የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ሕይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያን_በታሪኳ_የመጀመሪያዋን_ሐዋርያ_ሾመች
ጥር 2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በታሪኳ የመጀመሪያዋን ሐዋርያ ሾመች ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ወስጥ በነቢይነት ሲየአገልግለው የነበሩ ነቢይ ያዕቆብ ዮዶሩ ሐዋርያ ሆነው ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በቦታ ላይ በመገኘት የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
ሐዋርያው ያዕቆብ ቤተክርስቲያን መሠረት ነውና በዚህ ሥፍራ እኔን ስጋ ለባሹን በመጠቀም ይህን ቅዱስ ፍቃዱን ያከናወነ፣ለልዑል እግዚአብሔር ልጅ ለእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ምስጋና, አምልኮና ክብር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሐዋሪያው በሚያገለግሉበት የአዋዬ ቃራሮ አጥቢያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ምረቃ የህንጻ ምረቃም ተደርጓል።
ቃራሮ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ከዛሬ 50 ዓመት ነበር በጥቂት ክርስቲያኖች የተመሠረተችው፡፡በትንሽዬ ጎጆ ቤት የነበረች ሲሆን ግን በብዙ ፈተና በማለፍ፣ እግዚአብሔር በአባላት እድገት፣ በመንፈስና በአካል እያሳደጋት፣ በዘመናት ውስጥ በድል በማደግ፣ እንደዚህ ትልቅ ህንጻ በመገንባት ማስመረቅ ችላለች፡፡ክብር ሁሉ ለቅዱስ እግዚአብሔር ይሁን ሲሉ የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ፓስተር ታሪኩ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ፕርግራም መሳካት የግንባታ መሠረት ከተጣለ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ የምረቃው ሰዓት ድረስ፣ በጸሎት፣ በገንዘብ፣ በእውቀትና ጉልበት፣ ድጋፍ ያደረጋችሁና በተግባራት የተሳተፋችሁ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባሪክ ሲሉ ሐዋርያ ያዕቆብ ገልጸዋል፡፡
7👍3
#በኢትጵያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተ_ክርስቲያን_የሀዋሳና_ዲላ_አካባቢ_ክልል_መጽሐፍ_ቅዱስ_ኮሌጅ_ተማሪዎችን_አስመረቀ
ጥር በ24/2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ጽ/ቤት የስነ መለኮት ኮሌጆች ክትትል ክፍል ሀላፊ መጋቢ ታምራት አዉሎና ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሴሚናሪየም ምክትል ፕሬዚዳንት መ/ር አዛሪያ ሹሚ በተገኙበት 13 ተማሪዎችን በዲፕሎማ 46 ተማሪዎችን በድግሪ መርሃ ግብር በአጠቃላይ 59 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎችም በትምህርት ተቋሙ ባገኙት እውቀት እግዚአብሔርን ለመገልገል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍21
#የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተ_ክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ_ልማት_ኮሚሽን_የኖርዌይ_ሚሲዮን_ሶሳይቲ_ለኖርዌይ_ሉተራን_ሚሽን_እና_ለዲግኒ_ከፍተኛ_ተወካዮች_አቀባባል_አደረገ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማት ኮሚሽን የኖርዌይ ሉተራን ሚሽን እና ለዲግኒ ከፍተኛ ተወካዮችን አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሴቶች የሰላም ግንባታ ተሳትፎ፣ አረንጓዴ ልማትና SIM ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በሚሽኑ በሚደረገው ስራ መግለጫ ተሰጥቷል።
በዲግኒ ተወካዮች በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማት ኮሚሽን በዲግኒ፣በኖርዌይ ሚሲዮን ሶሳይቲና በኖርዌይ ሉተራን ሚሽን መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት በማድነቅ ስብሰባው ተጠናቋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍73