ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
💚💛ነሐሴ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ)
2.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
🌿ወርኀዊ በዓላት🌿
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
"እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" (፩ጢሞ. ፪፥፩-፬)
@senkesar @senkesar
💚💛 ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ 💛❤️
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒ እና ከአባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የመከራ ጊዜ) ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር::
ክርስቲያኖችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በተደረገው የአርባ ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

ይህች ዕለት ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የነገሠባት ናት:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በ312 ዓ/ም ዓለምን አስጨንቀው ሲገዙ ከነበሩ ነገሥታት አንዱ የሮሙ ቄሣር መክስምያኖስ ነበር:: ክርስቲያኖችን ከግዛቱ ያጠፋ ዘንድ ብዙ ጊዜ ሞክሯል::
በሰይጣን ምክር አብያተ ክርስቲያናትን ዘግቷል: መጻሕፍትን አቃጥሏል: ምዕመናንንም ጨፍጭፏል::

ነገር ግን ሰማዕታት አንዱ ሲሰዋ አንድ ሺውን እየተካ (በእምነት እየወለደ) ነውና እንኳን ሊጠፉ በየቀኑ ይበዙ ነበር::
ምንም የሚሊየኖችን ደም ቢያፈስም ክርስቲያኖች ከጽናታቸው የሚነቃነቁ አልሆኑም:: በዚህም ስለ ተበሳጨ ከክርስቲያኖች አልፎ በአሕዛብም ላይ ግፍን ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ የበራንጥያው ንጉሥ ቁንስጣ ዐርፎ ልጁ ቆስጠንጢኖስ ነግሦ ነበርና የሮም ሰዎች ዝናውን ሰሙ::

በእርሱ መንግስት ፍርድ አይጓደልም: ደሃ አይበደልም: ግፍም አይፈጸምም ነበርና ይህንን ያወቁ የሮም ሰዎች መልዕክተኛ ልከው ከአውሬው መክስምያኖስ እንዲያድናቸው ተማጸኑት:: እርሱም ነገሩን ሲሰማ አዝኖ: ከመከራ ሊታደጋቸውም ወዶ: ሠራዊቱን አስከትቶ ተነሳ::

ወደ ጦርነት እየሔደ ካረፈበት ወንዝ ዳር በመንፈቀ መዓልት (ስድስት ሰዓት ላይ) ድንገት ከሰማይ ግሩም ተአምርን ተመለከተ:: የብርሃን መስቀል በከዋክብት አጊጦ: ሰማይንም ሞልቶ: ብርሃኑ ፀሐይን ሲበዘብዛት: በላዩ ላይም "ኒኮስጣጣን" የሚል ጽሑፍ ተስሎበት አየ::
"ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ አንድ ደፋር ክርስቲያን ወታደር (አውስግንዮስ ይባላል:: አርጅቶ በመቶ አሥር ዓመቱ ሰማዕት ሆኗል::) ወደ ንጉሡ ቀርቦ "ይሔማ አዳኝ ሕይወት የሆነ መስቀለ ክርስቶስ ነው::" ብሎታል::
ይሕንን እያደነቀ ሳለም በሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ መጥቶ ነገሩን ገለጠለት: ምሥጢሩንም ተረጐመለት:: "ኒኮስጣጣን ማለት 'በዝየ ትመውዕ ጸረከ-በዚህ መስቀል ጠላትህን ድል ታደርጋለህ' ማለት ነው::" አለው::
በነጋ ጊዜም ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ በሁሉም የጦር እቃ (በወታደሩ: በጦሩ: በፈረሱ: በጋሻው . . .) ላይ የመስቀል ምልክትን ሠርቶ መክስምያኖስን ገጠመው:: በኃይለ መስቀሉም ድል አድርጐ ማረከው:: የተረፈው የአሕዛብ ሠራዊትም እሸሻለሁ ሲል ድልድይ ተሰብሮበት ወንዝ ውስጥ ገብቶ አለቀ::

ቅዱሱ ንጉሥም በኃይለ መስቀሉ ሮሜን እጅ አደረጋት::

"ሃይማኖተ ክርስቶስ ነሢኦ ወዘመስቀሉ ትርጓሜ:
ቆስጠንጢኖስ ዮም ነግሠ በሮሜ:
ዘመክስምያኖስ ዕልው ድኅረ ኀልቀ ዕድሜ::" እንዲል::
ቅዱሱ ንጉሥ ድል አድርጐ በዚህች ቀን ወደ ሮም ሲገባ ከመከራና ሞት የተረፉ ክርስቲያኖች ዕፀ መስቀሉን ይዘው በዝማሬ ተቀብለውታል::

እርሱም በዚህች ቀን በ312 ዓ/ም በሮም ግዛት ሁሉ ላይ ነግሦ ለሰባት ቀናት በዓለ መስቀልን በድምቀት አክብሯል:: በዘመኑ ሁሉም ቅዱስ ሚካኤል አልተለየውምና ወዳጁ ሲባልም ይኖራል::

ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያት እና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ አርፏል::

"ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው::
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: ደግ መሪ: መልካም አስተዳዳሪን ያድለን:: ከቅዱሱ ንጉሥም በረከትን ያሳትፈን::
@senkesar @senkesar
ቅኔ
"በታቦርሂ አመ ቀነጸ መለኮትከ ፈረስ
ኢክህሉ ስሂቦቶ ሙሴ ወ ኤልያስ”


ውርስ ትርጉም
በዘለለ ጊዜ፤
በደብር ርጉዕ ታቦር ፤ መለኮትህ ፈረስ፤ ባሕር ከፋይ ሙሴ ፤ እሳት ጣይ ኤልያስ ሊስቡት አልቻሉም፤ ሐዋርያቱማ ወደቁ ‘ኮ የሉም።”

(ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ)
🙏 እንኳን አደረሳችሁ 🙏
©ዳረጎት ዘተዋሕዶ
--------------------------------------------------
@daregot @daregot
@daregot
በዚኽች ዕለት ነሐሴ 13 ቀን ጌታችን ልክ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በሀገራችን በሚገኘው በዚህ ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል። የተገለጠውም እንደነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፋንታ የለተሰወሩት ለአቡነ ሊቃኖስ ነው። አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡ ይህንንም ገድለ አቡነ አረጋዊ ‹‹ቆመው ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶችና ዓሥሩ የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና የሚያበሩበትና እንደመብረቅ የሚብለጨልጩበት ጊዜ አለ›› በማለት ይገልጸዋል፡፡ በሥዕላቸውም ላይ ይህንኑ ለማሳየት አባቶቻችን የራሳቸውን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡ የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል አክሱም ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡

አቡነ ሊቃኖስ በጸሎታቸው አጋንንትን አውጥተዋል፣ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ዕውራንን አብርተዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡ ከተስዓቱ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ ሞትን ሳያዩ ተሰውረዋል፡፡ አቡነ አረጋዊ ጥቅምት 14 ቀን ተሰወሩ፡፡ አቡ ገሪማ ሰኔ 17 ቀን፣ አቡነ አፍጼ ግንቦት 29 ቀን፣ አቡነ ሊቃኖስ ህዳር 28 ቀን ተሰወሩ፡፡
ጌታችን ነሐሴ 13 ቀን ልክ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዓይነት መንገድ በዚህ በፎቶው ላይ በሚታየው በአቡነ ሊቃኖስ ገዳም ላይም ብርሃነ መለኮቱን ገልጦበታል።

አቡነ ሊቃኖስ እንደ ሙሴ ከደረቅ ጭንጫ ላይ ውሃ በተአምራት በማፍለቅ ይታወቃሉ። አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ጰንጠሌዎኖንና አቡነ ሊቃኖስ ሦስቱም የተሰጣቸው ጸጋ የተለያየ ነበር፡፡ አቡነ ገሪማ ለሠርክ መሥዋዕት የሚሆነውን ስንዴ በተአምራት ዕለቱን ዘርተው ዕለቱን አጭደው ነዶውን ዛፍ ላይ አውጥተው በሬዎቹንም ከዛፍ ላይ አውጥተው አበራይተው ዘሩን ከመሬት አጠራቅመው ዕለቱን ለቅዱስ ሥጋ ወደሙ መፈተቻ ያዘጋጁ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ አቡነ ጰንጠሌዎን ደግሞ በጠዋት ወይራ ተክለው ዕለቱን ግንዱን ፈልጠው ለማዕጠንት ፍሕም አገልግሎት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ አቡነ ሊቃኖስ ደግሞ በደረቅ ጭንጫ ላይ ውሃ በተአምራት አፍልቀው ለቅዳሴ ማይ ጸሎት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ዓለምን በእጃቸው እፍኝ የያዙ እነኚህ እጅግ የከበሩ ታላላቅ ቅዱሳን ከሚያደርጉት ተአምር ውስጥ ለአንዳቸው የተሰጠው ለሌላኛው አልተሰጣቸውም ነበር፡፡ የሦስቱም የተአምራት ውጤት የሆኑት ስንዴ፣ የማዕጠንት ፍሕምና ማይ/ውሃ ደግሞ የግድ ለቅዳሴው አገልግሎት አስፈላጊ ናቸው፡፡

ሦስቱም ቅዱሳን የሚገኙበት ገዳማቸው የተለያየና የተራራቀ ቢሆንም አቡነ ገሪማ በተአምራት ዕለቱን ዘርተው ያጨዱትን የስንዴ ነዶና ራሳቸውን በሬዎቹንም ከዛፍ ላይ አውጥተው አበራይተው ያመረቱትን ስንዴ ለአቡነ ጰንጠሌዎንና ለአቡነ ሊቃኖስ በነፋስ አውታር ጭነው ይልኩላቸዋል! አቡነ ሊቃኖስም እንደ መሴ ከጭንጫ ላይ ያፈለቁትን ውሃ በወንፊት አድርገው ለአቡነ ገሪማና ለአቡነ ጰንጠሌዎን ይልኩላቸዋል፡፡ አቡነ ጰንጠሌዎንም ዕለቱን ተክለው ዕለቱን ለሠርክ መሥዋዕት ያደረሱትን የወይራ የማዕጠንት ፍሕም በሻሽ አድርገው ለአቡነ ሊቃኖስና ለአቡነ ገሪማ ይልኩላቸዋል፡፡

አዎ! ቅዱሳን አባቶቻችን በሬዎችን ዛፍ ላይ አውጥተው ያበራያሉ፤ የእሳቱን ፍሕም በሻሽ፣ ውሃውን ደግሞ በወንፊት ቀድተው ሩቅ ቦታ ይልኩት ነበር! (ይህ በእርግጥ በምንፍቅና ጦር ተወግቶ ልቡን ላቆሰለ አእምሮውን ላሳደፈ የሃይማኖት ዘማ ለሆነ ለዚህ ክፉ ዘመን ትውልድ ተረት ይመስለው ይሆናል እንጂ) እውነታው ግን ቅዱሳኑ የቅዳሴውን አገልግሎት የሚፈጽሙት በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ነበር፡፡ ቅዱሳኑ የቅዳሴውን አገልግሎት የሚፈጽሙት በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ነበር፡፡ እኛ የተዋሕዶ ልጆች ቅዱሳን እንዲህ አድርገው ያገለገሉትን የእነርሱን አምላክ በማመናችን ብቻ ዕድለኞች መሆናችንን ከማሰብና ከማመስገን ውጭ ምን እንላለን!?

የዳግማዊው ሙሴ የአቡነ ሊቃኖስ ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን በጸሎታቸው ይማረን!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት ግቢጉባኤ ለግቢጉባኤው አዳራሽ ማስፈጸሚያነት ይሆን ዘንድ የበረከት ጉዞ ወደ ጥንታዊቷ ከዓለት የተፈለፈለች አስደናቂዋ ደብር አዳዲ ማርያም ተዘጋጅቷል።
የጉዞ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ
150.00 ብር ብቻ!!!
ለበለጠ መረጃ:-
ብሩክ 0953662929
ብሥራት 0923148536
ተስፋሁን 0932276644
ዳዴ 0911510103

  የጉዞ ቀን ነሐሴ 19/2011ዓ.ም
  መነሻ ሰዓት ጠዋት12:00
በዕለቱ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የተመረቁ የግቢጉባኤ ፍሬዎች ልምዳቸውን ያካፍላሉ።

ማሳሰቢያ:- ሰዓት ይከበር!
              ቀድሞ ቦታ በማሲያዝ በዕለቱ የሚኖረውን መጉላላት ይቀንሱ!
#ለአ.አ አቅራቢያ ከተማ የምትገኙ ከላይ ከተጠቀሱት ስልኮች በአንደኛው ደውሎ ቦታ ማስያዝ ወይም ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
#በተቻለን መጠን ሁላችንም የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፣ መልዕክቱን ላልሰሙት እናዳርስ።
#በአካባቢያችን ለሚገኙ የሌላ ግቢ ተማሪዎች፣ ለሰ/ትቤት ተማሪዎች እንዲኹም ምዕመናንን ማሳተፍ የሚበረታታ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ስንክሳር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት ግቢጉባኤ ለግቢጉባኤው አዳራሽ ማስፈጸሚያነት ይሆን ዘንድ የበረከት ጉዞ ወደ ጥንታዊቷ ከዓለት የተፈለፈለች አስደናቂዋ ደብር አዳዲ ማርያም ተዘጋጅቷል። የጉዞ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 150.00 ብር ብቻ!!! ለበለጠ መረጃ:- ብሩክ 0953662929 ብሥራት 0923148536 ተስፋሁን 0932276644…
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የጉዞ ቲኬት ብር ገቢ ለማድረግ በአካውንት የተሻለ መሆኑን አስበን ከዚህ በታች የቀረቡትን አማራጮች አቅርበናል።
Bisrat Mebratu:1000274987767
Tesfahun Abayneh:1000037310275
Dadi : 1000163386481
እናንተም በመረጣችሁት አስገቡና ያስገባችሁበትን የባንክ እስሊፕ በመያዝ እንደ መግቢያ ያገለግላቹኋል። እባክዎትን የባንክ እስሊፑን ባለመርሳት ተባበሩን!!!
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!
++ ድንግል ማርያም ተነሥታለች! +++

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ ፈቃድ ከሞት መነሣት ኦርቶዶክውያን አባቶች ሲያስተምሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት ማስረጃ በመዝ. 131፡8 ላይ ያለውን ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን ቃል ነው፡፡ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ትንሣኤ ጋር አያይዞ መጥቀስ አሁን የተጀመረ ነገር ሳይሆን ብዙ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነገር ነው፡፡ ሠላሳ ሦስተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ቀድመው የተነሡ አበው ያስተላለፉለትን የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ ታሪክ የዛሬ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በጻፈው ድርሳን ላይ ፣ በነገረ ማርያም ሊቃውንት ዘንድ Doctor of Dormition በመባል የሚታወቀው ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ ፣ ሐዋርያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በድርሳኖቻቸው ላይ ስለ ድንግል ማርያም ትንሣኤ ባነሡና በዓለ ዕርገትዋን ባከበሩ ቁጥር የሚያነቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ቃል ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? ‹ማርያም ተነሣች› የሚል ነገር አለውን? የሚለውን ጥያቄ በዚህች አጭር ጽሑፍ እንመለከታለን፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ግን አንድ ቁምነገርን እናስቀድም፡፡

በሐዲስ ኪዳን ለምናምን ፣ በወንጌል ለምንመራ ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ምን ያደርጉልናል? የሙሴ ሕግጋት ፣ የነቢያት መጻሕፍት ፣ የዳዊት መዝሙራት ለክርስቲያኖች ምን ይጠቅሙናል? ብለን ከመጠየቅ እንጀምር፡፡ የዚህ ጥያቄ መልሱ ጌታችን ‹‹በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ሊፈጸም ይገባል›› እንዳለው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ በምሥጢር የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ስለሆነ ነው፡፡ (ሉቃ. 24፡44) ‹ከሙሴና ከነቢያት ጀምሮ ስለ እርሱ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ተብሎ የተነገረላቸው የኤማሁስ መንገደኞች ‹በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትን ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?› ብለው እንደተናገሩ ብሉይ ኪዳን በእርግጥ ስለ ክርስቶስ እንደሚናገር በሚገባ ትርጉሙን ከተረዳን ልባችን በጥልቅ ተመሥጦ ይቃጠላል፡፡ ይህንን የአባቶችን ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መነፅር በዓይናችን ካጠለቅን ብሉይ ኪዳንን እያነበብን በሐዲስ ኪዳን ባሕር ውስጥ መዋኘት እንችላለን፡፡ በኅብረ አምሳል (Typology) አስቀድሞ የተነገረበትን ምክንያት (Primary application) እና ፍጻሜውን (Ultimate fulfillment) ስንረዳ በታሪክና ትንቢት ሁሉ ውስጥ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን እያገኘነው ስንደነቅ እንኖራለን፡፡

በገነት መካከል ተኝቶ ከጎኑ የሁላችንን እናት ሔዋንን ያስገኘውን አዳም ታሪክ ስናነብ በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ በመስቀል ላይ አንቀላፍቶ ከጎኑ በፈሰሰው የጥምቀት ውኃ የሁላችን እናት ቤተ ክርስቲያንን ያስገኘውን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ዕርቃኑን የወደቀውንና ካም ሲዘብትበት ፣ ሴምና ያፌት ዕርቃኑን የሸፈኑለትን የኖኅን ታሪክ ስናነብ የሞትን ጽዋ ጠጥቶ በሰው ልጅ ፍቅር ሰክሮ ዕርቃኑን የተሰቀለውንና አይሁድ ሲዘብቱበት ፀሐይና ጨረቃ ዕርቃኑን የሸፈኑለትን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ አብርሃም የሚወደውን ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ መፍቀዱንና በግ የመሠዋቱን ታሪክ ስናነብ አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን የወደደውን እግዚአብሔር አብንና እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ ልጁን ንጹሑን በግ ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ዳዊት ጎልያድን ድል አድርጎ እስራኤልን ነጻ ሲያወጣ ስናይ ክርስቶስ ዲያቢሎስን ድል አድርጎ የሰው ልጅን ነጻ ሲያወጣ ይታየናል፡፡ እስራኤል በበረሃ ተጉዘው በበትር ከተመታው ከዓለት ውኃ ፈልቆላቸው ሲጠጡ ስናይ በዕለተ ዓርብ ጎኑን በጦር ተወግቶ በደሙ ጥማችንን ያረካልን መድኃኔ ዓለም ይታየንና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ‹ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ› እንላለን፡፡

ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተን ደብተራ ኦሪትን ብንጎበኝ እንኳን ክርስትናችን አይለቀንም፡፡ በመሠዊያ ላይ የሚሠዋውን በግ ስናይ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕሊናችን ይመጣብናል፡፡ ወደ ድንኳኑ ዘልቀን በመቅረዙ ላይ መብራት ሲበራ ስናይ እውነተኛው ብርሃን ክርስቶስ ፣ ዕጣን ስናይ የኃጢአት ሽታችንን ያራቀልን ክርስቶስ ፣ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ስናይ በመለኮቱ መለወጥ የሌለበትን ክርስቶስ ፣ መናውን ስናይ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ እየታየን እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ‹‹ልባችን እየተቃጠለ ለካስ ኦሪትና ነቢያት ሁሉ የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ነበረ?›› እንላለን፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ከሆንን ደግሞ ጌታን ባገኘንበት ሥፍራ ሁሉ እመቤታችንን ፍለጋ ማማተራችን አይቀርም፡፡ አዳምን የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ስናየው አዳምን ያለ አባት ያስገኘችዋ መሬት ያለ ወንድ ዘር የወለደችውን ድንግል ሆና ትታየናለች፡፡ አብርሃም የሠዋውን ከዱር ቀንዱ እንደታሰረ የወጣ በግ ስናይ የድንግልናዋ ማኅተም ሳይፈታ የወለደችው የበጉ እናት ትታየናለች፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተንም አናርፍም ፣ እርሱ መብራት ሆኖ ሲታየን እርስዋ መቅረዝ ትሆንልናለች፡፡ እርሱ ዕጣን ሲሆን እርስዋ ማዕጠንት ትሆናለች ፣ እርሱ ታቦት ሲሆን እርስዋ ታቦቱ ያለበት ቅድስተ ቅዱሳን ትሆናለች ፣ እርሱ ጽላት ሲሆን እርስዋ የጽላቱ ማደሪያ ታቦት ትሆናለች ፣ እርሱ በጽላት ላይ የተጻፈው ቃል ሲሆን እርስዋ ጽላት ትሆናለች ፣ እርሱ የተሰወረ መና ሲሆን እርስዋ የመናው መሶበ ወርቅ ትሆናለች፡፡ ለሰብአ ሰገል ‹ሕጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት› እንደተባለላቸው እኛም በሔድንበት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ የጌታችንን ምሳሌ ባነበብንበት ሥፍራ ሁሉ እናቱንም እናያታለን፡፡

እውነቱን ለመናገር ለመመርመር ትዕግሥት ላለው ሰው ስለ ክርስቶስ በሚናገሩት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንኳን ድንግል ማርያምን ቀርቶ ከሐዲው ይሁዳንም ማግኘት ይቻላል፡፡ ዮሴፍ የክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ዮሴፍ በሃያ ብር እንዲሸጥ ሃሳብ ያቀረበው ወንድሙ ይሁዳ የአስቆሮቱ ይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ፍልስጤማውያንን ድል ያደረገው ናዝራዊው ሶምሶን የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ሶምሶንን እየሳመች አሳልፋ የሠጠችው ደሊላ ስሞ የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ አይደለችምን? አባቱን ለመግደል ሲያሴር ኖሮ መጨረሻ በዛፍ ላይ ተሰቅሎ የሞተው አቤሴሎምስ ጌታውን አሳልፎ ሠጥቶ ተሰቅሎ የሞተው የይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ‹የታመንሁበት የሰላሜ ሰው እንጀራዬን የበላ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ› ተብሎ የተነገረው ስለ ይሁዳ አይደለምን? ብሉይ ኪዳን እንኳን አምላክን ስለወለደችው ቅድስት ድንግል ቀርቶ አምላኩን ስለሸጠው ይሁዳም ትንቢት ተናግሯል፡፡

አሁን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ! ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ብሎ ዳዊት ስለ ቤተ መቅደስ መሠራትና ታቦቱም ወደ ቤተ መቅደሱ ስለመግባቱ የዘመረው መዝሙር ፣ ልጁ ሰሎሞንም መቅደሱ ተሠርቶ ሲያልቅ ደግሞ የዘመረው ይህ መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? (2ዜና 6፡41) ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ከጥንት ጀምሮ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ጋር የሚጠቅሱት ዳዊት ስለ መቅደሱ መሠራትና ስለ ታቦቱ መግባት የተናገረ መሆኑ ጠፍቷቸው ነው? ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ከድንግል
ማርያም ጋር አገናኝተን እንድናስብ ያነሣሣን ምንድር ነው? ወደሚለው እንምጣ፡፡

ዳዊት ስለ ታቦቱ የተናገረውን እኛ ስለ ድንግል ማርያም ሆኖ እንዲሰማን ያደረገው ራሱ ዳዊት ነው፡፡ ዳዊትን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እርሱ ስትመጣ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?›› ሲል አልሰማነውምን? (2ሳሙ. 6፡9) ይህን ንግግርስ ኤልሳቤጥ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› ብላ ለድንግል ማርያም አልደገመችውምን? (ሉቃ. 1፡43) ዳዊት የፈራው ታቦት ወደ እርሱ ሲቀርብ ከዙፋኑ ተነሥቶ በታቦቱ ፊት እየዘመረ ሚስቱ ሜልኮል እስክትንቀው አልዘለለምን? (2ሳሙ. 6፡16) በኤልሳቤጥ ማኅፀን የነበረው ዮሐንስስ የድንግልን ‹‹የሰላምታዋን ድምፅ በሰማ ጊዜ› እናቱ እስክታደንቀው ‹ፅንሱ በደስታ ዘለለ›› አልተባለምን? (ሉቃ. 1፡44) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የድንግል ማርያምና የልጅዋ ክብር ላልገባቸው ሰዎች ‹‹እንደ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ መዝለል ቢያቅታችሁ ምነው ነፍስ ካወቃችሁ በኋላ እንኳን ለእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ ዳዊት በምስጋና ብትዘሉ?›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ እኛ ምን እናድርግ የእግዚአብሔር ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች እንደተባለ ‹‹ማርያምም በዘካርያስ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች›› ተብሎ ተጽፎ አነበብን፡፡ (2ሳሙ. 6፡11 ፤ ሉቃ. 1፡56) ታዲያ የድንግል ማርያም ታሪክ ከእግዚአብሔር ማደሪያ ከታቦቱ ታሪክ ጋር አንድ ሆኖ ስናገኘው ዳዊት ስለ ታቦት የተናገረውን ስለ ድንግል ማርያም እንደምን አንጠቅስ? የነገረ ማርያምን ታሪክ እንጥቀስ ካልንማ ታቦቱ በወርቅ እንደተለበጠ በንጽሕና ያጌጠችውን ፣ ታቦቱ በመቅደስ እንደኖረ በመቅደስ ያደገችውን ፣ ታቦቱን በትሩ አብባ የተገኘች አሮን እንደ ጠበቃት በትሩ ያበበች ዮሴፍ የጠበቃትን፣ ታቦቱን የነካ ዖዛ እንደተቀሠፈ (2ሳሙ. 6፡7) የድንግልን ሥጋ ነክቶ የተቀሠፈውን ታውፋንያ ታሪክ እንጠቅስ ነበር፡፡

‹የመቅደስህ ታቦት› ማለት መቅደስ የተባለው የሰውነትህ ማደሪያ እናት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ሰውነቱን ‹ይህን መቅደስ አፍርሱት› አላለምን? ‹በጉ መቅደስዋ ነው› ተብሎ አልተጻፈምን? ስለዚህ ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ማለት ጳውሎስ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ እንዳለው ‹‹ጌታ ሆይ ‹ዕረፍትህ› ወደተባለ ወደ ሰማያት አንተ ብቻ ተነሥተህ አትቅር የመቅደስ ሰውነትህ ማደሪያ እናትህንም ይዘህ ተነሥ›› ማለት ነው፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤ ብዙዎችን ማከራከሩ እንዴት ያሳዝናል? ክርስቶስ ‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ› ብሏል፡፡ እውነት ትንሣኤን ለወለደች እናት መነሣትዋ ትልቅ ነገር ነው? የሕይወት እናት ሕያው ሆነች ቢባል ያስቆጣልን? ሞትን የሞተው በልጅዋ አይደለምን? የሕይወትን እናት ሞት ይዞ አስቀራት ማለት ደስታ የሚሠጠው ለሞት አበጋዞች ነው፡፡ ‹‹አምላክ ያደረባት የምትናገር ታቦት ፈርሳ ቀርታለች ማለት ፣ ታቦተ ጽዮን ድንግል በሞት ፍልስጤም ተማርካ ቀርታለች›› ማለት የሚያስደስተው በማኅፀንዋ ፍሬ የተፈረካከሰው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚደንቀን መሞትዋ እንጂ መነሣትዋ አይደለም፡፡

ቅዱስ ያሬድ ‹‹የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል›› እንዳለው ሕይወትን ያስገኘች ድንግል ፣ አምላክን የታቀፉ ክንዶች ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆኑ ጉልበቶች በሞት መሸነፋቸው ያስደንቀናል፡፡ መነሣትዋ ግን የምንጠብቀው ነው፡፡ አልዓዛርን ‹አልዓዛር አልዓዛር› ብሎ ያስነሣ ጌታ ፣ በዕለተ ዓርብ በሞቱ ብዙ ሙታንን ያስነሣ ጌታ እናቱን አስነሣ ሲባል የሚቆጡ እንዴት ያሉ ናቸው?

ሁለቱ ምስክሮች የተባሉ ሄኖክና ኤልያስ ወደ ምድር መጥተው አስተምረው ከተገደሉ ‹‹ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ… በሰማይም ፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ ወጡ›› ይላል፡፡ (ራእ. 11፡4-12) ሄኖክና ኤልያስን ከምጽአቱ በፊት ዳግም ላይሞቱ ከሞት አስነሥቷቸው በጠላቶቻቸው ፊት ወደ ሰማይ የሚያሳርጋቸው አምላክ እናቱን በወዳጆችዋ ፊት አስነሥቶ አሳርጓታል ሲባል በቁጣ መቃወም ምን ይባላል?

እንደልጅዋ በራስዋ ዐረገች (Ascension) በማለትና ልጅዋ ወደ ራሱ ነጥቆ ወሰዳት (Assumption) በማለት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከቻልን የእመቤታችን ማረግ ምኑ ያከራክራል? ዝናምን ከከለከለው ኤልያስ ንጹሑን ዝናም ያስገኘችው ድንግል አትበልጥምን ፣ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረገው ሄኖክስ ይልቅ ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው እመ አምላክ አትበልጥምን?

እኛ ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹‹በሞትዋ ምድር መራራ ኀዘን ስታዝን በሰማይ ደስታ ሆነ እንዳለ›› እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገርም ሆነ ፣ በልጅዋ ሥልጣን ተነሥታ ስታርግ በሰማይ የሚኖረውን ደስታ በእምነት እናስተውላለን፡፡ ያ ደሃ አልዓዛር እንኳን ሲሞት መላእክት ነፍሱን ወደ አብርሃም አጅበው ወስደውት ነበር ፣ ኤልያስም ሲያርግ መላእክት በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረሶች ነጥቀውት ነበር፡፡ የአምላክን እናት ዕርገት ስናስብ ከዚህ በላይ ዝማሬ ይታየናል ፤ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደጻፈው ቅዱስ ያሬድም ‹በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ› እንዳለው አባትዋ ዳዊት ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› እያለ እየዘመረ ወላዲተ አምላክ ወደዚያኛው ዓለም ተሸጋግራለች፡፡ ኤልያስ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ መጎናጸፊያውን ለበረከት እንዲሆነው ለደቀ መዝሙሩ ኤልሳዕ እንደሠጠው እመቤታችንም በልጅዋ ሥልጣን ወደ ሰማይ ስታርግ መግነዝዋን (መታጠቂያዋን) ለቶማስ በመሥጠትዋ ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት አሁንም ድረስ ተከፋፍለው በታላቅ ፍቅር በረከትዋን ይቀበሉበታል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ስለ እመቤታችን መነሣት ስናስብ የምንጠይቀው ‹ተነሣች ወይስ አልተነሣችም ፤ ወደ ሰማይ ዐረገች ወይንስ ዐላረገችም› ሳይሆን ‹በሰማይ የተደረገላት አቀባበል ምን ይመስል ይሆን?› ብለን ነው፡፡ ደሃው አልዓዛር በሞተ ጊዜ መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ከተባለ የአምላክን እናት ምን ያህል አጅበዋት ይሆን? ወደ ሰማይ ማረግ ለእርስዋ ቁምነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰማይን በእጆቹ የሚይዘውን አምላክ በእጆችዋ የያዘች ሁለተኛ ሰማይ ናት፡፡ እርስዋ ወደ ሰማይ በማረግዋም ዕድለኛዋ እርስዋ ሳትሆን ሰማዩ ነው፡፡ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ከእናትና ከዙፋን እናት ትበልጣለች፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አልወለደውም ፣ አላሳደገውም ፣ አላጠባውም ድንግል ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ ስለዚህ ወደ ሰማይ ማረግዋ ክብሩ ለሰማዩ እንጂ ለእርስዋ አይደለም፡፡

እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ በእርግጥ አቀባበሉ እንዴት ይሆን? እኛ የሰው ልጆች እናታችንን ማክበርም መጦርም የምንችለው በምድር እስካለችና እኛም እስካለን ድረስ ነው፡፡ ‹እናትና አባትህን አክብር› ያለን ፈጣሪ ግን እናቱን ማክበር የሚችለው በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ነው፡፡ እናቱ ወደ እርሱ ስትመጣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንዴት ተቀብሏት ይሆን?

ንጉሥ ሰሎሞን እናቱ ቤርሳቤህ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመጣች ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ‹‹ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም ፤ በዙፋኑም ተቀመጠ ፤ ለእ
ናቱም ወንበር አስመጣላት በቀኙም ተቀመጠች፡፡ እርስዋም ፡- አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች፡፡ ንጉሡም ፡- እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ለምኚ አላት›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (1ነገሥ. 2፡19-20) ከዳዊት ሆድ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ሰሎሞን ይልቅ በዳዊትን ዙፋን ለዘለዓለሙ ይነግሣል የተባለለት ክርስቶስ ይበልጣል፡፡ ስለ ክርስቶስ ‹‹ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማቴ. 12፡42) ክርስቶስ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከሆነ የክርስቶስ እናትም ከሰሎሞን እናት ትበልጣለች፡፡ ሰሎሞን ለእናቱ ከሠጣት ክብርም በላይ ክርስቶስ ለእናቱ የሚሠጣት ክብር ይበልጣል፡፡ የሰሎሞን ቤተ መንግሥት በምድር ነው ፤ የክርስቶስ ቤተ መንግሥት ግን በሰማይ ነው፡፡ መድኃኔ ዓለም ወደ ሰማያዊው መንግሥቱ እናቱን በጠራት ጊዜ እንደምን ተቀብሏት ይሆን? እንደ ሰሎሞን እናት ወንበር አስመጣላት እንዳንል በሰማይ መቆም መቀመጥ የለም፡፡ ነገር ግን ‹‹የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› ተብሎ ድንግሊቱ ስለተሠጣት ክብር ተጽፎአል፡፡ ወርቅ መልበስዋ አነሳት የሚል ካለ ደግሞ ‹‹አሕዛብን በብረት በር የሚገዛቸውን ወንድ ልጅ የወለደችው›› ድንግል ‹‹ፀሐይን ተጎናጽፋ ፤ ጨረቃም ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ፣ ዐሥራ ሁለትም ከዋክብት አክሊል የሆኑላት አንዲት ሴት ነበረች›› ተብሎ ተጽፎላታል፡፡ (መዝ. 44፡9 ፣ ራእ. 12፡1)

ለእኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር አቀባበል በሕሊናችን ከማሰብ በቀር ምን የሚያውከን ነገር የለም፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ድንግልን ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? እዚህ ‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ› ብሎ ሰላምታ ያቀረበላት ይህ መልአክ ጸጋን የተሞላችው ወደ እርሱ ስትመጣ ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? ቅድስት ኤልሳቤጥስ አሁንም ‹ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?› ብላት ይሆን? መጥምቁስ ዳግም በሰማይ በደስታ ዘልሎ ይሆን? ነቢያቱ ድንግልን እንዴት ተቀበሏት? ኢሳይያስ ‹ትፀንሳለች› ያላትን ድንግል ሲያያት ምን ይል ይሆን? ሕዝቅኤልስ ‹የተዘጋችዋ ደጅ› ወደ እርሱ ስትመጣ ምን አለ? ጌዴዎን ጸምሩን ፣ ኤልሳዕ ማሰሮውን ፣ አሮን በትሩን ፣ ኖኅ መርከቡን ባየ ጊዜ ምን ብሎ ይሆን? ሙሴስ ያልተቃጠለችው ዛፍ ወደ እርሱ ስትመጣ ዳግም እንደ ሲና ተራራው ጊዜ ጫማውን አውልቆ ይሆን? አዳም የልጅ ልጁን ሲያይ ሔዋንስ ዳግሚት ሔዋንን ስታይ ምን ብላ ይሆን? ሁሉንም በሰማይ ለመረዳት ያብቃን!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 21 2010 ዓ ም ተጻፈ
እንኳን ደስ አላችሁ ፡ እንኳን ደስ አለን
ማኅበረ ቅዱሳን በራሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ የ 24 ሰአት መርሐ ግብር ሊጀምር ነው። ከመስከረም 1 ጀምሮ የሙከራ ስርጭት ይካሄዳል።
ሁለተኛው የቴሌቪዥን ጣቢያችን እነሆ
"" የሙከራ ስርጭትን #እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነሐሴ 27 እንጀምራለን፡፡ ""

☞ከሁሉ ይልቅ ግን #ማኅበረቅዱሳን የ24 ሰዓት ስርጭት ሊጀምር በመሆኑ ደስ ብሎናል፡፡ የተሻለ ነገርን ሊሠሩ ይቻላቸዋልና፡፡
💚💛ነሐሴ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ጻድቅት)
3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
4.አበው አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ
🌿ወርኀዊ በዓላት🌿
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
4."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
5.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም

"ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል::" (ማቴ.10:40)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ከገጠመን ችግር ለመውጣት በፍጥነት ልናደርገው
የሚገባን ምንድን ነው?
YESTERDAY · PUBLIC
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ባለፉት ስምንት ዐመታት (ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ እና
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዕረፍት) ወዲህ ኢትዮጵያ ባልተቋረጠ
የለውጥ፣ የውዝግብና የነውጥ ሂደት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ሁለቱም ታላላቅ
መሪዎች ያረፉት በዘመነ ዮሐንስ ማጠቃለያ ወር ላይ ነበር፡፡ የእነርሱን
ዕረፍት ተከትሎ እንዳሁኑ ጎልቶ ባይነገርላቸውም ብዙ ለውጦችም
ነውጦችም በተከታዮች ዐመታት ውስጥ ነበሩ፡፡ ከዐራት ዐመታት በኋላ
ልክ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ አሁን ላለንበት ለውጥም እንበለው
ምስቅልቅል የዳረገን አብዮት ተቀሰቀሰ፡፡ አሁን ባለቤቱ እኔ ነኝ እኔ ነኝ
የሚባልለት ያ ሕዝባዊ ጫናን መሣሪያ ያደረገ (ከየት እንደሆነ ግን
ከግምት በቀር ብዙዎቻችን በትክክል የማናውቀው) ለውጥ ተፈጠረ፡፡
አራቱን ዐመታትም የማንጠበቃቸውና ሊተነበዩ የማይችሉ ተከታታይ
ለውጦች ከጥፋቶችና ምስቅልቅሎች ጋር በሀገራችን ተከሰቱ፡፡
ሁኔታዎቹም ለከፊሉ ደስታ ለከፊሉም ሐዘን የሆኑበት ብዙም ሳይቆይ
ደግሞ ደስታና ሐዘን በፍጥነት የተፈራረቁበት ሆነ፡፡ እንዲህ ያሉ ክስተቶች
ሳያቋርጡ ያለፉበት የዐራት ዐመታት አንድ የለውጥ ወቅት ሊፈጸም
ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል፡፡
ከርሞ ደግሞ እንደገና ዘመነ ዮሐንስ ይጀምራል፡፡ በእኔ እምነት ይህኛው
ዘመነ ዮሐንስ ደግሞ ካለፉት ጠንከር ያሉ ያልተጠበቁ ነገሮች ሊከሰቱበት
ይችላሉ የሚል ግምትን ይዣለሁ፡፡ ምን አልባትም ክፉውም ሊጨምር
ይችል ይሆናል፡፡ በዚህኛው የዘመነ ዮሐንስ ዙር እንጨርሰው አንጨርሰው
ለመናገር እውነተኛ ሀብተ ትንቢት የሚጠይቅ ቢሆንም ወደ አንድ መቋጫ
የምንሔድበት ምዕራፍ ላይ መድረሳችንን ለመረዳት ግን ካሳለፍናቸው
ሒደቶች ብቻ መረዳት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ምን ይሆን መድረሻችን?
አልፎ ያየው የታደለ ይመስለኛል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ማለፉ ብቻ ሳይሆን
ተከስቶ እንደነበር እንኳ እስኪረሳ ድረስ ለማለፍ መቃረቡን እኔ በግሌ
አምናለሁ፡፡
እየሆነ ያለውን ሁሉ ደግሞ ከልቡ በእኛ የፖለቲካ ፕሮግራም ነው፣ ወይም
በዚህ ዕቅድ መሠረት ነው ማለት የሚችል አንድም አካል ያለ
አይመስለኝም፡፡ ሁኔታውንና አጋጣሚውን ተጠቅሞ የለውጥ መሪና
ፊታውራሪ ለመምሰል በፕሮፓጋንዳ መድከምና ለውጡን አቅዶ ማምጣት
በእጅጉ የተለያዩ ናቸውና፡፡ እኔ በግሌና እኔን የሚመስሉት ሁሉ ከላይ
በአጭሩ ከጠቀስኳቸው ሁነቶች ጋር ሁኔታውን የእግዚአብሔር ፍርድ
ወይም ጣልቃ ገብነት ነው የምንለው ከላይ በተደረደሩትና ብዙ ሰው
በማያስታውላቸው ግን ማንም በማይለውጣቸው ሒደቶች ውስጥ
እያለፍን ነው ብለን ስለምናምን ነው፡፡ የሂደቱ ተሳታፊዎችን እኔ በግሌ
እንደ ገጸ ባሕርይ ብቻ ነው የማያቸው፡፡
በርግጥ ይህ ሃሳቤ የማይዋጥላቸው የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት አለ
የሚለውን የሚሞግቱ ብዙ አካላት መኖራቸውንም አውቃለሁ፡፡
የመጀመሪያዎቹ ስለ እግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት የራሳቸው ምናባዊ
ሥዕል ይኖራቸውና ከምናባቸው ጋር አልገጥም ሲላቸው ለመቀበል
የሚቸገሩት ናቸው፡፡ እንዲህ ዐይነት ሰዎች ለእነርሱ ክፉ የሚመስሏቸው
እየኖሩ ደግ የሚመስሏቸው የሞቱ የተጠቁ ሲመስላቸው እግዚአብሔር
አልታያቸው ይላል፡፡ በዚያውም ላይ እግዚአብሔር እንደ መብረቅ
ድብልቅልቅ አድርጎ እርሱ መሆኑን ለሁሉም አሳይቶ ጸጥ ለጥ አድርጎ ልክ
እንደ ወታደርም እንደ መንግሥትም ሆኖ ኅሊናቸው የሚጠብቀውን
አለማድረጉ የአግዚአብሔር ጣልቃገብነት እንደሌለ እንዲቆጥሩ
የሚደርጋቸው ናቸው፡፡ ለእኔ እንደሚገባኝ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር
ያልሠራ የመሰላቸው እነርሱ የመደቡለትን ባለማድረጉ ብቻ ነው፡፡ እንደ
እነዚህ ያሉ ሰዎች ሌላው ቀርቶ ክፉ ሰዎች መሾማቸው፤ አንዳንዶች
እያታለሉ መቀጠላቸው፣ … ወዘተ የመሰሉትን እየጠቀሱ እግዚአብሔርማ
ቢኖር እንዲህ አይረግም ነበር ይላሉ፡፡
ክፉና አታላይ ሰዎችን እግዚአብሔር በሒደት ውስጥ እንደሚፈቅድላቸው
የሚያሳዩ የቅዱስ መጽሐፍ ታሪኮችም ትዝ አይሏቸውም፡፡ ለእኔ እነዚህ
ሁኔታዎች እንዲያውም እግዚአብሔር ጣልቃ ለመግባቱ ምልክቶች
ሊሆኑም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከእሥራኤል ስደት በፊት የዮሴፍን መሸጥ፣
ከዳዊትም በፊት የሳዖልን መንገሥ መመርመር ለዚህ ማሳያ ሊሆን
ይችላል፡፡ ካስፈለገም የሐማ ተንኮል የፈጠረው ድንጋጤ ለኋላው ነጻነት
ያደረገውን አስተዋጽኦ ማሰብ ይቻላል፡፡ ወይም ደግሞ እንደ አኪጦፌል
ያለውን ተንኮለኛ እንደኩሲ ባለ ሌላ ተንኮለኛም የሚጥለው መሆኑን
መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ አኪጦፌልን የመሰለ ተንኮለኛ ለመጣል የግድ ደግ
ሰው ነው የሚያስፈልገው ማለት አይቻልምና፡፡ እነዚህና ሌሎች ታሪኮች
የሚነግሩን እግዚአብሔር ጣልቃ ሲገባ ደጎችንና ለእኛ ኅሊና የሚስማሙ
ክስተቶችንና ግለሰቦችን በማሳየት ብቻ ሳይሆን ክፉ የሚመስሉን
ሁኔታዎችን፣ ሰዎችን፣ መሪዎችን ሁሉ ጭምር ይጠቀማል፡፡
ሌሎች ሰዎች ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ጠባቂነት መናገር ዜጎች
ድርሻቸውን እንዳይወጡ የሚያዘናጋ ነው ብለው የሚሰጉት ናቸው፡፡
ይልቁንም ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ይህን የሚደግፉ ከሆነ
ሥራቸውን እግዚአብሔር አለ ብለው በመተው ሀገርን ለአደጋ ሊያጋልጡ
ይችላሉ የሚል ሥጋት ያይልባቸዋል፡፡ የእነዚህን አካላት ሥጋት በአክብሮት
የምወስድ ብሆንም እኔ የማምነው ግን የእግዚአብሔር ጣልቃገብነት
የፈለጉትን እያደረጉ ወይም ተንኮልና ሤራቸውን ወይም ቸልተኝነታቸውን
በእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት አመካኝተው የሚያላግጡትን ሰዎች ሀሳብ
የያዘ አይደለም፡፡ እንደዚያ ዐይነቱን ንግግር እኔ የማየው ልክ እንደ ሐሰተኛ
ትንቢት ነው፡፡ ምክንያቱም እንደዚያ ዐይነት ንግግሮች ታሳቢ ያሚያደርጉ
ሰዎች በርግጥ በንግግራቸው ከልብ የሚያምኑ ከሆነ ራሳቸውን ከምንም
ዐይነት ሸፍጥ፣ ማስመሰልና አድሎ ስለሚያጸዱ ሕዝብም ሊቀበላቸው
አይቸግረውም ብዬ አስባለሁ፡፡ ንግግራቸው ከሥራቸው ሳይገጥም
የሚናገሩት ከሆነ ግን ለእኔ የሚመስለኝ የንግግሩ ዐላማ የራስን ሥራ
(የተንኮልና የሸፍጥ ሥራዎችን ጨምሮ ከፉና ደጎችን ሁሉ) ሕዝብ
የእግዚአብሔር አድርጎ እንዲቀበልላቸው በማሰብ የተቀባይነት
ማግባቢያዎች አድርጌ ነው፡፡ ይህ ደግሞ መቅሰትን ከማፋጠን ያለፈ
ተግባር የሚኖረው አይመስለኝም፡፡
ሦስተኛዎቹ ደግሞ የእግዚአብሔርን ኃይል በመጠራጠር ሳይሆን
ኢትዮጵያን ብቸኛ(exceptional) አድርጎ እግዚአብሔር እንዲያስባት
የሚያደርግ ምክንያት አይታየንም የሚሉ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ
ተፈጥሮአዊና የሚጠበቅ የማያስነቅፍ ነገር ከመሆኑም በላይ እውነትነትም
አለው፡፡ የእኔና የእኔ ቢጤዎች እምነትም የሚመነጨው ይህን ካለመረዳት
ወይም ኢትዮጵያ ብቻ ልዩ(exceptional) ነች ከሚለው ብቻ አይደለም፡፡
ልዩ ሀገር የሚያሰኛት ነገር መኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚያ ይልቅ
በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሀገሮች እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ
የሚያስገድድ ልዩ ነገር መኖሩን ከመቀበል ላይ ነው፡፡
ይህ እግዚአብሔርን ጣልቃ እንዲገባ የሚያደርገው ሁኔታ በሀገራችን
እንዳለ ደግሞ አውቃለሁ፤ መሪዎቻችንና የፖለቲካ ተዋናዮችን
ስለመጨመሩ ባላውቅም እግዚአብሔርን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ጣልቃ
እንዲገባ የሚስገድደው ነገር እንዳለ ግን እኔ በግሌ በርግጠኝነት
አምናለሁ፡፡ ርግጠኝነቴ የሚመነጨውም አንዳንዶች ከሚጠረጥሩት
ወይም ከሚሰጉት ሐሰተኛ ራዕይ ወይም በመገለጥ ሰበብ የሚነገር
ከሚመስለኝ ቅዠት እንዳልሆነ ማረጋገጥ እፈልጋልሁ፡፡ ልዩ ናት
የሚለውንም ለምን እንደማልተው ከማስቀደም ልጀምር፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ከሆነ እሥራኤል