ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
~የጠበበኝ እኔ
(ሀናን ሁሴን)

በጥልፍልፍ ጉያ የተሰነቀርኩ
በጥብቅ መቀነት የተሰረሰርኩ
በጎታች እትብት ወግ የተሰየምኩ

እኔ የታፈንኩኝ ...እኔ

ከስዬ አላበቃሁ ግና ነው መጫሬ
ከአመዱ ስር ነው ውሎና አዳሬ
በትኜ ለመውጣት ከተዳፈንኩበት
ለትንፋሽ የሚሆን አየር ልስብበት
አመድን ምቾቴ ከማለት በሩቅ ስርቅ
በደራው ሂደቴ ሙቀትን መኖሬን ማሳብቅ

እኔ.... የጠበበኝ እኔ

ብናኝ ሲውጠኝ ተከማችቶ
ዝቆ አስተንፋሽን ገፍቶ
ግለቴ ቢያጎላው መኖሬን
ሊያየኝ የዳዳው ከብናኝ መደበኝ
ቀርቦ ሳይምሰው ከአመድ አስጠጋኝ

እኔ....የጠበበኝ እኔ

በጥልፍልፍ ጉያ የተሰነቀርኩ
በጥብቅ መቀነት የተሰረሰርኩ
በጎታች እትብት ወግ የተሰየምኩ

እኔ....የታፈንኩኝ እኔ

ከባቢው ያፍናል
ላያፈናፍን ይጋፋል
በክብደቱ የውስጥ ጠሊቅን ያናጋል
ከሸክሙ አስማምቶ አየር ያሳጣል።
ሽቅብ ለመቃናት
በነፃነት ለመቃኘት
ከስር ቆሰቆስኩ
ውስጤን አጋልኩ
ክምሩን ብሰጋ
ከአመድ አልረጋ
ጠፍቼ ያልጠፋሁ እኔ ነኝ የተዳፈንኩ....
አመዱን ገርስሼ ብቅ ልል የደፈርኩ...

እኔ...የጠበበኝ እኔ

#hanan_hussen #ሀናን_ሁሴን #ግጥምሲጥም #ጥበብበአደባባይ #ግጥማዊቅዳሜ
#tba #tibebbeqdebabay #digitalartfestival #artinaddis