ክፍል ፩
#የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው #“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
#ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም #በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
#ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው #ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· #ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· #ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· #ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
#“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
#“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡
©ቅዳሴ ማርያም ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ክፍል ፪
፪. ወዶም አልቀረም ዘር ምክንያት ሳይኾነው ከድንግል በሥጋ ተወለደ፡፡ “አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትሥብእቱ- በመለኮቱ የማርያም ልጅ አይደለም፤ በተዋሐደው ሥጋ ነው እንጂ” እንዲል ድርሳነ ቄርሎስ በመለኮት ሳይኾን በሥጋ ተወልዶ አዳነን፡፡
ከእናንተ መካከል፡- “ልደቱ በዘርዕ ያላደረገው እንበለ ዘርዕ ያደረገው ስለ ምንድነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
· አንደኛ፡ “ልደት ቀዳማዊ ተዐውቀ በደኃራዊ” እንዲል ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደ ተወለደ ለማጠየቅ፤
· ኹለተኛ ደግሞ ሊቃውንቱ እንደሚነግሩን በዘርዕ በሩካቤ ተወልዶ ቢኾን ኖሮ መናፍቃን “ዕሩቅ ብእሲ ነው” ባሉት ነበርና ነው፡፡ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ሲያብራራው፡- “ሰውም በኾነ ጊዜ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ አልተወለደም፤ አምላክ ሰው ኾነ እንጂ፡፡ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢኾንስ ብዙ ሰዎች በተሳሳቱ ነበር፤ አምላክ ሰው መኾኑንም ሐሰት ባደረጉት ነበር” ይላል /ሃይ.አበው. ፷፡፲፱/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፡- “እንደ እኔስ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢኾን ብዙ ሰዎች ዕሩቅ ብእሲ ባሉት ነበር፤ አምላክነቱንም በካዱት ነበር” ይላል /ሃይ.አበ. ፷፮፡፴፪/፡፡
አሁንም ከእናንተ መካከል፡- “ያውስ ቢሆን ተፈትሖ ካላት ያላደረገው፣ ተፈትሖ ከሌላት ያደረገው ስለ ምንድነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
· አንደኛ “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች” ተብሎ የተነገረውን /ኢሳ.፯፡፲፬/ ለመፈጸም ሲኾን፤
· ኹለተኛው ደግሞ ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ይኸውም አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል /ዘፍ.፩፡፳፮/፤ ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል /ሕዝ.፵፬፡፩/፡፡ ሔዋን በኅቱም ገቦ (ጐን) ተገኝታለች /ዘፍ.፪፡፳፩/፤ ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል፡፡ ቤዛ ይሥሐቅ የሚኾን በግዕ ከኅቱም ጉንድ ተገኝቷል /ዘፍ.፳፪፡፲፫/፤ ቤዛ ዓለም ክርስቶስም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል፡፡ ጽምዐ እስራኤልን ያበረደ ውሃ ከኅቱም እብን (ዐለት) ተገኝቷል /ዘጸ.፲፯፡፮/፤ ጽምዐ ነፍሳትን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡ ጽምዐ ሶምሶንን ያበረደ ውሃ በኅቱም መንሰከ አድግ (የአህያ መንጋጋ) ተገኝቷል /መሳ.፲፭፡፲፱/፤ ጽምዐ ኃጥአንን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡ የዚህ ኹሉ ምሳሌ ፍጻሜው አንድ ነው፡፡ ይኸውም ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘ከመ ትኩን መራሒተ ለሃይማኖት ዐባይ - ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ’ /ሃይ.አበ.፷፮፡፴፪/ እንዲላት እመቤታችን ጌታን ብትወልደው ማኅተመ ደንግልናዋ እንዳልተለወጠ ኹሉ እርሱም ሰው ሲኾን አምላክነቱ ላለመለመጡ ምሳሌ ነው፡፡ ዳግመኛም እርሷ “ድንግል ወእም” ስትባል መኖሯ እርሱም “አምላክ ወሰብእ” ሲባል ለመኖሩ ምሣሌ ነው፡፡
እናም አዳምን ያድነው ዘንድ የፈቀደ አምላክ ከይሲ ዲያብሎስ ያሳታት ሔዋንን “ጻርሽን ጋርሽን ምጥሽን አበዛዋለሁ” ብሎ እግዚአብሔር ከፈረደባት በኋላ ሊቁ አባ ሕርያቆስ “ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኀያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት- የሰው ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ጐትቶ አወረደው፤ ከሞትም አደረሰው” እንዲል /ቅዳ.ማር. ቁ. ፻፳፭/ ሰውን ወደደና ሔዋንን ነጻ አደረጋት /ገላ.፭፡፩/፡፡ ሔዋንን ነጻ ካደረገ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፫. ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ የፈቀደ፣ ሔዋንንም ወድዶ ነጻ ያደርጋት ዘንድ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /ዮሐ.፩፡፲፬/፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም የመለኮት ብቻ ወይም የትስብእት ስም ብቻ አይደለም፡፡ “ወእነግር አነሂ ከመ ኢመፍትው እስምዮ ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእንበለ ትስእብት ወኢ ለትስብእት ዘእንበለ መለኮት ክርስቶስሀ ይሰመይ ወእም ቅድመ ትሥጉት አልቦ ዘይሰምዮ በዝንቱ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ- ክርስቶስ ሲል ብትሰማ ብቻ አምላክ እንደኾነ ብቻ ሰውም እንደኾነ አታስብ፡፡ አንድ እንደ መኾኑ ሰው የኾነ አምላክ ነው እንጂ” /ሃይ.አበ.፷፰፡፵/ እንዲል ከኹለት አካል አንድ አካል ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢኾን የወጣለት ስም ነው እንጂ፡፡
አዳምን ነጻ ያደርገው ዘንድ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ ላይ አደረ /ዮሐ.፩፡፲፬/፡፡ ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ ክብር የሚኾን ክብሩንም አየንለት፡፡ ልጅ ለአባቱ አንድ የኾነ እንደኾነ ደጃፍ የመለሰው ማጄት የጎረስው ኹሉ ገንዘቡ ነው፡፡ ለእርሱም “እስመ ኵሉ ዘቦ ለአቡየ ዚኣየ ውእቱ- ለአብ ያለው ኹሉ የእኔ ነው” /ዮሐ.፲፮፡፲፭/ እንዲል የአብ ገንዘብ ኹሉ ገንዘቡ ነውና ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ የሚኾን ክብሩን አየንለት፡፡ “ወይሰገድ ከመዋሕድ- እንደ አባቱ ይመለካል” እንዲል ለአባቱ እንደ አንድ ልጅነቱ የሚኾን ክብሩን አየንለት፡፡ የአባቱን ጌትነት በደብረ ሲና እንዳየነ /ዘጸ.፲፱/ የእርሱንም ጌትነት በደብረ ታቦር አየንለት /ማቴ.፲፯፡፩-፰/፡፡ አባቱ በኤልያስ አድሮ አንድ ምዉት /፩ኛ ነገ.፲፯/፣ በኤልሳዕ አድሮ ኹለት ምዉት ሲያስነሣ እንዳየነው /፪ኛ ነገ. ፬/፤ እርሱም ሥጋን ተዋሕዶ የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን ሲያስነሣ አየነው /ዮሐ.፲፩/፡፡ ይህን ጠቅለል አድርጐ ቅዱስ ባስልዮስ ሲናገረው፡- “ስለ አብ የተናገርነው ኹሉ ለወልድ ገንዘቡ ነው፡፡ በመልክ ይመስለዋል፤ በባሕርይ ይተካከለዋልና፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ ለአባቱ አንድ እንደ ኾነ ልጅ ክብር ያለ ክብሩን አየን አለ” ይላል /ዮሐ.፩፡፲፬፣ ሃይ.አበ.፴፫፡፳፰/፡፡
የመጽሐፍ ልማድ ኾኖ የብሉዩን ለአብ የሐዲሱንም ለወልድ ሰጥቶ ተናገረ እንጂ ኹሉም በኹሉ አሉ፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ያውስ ቢኾን (ቅዱስ ኤፍሬም) ወዴት ነበርና ነው አየንለት የሚለው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- አየንለት የሚለው የብሉዩን የእነ ሙሴን ዐይን ዐይን አድርጎ፤ የሐዲሱን ደግሞ የእነ ጴጥሮስን ዐይን ዐይን አድርጎ መናገሩ ነው፡፡ ይኸውም አባ ሕርያቆስ የሓዋርያትን መብል መብል አደርጎ፡- “በላዕነ ወሰተይነ ምስሌሁ - ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን” እንዳለው ማለት ነው /ቅ.ማር. ቁ.፹፮/፡፡
ይህ ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የኾነው ክብሩን ያየንለት ወዳጅ ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ፡፡ ይቅር ይለን ዘንድ ከወደደ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፤ እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

ክፍል ፫
፭. ባሕርየ ዕጓለ እመሕያው (ሰው) ሆይ! እግዚአብሔር ሰውን ወዶታልና በውሰጥ በአፍአ፣ በነፍስ በሥጋ ደስ ይበልህ፡፡ “ወዶ ምን አደረገለት?” ትለኝ እንደኾነም “በእርሱ የሚያምን ኹሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” ተብሎ እንደተጻፈ /ዮሐ.፫፡፲፮/ ልጁን ለሕማም ለሞት እስከ መስጠት ደርሶ ለቤዛ ሰጥቶለታል ብዬ እመልስልሃለሁ፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ረቂቅ ክንዱን ሰደደልን /ኢሳ.፶፩፡፱፣ ፶፫፡፩/፡፡ ነገር ግን ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጐመበተ በ፫ኛው ድርሳኑ “ወልድ ዋሕድ እንደ መላእክት በተላከ ጊዜ ቦታውን የለቀቀ አይደለም፤ በአንድ ፈቃድ ከአባቱ ጋር እያለ ነው እንጂ” ብሎ እንደተናገረው በለቢሠ ሥጋ ነው እንጂ በመለኮት የተላከ አይደለም፡፡ ክንድ ከአካል ሳይለይ የወደቀውን ዕቃ አንሥተው ይመልሱበታል፤ የራቀውንም ያቀርቡበታል፡፡ የአብ ኃይል፣ ክንድ የሚባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የወደቀውን አዳምን ያዳነው ከባሕርይ አባቱ፣ ከአባቱ አንድነት ሳይለይ ነው፡፡
እዱ መዝራዕቱ ከሚባለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
፮. ሊቁ ምስጋናውን ሲቀጥል “እምቅድመ ዓለም የነበረው፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖረው፣ ለኩነት ሥጋ የመጣው፣ ዳግመኛም ዓለሙን ለማሳለፍ የሚመጣው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርሰቶስ ካንቺ ሳይለወጥ ፍጹም ሰው ኾነ” ይላል፡፡ ይኸውም በሌላ አንቀጽ “ባሕርዩን ከፍሎ አልተዋሐደም፤ ባሕርዩንም ሕፁፅ በማድረግ ኹለተኛ እንስሳ አልኾነም፡፡ አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመኾን ምሉ ፍጹም ሰው ነው እንጂ፡፡ የአምላክነትን የሰውነትንም ሥራ ይሠራል፤ ይህስ ባይኾን አንዱ ተለይቶ በቀረ ነበር” ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው /ዮሐ.፩፡፩-፲፬፣ ሃይ.አበ.ዘኤፍሬም ፵፯፡፴፪/፡፡
“ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ በሥራው ኹሉ ከነሣው ሥጋ አልተለየም፡፡” ይህም በኹለት መልኩ ይተረጐማል፡-
፩ኛ፡- “አካላዊ ቃል አንድ ግብር፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አካል ነው እንጂ” ማለት ሲኾን፤
፪ኛ፡- ደግሞ “ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ ሰውም ቢኾን ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ አልተለየም፡፡ አካላዊ ቃል አንድ ኅብረ መልክዕ፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አገዛዝ ነው እንጂ” ማለት ነው፡፡
ሰውም ቢኾን ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ ካልተለየ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኝል፡፡
፯. ዳግማይ አዳም (ክርስቶስ) ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ የቀደመ ሰው አዳምን ከሲዖል ወደ ገነት ከኀሣር ወደ ክብር ይመልሰው ዘንድ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ሊቁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዳግማይ አዳም ማለቱ ከቀዳማዊ አዳም ጋር የሚያመሳስለው ምን ስላለው ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- በቀዳማዊ አዳም ምክንያት የሰው ልጅ በሙሉ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት ነበር፤ በዳግማይ አዳም በክርስቶስ ግን የጽድቅ በር ለኹሉም ተከፍቷል፡፡ ከቀዳማዊ አዳም ጋር አብረው ዕፀ በለስን ያልበሉት ስንኳ ሞት ነግሦባቸው ይኖር ነበር፤ በዳግማይ አዳም በክርስቶስ ትሩፋት ግን የሰው ልጅ በሙሉ የድኅነት መንገድ ተሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ዳግማይ አዳም ሲባል በአዳም የመጣው በደል ክርስቶስ ከሰጠው ጸጋ ጋር ወይም ደግሞ በአዳም ምክንያት የመጣው ሞትና በክርስቶስ የተሰጠው ሕይወት ለማስተካከል ሳይኾን አዳም ለሚሞቱት ኹሉ አባት እንደኾነ ኹሉ ክርስቶስ ደግሞ ትንሣኤ ሕይወት ላላቸው ኹሉ አባታቸው መኾኑን ለመግለጥ ነው /St. John Chrysostom on Romans, Hom.10/፡፡ አንድም በጥንተ ተፈጥሮ ይመስሏልና፡፡
በዕፅ ምክንያት የወደቀ (ከገነት የወጣ፣ ከክብሩ የተዋረደ) አዳም ንስሐ ቢገባም፣ ጩኸቱን ሰምተው ነቢያት ካህናት ቢነሡም እንደ እርሱ ንጽሐ ጠባይዕ አድፎባቸዋልና በግዝረታቸው በመሥዋዕታቸው አዳምን ማዳን አልቻሉም /ኢሳ.፷፬፡፮/፡፡ ነገር ግን “አንሥእ ኃይለከ፤ ፈኑ እዴከ” /ኢሳ.፶፩፡፱/ ያሉትን ልመናቸውን ሰምቶ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወለደ (ሰው ኾነ)፡፡ የአዳምን ባሕርይ ባሕርይ አድርጐ “አዳም ጥንቱንም መሬት ነህ ወደ መሬትነትህ ተመለስ” ብሎ በአዳም የፈረደበትንም የሞት ፍርድ (መከራ) ተቀብሎ ያድነው ዘንድ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና፣ የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ብዙ ኃጢአት ካለች ዘንድ ጸጋ እግዚአብሔር ትበዛለች /ሮሜ.፭፡፳/፡፡ “በአንድ ሰው (አዳም) ምክንያት የገባች ኃጢአት ሕግ በተሰጣቸውና ባልተሰጣቸው ኹሉ እንዲህ ከነገሠች፣ በዳግማይ አዳም በአካላዊ ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠች ጸጋማ እንዴት አብልጣ አትበዛ?” /St. John Chrysostom, Ibid/፡፡ ዳግማይ አዳም ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኚልን፡፡
፰. የሰው ኹሉ አእምሮ በአፍአ በውስጥ በሥጋ በነፍስ ደስ ይላታል፡፡ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ- አምላክ ለኾነ ለሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በአንድነት ምስጋና ይገባዋል፡፡ በምድርም ዕርቅ ተወጠነ፡፡ የሰው ግዕዛኑ ይሰጠው ዘንድ” እያሉ ከመላእክት ጋራ (እንደ መላእክት) ንጉሥ ክርስቶስን ያመሰግኑታል /ሉቃ.፪፡፲፬/፡፡ አንድም “ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ በቃለ አሚን- ” እንዲል የሰው ፍቅር አገብሮት አምላክ ሰው ቢኾን ሰውም አምላክ ቢኾን በመላእክት ዘንድ ምስጋና ተደረገ፡፡ በምድርም አንድነት ተደረገ፤ ኖሎት (እረኞች) ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ /ሉቃ.፪፡፳/፡፡ “ኃጢአትን አጠፋ፤ በመስቀልም ተሰቅሎ ፍዳን አጠፋ፡፡ በመቃብርም ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አጠፋ፡፡ በሲዖልም ሞተ ነፍስን አጠፋ፡፡ ሥራ በሠራበት ኹሉ ድኅነትን አደረገልን” እንዲል የቀደመ መርገመ ሥጋ መረገመ ነፍስን አጥፍቷልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ /ሃይ.አበ.፹፱፡፳፬/፡፡ የጸላኢ የዲያብሎስ ምክሩን አፍርሶበታልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ፡፡ በመቅድመ ወንጌል “ወበከመ ኮነ በጉህለት ተኀብአ ሰይጣን ውስተ ሥጋ ከይሲ ከማሁ ኮነ ድኅነትነ በተሰውሮ ቃለ እግዚአብሔር ዘመድነ- ሰይጣን በተንኰል በሥጋ ከይሲ እንደተሠወረ እኛም ከፍዳ መዳናችን ቃለ እግዚአብሔር በባሕርያችን በመሠወሩ ኾነ” እንዲል በሥጋ ከይሲ ተሰውሮ ቢያስትበት በሥጋ ተሰውሮ አድኖበታልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ፡፡ ዲያብሎስ “ሥጋን በመቃብር ነፍስን በሲኦል ተቆራኝቼ እኖራለሁ” ብሎ ነበርና የመከረባቸውን ሥጋንና ነፍስን ተዋሕዶ አድኖበታልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው ንጉሥ ክርስቶስን አመሰገኑ፡፡ ይኸውም ጥበበኛው ሰሎሞን “ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥ የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል” እንዳለው ነው /ምሳ.፳፩፡፳፪/፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፤ የአዳምንና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤቸውን አጥፍቶላቸዋልና /ቈላ.፪፡፲፬/ “አምላክ ለኾነ ለሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በአንድነት ምስጋና ይገባዋል፡፡ በምድርም ዕርቅ ተወጠነ፡፡ የሰው ግዕዛ

ኑ ይሰጠው ዘንድ” እያሉ መላእክት አመሰገኑት /ሉቃ.፪፡፲፬/፡፡ ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ሥቃይ አጽንቶ “ስመ ግብርናት ጽፋችሁ ብትሰጡኝ አቀልላችኋለሁ” ብሏቸው አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋንም አመቱ በዲያብሎስ ብለው ጽፈው ሰጥተውት ነበር፡፡ ዲያብሎስም ያንን በእብነ ሩካም ጽፎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎት ነበር፡፡ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ኾኖ ሲመጣ ግን ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን ሲጠመቅ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ እንደ ሰውነቱ ተረግጦ አጥፍቶታል፤ በሲኦል የጣለውንም በዕለተ ዐርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ አጥፍቶላቸውና መላእክት አመሰገኑት /ቈላ.፪፡፲፬/፡፡ በዳዊት ሀገር ከዳዊት ባሕርይ የተወለደ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ሔዋንን ነጻ አድርጓቸዋልና አመሰገኑት /መዝ.፻፴፪፡፲፩/፡፡ አዳምንና ሔዋንን ነጻ ካደረጋቸው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፱. በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ኹሉ የምታበራ (ዕውቀትን የምትገልጥ)፣ ጠፈር ደፈር የማይከለክልህ፣ መዓልትና ሌሊትም የማይፈራረቅብህ ብርሃን ዘበአማን (እውነተኛ ብርሃን) ክርስቶስ ሆይ! ስለ ሰው ፍቅር ልሙት ልሰቀል ብለህ ወደ ዓለም በመምጣትህ ፍጥረት ኹሉ ደስ አለው፡፡ አዳምን ከስሕተት፣ ሔዋንንም ከሞት ፃዕረኝነት (ከመጣባቸው ፍዳ) ነፃ አድረገኻቸዋልና ለእኛ በተደረገው ክብር መላእክት ከእኛ ጋር ደስ አላቸው /ሃይ.አበ.፷፰፡፴፪/፡፡ የሰው ፍቅር አገብሮህ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስነህ ሲያዩህ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር” ብለው መላእክት አመሰገኑ፡፡ ከዚህም የተነሣ በጣዕም ላይ ጣዕም በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ እኛም ቅብዐ ትፍስሕት የሚኾን መንፈስ ቅዱስን አንድም ሀብተ ልደትን ተቀብለን ከመላእክት ጋር ደስ አለን፤ አመሰገንንህም፡፡ እንስሳት፣ አራዊት ስንኳ ሳይቀሩ ሰው ከፈጣሪው ጋር በመታረቁ ደስ ብሏቸዋል፡፡
ስርጉት በቅድስና ጽንዕት በድንግልና ቅድስት እመቤታችን ሆይ! ብርሃን ከሚባል ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ይህንን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ዐረገች፤ እርሱም እጅ ነሥቶ ቀርቷል፡፡
አነሣሥቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን፡፡

💚💛 ነሐሴ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር
4.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.አፄ ናዖድ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (ወልደ ያዕቆብ-ልደቱ)
7.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት
🌿 ወርኀዊ በዓላት🌿
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
"መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::" (መዝ. ፹፮፥፩-፮)
@senkesar @senkesar

💚💛 ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም 💛❤️
ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "#ጥንተ_መድኃኒት፤ #የድኅነት_መነሻ_ቀን" ሲሉ ይጠሯታል::
ስለ ምን ነው ቢሉ:-
ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ::
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::"
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::" (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)
ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል::
የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር::
ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::
ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ::
እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::
በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::
እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ"
"ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

#የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡
፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛ ሳሙ.፲፮፡፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡ በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

#፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡
በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡
ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
#፫. ነደ እሳት ሰፍሮባት፤ በነደ እሳት ተከባ (ጫፎቿ) ሳትቃጠል ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፫፡፩-፫/፡፡ ነደ እሳትም ያልኹት ሰው ኾኖ በማኅፀንሽ ፱ ወር ከ፭ ቀን ያደረው ወልደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ምንም እንኳን አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ቢኾንም እሳተ መለኮቱ አላቃጠለሽም፡፡ አባ ሕርያቆስ ይህ ከኅሊናት የሚያልፈውን ነገር ሲያደንቅ ፡- “ቅድስት ድንግልን ለኹሉ ድንቅ የሚኾን የፅንሷን ነገር እንዲህ እያልን እንመርምራት፡፡ ድንግል ሆይ! እሳተ መለኮት በማኅፀንሽ ባደረ ጊዜ አካሉ እሳት ነው፤ መጐናጸፍያው እሳት ነው፤ ቀሚሱ መቋረፍያው እሳት ነው፡፡ እንደምን አላቃጠለሽ? ብለን እንመርምር፡፡ ሰባት የእሳት ነበልባል መጋረጃ በማኅፀንሽ ወዴት ተዘጋጀ? ወዴት ተጋረደ? በቀኝ ጐንሽ ነውን? ወይስ በግራ ጐንሽ ነውን? ሦስት ክንድ ከስንዝር ቁመት የተወሰንሽ ስትኾኚ እንደምን ቻልሽው? የአሥራ አምስት ዓመት ቆንጆ ስትኾኚ አጎበሩ ሻኩራው ነደ እሳት የሚኾን፤ ዐይን የሚበዘብዝ ኪሩቤል የተሸከሙት መንበር ወዴት ተዘረጋ? ወዴት ቆመ?” ይልና /ቅዳ.ማር.ቁ.፸፯-፸፰/ “ኅሊናዬ ይህን አልመረምርም ብሎት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል” ብሎ ይቋጨዋል /ቁ.፹፬/፡፡
ሙሴ ያየው ሐመልማል ነበልባሉን እንዳላጠፋው ኹሉ ጌታም ምንም እንኳን ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽም ነፍስ ነሥቶ ቢዋሐድም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ ፡፡ ሙሴ በአምሳለ ሐመልማል ወነበልባል ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
#፬. አንቲ ውእቱ ገራኅተ ዘኢተዘርዐ ውስቴታ ዘርዕ - ዘር ያልወደቀባት፣ ገበሬ ያልጣረባት ያልጋረባት፣ ለታብቁል (ታብቅል) ባለው ቃል ብቻ ከልምላሜ፣ ከጽጌ (ከአበባ)፣ ከፍሬ የተገኘች ገራኅተ ሠሉስ (የማክሰኞ እርሻ) አንቺ ነሽ፡፡ የወንድ ዘር ሳይወድቅብሽ ፍሬ ሕይወት (የሕይወት መገኛ) ጌታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ካንቺ ተወልዷልና፡፡ አረጋዊው ዮሴፍ በትሩፋተ ደሙ የዋጀሽ /ቅዳ.ማር. ቁ. ፻፳፰/፣ ዕንቁ የተባለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ያገኘብሽ /ሃይ.አበ.፺፮፡፶፭/ የተቈለፈች ሣጥን አንቺ ነሽ፡፡ በዚህ አለ፣ በዚያ የለም የማይሉት ሙሉዕ በኵለሄ የኾነ አካላዊ ቃል በማኅፀንሽ አደረ /መዝ.፻፴፱፡፰/፤ በዚህ ዓለምም ማኅተመ ድንግልናሽ እንደተቈለፈ ወለድሽው /ሕዝ.፵፬፡፩-፪/፡፡ በዕንቁ ከተመሰለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፭. ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት ሲነግሩ የነበሩ፣ አሁን ደግሞ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር” ብለው በደስታ ያመሰገኑትን ጌታን የወለድሽው ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡
የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡- “ኦ ድንግል አምሳል ወትነቢት ዘነቢያት- ነቢያት ትንቢት የተናገሩልሽ ምሳሌ የመሰሉልሽ…” ይላታል /ቅ.ማር.ቁ.፴፯/፡፡ እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ኾኗልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ የሰው ኹሉ ደስታ የሚኾን የመልአኩን ቃል እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ /ዮሐ.፫፡፬-፱/ እንደ ዘካርያስም ሳትጠራጠሪ /ሉቃ.፩፡፳/ አምነሻልና ደስ ይበልሽ /ሉቃ.፩፡፵፭/፡፡ ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታ የወለድሽው ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
፮. በእውነት ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም በሚገባ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡- “ብልህ ሸክላ ሠሪ የሚሠራውን የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም ዕቃ እንዲሠራ፤ እንደዚህም ጌታችን የዚህችን ድንግል ንጹሕ ሥጋዋን ንጽሕት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ሥጋ ሊዋሐደው ፈጠረ” /ሃይ.አበ.፷፮፡፲፬/ እንዲል በቅተሸ ብትገኚ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡
የሔዋን ደኅንነቷ ሆይ! ደስ ይበለሽ፡፡ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግም እንዲህ ይላል፡- “የሕዝቦች ሴቶች ልጆች ሆይ! ከአባቶቻችሁ ስሕተት ነጻ ያወጣችሁን ቅረቡት፤ እርሱንም ማመስገን ተማሩ፡፡ ያ ሔዋን የዘጋችውን የማይናገር አፍ አሁን በእመቤታችን ማርያም ተከፍቷልና ለእኅታችሁ ምስጋናን ለመዘመር ቅረቡ፡፡ አሮጊቷ ሴት (ሔዋን) በምላሶቻችሁ ዙርያ የዝምታን ገመድ ቋጠረች፤ የድንግል ልጅ ግን ጮኻችሁ ታመሰግኑ ዘንድ እሥራታችሁን ፈታ…” /A Metrical Homily on Holy Ephrem, pp 47/፡፡ ከአባቶች አንዱም፡- “እንግዲህስ ሴቶች ኹሉ ሐሴት ያድርጉ፤ አሁን ሴቲቱ ዕፀ በለስን ሳይኾን ዕፀ ሕይወትን አስገኝታለችና፡፡ ዳግመኛም ደናግላን እናቶች ኹሉ በፌሽታ ይዝለሉ፤ ያለመታዘዝን ዕፅ በሴት ተፈውሷልና፡፡ እነሆ ክብሩ ከመላእክት ይልቅ የከበረ ኾኗልና ከእንግዲህ ወዲህ የሴትነት ጾታ የሞትና የውድቀት ምልክት መኾኑ ቀርቷል፡፡ ሔዋን ተፈወሰች፤ ድንግል ግን ከበረች፡፡ እነሆ ድንግሊቱ እናትም አገልጋይም፣ ደመናም ድንኳንም፣ ደግሞም የጌታ ታቦት ኾናለችና፡፡ እንግዲያውስ ኑ! አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ፤ የሔዋን መድኃኒቷ አንቺ ብቻ ነሽ፤ ዓለምን በደሙ የሚገዛትን ጌታ ያስገኘሽ አንቺ ብቻ ነሽ እያልን እናወድሳት” ብሏል፡፡
ፍጥረትን ኹሉ በፀሐይ አብስሎ በዝናብም አብቅሎ የሚመግበውን እርሱ ጡትሽን ይዘሽ አጥተሸዋልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ለመንፈሳውያን ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበውን እርሱን ጡትሽን ይዘሽ አጥብተሸዋልና ደስ ይበልሽ፡፡
ተጠምቀው ሕያዋን ኾነው የሚኖሩበት ማየ ገቦ ከአንቺ ከተገኘ ከጌታ የተገኘ ነውና የሕያዋን የጻድቃን እናታቸው ንእድ ክብርት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ መቅድመ ተአምርም፡- “ሕይወትየ ይቤላ አዳም ለብእሲቱ አእሚሮ ከመ ትወጽእ እግዝእትነ ማርያም እምሐቌሁ ወእምከርሠ ብእሲቱ - አዳምም እመቤታችን ማርያም ከሱ አብራክ እንድትከፈል ከሔዋንም ማኅፀን እንድትወለድ ዐውቆ ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር” ይላል /መቅድመ ተአምር ቁ. ፲/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም፡- “አዳም ያለ ሩካቤ ድንግል የኾነች ሔዋንን አስገኘ፤ የሕይወት እናት ብሎም ጠራት፡፡ በዚህም ነቢይ ኾነ፤ በኹለተኛ ልደት ከእርሷ የሚያበራ ሕይወት ይገለጣልና፤ በድንግልናዋም የእግዚአብሔር ልጅን ታስገኛለችና፡፡ በአዳም ትንቢት የእውነት ሕይወት የኾነው የጌታችንን መምጣት በምሳሌ ተናገረ፡፡ እናቱም ድንግል ማርያም ኾነች፡፡ ሔዋንን የሕያዋን ኹሉ እናት ብሎ ጠራት፤ ሕይወትን አስገኝታለችና፡፡ እርሱም ኢየሱስ የተባለው ጌታችን ነው” ይላል /Jacob of Serug, On the Virgin, pp 36/፡፡ አንድም “ነዋ ወልድኪ- እነሆ ልጅሽ” /ዮሐ.፲፱፡፳፮/ ባለ ጊዜ በዮሐንስ እኛን ለእርሷ መስጠቱ ነውና የሕያዋን ኹሉ እናታቸው ንዕድ ክብርት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ለምኚልንና ትልምኝልን ዘንድ ዓይነ ሕሊናችንን ወደ አንቺ እንሰቅላለን፡፡

Forwarded from Daregot Media
ዳረጎት ዘተዋሕዶ ነጻ መጽሔታችን #5ኛ ዕትሟን በቅርቡ ለእናንተው አድርሳለች፡፡ ብዙዎች ከማዕዱ ቀምሳችሁ ዳረጎታችሁን ለእራት ያብቃልን ብላችሁናል፡፡ ስለሰጣችሁን አስተያየቶች እናመሰግናለን! አሁንም የምሰፍሩልን አስተያየቶቻችሁ ከዚህ በላቀ በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጥለን የበሰለ መንፈሳዊ ምግብ ለማቅረብ ይደግፈናልና ተግሳጽ ምክራችሁን ያለስስት ለግሱን፡፡
----------------++++++-------------------
🙋♂ በቴሌግራም @daregot
ለአስተያየት @DaregotComment_bot
🤳 በፌስቡክ facebook.com/daregotzetewahdo
📲 message/call +251901955111/+251921484549
©ዳረጎት ዘተዋሕዶ

በሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት በሀገረሰላም እና ቦና ዙሪያ ወረዳ የታቃጠሉ አብያተክርስቲያናት መልሶ ለማቋቋም የተሰየመው ኮሚቴ ከኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን የገንዘብ አልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።
ይህ በፎቶ የሚትመለከቱት ልብስ የሐዋሳ ኦርቶዶክሳዊያን ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ምዕመናን ያበረከቱት ስጦታ ነው።
ንዋየ ቅድሳቱም በሐዋሳ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ያሉ አጥብያ ቤተክርስቲያናት ለተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት ያበረከቱት ስጦታ ነው።
ክርስቲያኖች ሁላችንም በያለንበት በግል ፣ በማኅበር ፣ በሰበካ ጉባኤ ወይም በአጥብያ ቤተክርስቲያን እና ወረዳ ቤተክህነት ደረጃ ይህን መሰል ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለዚህ አቅም ያለው ከላይ በተገለጸው መልኩ ሱታፌ እንዲታደርጉ እና ይህን መረጃ በማዳረስ የበኩላችሁን እንዲትወጡ እናሳስባለን።
**** ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ**********
የባንክ ቁጥር - 1000290647936
ለበለጠ መረጃ +251916274741
+251911534870
+251916307683
@via melese