የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የቢፍቱ_ቦሌ_መካነ_ኢየሱስ_ማህበረ_ምዕመናን_25ኛ_አመት_ክብረ_የምስጋና_ክብረ_በዓል_ወይም_ተነሺና_አብሪ_በሚል_መሪ_ቃል_አክብራለች

በክብረ በዓሉ ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ ያስገነባችውን የአምልኮ አዳራሽ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ ቄስ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።በ25ኛ አመት ክብረ በዓሉ፣ የስዕል እና የባህል አውደ ርዕይም ተዘጋጅቷል። ቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ያለፉትን 25 ዓመታት የወንጌል ስራን ስትሰራ ቆይታለች።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍3
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል_መሪዎች_የቢሊግራሃም_ኢቫንጀሊስቲክ_ኦሶሴሽንን_የሥራ_እንቅስቃሴ_ጎበኙ

በቄስ ደረጀ ጀምበሩ በካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ የተመራው ቡድን ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በቢግኢአ መስሪያ ቤት በመገኘት ካውንስሉ በአሁኑ ጊዜ እያከናወነ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ። በጉብኝቱ ወቅት በሚ/ር ጌሪ ሉንድስቶርም የቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ምክትል ኃላፊ እና በሚ/ር ሃንስ ማንሃግሪን የቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ ኢትዮጵያ ቢሮ እና የመለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ አስተባባሪ እና በተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል የተደረገ ሲሆን በመደረግ ላይ ስላለው የሥራ እንቅስቃሴ ገለጻ ተሰጥቷል። በአሁኑ ጊዜ ከአብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች እየተሰራ ስላለው “የእኔ እንድሪያስ ነኝ” የወንጌል ምስክርነትና የክርስቲያን ሕይወትና ምስክርነት ስልጠና ከፍተኛ ውጤት እያመጣ ያለ መሆኑ ተወስቶ ወደፊት የካቲት 29 እና 30፥ 2017 ዓ.ም በአደባባይ ስለሚደረገው የጀማ ወንጌል ስብከት ከፍተኛ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑንና ሥራዎችም እየተጠናቀቁ እንዳለ ተብራርቷል። በዚሁ ወቅት ዶ/ር ደስታ ደምሴ የማህበሩ አሴሼትድ ዳይሬክተር እና አቶ አዲሴ አማዶ የማህበሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በአሶሴሽኑ እየተሰራ ስላለው ክንውን ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የካውንስሉ ኃላፊዎች የቢሮውን የሥራ ክፍሎች በመጎብኘት ከሠራተኞቹ ጋር ትውውቅ አድርገዋል። ቄስ ደረጀ ጀምበሩ እየተሰራ ስላለው ሥራ ከልብ አመስግነው ሌሎች ተቋማት ከዚህ የወንጌል እንቅስቃሴ ሊማሩ የሚገባቸው አያሌ ነገሮች እንዳሉ ተናግረው በቢሊግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን እየተሰራ ያለው ሥራ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል የመንፈስ አንድነትን የሚያመጣ ተግባር መሆኑንና ካውንስሉ በሚያስፈልገው ሁሉ ከአሶሴሽኑ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል።



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏4
“በአንድነት ቆመን ለሀገራችን ሰላም እና የጋራ ጠላት የሆነውን ድህንነትን ለማሸነፍ በጋራ እንሰራለን” ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀበሩ ይህንን ያሉት "የጥምቀት በዓልን በጽዱ አዲስ አበባ! " በሚል መሪ ቃል የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በጃን ሜዳ የታቦታት ማደሪያ የጽዳት መርሐግብር በተካሄደበት ወቅት ነው።


በጽዳት መረሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ “በአንድነት ቆመን ለሀገራችን ሰላም እና የጋራ ጠላት የሆነውን ድህንነትን ለማሸነፍ በጋራ እንሰራለን” በዛሬው እለትም እዚህ የተገኘነው የጥምቀት በዓል የመላው ኢትዮጵያውያን እና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በዓል መሆኑን በማስመልከት አንድነታችንን ለመግለጽ ነው በማለት ለመላው ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ መልካም በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ሃይማኖታዊ በዓላት ሁሉም ህብረተሰብ አንድነቱንና ትብብሩን የሚያጠናክርባቸው መልካም እሴቶቻችን ናቸው ብለዋል።

ይህም በዓላቱ ደምቀውና አምረው እንዲከበሩ በማድረግ የሀገር ገፅታ እየገነባ መሆኑን የተናገሩት ዋና ጽሐፊው በዛሬው ዕለትም የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች አንድነታቸውን ለማሳየት በጥምቀት በዓል የታቦታት ማደሪያ የፅዳት ዘመቻ ላይ በመሣተፋቸው ምስጋናቸው አቅርበው አንዳችን የአንዳችን በዓል ደስታችን መሆኑን እና አክብሮታችንን ለመግለጽ ተገኝተናል ብለዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ለበዓሉ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርና በስኬት እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰሩ መቆየቱን አስታውሰው በዓሉን ለማክበር ወደ ከተራና ጥምቀት ለሚጓዙ እግረኞችና ለተሽከርካሪዎች መንገዶችን የማስተካከል ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ይህ መድረክ አንድነታችንን ይበልጥ አጉልተን የምናሳይበት መድረክ ነው እኛም ይህንን አንድነታችንን ለመግለጽ እዚህ ተገኝተናል ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሐዋርያዊ ጽ/ቤት ሐላፊ አባ ጴጥሮስ በረጋ ናቸው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ የጥምቀት በዓል ፍቅርንና አብሮነትን የሚያስተምር በዓል ነው በማለት በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ በአብሮነት በማጽዳት የተባበሩትን የሁሉንም ሃይማኖት ተወካዮችና የህብረተሰብ ክፍሎች በቤተክርስቲያኗ ስም አመስግነዋል።

በመረሃ ግብሩ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተዕምነት መሪዎች ፤ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እና የጽዳት አምባሳደሮች ፤ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ አባላትን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍7