ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ወመካነ ጻድቃን ብሩካን፡፡ በርገመ ጌባል ያልወደቀባቸው ኃጢአተ አዳም የሌለባቸው ንዑህቤየ ብሩካኑ ለአቡየ የተባሉ የጻድቃን ስማቸው የተጠራበት እንዳለፈው በል፡፡
ወመካነ መላእክት ትጉሀን፡፡
ጸሐይ ከመመላለስ ጸሐይ ከመፍሰስ እንዳያቋርጥ ምስጋና የማያቋርጡ የመላእክት ስማቸው በተጠራበት በተ ክርስቲያናቸው በታነጸበት ታቦታቸው በተቀረጸበት ስዕላቸው በተሳበት፡፡ #በህበ ኩሉ መካን በቦታው ሁሉ ርእስት እንቲ፡፡ ገዢ አለቃ ነሽ ወአርሶ ለጴጥሮስ ንነዲል ታሪክ ቤተ ክርሰቲያን ቅሉ መጀመሪያ በፊልጵስዮ የተሰራ በእሷ ሰም ነውና፡፡ ጳውሎስና በርናባስ ፊልጵስዮስ ገብተው አስተማሩ፡፡ ሕዝቡም አመኑ፡፡ ተጠመቁ ካመናችሁ ከተጠመቃችሁ እንግዴህ ወይ ቤተ ፃዖት አትሂዱ አሏቸው የለመድነውንም ከነሳችሁን መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡ አምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ብሎ አዟቸው አረገ፡፡ ሐንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ ከዚያ ወዲህ ነው እሰኪል ድረስ እንደ መጀመሪያው ታሪክ ተርከው፡፡ ምሳሌውንና ጥቀሱነ ጨምረህ ነው፡፡ እንድም ርስት ይላል ርስት ነሽ #ሐተታ፡- ፡፡ ሲሶ ለነጋሽ ሲሶ ለአንጋሽ ሕዝብ ሲሶ ለቀዳሽ ነው
እመቤታችንም በጽሕፈትም በቅርጽም በምስጋንም ሲሶ አላትና፡፡ በጸሐፈት ከላይ አልፋ ወዖ የጌታ ስም፡፡ ሁለተኛ ዮሐንስ ሦስተኛ ምስለ ፍቁር ወልዳ ነው፡፡ ይህ ታቦቱ ታቦተ ማርያም ታቦተ ኢየሱስ ታቦተ ዮሐንስ ቢሆን ነው፡፡ ታቦቱ ሰማዕት ጻድቅ የሆነ እንደ ሆነ አልፋ ወዖ የጌታ ዮሐንስን ዘረፈቀ ውስተ ሕጹ ይለዋልና አሰጠግቶ ታቦቱ ሰማዕትም ሦስተኛ ምስለ ፍቁር ወልዳን፡፡ ባቀራረጽም ከላይ ሥላሴን፡፡ ዝቅ ብሎ እመቤታችንን አንገቷን አቅንቶ ይቀርጻል፡፡ ዝቅ ብሎ ሰማዕትም ጻድቅም ቢሆን ባቤቱን አሰታጥቆ አንገቱን ወይ
አመቤታችን አቅንቶ ይቀርጸል፡፡ እሱ ከሱዋ እሱዋ ከሥላሴ የሚያማልዱን ሰለሆነ በምሰጋናም መጀመሪያ ተአምረ ማርያም ቀጥሎ ጻድቅም ሰማእትም ቢሆን የባለቤቱን ቀጥሎ ተአምረ ኢየሱስ ነውና አንድም ርስተ ሰማይም ርስተ ምድርም የተገኘ ጌታ ከእመቤታችን ሰው ከሆነ በዲህ ነውና፡፡ አንድም የምነቀበለው ስጋው ደሙ ከእሷ የነሳው ነውና፤ አጽመ ርስቴን በላሁ አንዲሉ ፡፡
ወስሉት ስምኪ በህበ እግዚአብሔር፡፡
ስምሽም በእግዚአብሔር በማማለድ ስሉጥ ነው ይህም በአንድ ሰው ታውቋል ታሪክ እጅግ ገንዘቡ የበዛ የተፈው አንድ ባለጸጋ ነበረ ለአዝማሪ ለዘዋሪ እየሰጠ አለቀበት፡፡ አንድም የዚህ ዓለም ገንዘግ ሲሰበሰብ እንጂ ኢጠፋ አይታወቅም እና ህልፈቱ ቅድም አስተርእዮቱ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ ገብሬ በኖሩኩበት ሀገር ተዋርጄ፤ ሰጥቼ በኖርኩበት ሀገር ለምኜ አልኖርም ብሎ ሀገር ጥሎ ቁርበት ጠቅልሎ ሲሄድ ሰይጣን የጨዋ ልጅ መስሎ ከጎዳና ቆይቶ ወዴት ትሄዳህ አለው ከብሬ በኖርኩበት ሀገር ተዋርጄ ሰጥቼ በኖርኩበት ሀገር ለምኜ
አለኖረም ብዬ ነው ሀገር ጥዬ ቁርበት ጠቅልዬ መሄዴ ነው ያዘነ መስሎ ደንጊያውን በምትሀት አስመስሎ ይህን ብሰጥህ አትመለስምን አለው፡፡ ይህንንማ ካገኘሁ ስንኳን ለእሙ ለልጅ ልጄ አይበቃምን ከዚህ በኋላ ሰጠው አንተም ፍቃዴን ፈጽምልኝ አለው ምን ላድርግልህ አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስን ካድልኝ ማእክት ጻድቃን ሰማእታት አያማልዱም በል አለው ካደ አያማልዱም አለ ከተለያዩ በኋላ ነገር ረስቼ ዎየሁን ምእመናን አፍረው አክብረው ስሟን የሚጠሯት ማርያም የምትባል አለች፡፡ ወላዲተ አምላክ መሆኗን ካድልኝ የለማኝ ምርኩዜን ምን ይዞ ይሄዷል ጉዞ እንዲሉ እሷስ አየሆንም አንኪያስ አምጣ ብሎ ወርቅ እስመስሎ የሰጠወን ደንጊያ ተቀብሎ ልብ ራሱን ብሎ ገደለው ወዲያውኑ መላእክተ ጽልምት መጥተው ነፍሱን ከስጋው ለይተው እጅ አድርገዋታል፡፡ መላእክተ ብርሀንም የጌታን ቁርጽ ፍርድ ሳያዩ አይለዩምና እመቤታችን ዘንድ ሄደው ምነው ዝም አልሽ ከስጋዋ የተለየች ባንች ምክንያት አይደለምን አታማልጅምን አሏት፡፡ እሷም መሃር ሊተ ወልድየ ዛቲ ነፍሰ አለችው፡፡ ከልብኑ ይትምሀር፡፡ አባቴን እኔን የባህርይ ህይወቴ መንፈስ ቅዱስን የወዳጆቼ የማእክት የታድቃን የሰማእታት አማላጅነታቸውን የካደ ይማራልን አላት፡፡
#ዘጸውአ ስምኪ ወዘገብረ ተዘካርኪ እምህር ለኪ ያልኸውን ቃል ይታበላልን አለችው፡፡ ያውስ ቢሆን ምግባር ነው እንጂ ሐይማኖት ነውን ከገር ግን ከስጋስ ስጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቼ ሰው መሆኔ ፍቃድሽን ላልፈጽምልሽ ነውን ምሬልሻለሁ እንኪያስ ከማረህልኝ ነፍሱን ከስጋው አዋህደህ አስነሳልኝ ነፍሱም ከስጋው ጋራ አዋህዶ አስነሳላት ለምን ካድህ አለችው ባጣ አላት ያጣ ይለምናል እንጂ ይክዳል አሁንም ከልጄ አማልጄህ አንዲህ ካለ ቦታ ምግብህን አዞልሀልና ሂድ አለችው፡፡ በዚያች ቦታ አንድ ባለጸጋ ነበረ አንዲት መልከ መልካም ልጅ ነበረች ባለጸጋው መጥቶ ልጅህን ስጠኝ ያለው እንደ ሆነ ልጄን በመልክ አትተካከላተም ይለዋል፡፡ መልከ መልካም መጥቶ ስጠኝ የለው እንደ ሆነ ልጄን በገንዘግ አትተካከላትም ይለዋል፡፡ አንዲህ አድረጎ ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ያኖራት ነበር፡፡ በዚያች ቀን እመቤችን ከቤተ ክርሰቲያን እንዲሄድ አድረጋዋለች፡፡ የባጸጋ ጸሎት አጭር ነውና
የሰጠኸኝን አትንሣኝ፡፡ ይህችን አንዲት ቅነተጣት ልጄን ባርክልኝ ብሎ ተቀመጠ ወዲያው ተደሞ መጣበት፡፡ ያም ሰው ጠፈር ጠፈሩን እያየ ሲዞር ከሱ አተገብ ደርሶ ቆመ፡፡ ልጅህንም ከብትህንም ለዚህ ሰው ስጠው አለችው ቀና ቢል አየው፡፡ ከዚህ በኋላ ወስዶ ልጁንም ከበቱንም ሰጥቶት ወድያው ወረፈ፡፡ ስሱም ቆርቦ የእመቤታችን ስሟን ሲጸረ ዝክሯን ሲዘክር በዚህ ጊዜ ያልፋል፡፡ የመይባል መንግሥተ ሰማያትን አውርደሰዋለችና አንዲህ አለ፡፡ ፩ዱ ነዳይ ዘክሕደ ሃማኖተተ ኪያ ከሐደ ቦበ ዐበየ በቅድመ ሰይጣን ዘአስሐቶ አሚነ ኢዘኪ ድንግል ለአድኀኖ ነፍሱ በቁዐቶ እንዘ ሰብሕ ተአምረኪ ወለጸጌኪ ምህረቶ ተንሥአ እምንዋሙ ወእተወ ሰቤቶ አንዳለ ደራሲ፡፡
#ይ ዲ እለ ትነብሩ ተንሥኡ ብቅዳሴ ጊዜ የተቀመጣችሁ ተነሡ፡፡ አሁን በቅዳሴ ጊዜ ከህሙም ከአረጋዊ በቀረ የሚቀመጥ ኑሮ አይደለም፡፡ ከዓራቱ ዝንጋዔ በተዘክሮ ከዓራቱ ሐኬት በአንክሮ ተነሡ ሲል ነው፡
#ይ ካ ንትነሣእ በፍርሃት እግዚአብሔር፡፡ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ምርኩዝ አድገን እንነሣ
ይበል ፊሪሃ እግዚብሔርን በትር ነምፈሳዊት ይላታልና #ሐተታ ዲያቆኑ ቢያዝዝ አይሰሙትምና ቄሱ ንትነሣእ ይላል፡፡
ከመ ናዕብያ ወንወድሰ ለምልእተ ውዳሴ፡፡ ምስጋናን የተመላች እመቤችንን ፈጽመን እናገናት እናመስግናት ዘንድ፡፡
አንዘ ንብል ኦ ምልእተ ጸጋ፡፡
ጸጋ ሰማያዊን ጸጋ ምድራዊን የተመላሽ፡፡
ኦ ሙሐ ፍሥሓ፡ የደስታ መገኛ የምትሆኝ እመቤችን #ሐተታ፡፡ መልአኩ ተፈሥሒ ፍሥሕት ያላት እንደ ነቅዕ እንደ እሰትንፋስ ሳያቋርጽ ሲነገረ ይኖራልና አንድም ጻጋን ፍሥሓን አንድ ወገን አድርጎ የጌታ መገኛ የምትሆኝ እመቤታችን እያልን እናገናት እናከለብት ዘንድሰ እንነሣ ይበል፡፡
#ፈድፋደ ብኪ ግማ ራዕይ ዘየወቢ እምኪሩቤል እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ፡፡
ዐይናቸው ብዙ ከሚሆን ከኪሩቤል፡፡ እለ 6 ከነፈሆሙ ክንፋቸው ስድስት ከሚሆን ከሱራፌል ይልቅ መልከ አለሽ፡፡ አንድም የመወደድ ግርማ የባለሟልነት መልክ አለሽ ፈድፋደ ይላል በዘልሽ መፈራት በአጋንንተ በመናፍቃን በአይሁድ ዘንድ በለሟልነት በሥላሴ ዘንድ ነው፡፡ እለ ብዙኃት አዕይቲሆሙ ያላቸው፡፡ እለ ስድስቱ ከነፊሆሙ ዩላቸው እለ ቡዙሀት አዕይንቲሆሙ ካላቸው ይገባሉ፡፡ #ሐተታ፡- ከነገደ ኪሩቤል ገጸ ላህም ገጸ ብእሲ ከነገ ሱራፌል ገጸ ንስር ገጸ አንበሳን አውጥቶ መንበሩን አሸሟቸዋል፡፡ #እለ ብዙኋት አዕይቲሆሙ አለ ከፊት ከገንራቸው እስ