የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#አንድ_የኡጋንዳ_ቤተ_እምነት_በጭብጨባ_የዓለም_ጊነስ_ክብረ_ወሰንን_ሰበረ
“ለኢየሱስ አጭብጭቡ” ("Clap For Jesus") በሚል የተሰየመው ይህ ክብረ ወሰንን የሰበረ ጭብጨባ የተደረገው በኡጋንዳ ዋና መዲና ካምፓላ ውስጥ በሚገኝ ፋኔሩ በሚባል ቸርች ነው።
የጭብጨባ ክብረ ወሰኑን የሰበሩት የዚህ ቸርች ምዕመናኑ ለረዥም ሰዓት ያለማቋረጥ በከፍተኛ ድምጽ በማጨብጨባቸው ነው።
ጊነስ እንዳረጋገጠው የምዕመናኑ ጭብጨባ ለሦስት ሰዓታት ሳይቋረጥ የዘለቀ ሲሆን ለሦስት ሰዓት ከ16 ደቂቃ ቀጥሏል።
ጭብጨባው በክብረ ወሰን እንዲመዘገብ ያስቻለው ለዚህን ሰዓት መቆየቱ ብቻ ሳይሆን እንደጋለ መዝለቁ ነበር።
የጭብጨባው የድምጽ ምጣኔው 88.5 ዲሳይቤል (dB) ሲሆን ጊነስ ክብረ ወሰን ለመመዝገብ ትንሹ የድምጽ ምጣኔ 80 ዲሳይቤል (dB) ነው።
ጭብጨባውም የዚህን ቸርች 9ኛ ዓመት ክብረ በዓል በማስመልከት የተሰናዳ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ከሦስት ሰዓት በዘለቀው ጭብጨባ 926 ምዕመናን እጃቸው እስኪቀላ ድረስ አጨብጭበዋል።
ጭብጨባው ከአቅም በላይ ሆኖባቸው መቀጠል ያልቻሉት ከቸርቹ እንዲወጡ ሲደረግም ነበር ተብሏል።
ይህ ሥነ ሥርዓት በቀጥታ ለሕዝብ ሲተላለፍ የነበረ ሲሆን የኡጋንዳ ደረጃ ምደባ ኤጀንሲ እና የብሔራዊ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ባለሥልጣናት ታዝበውታል።
ይህ አዲስ ክብረ ወሰን ከመሰበሩ በፊት በዩኬ በ2019 ክላርክ ስቲቨንስ እና ፌስቲቫል ኦውሰምነስ ረዥም ሰዓት አጨብጫቢ ተብለው ተይዘው ነበር። ሰዓቱም ሁለት ሰዓት ከ15 ደቂቃ ነበር።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/uFHaoOhpwKo
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
1