የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በባንግላዲሽ የሚገኘው አለመረጋጋት ክርስቲያን ጠል ለሆኑ ጥቃቶች በር እንደከፈተ ተገለጸ።

እንደ ኦፕን ዶርስ ዘገባ በባለፈው የፈረንጆቹ አመት ጠቅላይ ሚኒስተር ሼክ ሃሲና ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ በፓኪስታን የሚገኙ ክርስቲያኖች እየደረሰባቸው የሚገኘው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በሀገሪቱ ውስጥ ጠንካራ ማዕከላዊ አስተዳደር አለመኖሩ እንደ ሃፍዛት እና ሂዝብ ኡት ታህሪር ያሉ ብድኖች በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እንዲያደርሱ እድል ሰጥቷል።

የሃሲና መንግስት ከስልጣን ከወረደበት ጊዜ አንስቶ ወደ 100 የሚጠጉ ክርስቲያን ቤተሰቦች ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲክዱ ተጽዕኖ እንደተደረገባቸው የተገለጸ ሲሆን ቢያንስ 36 ክርስትያኖች በራሳቸው አልያም በንብረታቸው ላይ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

በባለፈው አንድ አመትም ቤተክርስቲያኖች የተበዘበዙ ሲሆን አማኞችም ከሚደርስባቸው እንግልት እና ጥቃት የተነሳ አንዳንዶች ለመደበቅ እንደተገደዱ ክርስቲያን ቱዴይ አስነብቧል።

ክርስቲያኖች ብዙዉን ጊዜ የቀደመውን የሀገሪቱን መንግስት ደጋፊ ናቸው በመባል የሚከሰሱ ሲሆን ይህም የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ምህዳር ባልተረጋጋበት ጊዜ ክርስቲያኖች የሌሎችን በደል ተሸካሚ እንዲሆኑ ዳርጓቸዋል። ከዚህም ባለፈ ስለ ክርስቲያኖች ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች እና አስተምህሮዎች እየደረሰ ያለውን አደጋ እንዲጨምር አድርገውታል። በዚህም ውስጥ የሀገሪቱ የሕግ አካላት ተጠቂዎችን ለመጠበቅ እና ጥቃት አድራሾችን ተጠያቂ ለማድረግ አለመቻላቸው እያስወቀሳቸው ይገኛል።

ብሔራዊ ምርጫ ለማድረግ ጥቂት ወራት በቀራት በባንግላዲሽ ጽንፈኛ ቡድኖች ወደ ስልጣን ከመጡ በሀገሪቱ የሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል መላምቶች ተቀምጠዋል። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶችም በባንግላዲሽ የሀይማኖት ነጻነት እንዲከበር እና ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች ጥበቃ እንዲያገኙ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት መስጠት እንዳለበት በማሳሰብ ላይ ናቸው።


መረጃውን ከክርስቲያን ቱዴይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በልማት ኮሚሽኑ ለመኖሪያነት የተገነቡ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረከበ።

ነሐሴ 03/2017 ዓ .ም የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ ጂዶ ኮምቦልቻ በችግር ውስጥ ላሉ ማህበረሰቦችና ቤተሰቦች ለመኖሪያነት የተገነቡ ቤቶችን ጨርሶ ለተጠቃሚዎች አስረክቧል ።

በስነ ስርዓቱ ላይ የምስራቅ ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጉታ ገዳ ፣የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፓስተር ብርሃኑ ታረቀኝ፣የአካባቢው አስተዳደር ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች ሀዳ ሲንቄዎች፣ የማህበረሰብ ክፍሎች ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት ቀደም ሲል ቤታቸው በጎርፍ ለፈረሰባቸው ቤተሰቦች ስድስት አዳዲስ ቤቶች ተገንብተዋል። በርክክቡ ወቅት አቶ ጉታ ጋዳ የተሠራውን በጎ ተግባር በማድነቅ " ይህ ሥራ በጣም ጥሩ ምሳሌነት ያለውና እና እውነተኛ እግዚአብሔርን የመውደድ ማሳያ ተግባር ነው እንዲህ ያለው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ አድራጎት ተግባር የሀገራችንን የልማት ጥረት የሚደግፍና ልማቱን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት እና የሚደግፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያንን እና ይህ ፕሮጀክት እውን እንድሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አስተላልፈዋል ።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፓስተር ብርሃኑ ታረቀኝ "የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ነው።” ያሉ ሲሆን ይህ የዛሬው ፕሮጀክትም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነው ብለዋል ።

የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሆኑ አቅመ ደካሞች ደስታቸውን የገልጹ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል እማኞች ቤተ ክርስቲያን የመንግስት ተወካዮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርባለች ።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካ ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍ እና ልማት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች እና ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ወጣቶች በዘላቂ ሠላም ግንባታ ዘርፍ የወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጥ እና የምክክር ስልጠና መድረክ በሀዋሳ ከተማ አካሄዷል፡፡

በስልጠናውም 60 ሰልጣኞች የተገኙ ሲሆኑ ሰልጣኞች የመጡትም ከሆሳዕና ፣ ከሀላባ ፣ ወራቤ ፣ ሻሽመኔ ፣ ከወላይታ ሶዶ፣ ከሀዋሳ/ስዳማ እና አረባምንጭ አከባቢ ከሚገኙ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት እና ከቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ነው፡፡

ስለ ግጭት አፈታት ፣ ሠላም ግንባታ እና የተለያዩ የሠላም ጉዳዮችን በተመለከተ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለ60 ወጣቶች ስልጣና ተሰጥቷል፡፡ ወጣቶች በመንፈሳዊ እና በሠላም ግንበታ ዘረፍ ያለቸውን ሚና በማንሳት ይህ ዓለም እንዳያሸንፋቸው በእግዚአብሔር ቃል እውነት መሞላት እና መታጠቅ እንደሚያስፈልግ የገለጹት በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የወጣቶች አገልግሎት አስተባበሪ ወንጌላዊ ያቆብ በዛብህ ናቸው፡፡

የወጣቶች ተሳትፎ ለዘላቂ ሠላም ግንባታ ወሳኝ ሲሆን ወጣቶች የሠላም ግንበታ ቁልፍ ባለድርሻ አካል ናቸው ብለው በሁሉም ቦታ የሠላም መሳሪያ በመሆን የመጪወን ትውልድ ተስፋ ማደስ አለባቸው ሲሉ ለሰልጣኝ ወጣቶች የአደራ መልዕክትቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኮሚሽኑ የጄስራ ፕሮጀክት ኃላፊ/ማናጀር አቶ እንደለ ወ/ሳማያት ወጣቶች የግጭትን አስከፊነትን በማወቅ ከግጭት ይልቅ ለሠላም እንድሰሩ መክረዋል፡፡ ይህም እንደ ግለሰብ እና እንደ ማህበረሰብ ሁሉም ለዘላቂ ሠላም መስራት አለብን ብለዋል፡፡

በስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም ከስልጠናው ጠቃሚ ልምድ መቅሰማቸውን ገልጸው ስልጠናው እንዴት ከሌሎች ኃይማኖቶች እና ማህበረሰብ ጋር በሠላም ተከባብረን መኖር እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየ እና ጠቃሚ ልምድ ያገኘንበት ነው ሲሉም ገልጾዋል፡፡

መረጃውን ከአገልግሎት ክፍሉ አገኘነው

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ