ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ቅዱስ ብስንድዮስ ጻድቅ
ቅዱስ_ብስንድዮስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ድንቅ ሥራ
ከሠሩት እንደ አንዱ ሆኖ ይዘከራል:: ቅዱሱ ግብፃዊ
ሲሆን በልጅነቱ ወደ ትምሕርት ቤት ገብቶ ቅዱሳት
መጻሕፍትን ተምሯል:: የሚገርመው የብሉይም ሆነ
የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በሙሉ ያጠናቸው በቃሉ ነበር::
በርግጥ ይሕንን ማድረግ የቻሉ በርካታ የሃገራችን
ሊቃውንት ዘንድሮም አሉ:: ልዩነቱ ግን ወዲህ ነው:: ቅዱስ
ብስንድዮስ መጻሕፍቱን ያጠናቸው ለሕይወት እንጂ ለእውቀት አልነበረምና ሁሌም ነግቶ እስከሚመሽ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እያጣጣመ ይጸልይ ነበር:: ይሕንን ሲያደርግ ደግሞ
ባጭር ታጥቆ:
ጫማውን አውልቆ:
በባዶ ሆዱ ቁሞ ነው::
ታዲያ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ክፍል ሲጸልይ #ነቢይ
ቢሆን #ሐዋርያ ወደ እርሱ ይወርድለት ነበር:: ለምሳሌ
#ዘፍጥረትን ሲጸልይ ሊቀ ነቢያት #ሙሴ ይመጣና ከፊቱ ተቀምጦ ይሰማዋል:: #ትንቢተ_ኢሳይያስ ላይ ሲደርስ
#ኢሳይያስ : #ወንጌለ_ማቴዎስ ላይ ሲደርስ
#ቅዱስ_ማቴዎስ ይመጡና ደስ እያላቸው ያደምጡት
ነበር:: አንዱ ነቢይ: ወይ ሐዋርያ ሲወጣ ቅዱስ ብስንድዮስን
ባርኮ ሌላኛውን ተክቶ ነው:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሕይወት በምድር እያለ ሰማያዊ ሆነ:
81ዱን አሥራው መጻሕፍት የጻፉ ቅዱሳንን ለማየት በቃ:
በእጆቻቸውም ተባረከ::
የቅዱስ ብስንድዮስ ቀጣይ የሕይወቱ ተግባር ብሕትውና
ሆነ:: ዓለምንና ግሳንግሷን ትቶም ወደ በርሃ መነነ::
በአጽንዖ በዓት: በጾምና በጸሎት:
በትሕርምት ተጋደለ:: በየደረሰበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር
በእጆቹ ድንቅ ተአምር ይሠራ ነበር:: ብዙ ድውያንን ፈወሰ:
አጋንንትንም ከአካባቢው አሳደደ::
በነዚህ ሁሉ ጊዜያት ግን ስዕለት ስላለበት ሴቶችን ላለማየት ይጠነቀቅ ነበር:: በሆድ ሕመም ትሰቃይ የነበረችና ጥሪቷን በመድኃኒት የጨረሰች አንዲት ሴት ስለ ቅዱሱ ዝና ትሰማለች:: ችግሩ ግን እርሱ ከውዳሴ ከንቱና
ከሴት የሚርቅ ነውና እንዴት ብላ ታግኘው? አንድ ቀን ከበዓቱ አካባቢ ተደብቃ ውላ ሲመጣ የልብሶቹን ዘርፍ ለመንካት በእምነት አሰበች:: ልክ ከበዓቱ ሲዘልቅ # ስሉጥ (ፈጣን) ነበርና ገና እንዳያት ሩጦ አመለጣት:: እንዳትከተለው ድውይ ናትና
አልቻለችም::አዝና ዝቅ ስትል ግን የረገጠውን ኮቲ ተመለከተች:: በፍጹም ልቧ : በእምነት "የጻድቁ አምላክ ማረኝ" ብላ ከአፈሩ ቆንጥራ በላች:: ደቂቃ አልቆየችም:: ፈጥና ከደዌዋ ዳነች:: እንደ እንቦሳ እየዘለለች ወደ ከተማ ሔዳ ተአምሩን ተናገረች:: ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ
#ቅፍጥ (Qift) በምትባል ሃገር ዽዽስናን (እረኝነትን) ተሹሟል:: ወደ ከተማ ሲገባ የቀደመ ተጋድሎውን ቸል አላለም:: ይልቁኑ ይተጋ ነበር እንጂ:: ከብቃት መዓርግ
ደርሷልና ሲቀድስ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በገሃድ
ያየው : ሠራዊተ መላእክትም ይከቡት ነበር:: ሕዝቡ ሊቆርቡ ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት
በግንባራቸው ተጽፎ ይታየው ነበር:: የበቁትን እያቀበለ :
ያልበቁትን እየመከረና ንስሃ እየሰጠ ይመልሳቸዋል::
እንዲሕ በጽድቅ : በሐዋርያዊ አገልግሎትና በንጽሕና
ተመላልሶ ቅዱስ ብስንድዮስ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ቅዱስ ብስንድዮስ ካረፈ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩ ከመግነዙ ጥቂት ቆርጦ አስቀርቶ ብዙ ድውያንን
ፈውሶበታል::
ቸር አምላክ ለአባቶቻችን የሰጠውን ጸጋ ለእኛ
ለባሮቹም አይንሳን:: ከቅዱሱ በረከትም ያድለን::
ከገነት በተሰደደ ጊዜ #የአዳም ተስፋ አንቺ ነሽ፡፡ በግፍ የተገደለ #የአቤል የውሃቱ አንቺ
ነሽ፡፡ #የሴት ቸርነት አንቺ ነሽ፡፡ #የሄኖክ ሥራዎቹ ከክፉ ጥፋት የዳነባት #የኖህ መርከብ
#የሴም ቡራኬው ዕድል ፈንታውም አንቺ ነሽ፡፡
# የአብርሃም እንግድነት #የይስሃቅ መዓዛ #የያዕቆብም መሰላል አንቺ ነሽ፡፡
#ዮሴፍንም የምታረጋጊው አንቺ ነሽ፡፡
#የሙሴ ጽላት #ጳጦስ የተባለች የሲና ዕፅ በካህን #አሮን ልብስ የነበረች ጸናጽል
ዳግመኛም የበቀለች እና ያበበች ያፈራችም በትር አንቺ ነሽ፡፡ #የኢያሱ የምስክሩ ሐወልት
#የጌድዮን ፀምር #የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ እና የዘይት ቀንድ አንቺ
ነሽ፡፡ የተመካባት #የዕሴይ ሥር #የአሚናዳብ ሠረገላ #የዳዊት መሰንቆ #የሰሎሞንም
አክሊል አንቺ ነሽ፡፡ የታጠረች ተክል የተዘጋች የውሃ ምንጭ አንቺ ነሽ፡፡ #የኤልያስ የወርቅ
መሶብ #የኤልሳዕ ጋን አንቺ ነሽ፡፡ #ኢሳይያስ ፅንስን ከድንግልና ጋር የተናገረልሽ #ዳንኤልም ያለሩካቤ መውለድን የተናገረልሽ አንቺ ነሽ፡፡ #ፋራን የምትባል #የዕንባቆም
ተራራ የተዘጋች #የሕዝቅኤል ምስራቅ የቤቴ-ልሔም ሕግ መውጫ #ኤፍራታ የምትባል
ምድር አንቺ ነሽ፡፡ #የሲሎንዲስ ዕፀ ሕይወት #የናሆምንም ቁስል የምታድን #የዘካርያስ
ደስታው #የሚልክያስ ንፅሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ፡፡