የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከኢትዮጵያ_መጸሐፍ_ቅዱስ_ማህበር_ጋር_በመተባበር_በኢትዮጵያ_ዘላቂ_ሰላም_ጉደይ_ላይ_የተዘጋጀ_አውደ_ጥናት_ተካሄደ

ጥር 16 ቀን 2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከኢትዮጵያ መጸሐፍ ቅዱስ ማህበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ጉደይ ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት በስካይላይት ሆቴል የተካሄደ ሲሆን የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እስኪ መጣ ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ስራውን ይቀጥላል ሲሉ ገልፀው በሀገር ደረጃ የኢትዮጵያ መጸሐፍ ቅዱስ ማህበር እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ።


ቀሲስ ሊቅ ትጉዋን ይልማ ጌታሁን የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በሀገር ደረጃ በሰላም ዙሪያ ምን አይነት ተጽእኖ እየፈጠረን ነው ብለን ልንጠይቅ ይገባል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ።በዚህ መርሐግብር ላይ ከተለያዩ አብያተክርስቲያናት የተወከሉ መሪዎች በሰላም ዙሪያ ላይ እየሰራው የሚገኙት የልምድ ማካፈል ጊዜ አከናውነዋል።
በዶ/ር ሳምሶን እስጢፋኖስና በቄስ ዶ/ር ገለታ ሲሜሶ ቀጣይ አካሄዶችና እርምጃዎች ላይ ጠቃሚ አሳቦችን በማቅረብና ውይይት በማድረግ መርሐግብሩ በጸሎት ተጠናቋል ።



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍43
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_46ኛው_የሥራ_አስፈጻሚ_ኮሚቴ_ስብሰባ_በጉዲና_ቱምሳ_ሁለገብ_ማሰልጠኛ_ማዕከል_ተካሄደ
ጥር 22 ቀን 2017/ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 46ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል አካሄዶዋል። ቄስ ተሾመ አመኑ የአግዚአብሔር ቃል ያካፈሉ ሲሆን በካውንስሉ የተሰሩ የሥራ ሪፖርት ተደምጧል ።ከነዚህም መካከል የካውንስሉ የውጭ ግንኙነት መመሪያ ፣የታሪክ መጽሐፍ ዝግጅት ኮሚቴ ፣የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ኮሚቴ እና የልጆች ፌሰቲሻል ፕሮግራምን በተመለከተ በነዚህ ርዕሰ ጉዳዬች ሪፖርት ቀርቦዋል።
የካቲት 29-30 ካውንስሉ ከቢሊግርሃም ኢሻንጀልስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀውን ፕሮግራም በሚመለከት አስካሁን የተሰሩትንና ልሰሩ በሚገባቸው ጉደይ ላይ ውይይት ተደርጓል ።የበዓለ ሃምሳ ቀን አከባበር በኢትዮጵያ ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ትልቅ የሆነ ውይይት እና አቅጣጫዎች ተቀምጦአል ።
በዚህ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አሳቦች የተነሱ ሲሆን በካውንስሉ ፕሬዚዳንት ጣሰው ገብሬ(ዶ/ር) ፣በምክትል ፕሬዚዳንት ሐዋርያው ዮሐንስ ግርማ እና በካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፈ ደረጀ ጀምበሩ ምላሽ ተሰጥቶበታል ።ቀጣይ የቦርድ እና የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ቀን በመወሰን ተጠናቋል ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2