የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.54K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በአማሪካ ውርጃን የሚቃወሙ ብድኖች በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸውን ያጡ ከ390,000 በላይ ልጆችን በማሰብ የዳይፐር እደላ አደረጉ።


የውርጃ ተቃውሚ የሆኑት ቡድኖች በጋራ በመሆን ከ390,000 በላይ ዳይፐሮችን ለወላጆች አድለዋል። ይህም የሆነው ሕይወትን የማክበር ፕሮግራም በተካሄደበት ጊዜ ነበር።


“Students for life of America” እና “Everylife”ን የመሳሰሉ የውርጃ ተቃዋሚ ቡድኖች በካፕቶል በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን ዳይፐር የማደል የማደል እንቅስቃሴ አካሂደዋል።


ይህም የሆነው በሀገሪቱ ውርጃን የመከልከል ምርጫ ለግዛት አስተዳደሮች ከተሰጠ አንድ አመት በሞላበት ጊዜ ነው። የተደረገው እንቅስቃሴ ዓላማው በውርጃ አማካኝነት ምን ያህል ልጆች ሕይወታቸውን እንዳጡ ለማስገንዘብ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓትም እናቶችን ፣ ካለጊዜያቸውን የተወለዱ ሕጻናት እና ቤተሰቦችን ማገዝ ነው።


ፕላንድ ፓረንትሁድ የተሰኘው በአሜሪካ ግንባር ቀደም የውርጃ ማዕከል በ2022 እና በ2023 ስለ ሰራው ስራ ሲናገር 393,715 ልጆችን ማስወረዱን አሳውቆ ነበር።

በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸውን የሚያጡ ልጆች ቁጥርም በፈረንጆቹ 2024 መጨመሩን ቡድኖቹ ያነሳሉ።
መረጃውን ከሲቢኤን ሊውስ አገኘነው።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
3
በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አባያተክርስቲያናት ካውንስል የሚሰጠውን የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚተካ ሀሰተኛ ሰርተፍኬት የሚሰጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጠ
የካውንስሉ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ፓስተር ጌትነት ለማ ለኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ አንዳንድ ህብረቶች የካውንስሉ ፈቃድ እንደማያስፈልግ እያሳመኑ ህገወጥ ሰርተፍኬት በማደል ላይ መሆናቸውን እንደደረሱበት ተናግረው፣ ይህ ሀሰተኛ እና በህግ የሚያስጠይቅ የወንጀል ድርጊት በመሆኑ ይህን የሚያደርጉ አካልት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል
ማንኛውም ህብረት በስሩ የሚመዘግባቸው ቤተ እምነቶች መጀመሪያ ከካውንስሉ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ሳያቀርቡ የማንኛውም ህብረት አባል መሆን እንደማይችሉ እየታወቀ እና ህብረቶቹ ራሳቸው ህጋዊ ሰርተፍኬት ከካውንስሉ ወስደው ሌሎችን መሳሳት ሀጢያትም ወንጀልም ነው ብለዋል
በማከልም አዳዲስ የሚቋቋሙ ቤተ እምነቶች መተዳደሪያ ደንብ ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ በደላሎች እየተጭበረበሩ ስለሆነ ካውንስሉ በህግ ባለሙያ የተዘጋጀ የመተዳደሪያ ደንብ ናሙና ያዘጋጀ በመሆኑ በነጻ ከካውንስሉ ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል
የመተዳደሪያ ደንቡ ቤተ እምነቶቹ እንዳለ ገልብጠው እንዲያመጡ ሳይሆን እንደ ናሙና ወስደው ሁሉንም ግብአቶች በሚፈልጉት መልኩ አስተካክለው ቢያመጡ ከመበዝበዝ እንደሚድኑ ተናግረዋል
ስለ ጉዳይ አስፈጻሚ ነን ባዮችም ካውንስሉ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ በማስረዳት ከህጋዊ ወኪል በስተቀር ማንኛውም ጉዳይ አስፈጻሚ ነኝ የሚል ካውንስሉ እንደማያስተናግድ አጽንዎት ሰጥተው ተናግረዋል
ዜናውን ያደረሰን ባልደረባችን ተስፋዬ ካሳሁን ነው
24👍7
በአርባ ምንጭ ልማት ቃ/ሕ /ቤ/ክ የመዘመራን ስልጠና ተሰጠ።

ከሰኔ 13 እስከ 15/ 2017 ዓ/ም በደቡብ ምዕራብ ቀጠና በአርባ ምንጭ ዙሪያ የህብረት ልማት የቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤ/ክ ለዝማሬ እና ለሙዚቃ አገልጋዮች መሠረታዊ ሥልጠና ተሰጥቷል ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የአጥቢያዋ አዳራሽ የድምጽ ማስተጋባት ችግር ለአገልግሎቶች እንቅፋት እየሆነ በማስቸገሩ ሙያዊ ምክር እና አስፈላጊው የአኮስቲክ ሥራ እንዲጀመር ተደርጎ፣ በዕሁድ አምልኮ ለዚሁ ሥራ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤ/ክ የወጣቶች አገልግሎት የሙዚቃና አምልኮ ክፍል ብሔራዊ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ም ረታ ጳውሎስ ይህ አይነቱ ስልጠና እና የአዳራሽ የድምጽ ችግር ማስተካከያዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልጸው በየቀጠና ያሉ አጥቢዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አድርገዋል።

መረጃውን ከአገልግሎት ክፍሉ አገኘነው
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
8
የኢትዮጵያ ቃ/ሕ/ቤ/ክ ልማት እና ሰብዓዊ ድጋፍ ኮሚሽን 1.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማሕበረሰብ አደረገ።

የኢትዮጵያ ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን 1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በጸጋ ቃ/ሕ/ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተቀናጀ የልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት ለተመረጡ የማህበርሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በፀጋ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተቀናጀ የልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶክተር አስቴር ነጋ ጥበብ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ ፕሮጀክት በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ልጆችንና ቤተሰቦችን ስትደግፍ መቆየቷን ገልጸዋል ፡፡

የተደረገው የድጋፍ አይነትም 25 ኪ.ግ የምግብ ዱቄት፣ 5 ሊትር ዛይት፣ የሴቶች የንጹህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ያጠቃለለ ሲሆን 217 ቤተሰቦችም ድጋፉ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

ባለፉት 28 ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በርካታ ልጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማረተው ለአገር እና ለቤተ ክርስቲያን እድገት የበኩላቸውን አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ዶክተር አስቴር በዓመት 6 ሚሊዮን ብር በመመደብ ልጆች በአምሮአዊ ፣በመንፈሳዊ እና በማህበራዊ ሕይወታቸው የበቁ እና ያደጉ እንዲሆኑ ፕሮጀክቱ አጠንክሮ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

የዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተገኘ ሲሆን በልማት ኮሚሽኑ አመራር ሰጭነት በጸጋ ቃ/ሕ/ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል።
6
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የልጆች አስተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ።


ሰኔ 21/2017 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው ስልጠና ላይ በክልሉ ከሚገኙ 98 አጥቢያዎች የተወጣጡ 350 የልጆች አስተማሪዎች ተገኝተዋል።

የዝማሬ እና የጸሎት ጊዜ የተደረገ ሲሆን ነብይ ብስራት የእግዚአብሔር ቃል በማቅረብ ጸሎት አድርገዋል።

በመቀጠልም የክልሉ የወጣቶቸ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ የሆኑት መጋቢ ኤልያስ አየለ አዲሱ የልጆች ማስተማርያ መጸሃፍ ጠቃሚነቱን አጽንኦት በመስጠት በመናገር በቀጣይ ክልሉ በልጆች አገልግሎት ላይ ሊያከናውናቸው የታሰበውን ተናግረዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
9👍6