የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ሕይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያን_በታሪኳ_የመጀመሪያዋን_ሐዋርያ_ሾመች
ጥር 2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በታሪኳ የመጀመሪያዋን ሐዋርያ ሾመች ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ወስጥ በነቢይነት ሲየአገልግለው የነበሩ ነቢይ ያዕቆብ ዮዶሩ ሐዋርያ ሆነው ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በቦታ ላይ በመገኘት የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
ሐዋርያው ያዕቆብ ቤተክርስቲያን መሠረት ነውና በዚህ ሥፍራ እኔን ስጋ ለባሹን በመጠቀም ይህን ቅዱስ ፍቃዱን ያከናወነ፣ለልዑል እግዚአብሔር ልጅ ለእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ምስጋና, አምልኮና ክብር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሐዋሪያው በሚያገለግሉበት የአዋዬ ቃራሮ አጥቢያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ምረቃ የህንጻ ምረቃም ተደርጓል።
ቃራሮ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ከዛሬ 50 ዓመት ነበር በጥቂት ክርስቲያኖች የተመሠረተችው፡፡በትንሽዬ ጎጆ ቤት የነበረች ሲሆን ግን በብዙ ፈተና በማለፍ፣ እግዚአብሔር በአባላት እድገት፣ በመንፈስና በአካል እያሳደጋት፣ በዘመናት ውስጥ በድል በማደግ፣ እንደዚህ ትልቅ ህንጻ በመገንባት ማስመረቅ ችላለች፡፡ክብር ሁሉ ለቅዱስ እግዚአብሔር ይሁን ሲሉ የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ፓስተር ታሪኩ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ፕርግራም መሳካት የግንባታ መሠረት ከተጣለ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ የምረቃው ሰዓት ድረስ፣ በጸሎት፣ በገንዘብ፣ በእውቀትና ጉልበት፣ ድጋፍ ያደረጋችሁና በተግባራት የተሳተፋችሁ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባሪክ ሲሉ ሐዋርያ ያዕቆብ ገልጸዋል፡፡
7👍3