የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.59K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከmission_of_hope_international_ጋር_ወይይት_አደረገ

ጥር 26 ቀን /2017 ዓ.ም mission of hope international በኬንያ መሰረት አድርጎ እየሰራ ያለ ተቋም ሲሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ስራ ለመስራት በካውንስሉ ቢሮ በመገኘት የውይይትና የምክክር ጊዜ አድርጓል።

እ.ኤ.አ 2000 ዓ.ም 50 ሕፃናትን በመረዳት የትምህርት እድሎችን በማመቻቸት የጀመረ ሲሆን በአሁን ጊዜ በኬንያና በለቤሪያ ከ37 በላይ የሚሆኑ ትምርህት ቤቶችን እና በርካታ ሕፃናትን በመረዳት እያገለገለ ያለ ተቋም ነው።በተደረገው ወይይት ከኬንያና ከአሜሪካ የመጡ 18 የሉካን ቡድን ተገኝተዋል።የካውንስሉ የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ ካውንስሉ እየሰራ ስላለው ስራ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ውሰጥ ተመሳሳይ ስራዎችን ከካውንስሉ ጋር በመሆን ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸውንና የመጀመሪያውን ምዝገባ በካውንስሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።በሚቀጥሉት ጊዜያቶች የምክክሩ ወጤት ከምን እንደደረሰ የምን ገልጽ የሆናል ሲሉ የካውንስሉ የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ ለኢቫንጀሊካል ቴሌቬዥን ገልጸዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍114🙏1
#የኢትዮጵያ_ሕይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያን_በታሪኳ_የመጀመሪያዋን_ሐዋርያ_ሾመች
ጥር 2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በታሪኳ የመጀመሪያዋን ሐዋርያ ሾመች ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ወስጥ በነቢይነት ሲየአገልግለው የነበሩ ነቢይ ያዕቆብ ዮዶሩ ሐዋርያ ሆነው ተሹመዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በቦታ ላይ በመገኘት የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
ሐዋርያው ያዕቆብ ቤተክርስቲያን መሠረት ነውና በዚህ ሥፍራ እኔን ስጋ ለባሹን በመጠቀም ይህን ቅዱስ ፍቃዱን ያከናወነ፣ለልዑል እግዚአብሔር ልጅ ለእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ምስጋና, አምልኮና ክብር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሐዋሪያው በሚያገለግሉበት የአዋዬ ቃራሮ አጥቢያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ምረቃ የህንጻ ምረቃም ተደርጓል።
ቃራሮ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ከዛሬ 50 ዓመት ነበር በጥቂት ክርስቲያኖች የተመሠረተችው፡፡በትንሽዬ ጎጆ ቤት የነበረች ሲሆን ግን በብዙ ፈተና በማለፍ፣ እግዚአብሔር በአባላት እድገት፣ በመንፈስና በአካል እያሳደጋት፣ በዘመናት ውስጥ በድል በማደግ፣ እንደዚህ ትልቅ ህንጻ በመገንባት ማስመረቅ ችላለች፡፡ክብር ሁሉ ለቅዱስ እግዚአብሔር ይሁን ሲሉ የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ፓስተር ታሪኩ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ፕርግራም መሳካት የግንባታ መሠረት ከተጣለ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ የምረቃው ሰዓት ድረስ፣ በጸሎት፣ በገንዘብ፣ በእውቀትና ጉልበት፣ ድጋፍ ያደረጋችሁና በተግባራት የተሳተፋችሁ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባሪክ ሲሉ ሐዋርያ ያዕቆብ ገልጸዋል፡፡
7👍3
#በኢትጵያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተ_ክርስቲያን_የሀዋሳና_ዲላ_አካባቢ_ክልል_መጽሐፍ_ቅዱስ_ኮሌጅ_ተማሪዎችን_አስመረቀ
ጥር በ24/2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ጽ/ቤት የስነ መለኮት ኮሌጆች ክትትል ክፍል ሀላፊ መጋቢ ታምራት አዉሎና ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሴሚናሪየም ምክትል ፕሬዚዳንት መ/ር አዛሪያ ሹሚ በተገኙበት 13 ተማሪዎችን በዲፕሎማ 46 ተማሪዎችን በድግሪ መርሃ ግብር በአጠቃላይ 59 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎችም በትምህርት ተቋሙ ባገኙት እውቀት እግዚአብሔርን ለመገልገል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍21