የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የዓለም_ባንክ_ባህላችንን እና ሀይማኖታችንን #በገንዘብ_እንድንቀይር_እያስገደደን_ነው ፤ ነገር ግን ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ ብድር ማደግ ትችላለች ።” #ፕሬዝዳንት_ሙሴቪኒ
ምስራቅ አፍሪካዊቷ ኡጋንዳ #የግብረ_ሰዶም_እርኩሰት_ጋብቻ_የሚከለክል_ህግ_ማጽደቋን ተከትሎ በምዕራባዊያን ሀገራት ስትወገዝ ቆይታለች።
አሁን ደግሞ የዓለም ባንክ ለኡጋንዳ አዲስ ብድር እንደማይሰጥ ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ ወገኖች ቁጣቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ በበኩላቸው ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ ብድር ማደግ ትችላለች ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም “የዓለም ባንክ እምነታችንን፣ ሉዓላዊነታችንን እን ባህላችንን በገንዘብ እንድንቀይር እያስገደደን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
ምዕራባዊያን “አፍሪካን ዝቅ አድርገው መመልከት እና ጫና ማሳደር ይፈልጋሉ፣ እኛ ችግራችንን እንዴት መፍታት እንዳለብን እናውቃለን፣ እነሱም የእኛ ችግሮቻችን ናቸው” ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኡጋንዳ ከዓለም ባንክ ጋር ያለባትን ችግር ለመፍታት የሚቻል ከሆነ ውይይት ለማድረግ ትቀጥላለች ሲሉም ተናግረዋል።
ኡጋንዳ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ የግብረ ሰዶም እርኩሰት ጋብቻን የሚከከለክል ህግን ያጸደቀች ሲሆን ፕሮዝዳንት ሙሴቪኒም ህጉ እንዲተገበር መፈረማቸው ይታወሳል።
አሜሪካ ኡጋንዳ ያጸደቀችውን ህግ ከመቃወም ባለፈ ማዕቀብ የጣለች ሲሆን አሁን ደግሞ የዓለም ባንክ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥሏል።
ዘገባው፤ የሮይተርስ ነው፡፡
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/vAIu_qV_4RY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2