የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከቢሊግረሃም_አሶሴሽን_ጋር_በመተባበር_ለአገልጋይ_ሴቶች_ስልጠና_ተሰጠ

ህዳር 12 ቀን 2017ዓ/ም በዩጎ ቤተክርስቲያን በተሰጠዉ ስልጠና ከልዩ ልዩ ቤተ-ዕምነት እና ህብረቶች የተወጣጡ 260 የሚሆኑ ሴት አገልጋዮች በስልጠናዉ ተካፍለዋል።

የካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ዳይሬክተር ፓስተር ስንሻት ተካ እንደገለፁት የስልጠናዉ አላማ አገልጋይ ሴቶች ውጤታማ የወንጌል መስካሪዎች እንዲሆኑ ለማስታጠቅ መሆኑን በመግለፅ ይህ ፕሮግራም በተመሳሳይ ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017ዓ.ም. ከ2:30 ጀምሮ ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው በናዛሪን ቤ/ክ የሚሰጥ መሆኑን አክለዉ ተናግረዋል።

ከቢሊግርሃም ኢቫንጀልስቲክ አሶሴሽን ስልጠናዉን የሰጡት ቄስ ፀጋነሽ በበኩላቸዉ እኔ እንድሪያስ ነኝ በሚል መሪ ሃሳብ በስልጠናዉ የተሳተፋ ሴት አገልጋዮች ወደመጡበት ሲመለሱ ወንጌልን በአካባቢያቸዉ መመስከር እንዲችሉ የሚያበቃ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

ከስልጠናዉ በኋላ የጋራ የዉይይት እና የምክክር እንዲሁም የትዉዉቅ ጊዜ ተከናዉኖ ስልጠናዉ ተጠናቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍6
#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግረሃም አሶሴሽን ጋር በመተባበር የአገልጋይ ሴቶች ስልጠና ሁለተኛ ዙር ህዳር 17 ቀን 2017ዓ/ም በናዛሪን ቤተክርስቲያን አካሄደ::

አላማው አገልጋይ ሴቶች ውጤታማ የወንጌል መስካሪዎችና ለታላቁ ተልእኮ አገልግሎት ብቁ እንዲሆኑ ለማስታጠቅ ነው።
ስልጠናው ለ200 አገልጋይ ሴቶች የተሰጠ ሲሆን በህይወታቸውና በአገልግሎታቸው የጌታ ኢየሱስን አዳኝነት የሚመሰክሩ ለሌሎች የጌታን ብቸኛ አዳኝነት የሚናገሩና የሚያሳዩ ሴቶች እንዲሆኑ የሚያበቃ ነው:: የኢትዬጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሴቶች አገልግሎት ክፍል ሴት አገልጋዬች የወንጌልን ተልእኮ በመወጣት የእግዚአብሔርን መንግስት በማስፋት ብቁ እንዲሆኑና እንዲተጉ ልዩ ልዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሆነ ተገልጿል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍94🙏1