የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.59K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#በመሠረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን_የደቡብ_ኢትዮጵያ_ቀጠና_የመጀመሪያውን_ዋና_ጸሐፊ_ሾመ
የደቡብ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ቀጠና ከምዕራብ ኢትዮጵያ በመቀጠል የቤተክርስቲያኒቱ ሁለተኛው ቀጠና ሆኖ በይፋ የጸደቀው ባለፈው ነሀሴ ወር በተካሄደው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎች ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሐዋሳ ክልል ዋና ጸሐፊ የሆኑትን መጋቢ ደነቀ ሁሴንን የቀጠናው ዋና ጸሐፊ አድርጎ መርጧል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋና ቢሮን በመወከል በጠቅላላ ጉባኤውን የተገኙት የቤተክርስቲያኒቱ እረኝነት መምሪያ ዳይሬክተር መጋቢ ሰብረላ ከድር የሹመት ስነስርዓቱን ሲያካሂዱ መጋቢ ደነቀ ሁሴን ለቀጣዮቹ አራት አመታት 13 የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክልሎችና 375 አጥቢያዎችን ያቀፈውን የደቡብ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ቀጠናን በዋና ጸሐፊነት የሚመሩ ይሆናል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በነደፈችው የአምስት ስልታዊ እቅድ መሠረት በቀጣዮቹ አመታት የቀጠናዎች ቁጥር ወደ አምስት እንደሚያድግ ይጠበቃል።
መረጃዉ በመሠረተ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4