የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ጥር_4_የእኔ_እንድሪያስ_ነኝ_ቀን

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል: ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት "የእኔ እንድሪያስ ነኝ" የፀሎትና የወንጌል ስርጭት እንደሚያካሄድ ታወቀ::

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ በቄስ ደረጀ ጀምበሩ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደታወቀው የወንጌል ምስክርነቱ ካለፈው ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በ400 አጥቢያዎች ከተካሄደው ተመሳሳይ የወንጌል ስርጭት ቀጣይ እንደሆነ ታውቋል::

በዚሁ የቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ኃላፊዎች በተገኙበት በዚሁ መግለጫ በወንጌል አገልግሎቱ ከ26ሺ በላይ አገልጋዮች የክርስቲያን ህይወትና ምስክርነት ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ከ200ሺ በላይ "የእኔ እንድሪያስ ነኝ" የፀሎት ካርድ ተበትኖ ክርስቶስን ለማያውቁ ወገኖች ወንጌል የደረሰ መሆኑ በመግለጫው ተብራርቷል::

ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚደረገው የፀሎትና የምስክርነት መርሐግብርም ምዕመናን መለኮታዊው የእግዚአብሔር ጉብኝት በምድሪቱ ላይ እንዲገለጥ እንዲፀልዩና ለዚሁ ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠቅላይ ጸሐፊው ጥሪ አቅርበዋል::



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍51