#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል
#በሰሜን_አሜሪካ_የሚገኙ_አብያተክርስቲያናትን_በማደራጀት_ቅርንጫፍ_ፅ/ቤቱን_አቋቋመ።
ሴብቴምበር 28/2024 በተካሄደዉ የማደራጀት መርሃ ግብር ላይ የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በስፍራዉ ተገኝተዉ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል ፣ስለካዉንስሉ ገለፃ በማድረግ እና የቦርድ አባላትን በመሰየም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን አቋቁመዋል።
የካዉንስሉ ፅ/ቤት ሃላፊ ፓ/ር ጌትነት ለማ ለጉባኤዉ በዙም አማካኝነት ሰላምታ በማቅረብ ካዉንስሉ ከተመሰረተ ጀምሮ ላለፋት አራት አመታት ያከናወናቸዉን አበይት ተግባራት ገለፃ በማድረግ ማብራሪያ ሰተዋል።በዚህም ካዉንስሉ ለወንጌል አማኙ ታሪካዊ የሆነ መዋቅር እና ከእግዚያአብሔር የተሰጠ መለኮታዊ እድል መሆኑን ተናግረዋል። ተለያይቶ እና ተበታትኖ የነበረዉን የወንጌል አማኝ ወደ አንድነት የማምጣት ስራ ሰርቷል ብለዋል። ለወንጌል አማኙ በተቀናጀ አሰራር የጋራ ድምፅ በመሆን እያገለገለ እንደሚገኝ እና ቤተ ዕምነቶችን፣ሚኒስትሪዎችን በማደራጀት በመመዝገብ እና ፍቃድ በመስጠት እንዲሁም በማስተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ከጉባኤዉ ለተነሳላቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ካዉንስሉ በዓለም አቀፍ ዙሪያ ለመቋቋም ሲንቀሳቀስ የገጠሙት እንከኖች እንዳሉ በመግለፅ አሁንም በካዉንስሉ ዙሪያ እየተወራ የሚገኘዉ ወሬ መሰረት የሌለዉ እና ሃሰት መሆኑን ተናግረዋል።ካዉንስሉ መለኮታዊ ጥሪ እንጂ የፖለቲካ አጀንዳ እንደሌለዉ በመናገር በሃሰተኛ አስተምህሮ ዙሪያ ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ካዉንስሉ ከተመሰረተ አራት አመት እንደሆነዉ እና ሃሰተኛ አስተምህሮ ቀድሞ የነበረ ልምምድ እንደሆነ በማስታወስ ነገር ግን ከመንግስት የወሰዱትን ፈቃድ በመዉሰድ የካዉንስሉ ፈቃድ ሰለተሰጠ ከዚህ በኋላ መጠየቅ እንደሚቻል ተናግረዋል።በአጠቃላይ ከመወቃቀስ እና ከመካሰስ ይልቅ ለመመካከር ቅድሚያ እንስጥ በማለት በሃገር ዉስጥ እና ከሃገር ዉጪ በዓለም አቀፍ የምንገኝ የወንጌል አማኝ ተሰባስበን በአንድነት የክርስቶስን ወንጌል እንስራ ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በቴክሳስ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ፕሬዝዳንት ሆነዉ የተመረጡት ፓ/ር ዶ/ር መላኩ ተስፋዬ ካዉንስሉን አመስግነዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍7🙏1