የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በአሜሪካን ኮሎራዶ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የዉይይት እና የአንድነት ጊዜ አካሄደ።

ሚያዚያ 25 ቀን 2017ዓ/ም በተካሄደዉ የዉይይት መድረክ በኮሎራዶ የሚገኙ የካዉንስሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ልዩ ልዩ የሚንስትሪ አገልጋዮች በዉይይት መድረኩ ተሳትፈዋል።

በኮሎራዶ የካዉንስሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ጌታቸው ታደሰ በእለቱ የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክት በማስተላለፍ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዉ የካውንስሉ አመሰራረት እና ጠቃሚነቱን በመግለፅ አብራርተዋል።

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን በዋና ፀሃፊነት እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር አድያምሰገድ ወልደማርያም የካዉንስሉ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ፥ ዓላማ ፥ ራዕይ እንዲሁም ቀጣይ ተግባራቶችን ለአባላቱ  በዘርዝር አቅርብዋል። ካዉንስሉ በአሜሪካ እና በአለም አቀፍ ሊሰሩ የታሰቡ ስራዎችን በማብራራት በኮሎራዶ ከሚገኙ አብያተክርስቲያናት እና ህብረት ጋር አሁንም ለመስራት ዝግጁ እንደ ሆኑ አስረድተዋል። በዚህም ከካውንስሉ ጋር በመተባበር አብረን ታላቁን ተልዕኮ በፍቅር እና በአንድነት እናገልግል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መጋቢ ያሬድ ፀጋዬ ምክትል ዋና ፀሐፊ ሲሆኑ የካውንስሉ የትኩረት መስክ ፣ ሚዲያ ፣ የአባለት መብትና ግዴታ ዙሪያ በተመለከተ ማብራሪያ ሰተዋል።

በመጨረሻም ከአባል ቤተ እምነቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶባቸዉ ስብሰባዉ ተጠናቋል።

#ሪፖርተር_ብንያም_ሱፋ

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
👍71
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከኦሮሚያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክረስቲያን መንበረ ፓትርያሪክ በመገኘት በጋራ ጉዳይ ላይ ወይይት አደረጉ።

ሰኔ 16/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከኦሮሚያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኦሮሚያ የሃይማኖት ተቋማር ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ጋር በሰላም ጉዳይ በተለይም በማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚነሱትን ግጭቶች በምክክርና በወይይት መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክራዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ፅ/ቤት ሃላፊ ፓስተር ጌትነት ለማ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክረስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደሰታ በመግለፅ ፣በሰላም ጉዳይ ላይ እንደ ሃይማኖት ተቋም በርካታ ስራዎችን በጋራ እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል።

በምክክራቸውም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ልዩነታችንን በሰላማዊ መንገድ በምክክርና በውይይት መፍታት እንደሚችሉ አንስተው ፣ በቀጣይም በአንድነት ብዙ ስራዎችን መስራት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ዜናውን ያደረሰችን ባልደረባችን
ቤተልሔም ደረጄ ናት
20👍4🙏4
ታቦር ኢቫንጄሊካል ኮሌጅ በሥነ-መለኮት የትምህርት ያሰለጠናቸውን 47 ተማሪዎች ተመረቁ።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አካል የሆነው ይህ ኮሌጅ በመደበኛ፣ በማታ እና በክረምት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 21 ተማሪዎችን በሚስዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እና በመደበኛና በርቀት መርሃ ግብሮች በሚስዮሎጂ በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 26 ተማሪዎችን አስመርቋል። ሲል በማህበራዊ ገጹ ላይ አሳውቋል።
👍1