ፍርፋሪ ታሪክ
- - - — - - -
"ከጅምሩ ማን ፍጠር አለህ እንዲህ ያለ ነገር? ይሄ ነው ፍርድህ? ዛሬስ አትወርድም፣ አትጽፍም ከግንባሩ ላይ ኃጢያቱን የሚያጽፍ ድፍን የቀዮ ጎረምሳ ተሰልፏል..."
"ተው አርዮስ! ተው! ከፈጣሪ አትጋፋ!...አዋቂ ነው...ተው"
"ድንቄም አዋቂ! ሲታወቅ እንዲህ ከሆነ እውቀት በአፍንጫዬ ይውጣ። አይገርምህም!"
"ለአንዲት ጋለሞታ ፈጣሪህን...ትክዳለህን!"
"ጋለሞታ? ጋለሞታ አልህ?...የት አየህ ስትዘሙት?...የት?...አዘሟች ከሌለ ዘማዊት ትፈጠር ይመስል።እንደወይራ፣እንደቀጋ አትበቅል ዘማዊት..."
"ይወራል።...ድፍን መቂ እሱኑ ነው የሚያወራው"
"እና አመንህ አንተ?"
"ምን አማራጭ ይኖራል? ሰው ተኩኖ።...ሁሉ አምኗል እኔ ማነኝና ሰው ያመነውን አላምን የምለው?"
"አልገባኝም?"
"አይገባህም። አንተ ብቻ ከሰው፣ ከቀየው ተነጥለህ፣ ለዘማዊት ሴት ጥብቅና የሚያስቆምህ ነገር። ብቻህን ከአድባር ትጋጫለህ?...ሴት ጠፋ? ከሸርሙጣ?"
"ዝም በል አንተ!!...ምፅዋ ሸርሙጣ አይደለችም።"
"ነች!"
"አይደለችም! ምፅዋ ሸ...ር...ሙ...ጣ... አይደለችም!! ትሰማኛለህ...አንተ ካላባለግኃት አንዲት ምስኪን ሯጭ ከመሬት ተነስታ ሸርሙጣ አትሆንም።"
"ትጠረጥረኛለህ?"
"አላምንህም"
"አህመድንስ ትጠረጥራለህ? ከእርሳቸው አፍ ነው ቀድሜ የሰማሁት።"
"እሳቸው ቅዱስ ገብርኤል ናቸው? የማልጠረጥራቸው?"
"እና እርሳቸውንም ጠርጥረህ?"
"እንክት! ምፅዋዬ እኮ ናት!"
"በል ወግድልኝ ልሂድበት መንገዴን! እውነትም አሪዎስ!...ያሳደጉህ የእናትህ ጡት ሳይሆን ስምህ እንደሆነ ገና ዛሬ ገባኝ!"
"የምን መንገድ?...የሰው መንገድ አበላሽቶ ...ወዴት?"
"የማን መንገድ ተበላሸ? አንተ ኩሩሩ ወግድልኝ!"
"የምፅዋ። የምስኪኗ...በወሬ ገፍታችሁ የጣላችኋት።...ህልሟ መንገዷ አልነበረም? እ!"
"የምን ህልም አላት ደግሞ ሸርሙጣ? ምን ትሰራበታለች ቢኖራትስ?"
"አንተም አለህ አይደል፤ አይደል እሷ? ሯጭ ነበረች ታውቃለህ።... አቦ ሸማኔ የሚያሳድድ ፍጥነት ነበራት።...የጥንቸል ሳንባ ምታስተፋ ነበረች ይህን አንተም ታውቃለህ....ምን ያረጋል!"
"ጋለሞቶች።"
"አልገለሞተችም።....አንተ ውሻ እንዳልዘነጥልህ በዚህ ከዘራ!"
"ኧረ በህግ...በህግ አምላክ!...ምን ታረግበት ነው እሱ...ኧረ ኡ!...ኡ!...ኧረ በህግ!..."
"ልጄን!...አይኔን!...በማህፀኗ...እንደያዘች...አስኮበለላችኋት...ምፅዋዬን አሸሻችኋት"
"ተው አሪዎስ!...ተው አንተ ከሐዲ!...ባለውለታህን?"
"የት ብዬ ልፈልጋት እሺ አሁን?...ንገረኝ!...እ!..."
"እንካ ቅመስ ይችን ለምፅዋዬ!!...እ!...ይህችን ደግሞ በማህፀኗ ይዛ ለተሰደደችው ልጄ...እንካ!!"
"ኡ!...ኡ!...ኡ!...ኧረ የሰው ያለህ!!!"
"የት ብዬ ነው የምፈልጋት አሁን?...እ!...ምፅዋዬ...የበኩር ልጄን እናት?"
©ምግባር ሲራጅ
ዘንባባ
ከገፅ 132 - 134
#ዘንባባ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም