የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን 6 ኪሎ አጥቢያ ባገኘችው 2000 ካሬ መሬት ላይ ልትገነባ ያሰበችውን ግንባታ አስመልክቶ የምስጋና ፕሮግራም አደረገች።

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን 6 ኪሎ አጥቢያ በቀጣይ ልትሰራ ያሰበችውን የቤተክርስቲያኒቷን የህንፃ ዲዛይን ይፋ ያደረገች ሲሆን ሁሉም አማኝ በዚህ ትውልድ ተሻጋሪ ስራ ርብርብ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን 6 ኪሎ አጥቢያ ዋና መጋቢ የሆኑት ሐዋሪያ መርጋ አብዲሳ ቤተክርስቲያኒቱ በመላ ሀገሪቱ ላሉ አጥቢያዎች መሰረት የጣለች እናት ቤተክርስቲያን መሆኗን ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የእግዚአብሔር መገኘት እንዳለና በእግዚአብሔር መገኘት በአጥቢያዋ ክርስቶስን እየተቀበሉ ያሉ ነፍሳት በርካታ እንደሆኑም በተደረገው የአንድነት ፣ የፀሎት እና የምስጋና ጊዜ በመድረኩ ተገልጿል።

በዕለቱም የእግዚያብሔር ቃል ትምህርት የቀረበ ሲሆን በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ማመስገን እንጂ ማጉረምረም ተገቢ አለመሆኑ የትምህርቱ ዋና ጭብጥ ነበር። ማገልገል እና ማመስገን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጥሪ እንደሆነ እና ክርስቶስም እንዲሁ በነፃ የምንሰጠውን አምልኮ እንደሚፈልግም የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የሆኑት መጋቢ አያንሳ ኦፕሲ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል። የቤተክርስቲያኒቱ ሕንጻ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም 3ሺ የሚጠጉ ሰዎችን የመያዝ አቅም እንዳለው ተነግሯል።

በቤተክርስቲያኒቱ የግንባታ ፕሮጀክት ላይ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ በቀረበበት ፕሮግራም ላይ በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቱ ለማስፋፊያ ስራ የተረከበችውን 2000 ካሬ መሬት አስመልክቶ መላው ምዕመናንና የቤተክርስቲያኒቱ ወዳጆች በተገኙበት የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።
10👍1
በእንባ የተሞላው የ”ዘቾዝን” ተከታታይ ፊልም የስቅላት ትዕይንት ዝግጅት በብዙ ተመልካቾች ዘንድ ትኩረትን መሳቡ ተገለጸ።


ስድስተኛው ምዕራፍ ላይ የደረሰው ፤ “ዘ ቾዝን” የተሰኘው እና ትኩረቱን በወንጌላት ላይ ያደረገው ተከታታይ ፊልም በስድስተኛው ምዕራፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅላት የሚያሳየው ትዕይንት በምን አይለት መልኩ እየተሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ምስል በቅርብ ለሕዝብ እይታ ይፋ ሆኖ ነበር።


በዩትዩብ ላይ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ተዋኒያን ሲተውኑ እንዲሁም ዳይሬክተሩ ዳላስ ጄንኪስ የሚሰራበትን ምሪት ሲያስቀምጥ ይስተዋላል። ሆኖም የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ቀረጻ ከተቋረጠ በኋላ ተዋናይ እና ባለሙያዎች ፊት ላይ የነበረው ስሜት ነበር።


በጣሊያን የተቀረጸው የሁለት ደቂቃ ቪድዮ ምንም አይነት ቃለ ምልልስ ያለነበረው ሲሆን በፊልሙ ላይ ኢየሱስን ሆኖ የሚጫወተው ጆናታን ሩሚ አይታይበትም። ነገር ግን ምስሉ ተዋናዮች እና የፊልሙ ባለሙያዎች በጊዜው የተሰማቸውን ስሜት ለተመልካቾች ያጋራ ነበር።


በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ መግደላዊት ማሪያምን የምትጫወተው ኤልሳቤት ታቢሽ፣ የጴጥሮስ ባለቤት የሆነችውን ገጸ ባህሪ የምታጫወተው ላራ ሲልቪያ እንዲሁም ታማር የተሰኘች ገጸ ባህሪን የምትጫወተው ሻና ዊሊያምስ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲያለቅሱ ይታያሉ።

ተንቀሳቃሽ ምስሉ በዩትዩብ ከ800,000 ጊዜ በላይ የታየ ሲሆን ከ1000 በላይ ሰዎች አስተያየታቸውን አስፍረውበታል።የ6ተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያዎቹ ክፍሎች በ2026 ማብቂያ ላይ ወደ ሕዝብ እንደሚደርሱ ይጠበቃል።


መረጃውን ከክሮስ ዋክ አገኘነው።
4
በአማሪካ ውርጃን የሚቃወሙ ብድኖች በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸውን ያጡ ከ390,000 በላይ ልጆችን በማሰብ የዳይፐር እደላ አደረጉ።


የውርጃ ተቃውሚ የሆኑት ቡድኖች በጋራ በመሆን ከ390,000 በላይ ዳይፐሮችን ለወላጆች አድለዋል። ይህም የሆነው ሕይወትን የማክበር ፕሮግራም በተካሄደበት ጊዜ ነበር።


“Students for life of America” እና “Everylife”ን የመሳሰሉ የውርጃ ተቃዋሚ ቡድኖች በካፕቶል በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን ዳይፐር የማደል የማደል እንቅስቃሴ አካሂደዋል።


ይህም የሆነው በሀገሪቱ ውርጃን የመከልከል ምርጫ ለግዛት አስተዳደሮች ከተሰጠ አንድ አመት በሞላበት ጊዜ ነው። የተደረገው እንቅስቃሴ ዓላማው በውርጃ አማካኝነት ምን ያህል ልጆች ሕይወታቸውን እንዳጡ ለማስገንዘብ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓትም እናቶችን ፣ ካለጊዜያቸውን የተወለዱ ሕጻናት እና ቤተሰቦችን ማገዝ ነው።


ፕላንድ ፓረንትሁድ የተሰኘው በአሜሪካ ግንባር ቀደም የውርጃ ማዕከል በ2022 እና በ2023 ስለ ሰራው ስራ ሲናገር 393,715 ልጆችን ማስወረዱን አሳውቆ ነበር።

በውርጃ አማካኝነት ሕይወታቸውን የሚያጡ ልጆች ቁጥርም በፈረንጆቹ 2024 መጨመሩን ቡድኖቹ ያነሳሉ።
መረጃውን ከሲቢኤን ሊውስ አገኘነው።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
3