የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ከፎከስ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄደ።

ሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ከፎከስ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር ዛሬ ነሀሴ 3 2017 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂዷል።

በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ፕሬዚደንት ሪቨረንድ ታሪኩ ገብሬ እንዲሁም የፎከስ ሚኒስትሪ ናሽናል ዳይሬክተር የሆኑት ሚልኪያስ ኢትቻ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር የተገኙ ሲሆን በዛሬው ቀን ሃምሳ ተማሪ ለሃምሳ ቀን የሚል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አስተባብረው ችግኞችን ተክለዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ተስፋኢየሱስ ፍቃዱ
ሰሜንን ለኢየሱስ አገልግሎት ከቢሊግራሃም ኢቫንጀሊስትክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል አንጾኪያ እና ገምዛ ወረዳ የሶስት ቀናት ስልጠና ሰጠ።

ሰሜንን ለኢየሱስ አገልግሎት ላለፉት 15 ዓመታት በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ማለትም በአፋር ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በትግራይ ክልል እንዲሁም ከሀገር ውጪ በኤርትራ የሚገኙ ወገኖችን በወንጌል ለመድረስ የሚሰራ አገልግሎት እንደሆነ የአገልግሎቱ አስተባባሪ የሆኑት ወንጌላዊ አለምዬ አሰፋ ያስረዳሉ።


ከሐምሌ 25 እስ 27 የተደረገው ስልጠና ከቢሊግራሃም አሶሴሽን ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን በማሰልጠኑ ላይም ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ወንደም ሰለሞን እና ወንድም አስልፍ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ወንጌላዊ አለምዬ አሰፋም ወንጌል ስርጭት አስለምክቶ ስልጠና ሰጥተዋል።


በስፍራውም ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የመጡ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ስልጠናው በተሳካ መንገድ እንዲሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያደረጉትን ቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽንን እና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋና ቢሮን አመስግነዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎችን ለማገዝ 250 ሺህ ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ብራይት ስታር ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ከዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ እና ከአዲስ አበባ ሴቶች እና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ 10 የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚ ለነበሩ ሴቶች ድጋፍ አደረጉ።

በድጋፉ ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺህ የብር ግምት ያለው የመስሪያ እቃዎችና ግብአት (የአንጀራ መጋገሪያ ምጣድ እና የችብስ መጥበሻ) እንዲሁም ስራ ማስጀመሪያ መቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ያካተተ ድጋፍ ተደርጓል።

በዚህ መርኃ ግብር የብራይት ስታር ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካ፣ የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላን ጨምሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ተጠቃሚዎች በፍላጎታቸው መሠረት የተደረገላቸው መነሻ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፍን ተጠቅመው ጠንክረው በመስራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከተረጂነት በማላቀቅ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በማሳሰብ የቢሮውም ክትትልና ድጋፉን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በመጨረሻም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን አሁንም በጊዜያዊ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ሆነው መቋቋም የሚፈልጉ ነዋሪዎችን ለማገዝ አቅሙ ያላቸው ድርጅቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ቢሮው በጋራ ለመስራት ዝግጁ ስለመሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

መረጃውን ከክርስቲያን ዜና አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
1