደረጉት እነርሱ ምሕረትን ሲያገኙ ያ አዕምሮ የጐደለውን
ደሃ ግን ዘወር ብለው ሲያዩት ወደ ድንጋይነት ተቀይሮ ነበር::
ነፍሱንም: ሥጋውንም በፈቃዱ አጠፋ::
የአይሁድ አለቃም ዐይነ ሥውር ዘመድ ነበረውና ወዲያው
አምጥቶ ከደሙ ቢቀባው ዐይኑ በራ:: ታላቅ ደስታም በዚያ
ሥፍራ ተደረገ:: ነገሩን የሰሙት #ቅዱሳን #ቴዎፍሎስ እና
#ቄርሎስ ሲመጡ ደሙ ከመፍሰስ አላቆመም ነበር::
በተአምሩ ደስ ተሰኝተው: ከደመ ክርስቶስ ለበረከት ተቀቡ::
የፈሰሰውን #ቅዱስ_ደም ከነ አፈሩ አንስተው: መስቀሉን
በትከሻ ተሸክመው: በፍፁም እልልታና ዝማሬ ወስደው በቤተ
መቅደስ አኑረውታል:: የከተማዋ ሁሉም አይሁድም
በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል::
#ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ _መላዕክት
#ሢመት
ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ7ቱ ሊቃነ
መላእክት በደረጃው 3ኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት
እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በ10 ከተማ
ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች::
በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ 10ሩ ነገድ አለቃ
(መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል::
በሁዋላም "#መጋብያን " በሚባሉ በ23ቱ ነገድ ላይ
ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት::
#ቅዱስ_ሩፋኤልና_ሐዋርያት
አንድ ቀን #ጌታችን_ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ
ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት::
ጌታም 3ቱን ሊቃናት ( #ሚካኤል: #ገብርኤል እና #ሩፋኤል
) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው::
ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው" አለው::
እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው::
በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ
የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ::
#ረዳትነት
በመጽሐፈ #ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ
መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ:
ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዐይን
አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን
ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል::
#ቅዳሴ ቤት
ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ
ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ #ቴዎፍሎስ
ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ
የታነጸው በአሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ
አጋዥነትም ለ300 ዓመታት አገልግሏል::
#ቅዱስ_ሩፋኤል
¤መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
¤አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
¤መዝገበ ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
¤ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት
መሪ)
¤ፈታሔ ማሕጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማሕጸን
የሚፈታ)
¤መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል::