የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.59K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የመሠረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን_በታሪኳ_የመጀመሪያዋን_ሴት_ዋና_ጸሐፊ_መረጠች

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደቡብ አዳማ ክልል ሰባተኛውን ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ በትላንትናው ያከናወነ ሲሆን በጉባኤው የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ገመቹ ደበሎ ተገኝተዋል።

በዕለቱም መሪዎቹ ባደረጉት የክልሉ ዋና ጸሐፊ ምርጫ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ዋና ጸሐፊ አድርገው ወጣቷን መጋቢ ሻሾ ቱሉን ሾመዋል። በተጨማሪም ጉባኤው ክልሉን ከ9 ዓመታት በላይ ያገለገለውን መጋቢ ዳመነ ደጉን ከባላቤቱ ጋር በጸሎት ባርኮና አመስግኖ ሸኝቷል።

መጋቢ ሻሾ ቱሉ ለቀጣዮቹ አራት አመታት በክልሉ ስር የሚገኙትን ከ69 የሚልቁ አጥቢያዎች የምትመራ ይሆናል ሲሉ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በማህበራዊ ትስስር ላይ ገልጾዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍4