የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ጥብቅ ማሳስቢያ
👍43😱85👎1😢1
የካቲት 29 እና 30 2017 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ የተሰኘውን የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ የተሰጠ መግለጫ።መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ከዓመት በላይ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ ሲሆን በመስቀል አደባባይ በሚከናወነው በዚህ ኮንፈረንስ ላይ በዋናነት ለአገራችን የምንጸልይበት ፣እግዚአብሔርን በአምልኮ፣ በቃል የምናመልክበት ትልቅ ቀን ብለዋል። በዚህ ፕሮግራም ላይ የወንጌል አማኞች ብቻ ሳይሆን ሌሎችን በመጋበዝ እንድትገኙና፣
6👍4
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
የካቲት 29 እና 30 2017 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ የተሰኘውን የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ የተሰጠ መግለጫ።መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ከዓመት በላይ ዝግጅት…
የቤተክርስቲያን መሪዎች የፊታችን እሁድ ባለው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን መርሃግብርን ቶሎ በመጨረስ ምዕመናን ወደ መስቀል አደባባይ እንዲመጡ ለማድረግ ተባበሩ ብለዋል ጠቅላይ ጸሐፊው።
በመግለጫው አውቶብሶች በሚቆሙበት ስፍራዎች በጊዜ በመገኘት ወደ መስቀል አደባባይ እንድትመጡ ይሁን በአካባቢው ከሚኖሩ የጸጥታ አካላት ጋር ትብብር በማድረግ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ አደራ ሲሉ ገልጸዋል። በነዚህ ቀናት እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ በጾም ላይ ከሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ወገኖቻችን በጾም ላይ በመሆናቸው የእነርሱን ነገር ያከበረ ኦንዲሆንና የምታደርጉት በሙሉ የወንጌል ምሳሌነት የተከተለ ይሁን። በንግግርም በድርጊትም የምናደርጋቸው ነገሮች የወንጌል ምሳሌ ይሁን ብለዋል።
በሁሉም አቅጣጫ ለምትመጡ ትራንስፖርት ባሶች ተዘጋጅተዋል። ባሶች የሚቆሙበትን በማህበራዊ ሚዲያ ማግኘት ይችላል። በመጨረሻ ጠቅላይ ጸሐፊው በመግለጫቸው የከተማውን ጽዳት ጠብቁ፣ በማንኛውም መልኩ ቆሻሻዎችን በየመንገዱ ከመጣል እንቆጠብ፣ እየተሰሩ ያሉትን መሰረተ ልማቶች ዙሪያ ቆሻሻ እንጣል ብለዋል።
👍142
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
Photo
#እውቁ_የወንጌል_አገልጋይ_ፍራንክሊን_ግራሀም_በመስቀል_አደባባይ_የሚደረገውን_ፕሮግራም_አስመልክቶ_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ሰጡ

የካቲት 28 2017 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና በቢሊግራሀም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ትብብር የተዘጋጀውን ፕሮግራም በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ላይ ፍራንክን ግራሀም “በዚህ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ በመገኘቴ ደስታ ይሰማኛል።” ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያን እንደሚወዱ የተናገሩት ፍራንክሊን ግራሀም ወደ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጡት እ.አ.አ በ1985 እንደሆነ አስታውሰው ከዛም ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ ብዙ ለውጦችን እንዳስተዋሉ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይሄ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ባይሆንም “በእንደዚህ አይነት መንገድ ወንጌልን ለማድረስ እታደላለው!” ብለው አስበው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ከ1988 ዓ.ም ጀምሮም በሳማሪታን ፐርስ አማካኝነት በሀገራችን በግብርናው እና በህክምናው ዘርፍ ብዙ ስራ ለመስራት መቻላቸውንም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ አንስተዋል።

በዶናልድ ትራምፕ አዲሱ የስልጣን ዘመን ከአሜሪካ የሚመጣው ዩኤስ ኤድ መቋረጡ አሳሳቢ መሆኑን እንደሚቀበሉ የተናገሩት ፍራንክሊን ግራሀም እርዳታውን ሰበብ በማድረግ በአሜሪካ የሚደረገውን ከፍተኛ ምዝበራ ለማስቆም የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊ እንደሆነ እና አስፈላጊው ነገር ከተደረገ በኋላ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚመለስ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

በዚህም ጊዜ ውስጥ በሰማሪታን ፐርስ አማካኝነት በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው ስራ እንደማይቋረጥ ያስታወቁት ፍራንክሊን ግራሀም “የእኛ አቅርቦት ከመንግስት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው።” ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም በኢትዮጵያ ስላስተዋሉት ለውጥ ለፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለመናገር ቃል ገብተዋል።

በዚህኛው ጊዜ የመጡበትን ምክንያት ሲያነሱም “ የመጣሁበት አላማ አንድ መልዕክትን ለማስተላለፍ ነው። ይህም መልዕክት ወንጌል ነው። ኢየሱስ ኢትዮጵያን እንደሚወዳት ለመንገር መጥቻለሁ። ኢየሱስ ስለ እኛ ሀጥያት ብሎ በመስቀል ተሰቅሏል። ያንን ብናምን እና ንስሀን ብንገባ የእግዚአብሔር መንግስት ወራሾች እንሆናለን።” ብለዋል።

በቀጣይነት ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመሆን ሊሰሯቸው ያሰቧቸውን ስራዎች በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ከተለያዩ ዓለማት ለልጆች ስጦታ በማሰባሰብ ስጦታ የመቀበል እድል ለሌላቸው ልጆች በቤተ ክርስቲያን በኩል ስጦታ የመስጠት እና በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ስለሰጠው ስጦታ የመመስከር ስራን የሚሰራው የክሪስማስ ጊፍት ስራ በኢትዮጵያ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አባታቸው ቢሊ ግራሀም ከ65 ዓመታት በፊት ባገለገሉበት ተመሳሳይ ከተማ እና ቀን በማገልገላቸው ምን እንደሚሰማቸው በተጠየቁበትም ጊዜ “እግዚአብሔር ወደዚህ ከተማ እንደጠራን አምናለሁ። አባቴ ይዞ የመጣውን ተመሳሳይ ወንጌል ነው ይዜ የመጣሁት። በጊዜ ሂደት ውስጥ ብዙ ነገሮች ቢለዋወጡም ወንጌል የሚለዋወጥ መልዕክት አይደለም።” በማለት ተናግረዋል።

በነዚህ ሁለት ቀናት በሚኖረው ፕሮግራም ምን እንደሚጠብቁም በተጠየቁበት ጊዜ “በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ንስሀ በመግባት ሕይወታቸውን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚሰጡ አምናለሁ።” ብለዋል።

በስፍራው የተገኙ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩም በበኩላቸው የቢሊግራሀም ኢቫንጀልስቲክ አሶሴሽን እንዲሁም ሳማሪታን ፐርስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገራችን የሰራቸውን ስራዎች በመመልከት ካውንስሉ እንደጋበዛቸው ያነሱ ሲሆን ይሄ መንፈሳዊ ፕሮግራም የሚካሄደው በሀገራችን የኦርቶዶክስ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች በጾም እና በጸሎት ወደ አምላክ ራሳቸውን በሚይቀርቡበት ጊዜ መሆኑ ሁኔታውን ለሀገራችን ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

አክለውም ለሀገራችን ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ሲሉ ተናግረው ፍራንክሊን ግራሀምን በማመስገን ንግግራቸውን ቋጭተዋል።
👍3817😱2
#በቢሊግራሀም_ኢቫንጀሊስቲክ_አሶሴሽን_የሚመራው_ኦፕሬሽን_ክሪስማስ_ቻይልድ ኦሲሲ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ በመሆን ለአራት መቶ ሰማኒያ ልጆች ስጦታን አበረከተ።
👍2
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
#በቢሊግራሀም_ኢቫንጀሊስቲክ_አሶሴሽን_የሚመራው_ኦፕሬሽን_ክሪስማስ_ቻይልድ ኦሲሲ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ በመሆን ለአራት መቶ ሰማኒያ ልጆች ስጦታን አበረከተ።
የቢሊግራሀም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን አንድ ክንፍ የሆነው ኦፕሬሽን ክሪስማስ ቻልይድ ኦሲሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያየ ችግር ውስጥ ለሚያልፉ ልጆች ስጦታን በመስጠት ወንጌል ለማድረስ የሚሰራ አገልግሎት ነው።
ይህም አገልግሎት ከኢትዮጵያ ወንጌል አምኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመተባበር የካቲት 27 እና 28 በቻይና ካምፕ አከባቢ በሚገኙ የቃለ ሕይወት እና መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኖች ላይ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ለ480 ልጆች ስጦታ የመስጠት መርሃ ግብር አካሂዷል።
ኦሲሲ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጥምረት ሲሰራ ይሄ የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። ከዚህ በፊት ለ50 የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ለ200 የልጆች አገልጋዮች ግንዛቤን የመፍጠሪያ ስልጠና በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አማካኝነት አካሂዶ ነበር።
የካቲት 27 እና 28 ሀሙስ እና አርብ ላይ በተካሄደው ለልጆች ስጦታ የመስጠት መርሃ ግብር ላይ ኦሲሲን በመወከል ትልቅ ሚና የተጫወቱትን ፖል የተሰኙ የኦሲሲ ተወካይ ሲሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ለልጆች ስጦታውን ለመስጠት የፍራንክሊንግ ግራሀም ልጅ የሆኑት ኤድዋርድ ግራሃም ተገኝተው ነበር።
አብረዋቸው የመጡት የቡድን አባላትም ለልጆች የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
በልጆች ላይ ከፍተኛ የደስታን ስሜት በፈጠረው ፕሮግራም ላይ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና የልጆች አገልጋዮች ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የውጭ ግኑኝነት ሀላፊ የሆኑት መጋቢ አሸብርም ይህንን መርሃ ግብር አስመልክቶ ይሄ ገና ጅማሬው ነው በማለት ተናግረዋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የውጪ ግንኙነት መምሪያ አገኘነው።
9👍1
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል_ከቢሊ_ግራሀም_ኢቫንጀልስቲክ_አሶሴሽን_ጋር_በጋራ_በመሆን_ያዘጋጀው_መለኮታዊ_ጉብኝት_ለኢትዮጵያ_የተሰኘው_መረሃ_ግብር_በታላቅ_ድምቀት_ተጠናቀቀ፡፡
የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ.ም መለኮታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ" የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስል እና በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር ትብብር በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ፤ የሬቨረንድ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ቢሊ ግራሃም ያገለገሉ ሲሆን የጸሎትና እና የዝማሬ መርሃ ግብሮችም ተከናውኗል፡፡

መለኮታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር ላይ በርካታ ቁጥር ያለቸው ሰዎች ወደ አግዚአብሔር መንግስት ተጨምረዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ


ከ320 ሺህ በላይ ሰው መስቀል አደባባይ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በመገኘቱ የተሰማኝን ትልቅ ደስታ እገልጻለው ሲሉ ፍራንክሊን ግርሃም ።

ፍራንክሊን ግርሃም ከየመስቀል አደባባይ የማጠቃለያ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው “ወንጌል ሃይል አለው። ዛሬ ንሰሃ በመግባት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ስለ ወሰኑ ሰዎች ጌታን እናመሰግናለን።

ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም”
ዮሐንስ 11፥25-26

ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ትልቅ አስተዋጾ ላደረጉ ፣ለጸለዩ ወዳጆቼ እና አብያተ ክርቲያናት በሙሉ ትልቅ ምስጋና አለኝ። አብያተ ክርስቲያናት በእግዚአብሔር ቃል እየጸናችሁ፡ የምትሰሩትን የደቀ መዝሙር ማፈራት ስራ እግዚአብሔር ይባርክ።

ዛሬ በነበረን የዝማሪው ጊዜ በርካታ ዘማሪዎች በዝማሬ እና አምልኮ ከቀትር በኋላ እስከ ምሽት ድረስ በጥሩ ሁኔታ አገልግለዋል። መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ መርሃ ግብር ላይ ለተሳፋችሁ በሙሉ አመሰግናለሁ።” ብለዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍19