የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንሰል መገለጫ ሰጠ።

ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ ወደ ምድራችን የሚመጡ የንስሐ ግቡ ሐልዕክቶች ሰለሆኑ ባላፈው ዓመት ታላቅ የአገራዊ ንስሃ ጊዜን በአደባባይ አከናውነናል። ይህንን ንስሃ መቀጠል ስለታመነበት የአገራዊ ንስሃ የሚያስተባብር ግብረ ኃይል በወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ይሁንታ ተቋቁሞ ተግባሮቹን በተሻለ መንገድ ለመወጣት በመሥራት ላይ ይገኛል።

ስለዚህ ፦

1.ከሚያዝያ 6 እስከ 11/2017 ዓ.ም ከሰኞ- ቅዳሜ በሉት የህማማቱ ሳምንት በመላው አገሪቱ ባሉ ማህበር ምዕመናን ቢቻልም በከተሞች አመቺ በሆኑ በተመረጡ አብያተክርስቲያናት በአንድነት በመሰባሰብ የኑዛዜና የንስሐ ቀናቶች እንዲሆኑ።

2. ከሚያዝያ 19 እስከ ግንቦት 17/2017 ዓ.ም ባሉት ሳምንታት ኑዛዜ ያደረግንባቸው ጉዳዮችን ወደ ፍሬ እንዲመጡ በየአጥቢያው የንስሐ አቅጣጫዎች የትምህርት እና ንስሃውን ከሕይወት ጋር የምሰናዛምድባቸው ጊዜያቶች እንዲሆኑ።

3.ግንቦት 24 ቀን 2017ዓ.ም በሁሉም ከተሞችና አካባቢዎች የማጠቃለያ የንሰሐ ጊዜ መሪዎች በየክልሎቻቸው የካውንስል እና የኀብረቶች አደረጃጀቶች እንዲያደርጉና በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ለአገር አቀፉ የማጠቃለያ የንስሐ ጊዜ ከልሉን የሚወክሉ መሪዎችን ወክለውና በክልሉ ቤተክርስቲያን መለኮታዊ ሥልጣን ጸልየውላቸው ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ።

4.ከግንቦት 25 አስከ 27 2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ከመላው ኢትዮጵያ ክልሎች እና ከዲያስፖራ በክልሎች ቤተክርስቲያን መለኮታዊ ሰልጣን በሚወከሉ መሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ማጠቃለያውን በተወከሉ መሪዎች የንስሐ ጊዜ በማድረግ የንሰሐ ማጠቃለያ እንዲሆን ታቅዷል።

በመላው ኢትዮጵያ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የወንጌላውያን አማኞች ሁሉ በዚህ በወጣው ፕሮግራም መስረት አሰተባባሪ ግብር ኃይል በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች በሚያሰራጫቸው የንስሐ አቅጣጫዎች እና የኑዛዜ የጸሎት ርዕሶች አየታገዛቸሁ የንስሐ ጊዜውን አብረን በጋራ እንድናከናውን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

“ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፥ ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።”ትንቢተ ኢሳይያስ 62፥6-7

ልዑል አግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያን ይባርክ!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ከርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

መጋቢት 3/2017 ዓ.ም #ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏10👍53🔥2
አስቸኳይ መልዕክት ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መስራች አባል የሆነችው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መዋቅር ስር በጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ ጋቲራ ከተማ የምትገኘው ማህበረ ምዕመናን ላይ ለእምነቱ ጭፍን ጥላቻ ባላቸው አካላት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ።
መንግስት እነዚህን ግለሰቦች ለህግ በማቅረብ አስፈላጊውን ቅጣት በመስጠት ያፈረሱትን የጸሎት ቤት በአስገዳጅነት እንዲሰሩ በማድረግ እና ጭፍን ሐይማኖታዊ ጥላቻቸውን በምዕመኖቻችን ሕይወት ላይ ተግባራዊ ባደረጉ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ ወስዶ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ።
🙏15👍93