ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን #አብርሃም : #ይስሐቅ
እና #ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞
እኒህ ቅዱሳን ከሰው ወገን እጅግ ክቡራን ከመሆናቸው የተነሳ መንግስተ ሰማያት በእነርሱ ስም
ተጠርታለች:: ጽድቃቸውና ክብራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ነውና ጽፈንም: ተናግረንም
አንፈጽመውም:: እንዲሁ "ዕጹብ! ዕጹብ!" እያልን
ፈጣሪያቸውን ከማመስገን በቀር::
+"#ቅዱስ_አብርሃም_ርዕሰ_አበው "*+
የሃይማኖት: የደግነት: የምጽዋት: የፍቅር አባት
የሆነው አብርሃም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት
አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ
የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::
¤በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ
ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ
እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ::
"አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ::
መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን
አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::
¤"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ
አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ
አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ
ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን
እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ
የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
¤ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ
ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት
ሔደዋል:: ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ #አብርሃም
እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ
የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው::
¤ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው::
የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ
አባታችን አብርሃም፡
የሕዝብና የአሕዛብ አባት የሆነው አብርሃም
እግዚአብሔርን አምልኮ: ጣዖታትን ሰብሮ ወደ # ከነዓን
ከወጣ በሁዋላ ብዙ ችግርን አሳልፏል:: በረሃብ
ምክንያት ከአንድም 2 ጊዜ ወደ ግብጽና ፍልስጥኤም
ተሰዷል:: በዚያ ግን ፈጣሪው አክብሮታል::
¤2ቱ ነገሥታት (ፈርኦንና አቤሜሌክ) ሣራን እንነካለን
ቢሉ ተግሣጽ ደርሶባቸዋል:: #ነቢይ ነውና በአብርሃም
ጸሎት ተፈውሰዋል:: ቅዱስ አብርሃም ከደግነቱ የተነሳ
በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ) ላይ ድንኩዋን ሠርቶ
እንግዳ ይቀበል ነበር:: ምሥክር ሳይይዝም እህል
አይቀምስም ነበር::
¤ሰይጣን ከፍቶ እንግዳ ቢያስቀርበት ያለ ምግብ ለ3 ቀናት
ቆይቷል:: በፍጻሜውም #ሥላሴ በእንግድነት
መጥተውለት በክብር ላይ ክብር: በጸጋ ላይ ጸጋ:
በጣዕም ላይ ጣዕም ተጨምሮለታል:: እርሱ የሥላሴን
እግር ያጥብ ዘንድ: በጀርባውም ይሸከማቸው ዘንድ
አድሎታልና:: ሥላሴም በቤቱ ተስተናግደው: ልደተ
ይስሐቅን አክብሥረውታል:: ጻድቁ ሰውም በፈጣሪው ፊት
ስለ ሰዶምና ገሞራ ለምኗል::
¤አብርሃም በአምልኮው ፍጹም ነውና የሚወደውን ልጁን
ይስሐቅን ለመስዋዕት አቅርቧል:: በዚህም የነቢያት:
የሐዋርያት: የነገሥታት: የካህናት አባት:
#ሥርወ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ሥር) ተብሏል::
ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ አያቱም ተብሏል::
¤አንድ ቀን #እግዚአብሔር መላእክቱን "ብየ አርክ
አብርሃም በዲበ ምድር - በምድር ላይ ወዳጄ አብርሃም
አለ" አላቸው:: ያን ጊዜ 99ኙ ነገደ መላእክት
ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ:-
*"አብርሃም አርከ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ወዳጅ)"
*"አብርሃም ብእሴ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ሰው)"
*"አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር አገልጋይ)"
*"አብርሃም ምዕመነ እግዚአብሔር
(አብርሃም የእግዚአብሔር ታማኝ)
"አብርሃም ፍቁረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ተወዳጁ ነው) እያሉ አሰምተው
ተናግረዋል::
¤አባታችን አብርሃም በክብር: በቅድስናና በሞገስ
ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ተጠቅሷል::
ፈጣሪ በስሙ ለቅዱሳን ተለምኗል:: ስለ ክብሩም
በሲዖል ውስጥ እንኩዋ ማረፊያን ሠርቶለታል::
አጋንንትም ሊቀርቡት አልተቻላቸውም:: ያረፈውም
ከክርስቶስ ልደት 1,900 ዓመታት በፊት ነው::
እድሜውም 175 ዓመት ነበር::
*ፍቅሩን የተረዱ ሊቃውንት ድንግል ማርያምን "ሐይመቱ
(ድንኩዋኑ): ተናግዶቱ (እንግድነቱ) ለአብርሃም" ሲሉ
አመስግነዋታል:: ሊቁም:-
"አብርሃም ፍጹም በሒሩት ወበአምልኮ:
እግዚአብሔር አዕበየከ ወባረከከ ባርኮ:
እስከ ሰመየከ ዲበ ምድር አርኮ::" ብሎ በምሥጢር
ገልጾታል::