የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ አደረገች::

ነሐሴ 1/2017 ዓ/ም በደብረ ብርሃን ከተማ ከ23,000 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች በካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የሚገኙበት ሁኔታ እጅግ አስከፊና አስቸጋሪ መሆኑ ታውቋል።
ካምፑ በዚህ ከባድ በሆነው የክረምትና የዝናብ ወቅት የውሀ ችግር ፣ የመጠለያ ችግር ፣የመፀዳጃ ችግር ፣ የመኝታና የሌሊት ልብስ እጦት ችግር ምክንያት ተፈናቃዮቹ እየተሰቃዩ ሲሆን ህጻናት ፣ እናቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ብዙ አቅመ ደካሞች እንደምገኙበት ቤተክርስቲያኒቷ በፌስቡክ ገጿ ላይ አስፍራለች።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሽንን በመወከል መጋቢ ብርሃኑ ታረቀኝ በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን "እንዲህ ዓይነቱን የወገኖቻችንን ስቃይና አስከፊ መከራ መመልከት በእውነት ልብን ይሰብራል፣ እጅግ በጣምም ያሳዝናል እንደ ኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን፣ ይህ ድጋፍ በቂ ባይሆንም ጅማሬ ነው።የተቸገሩና የተጎዱትን መንከባከብ፣ መርዳት የክርስቶስን ፍቅር ማሳየት መንፈሳዊ እና የዜግነት ግዴታችን ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት፣ ሰብዓዊ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ በጸሎት፣ በገንዘብ ፣ በቁሳቁስ እና በአካል በስፍራው በመገኘት ተግባራዊ ምላሽ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል ።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያንና ልማት ኮሚሽኑ ከአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪም ሌሎች ዘላቂና ቀጣይነት ያለው የህፃናት ልማት እና የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን በአከባቢው ላይ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ገልጻለች ።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል ጠቅላላ ጉባኤ በጾም ጸሎት ተጀመረ።

ነሐሴ አርብ 2/2017 ዓ.ም በ 22 ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል ጠቅላላ ጉባኤ በጾም ጸሎት ተጀምሯል።


የቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ B ኳየር በዝማሬ በማገልገል ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኮአል።
በመቀጠል በቤተ እምነቱ የቦርድ ስራ አስፈጻሚ ሰብስቢ በመጋቢ ተመስገን አዋኖ ከሐዋሪያት ስራ ምዕራፍ 20 ከቁጥር 1 እስከ 25 ካለው ክፍል "የሐዋርያው ጳውሎስ ሕይወትና አገልግሎት " በሚል ርዕስ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ለጉባኤው አቅርበዋል።

በጾም ጸሎቱ እግዚአብሔር ያለፈውን በጀት አመት በብዙ ፀጋ ክልሉን ስለረዳ በማመስገን ቀጣይን አመት ለጌታ አደራ በመስጠት ፣ እግዚአብሔር ምድራችን ሰላም እንዲያደርጋት ጸሎት ተካሂዷል።

ጌታ መልካም የጸሎት ጊዜ እንደሰጣቸው አዘጋጆቹ መግለጻቸውንም ቤተ ክርስቲያኒቱ በፌስቡክ ገጿ ላይ አስፍራለች።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
1
በፓኪስታን በክርስቲያን ልጆች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መምጣቱ ተገለጸ።

በባኪስታን የልጆች መብት ኮሚሽን ያወጣው አዲስ ሪፖርት ክርስቲያኖችን ጨምሮ በተለያዩ አናሳ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚገኙ ልጆች ከፍተኛ ለሆነ ጥቃት እየተጋለጡ እንደሆነ ያስነብባል። ሪፖርቱ ከፍተኛውን ጥቃት ያስተናግዳሉ ያላቸው ደግሞ የክርስቲያን ቤተሰቦችን ልጆች ነው። ሪፖርቱ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በክርስቲያን ልጆች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያነሳ ሲሆን ከእነዛም ውስጥ አስገድዶ እምነት ማስቀየር ፣ ያለአቻ ጋብቻ እና የጉልበት ብዝበዛ ተጠቀሰዋል።


ኮሚሽኑ ከፈረንጆቹ 2023 እስከ 2024 ደረስ የልጆች መታገትን ፣ግድያን እና ያለአቻ ጋብቻን አስመልክቶ 27 አቤቱታዎች ቀርበውለታል። እናም ጥቃት ከደረሱባቸው ልጆች መካከል 547 የሚሆኑት ልጆች የሚገኙባት የፑንጃብ ግዛት በሀገሪቱ ከሚደርሱ ጥቃቶች ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነውን ትይዛለች።

የተደረገው ጥናትም የሃይማኖት አካታችነት የማይስተዋልበትን የፓኪስታንን አንድ ወጥ ሀገራዊ የትምህርት ካሪኩለም ነቅፏል። በሀገሪቱ የሚገኙ ክርስቲያኖች የማይከተሉትን ሃይማኖት በትምህርት ቤት እንዲያጠኑ እና እንዲማሩ መገደዳቸው የሃይማኖት ነጻነት ከመግታት ባለፈ የትምህርት ውጤት እንደሚጎዳ እና በማህበረሰብ ውስጥ መገለልን እንደሚያስከትል ተጠቅሷል።


የሃይማኖት መሪዎች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የፓኪስታን መንግስት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ማህበርሰቦች ሕጋዊ ጥበቃ እንዲያደርግ ፣ የትምህርት ፖሊሲዎችን እንዲያሻሽል እና ተቋማዊ ዝንፈቶችን እንዲያስተካከል ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

መረጃውን ከክርስቲያን ፖስት አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
1🙏1