+++ የጽሙና ጊዜ አለህ? +++
የቆርቆሮና የብረት ጩኸት ጋጋታ ባለበት ውብና ለስላሳ የሆነውን የዋሽንት ድምጽ መስማት የሚቻለው ማን ነው? ሁከትና ረብሻ በሚነግሥበት፣ የማይቋረጥ ግፊያና አለመረጋጋት ባለበት የሰዎች ግርግር ውስጥ ሆነህ እንዴት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ልትሰማ ትችላለህ? የእግዚአብሔርን ድምጽ በአውሎ ነፋስ ፋጨት፣ በምድር መናወጥ፣ በሚያስገመግም የእሳት ድምጽ ውስጥ አታገኘውም። እርሱ የሚናገረው ከእነዚህ ሁሉ በኋላ በሚሆነው "ትንሽ የዝምታ" ጊዜ ነው።(1ኛ ነገ 19፥12)
ልክ የመድኃታችንን የልብሱን ጫፍ በስውር ነክታ ከቁስሏ እንደ ተፈወሰችው ሴት፣ አንተም የነፍስህን ቁስል ለማድረቅ በመቅደሱ የሞላውን የጌታን የልብሱን ዘርፍ በምሥጢር የምትዳስስበት የብቻ ጊዜ ያስፈልግሃል።
ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ ከሰው ርቀህ በርረህ ወደ ፈጣሪ የምትሄድበት የጽሙና ጊዜ ይኑርህ።
ጌታን ያጠመቀውና ለብዙዎች በብርሃኑ ደስ የሚያሰኝ "የሚነድ መብራት" የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሁሉ በፊት ብቻውን ከአምላኩ ጋር በበረሃ ነበር። የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እነዚያን ሁሉ ሰማያዊ ምሥጢራት የተመለከተው ብቻውን በፍጥሞ ደሴት ሆኖ ነው። ስሙን በአሕዛብ፣ በነገሥታቱና በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ይሸከም ዘንድ የተመረጠው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ግን የመረጠው አምላኩ መንፈሳዊውን ኃይል ያስታጥቀው ዘንድ የገዛ ድክመቶቹን ተሸክሞ ብቻውን ወደ አረብ በረሃ ገስግሶ ነበር።
ያንተስ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በመንፈስ የምትጎለምስበት በረሃህ ፣ እንደ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን የምትዘከርበት ፍጥሞ ደሴትህ፣ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በነፍስ ታድሰህ የምትወጣበት አረባዊ ገዳምህ የት ነው? መቼ መቼስ ወደዚያ ትወርዳለህ?
ፎቶው: በንጥርያ የሚገኘው የአል-ባራሞስ ገዳም ነው። በብቸኝነት ሕይወቱ ይታወቅ የነበረው አባ አርሳንዮስ፣ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል በንጥርያ ገዳም ወዳለችው ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ "ሰዎች እርሱን እንዳያዩት፣ እርሱም ሰዎችን እንዳያይ" ተደብቆ(ተከልሎ) የሚያስቀድስባት ምሰሶ ነበረችው። ይህች ምሰሶ አሁንም ድረስ በገዳሙ ትገኛለች።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

+++ "የእግዚአብሔር ዝምታ" +++
እግዚአብሔር ፍጥረታትን ከፈጠረባቸው መንገዶች አንዱ ‹በአርምሞ› ወይም ‹በዝምታ› ነው፡፡ ዝምታ የመናገር ተቃራኒ ወይም ያለ መሥራት ውጤት ነው፡፡ ሰው ዝም አለ የሚባለው ባልተናገረ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሥራ መሥራት ባቆመም ጊዜ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሶምሶምን ነፍስ ይፈልጉ የነበሩ የጋዛ ሰዎች ሶምሶም ወደ ጋዛ መምጣቱንና ወደ አንዲት ጋለሞታ ቤት መግባቱን ባወቁ ጊዜ፣ እርሱ ያለበትን ሥፍራ ከበው ማለዳ ላይ እንገድለዋለን በማለት ሌሊቱን ሙሉ አንዳች ክፋት እንዳላደረጉበት ሲናገር ‹ማለዳ እንገድለዋለን ብለው ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ› ይላል፡፡ በሌላም ሥፍራ ኃጢአተኞች ጽድቅን በመሥራት ኃጢአትን እንደማይቃወሟት ለመናገር ‹እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል፡፡ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ› ሲል እናነባለን፡፡(መሳ 16፥2 ፣1ኛ ሳሙ 2፥9)
ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፤ ዝም በሉ› ብሎ እንደዘመረው የሰው ልጅ ዝም ባለ ጊዜ በአእምሮው ከማሰብ በቀር ምንም ዓይነት የሚያከናውነው ሥራ የለም፡፡ ምክንያቱም ማሰቡ ብቻ ተግባር ስለማይሆንለት ያሰበውን ለማሳካት የግድ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም መሥራት አለበት፡፡ የእግዚአብሔር ዝምታ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዝም ባለ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የሥራ እፎይታ የለም፡፡
ዝምታ ለእግዚአብሔር ሲሆን ኃይሉን የሚገልጥባት የሥራ ወቅት ትሆናለች፡፡ በእግዚአብሔርም ዝምታ ውስጥ ያለች ሐሳብ ፍጥረታትን የማስገኘት አምላካዊ ኃይል አላት፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ‹አሰበ› ተብሎ ሲነገር እንደ ፍጥረታት ሐሳብ ታስቦ ብቻ የሚቀር ሥራ መሥራት የማይችል ዝርው አድርገን እንዳንረዳ፡፡ የእርሱ አሳብ ኃይል አለው፡፡ በአሰበ እና በፈቀደ ጊዜ ሁሉን ካለመኖር ወደ መኖር የሚያመጣ ሥራን የሚሠራ ልዩ ሐሳብ ነው፡፡
እግዚአብሔር ዝም ሲልም ይሠራል!

+++ "አብረን ዝም እንበል" +++
አባ በምዋ (Abba Bemwa) ዓለምን ትቶ ወደ በረሃ በሄደ ጊዜ፣ ለዚህ አዲስ ሕይወቱ የሚጠቅመውን ምክር ይሰጡት ዘንድ ወደ አንድ ቅዱስ አረጋዊ ቀርቦ "ምን ላድርግ" ሲል ጠየቃቸው። እኒህም አረጋዊ ንግግራቸውን የጀመሩት "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ" በሚለው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር ቃል ነበር። (መዝ 39፥1) አባ በምዋም ይህንን የመጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ "ይበቃል አባቴ፣ ይህን ተምሬ እስክፈጽም ድረስ ሌላ ምንም አዲስ ትምህርት አይንገሩኝ" በማለት ወደ በዓቱ ሄደ።
ከዚያም ቀን ጀምሮ ለብዙ ጊዜያት ወደ አረጋዊው አልተመለሰም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋዊው ጻድቅ አባ በምዋን አግኝተው ለምን ለሌላ ተጨማሪ ትምህርት መልሶ ወደ እርሳቸው እንዳልመጣ ጠየቁት። እርሱም "እመኑኝ አባቴ፣ ገና የመጀመሪያውን ትምህርት በሚገባ አልተማርኹትም" ሲል መለሰላቸው። ከረጅም ዓመታትም በኋላ ወዳጁ የሆነ አንድ መነኩሴ የሰማውን የነቢዩ የዳዊትን ቃል እስከ አሁን አጥንቶ ጨርሶ እንደሆነ አባ በምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም "በዚህ የነቢዩ ቃል ላይ ለማሰላሰል እና በሚገባ ወደ ተግባር ለመቀየር አርባ አምስት ዓመታት ወስዶብኛል" ሲል በትሕትና መለሰለት። የአባ በምዋን ታሪክ የጻፈልን ቅዱስ ጰላድዮስ እንደሚናገረው አባ በምዋ በሕይወቱ ሁሉ ፍጽምት የሆነች የዝምታን ሕይወት የመራ ሲሆን፣ በሞቱም ጊዜ "ምነው ይህን ባልተናገርኩ" የሚል አንድም የሕሊና ወቀሳ ሳያገኘው በሰላም አርፏል።
ቅዱስ እንጦንስም በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል መክሯቸው ነበር ፦ "ዝም በሉ፤ ዝምተኛን ሰው እግዚአብሔር በፊቱ ካሉት ሠራዊተ መላእክት እንደ አንዱ ይቆጠረዋልና"
ስለዚህ ከመላእክት ጋር እንቆጠር ዘንድ አብረን ዝም እንበል!

"በረከትን ሁሉ የተሸከምሽ አንቺን የማይወድ ማን ነው? አንድ ጊዜ ቀምቶ የወረሳቸውን ንብረቶች ሁሉ መልሰሽ ከወሰድሽበትና ባዶውን ካስቀረሽው ከሰይጣን በቀር አንቺን ማን ይጠላል? አንቺን ተስፋ አድርጎ ወደ ሲዖል የወረደ የለም። ያለ አንቺም ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም። ያለ ንስሐ እግዚአብሔርን ማየት የሚችል ማን ነው? በአንቺስ ተስፋውን አድርጎ በሰይጣን እጅ የወደቀ ማን ነው? በአንቺ ሳይታጠብ ንጹሕ ሆኖ የተገኘ አለን? በአንቺ ውኃነት ተክሉን አጠጥቶ የደስታን ፍሬ ያልቀጠፈ ማን ነው? በንስሐ እንባ ፊቱን አጥቦ በልቡ እግዚአብሔርን ያላየስ ማን ነው? ለበደለኞች አማላጅ ትሆኝ ዘንድ የተሰጠሻቸው የይቅርታ እናቱ ንስሐ ሆይ፣ አንቺ ብጽዕት ነሽ፤ የመንግሥቱን ቁልፍ ሰጥቶሻልና አንቺ ለምነሽ እግዚአብሔር የሚዘጋው በር የለም"
አባ ዮሐንስ ሳባ (አረጋዊ) (Abba John Saba)
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
አባ ዮሐንስ ሳባ (አረጋዊ) (Abba John Saba)
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
በዕውቀትና የሥራ ልምድ የተሻለ ከሚባል ሰው ጋር አብሮ መሥራት ያስደስትህ ይሆናል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ከሆነ ባለሙያ ጋር መሥራት ደግሞ ያለውን ስሜት በቃላት ለመግለጽ ሊከብድህ ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቤት የሚያገለግል ሰው ከማን ጋር የሚሠራ ይመስልሃል? ሐዋርያው እንዲህ ሲል ይመልሳል "ከእርሱ(እግዚአብሔር) ጋር አብረን የምንሠራ ነንና"። (1ኛ ቆሮ 3፥9) ለጥበቡ ስፍር ቁጥር ከሌለው፣ ሁሉን ከሚችልና በሁሉ ካለ አምላክ ጋር አብሮ ከመሥራት የሚበልጥ ክብር ከየት ይገኛል?! የዕውቀት ተከፍሎ ካለበት፣ ስሕተት ሊገኝበት ከሚችል ደካማ ሰው ጋር አብሮ መሥራት ይህን ያህል የሚያኮራ ከሆነ፣ ሁሉን ከሚያውቅ ፈጽሞ ከማይሳሳት ኃያል አምላክ ጋር "አብሮ ሠራተኛ መሆን" ምን ያህል እጥፍ ድርብ ያኮራ ይሆን?!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
+++ ‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድመስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ› +++ ማቴ 16፡24
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሽማግሎች ፣ ከጻፎች እና ከካህናት አለቆች ብዙ መከራ ተቀብሎ እንደሚሞት ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት እንደሚነሣ ለሐዋርያቱ ገልጦ ሲያስተምራቸው ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታውን ‹አይሁንብህ!› ብሎ ሞቱን ሊከላከል ጀምሮ ነበር፡፡ ጌታችን ግን ቅዱስ ጴጥሮስ ለጌታው ያለውን ፍቅር ተጠቅሞ ይህን ተቃውሞ እንዲያሰማ ሹክ ያለውን በረቂቅ የሚሠራውን ክፉውን መንፈስ ‹ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን› ብሎ ገሰጸው፡፡ አረጋዊው ጴጥሮስ አይሁንብህ ሲል ከመምህሩ ሊያሸሸው የነበረው የሞት ጽዋም ወድዶ ወደሚከተለው ወደ እርሱ ተላልፋ ትሰጣለችና ፤ ‹ለአንተስ ቢሆን መች ይቀርልሃል!› በሚል ዓይነት ብሒል ‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ› አለው (ማቴ 16፡24)፡፡
በርግጥ ይህ ቃል ለቅዱስ ጴጥሮስ ብቻ የተነገረ አይደለም፡፡ ክርስቶስን ለመከተል ፈቃድ ላለን ለእኛ ክርስቲያኖች ሁሉ እንጂ፡፡ ልብ ብለን ካነበብነው ከላይ ባነሣነው የጌታችን ትምህርት ውስጥ ሦስት ዋና ዋና ነገሮች በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህም አንደኛ ‹ራስን መካድ› ፣ ሁለተኛ ‹መስቀልን መሸከም› ፣ ሦስተኛ ‹እርሱን መከተል› ናቸው፡፡ የክርስቶስ የሆኑት ክርስቲያኖች ሁሉ እነዚህ ሦስቱን ነገሮች በማድረግ ይታወቃሉ፡፡
የራሳቸውን ፍላጎት እና ስሜታቸውን ገትተው በፈቃደ ክርስቶስ የሚኖሩ ፤ ሰው እንደ መሆናቸው የተለያየ ዝንባሌ እና ምኞት ቢኖራቸውም ሃይማኖታቸውን በተመለከተ ‹የእምነታቸው ራስና ፈጻሚ የሆነው› መድኃኔዓለም ክርስቶስ የወደደውን ብቻ በአቋምነት አጽንተው የሚይዙ ፤ ከእከብር ባይነትና ከእኔ ብቻ ልደመጥ ፉክክር ወጥተው አንዱን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርጉ እነርሱ ራሳቸውን የካዱ ናቸው፡፡ ራስን መካድ በአጭሩ የራስ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አውጥቶ ለአምላክ የተወደደ ማኅደር ለመሆን ራስን ባዶ ማድረግ ማለት ነው፡፡
ሁለተኛው እንድናደርግ የታዘዝነው ደግሞ ‹መስቀል› መሸከም ነው፡፡ በዚህ ክፍል መስቀል የሚለው ቃል መከራና ሥቃይን ተክቶ ለመግለጽ የተነገረ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ መከራዎች ልክ አምላካችን በዕለተ አርብ እንደተቀበላቸው ያሉ የንጽሕና መከራዎች ፤ ያለ በደልም በግፍ አድራጊዎች የሚደርሱ መገፋቶች ናቸው፡፡ ሰው በሁለት ዓይነት ምክንያት መስቀል ሊሸከም ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ የክርስቶስ ተከታይ የሚያስብለውና ዋጋ የሚያሰጠው ግን አንዱ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም የክርስቶስ ስለሆንን ዓለም ጠልታን በእኛ ላይ በግፍ የምትጭንብን የንጽሕናችን መስቀል ነው፡፡
ሌላኛው ግን ሰው በሠራው ክፋት እና በኃጢአቱ ምክንያት የሚደርስበት መከራ ሲሆን በዚህም ምክንያት የሚሸከመው መስቀል የራሱ ሳይሆን (‹መስቀሉን› የሚለውን ቃል ልብ ይሏል) ‹የኃጢአትን መስቀል› ነው፡፡ በዚህም መስቀል የክርስቶስ መሆኑ ሊገለጥ ፣መንፈሳዊ ክብርንም ሊያገኝበት አይችልም፡፡ እንዲህ ያለውም ጎስቋላ ሰው ልክ በጌታችን ቀኝ እና ግራ ስላደረጉት በደል የሚገባቸውን ፍርድ ተቀብለው እንደ ተሰቀሉት ወንበዴዎቹ ይቆጠራል (ሉቃ 23፡41)፡፡
እኛስ ስንት ጊዜ በተሸከምናቸው የመከራ መስቀሎች ወገባችን ዛለ? በእነዚያ ጀርባችን ላይስ በጮኹት የስቃይ ጅራፎች ምን ያህል በደም ታለልን? እንዲህስ ከሆነ ታዲያ ክብራችን ወዴት አለ? የንጽሕናችንንስ አክሊል ወዴት አሽቀንጥረን ጣልናት? ይህ ሁሉ የደረሰብን የመከራ ውርጅብኝ ረድኤት ያሳጣን የኃጢአታችን ቢሆንብን አይደል?፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ በፈጣሪያችን ፊት ራሳችንን ከመጣልና ንስሓ ከመግባት ውጭ ምን ተስፋ አለን?
ራስን ከካዱ እና መስቀሉን ከተሸከሙ በኋላ ያለው ሦስተኛው እና የመጨረሻው ትዕዛዝ ክርስቶስን መከተል ነው፡፡ ልብ በሉ የክርስቶስ ተከታይ መሆን እንዲሁ በንግግር እና በዋዛ የሚደረግ አለመሆኑን መጽሐፍ ቅዱሱ ሲነግረን ከእርሱ በፊት ሁለቱን ወሳኝ ነገሮች አስቀመጠልን፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ለማለት በቀዳሚነት ራሱን መካድ አለበት፡፡ ቀጥሎም በጽኑዕ ጫንቃው የንጽሕናውን መስቀል የሚሸከም ሊሆን ይገባዋል፡፡ ካለዚያ ግን የክርስቶስ አድናቂ እንጂ ተከታይ መሆኑ የሚያጠራጥር ይሆናል፡፡ እኛስ የቱ ላይ ነን ያለነው?
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!

እኔ ገደሉን ለማለፍ ወደ ብርሃን ሥፍራ ለመድረስ የቸኮልሁ ነኝ፡፡ አንቺ የመድኃኒት ድልድይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለተገፉት መጠጊያ የተድላ ደስታ ሥፍራ ነው፡፡
የመለኮትን ዕንቁ ለመግዛት እኔ ነጋዴ ነኝ፡፡ አንቺ የሕይወት መርከብ ነሽ፡፡ ልጅሽም የበጎ ነገር ሁሉ ድልብ በውስጡ ያለበት የትርፍ ሥፍራ ነው፡፡
እኔ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የምፈልግ ደሃ ነኝ፡፡ አንቺ የክብር ሁሉ መከማቻ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለባለሟልነትና ለክብር ለማሞገስ የሽልማት ጌጽ ነው፡፡
እኔ የታረዝሁ የብርሃን ልብስ የምሻ ነኝ፡፡ አንቺ የሸማኔ ዕቃ ነሽ፡፡ ልጅሽም የማያልቅ የማያረጅ የሃይማኖት ልብስ ነው፡፡
እኔ ቁስለኛ ነኝ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡
===========
የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት የስም አጠራሯ ከአንደበቱ የማይለየው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
በጸሎቷ የምናምን ሁላችንንም በቃል ኪዳኗ ጥላ ትከልለን!!!
በጦር ወሬ ለቆሰለው ጆሮአችን የልጇ ሰላም ካሣ ይሁነን!
ከአምባዋ ታገናኘን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
የመለኮትን ዕንቁ ለመግዛት እኔ ነጋዴ ነኝ፡፡ አንቺ የሕይወት መርከብ ነሽ፡፡ ልጅሽም የበጎ ነገር ሁሉ ድልብ በውስጡ ያለበት የትርፍ ሥፍራ ነው፡፡
እኔ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የምፈልግ ደሃ ነኝ፡፡ አንቺ የክብር ሁሉ መከማቻ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለባለሟልነትና ለክብር ለማሞገስ የሽልማት ጌጽ ነው፡፡
እኔ የታረዝሁ የብርሃን ልብስ የምሻ ነኝ፡፡ አንቺ የሸማኔ ዕቃ ነሽ፡፡ ልጅሽም የማያልቅ የማያረጅ የሃይማኖት ልብስ ነው፡፡
እኔ ቁስለኛ ነኝ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡
===========
የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት የስም አጠራሯ ከአንደበቱ የማይለየው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
በጸሎቷ የምናምን ሁላችንንም በቃል ኪዳኗ ጥላ ትከልለን!!!
በጦር ወሬ ለቆሰለው ጆሮአችን የልጇ ሰላም ካሣ ይሁነን!
ከአምባዋ ታገናኘን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
በገነተ አበው (Paradise of the fathers) እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብርድ ይሰቃይ ለነበረ ምስኪን የለበሰውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ አውልቆ ሰጠው። ከጥቂት ጊዜ በኋላም በገዳም ሆኖ የሰፋቸውን ሰሌኖች ለመሸጥና የእለት ምግቡን ገዝቶ ለመመለስ ወደ ገበያ ሲወጣ፣ በመንገድ ዳር የቆመች አንዲት ዘማ ያን ለምስኪኑ ሰው የሰጠውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ ለብሳው ያያታል። ባየው ነገር የተደናገጠው መነኩሴ "የምድር መላእክት የሚለብሱትን ይህን የክብር ልብስ በከንቱ ቦታ እንዲውል አደረግኹት" እያለ ማልቀስና መቆጨት ጀመረ። ሲያዝንም ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አይዞህ አትዘን፤ መጎናጸፊያህን ለዚያ ምስኪን በሰጠህበት ቅጽበት ከእጅህ ተቀብሎ የለበሰው ክርስቶስ ነው። ከዚያ በኋላ ለሆነው ሁሉ አንተ ተጠያቂ አይደለህም" ሲል አጽናናው።
ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ጠጥቶ ሊሰክር ወይም ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። ያ የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ጠጥቶ ሊሰክር ወይም ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። ያ የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
የኃጢአተኞች ተስፋ የሆነው መድኃኒታችን በኢያሪኮ ገብቶ ሲያልፍ፣ የቀራጮች አለቃ ባለጠጋው ዘኬዎስ ሊያየው ወድዶ ነበር። ነገር ግን አልቻለም። ያለማየቱንም ምክንያት ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ሲነግረን "ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው" ይለናል።(ሉቃ 19፥3) ዘኬዎስ ጌታን ማየት ያልቻለው በእርሱ የቁመት ማጠር ላይ የሕዝቡ ብዛት ተጨምሮበት ነው። ታዲያ ለዚህ ችግር ጥሩ መፍትሔ የሚሆነው "እስኪ ዘወር በሉ" እያለ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር መጣላት ሳይሆን፣ የራሱን ቁመት ማጠር የሚፈታበት ሌላ መንገድ መፈለግ ነው። ስለዚህም ከፊቱ ወዳለው የሾላ ዛፍ ሮጦ ወጣ። "ባለጠጋ ነኝ፤ በዚያ ላይ ትልቅ ሰው። ራሴን እንደ ትንሽ ልጅ እዚህ ዛፍ ላይ ሳንጠለጥል የሚያየኝስ ምን ይለኛል?" አላለም። ዘኬዎስ ስለ ክብሩና ስለ ሰው አስተያየት ቢጨነቅ ኖሮ "ሰው የሆነውን አምላክ" ማየትና በቤቱ ማስተናገድ ይቀርበት ነበር። ብዙዎቻችን እኛ ክርስቶስን ክርስቶስም እኛን ከሚያይበት የሾላ ዛፋችን "ንስሐ" የማንወጣው "ሰው ምን ይለኛል?" በሚል አጉል ጭንቀት ነው።
አሁን ዘኬዎስ ከሾላው ዛፍ ላይ ነው። የቁመቱን ማጠር ችግር ለመፍታት ባደረገው ጥረት ከአንድ ሰው ጋር ሳይጣላ ያለ ማንም ከልካይ የፈለገውን ክርስቶስ ለማየት በቃ። ጌታም ከበለሷ ተክል ፈልጎ ያጣውን ፍሬ አሁን ከሾላው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አገኘው።(ማቴ 21፥19) ይህም በሾላው ዛፍ ላይ የተገኘው ፍሬ "የዘኬዎስ ተነሳሒ ልብ" ነው።
አንዳንድ ጊዜ መንፈሳዊ ሕይወትህን፣ ዓላማህን እንዳታይ ከፊትህ ቆመው የሚጋርዱህ ውጫዊ ነገሮች ይኖራሉ። "ዘወር በሉልኝ!" እያልክ ከእነርሱ ጋር አትጋጭ። "ለምን ትከልሉኛላችሁ?!" በማለትም በብስጭት አታጉረምርም። እንደ ዘኬዎስ የራስህ ችግር ላይ አተኩር። የውጭውን ነገር ማማረር ትተህ እጥረትህን የሚቀርፍልህ የምትወጣበት ዛፍ ፈልግ። እዚያው ሆነህ ለመንጠራራት አትሞክር። ችግርህ ከመንጠራራት በላይ ነው። አትታክት፣ እስኪ መጋፋት ተውና መሬቱን ልቀቅ አድርግ። ያን ጊዜ ከማንም ሳትጣላ ከምትፈልገው እና ከናፈቅኸው ነገር ጋር ያለ ምንም ከልካይ በግልጽ ትተያያለህ። ብቻ የሕዝቡን ብዛት ትተህ የራስህ ማጠር ላይ አተኩር።

አንድ ሰው አባ አርሳንዮስን "ስለ እግዚአብሔር ብዬ ከአንተ ኋላ እከተልሃለሁና ቆየኝ" አለው። አባ አርሳንዮስም መልሶ "ስለ እግዚአብሔር ብዬ ከአንተ እሸሻለሁና ተወኝ" ሲል መለሰለት።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
+++ ሕማም የማያውቀው +++
በአካላዊ ቅርጹ ከእንጉዳይ (የጅብ ጥላ የምንለው) ጋር የሚመሳል፣ በክብደት መጠኑ ደግሞ በአማካይ ከ1.5 ኪሎ ግራም በላይ የማይመዝን፣ ነገር ግን ባለው የሥራ ድርሻ እና በማከማቻ ቋትነቱ ከምንኖርባት ዓለም በብዙ እጥፍ የሚበልጥ እጅግ በጣም ውድ የሆነን ስጦታ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ አኑሯል፡፡ ስለዚህ ስጦታ ምንነት እና ያለውን እምቅ ኃይል ፈልጎ ለማግኘት ብዙ ምርምሮች እና ብዙ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ የሚያስገርመው ግን አጥኚውም ተጠኚውም አንድ መሆኑ ነው፡፡ ራሱን በራሱ ያጠናል፣ ከጥናቱም ባገኘው አዲስ መረጃ በራሱ ይገረማል፣ ስለ ራሱም ብዙ የጥናት ወረቀቶችን ያሳትማል፡፡ አሁንም ይህን የምታነቡትን አጭር ጽሑፍ እያደረሳችሁ ያለው እርሱ ነው፡፡ ለመሆኑ እርሱ ማነው? የዚህም ጥያቄ ጠያቂና መላሹም እርሱ ነው፡፡ ማን? የሰው ልጅ ናላ (Human Brain)
ለዛሬ ስለዚህ እጅግ አስደናቂ ሕዋስ ምንነት ሰፊ ትንታኔ ማቅረብ ወይም ስለ ሥሪቱ መናገር የጽሑፋችን ዓላማ አይደለም፡፡ ነገር ግን ስለ ሰው ልጅ ናላ ሳይንሱ ከነገረን እውነታዎች ውስጥ አንዱን ብቻ መርጠን ጥቂት ነገር ለማለት ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው አብዛኛው የሰውነታችን ክፍሎች የሕመምን ስሜት ተሸክመው ወደ ናላ የሚወስዱ ጥቃቅን መልእክተኞች (pain receptors) ስላሏቸው፣ አንድ ሰው እጁ አካባቢ በመርፌ ቢወጋ ቶሎ የሕመሙ ስሜት ይሰማዋል፡፡ ይሁን እንጂ ናላን (Brain) ግን ክፍት ሆኖ የማግኘት ዕድሉ ቢኖረንና በዚሁ መርፌ የላይኛውን ክፍል (Cortex) ብንወጋው እንደ ቀድሞው ተመሳሳይ የሆነ የሕማም ስሜት አይኖረንም፡፡ ምክንያቱም ናላችን የራሱን ሕመም የሚሸከሙለት መልእክተኞች (pain receptors) የሉትም። (አሁን እየተናገርን ያለነው በዋናነት ስለ ናላ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከናላ በላይ ያለው እርሱን የሸፈነው ክርታስ (membrane) pain receptors ስላሉት የሕመም ስሜት ይፈጥራል፡፡)
በዚህም ምክንያት የናላ ቀዶ ሕክምና የሚደረግላቸው አንዳንድ ሕመምተኞች ንቁ ሆነው ሳለ ቀዶ ሕክምናው ሊከናወን ይችላል፡፡ በዚህም ጊዜ የትኛው የናላቸው ክፍል የበለጠ ጉዳት እንደ ደረሰበት በመሳሪያ ታግዘው ጥቆማ በማድረግና በሌላም አስፈላጊ በሆኑ መንገዶች ሐኪሞቻቸውን ሊያግዙ ይችላሉ፡፡ (በቀዶ ጥገናዋ ጊዜ የእጇን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው የአዕምሮ ክፍሏ እንዳይጎ ቫዮሊን በመጫወት ሐኪሞቹን ታግዛቸው የነበረችው ዳግማር ተርነር (Dagmar Turner) የተባለች የ53 ዓመቷ ታካሚ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ናት፡፡) ይገርማል የሰው ልጅን የሕመም ስሜቶች ሁሉ የሚቆጣጠረው ሕዋስ ለራሱ ግን ሕመም ተቀባይ የለውም።
ይሁን እንጂ ይህ ውጋት የማያውቀው፣ በሕመም ለሚገኙ የአካል ክፍሎቻችንም የሚድኑበትን እዝ የሚያስተላልፈው ሕዋስ አንዳንድ ጊዜ ግን ለሰውነታችን መታመም ምክንያት ሊሆን ይችላል። ይኸውም ክፉ የኃጢአት ሐሳቦችን በሕሊናችን ባነገስን ጊዜ ናላ የሚያመነጨው ኮርቲሶል (Cortisol) የሚባል ኬሚካል አለ። ኮርቲሶል የውጥረት ኬሚካል (Stress chemical) ሲሆን፣ ንቁ የሆነውን የአዕምሮ ክፍል እንቅስቃሴ የሚቀንስ ነው። በመሆኑም ይህ ኬሚካል በመነጨ ጊዜ አመክንዮአዊነት፣ ችግር ፈቺነት፣ የሌሎችን ስሜት መረዳት፣ ርኅራኄና ይቅር ባይነት በአዕምሮአችን ቦታ አይኖራቸውም።
ክፉ ስላሰብን ናላችን ባመነጨው ኬሚካል (ኮርቲሶል) ምክንያት የሚፈጠረው ውጥረት (stress) ደግሞ መዘዙ ቀላል አይደለም። ሌሎች የአካል ክፍሎቻችንም እንዲታመሙ (psychosomatic disorder ይባላል) ሊያደርግ ይችላል። ታዲያ ወደዚህ ሁሉ የጤና ቀውስ ላለመግባት ሕሊናን ከክፋት መጠበቅ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው። ሰይጣን በሚያመጣብን የክፉ ሐሳብ ሞገድ ላለመናወጽ ራስን በበጎነት አጽንቶ መጠበቅ ግድ ይለናል። አበው የክፉ ሐሳብ አማራጮችን በሕሊናችን የሚያንሸራሽረውን ሰይጣን በዝንብ ይመስሉታል። ዝንብ ወደ ቤታችን የሚገባው በር ወይም መስኮታችንን ክፍት ስናደርግ ነው። ባገኘው ክፍተት የገባውም ዝንብ ማረፊያ ቆሻሻ ነገር በቤትህ ካገኘ ይሰነብታል፣ ይራባል (ይባዛል)። ቤትህ ንጹሕ ከሆነ ግን እንደ ገባ ፈጥኖ ይወጣል። ሰይጣንም እንዲሁ ነው፤ ክፉ ሐሳብን ይዞ ወደ ሕሊናህ ሲበር ይመጣል። ለእርሱ ክፋት የሚስማማ ማንነት ይዘህ ከጠበቅኸው፣ ያድርብሃል። አዕምሮህን መናገሻ ከተማው ያደርገዋል። በንጹሕ ሕሊና በበጎ ሰብዕና ሆነህ ካገኘህ ደግሞ እንዲህ ካለው አዕምሮ ውስጥ ማደር ስለማይቻለው ፈጥኖ ከአንተ ይለያል። የውስጥ ሰላምህም እንደ ወንዝ ይፈስሳል። ነፍስህ እና ሥጋህንም ከሕመም ታድናቸዋለህ።

+ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የመጻሕፍት ጉባኤ በሐዋሳ ሊጀመር ነው! +
ለአንድ ዓመት ያህል በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ የነበረው በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የሚካሔደው የጃንደረባው የመጻሕፍት ጉባኤ ሠረገላ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በመገስገስ ከአዲስ አበባ ውጪ የመጀመሪያውን ጉባኤ በሐዋሳ ሊያደርግ ዝግጅቱን አጠናቅቆአል:: ከወራት በፊት ከሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ጋር በመተባበር በኢጃት ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት ያደረጉት የሐዋሳ አገልጋዮች በንቃት የሚሳተፉበትን ይህንን ልዩ የመጻሕፍት አንባቢያን ጉባኤ በሐዋሳና አካባቢዋ ያላችሁ ሁሉ እንድትታደሙ ተጋብዛችኁዋል::
በዕለቱ የሐዋሳ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አንባቢያን ኅብረት (Book Club) በይፋ ይመሠረታል:: የጃንደረባውን ባኮስ ዜና ጥምቀት የሚተርከው "ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ" መጽሐፍ ዳሰሳ ቀርቦበት ውይይት ይካሔዳል::
"ጃንደረባውም ደስ ብሎት መንገዱን ይሔድ ነበር" ሐዋ. 8:39
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው?

+++ ሦስቱ ስሜቶች +++
አንድ በጨለማ ቤት ውስጥ ለረጅም ሰዓታት የተቀመጠ ሰው የቤቱን መስኮት በከፈተ ጊዜ ከውጪ የሚገባውን ብርሃን ሲመለከት መልሶ ለጥቂት ደቂቃዎች ዓይኑ እንደሚጭበረበር (እንደሚታወር)፣ እንዲሁ ፈጣሪውን ካለማወቅ ጨለማም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ ብርሃን የሚቀርብ ሁሉ አላዋቂነቱን ይረዳል፡፡ ይህን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለመደገፍ የሙሴን ታሪክ ማስረጃ አድርገን እስኪ እናቅርብ፡፡
ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ቤዛ እንዲሆን የመረጠው ሙሴን እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ሲያስተዋውቀውና ወደ አገልግሎት ሲጠራው የተገለጠለት በቁጥቋጦ ላይ በሚነድ ብሩህ እሳት አምሳል ነበር፡፡(ዘጸ 3፡2) ቀጥሎም ሙሴ ወደ ፈጣሪው ከቀረበ በኋላ ደግሞ ወደ ከነዓን የነጻነት ጉዞ ሲያደርጉ እግዚአብሔር ‹በደመና እና በእሳት ዓምድ› ተገልጦ መንገድ ይመራቸው ነበር፡፡(ዘጸ 13፡21) በስተመጨረሻም በሲና ተራራ ሕግን በሰጠው ጊዜ ራሱን ለሙሴ የገለጠለት ‹በጨለማ ፣በነፋስ ፣በጢስ› ነበር፡፡(ዘጸ 20፡18-21)
እስኪ የተገለጠባቸውን ሦስቱን ምሳሌዎች ቅደም ተከተሉን በደንብ እናስተውል፡፡ መጀመሪያ በብርሃን ፣ሁለተኛ ደመና በቀላቀለ የተከፈለ ብርሃን ፣በስተመጨረሻም በጨለማ ነበር፡፡ ይህም ሰው እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በር ሲገባ የሚሰሙትን ሦስቱን ውስጣዊ ስሜቶች የሚያሳይ ነው፡፡ በመጀመሪያ በተማረው ጥቂት ትምህርት ብዙ ነገር ያወቀ፣ እግዚአብሔርንም በሰፊው የተረዳውና ሁሉ ነገር ብርሃን መስሎ ይሰማዋል፡፡ ከእኔ በላይ ዕውቀት ለሐሳር ይላል። ሆኖም ግን መንፈሳዊ ትምህርቱን እና ንበባቡን እያጠናከረ ሲመጣ ልክ ብርሃኑ በደመና እንደተከፈለ፣ ስለ እግዚአብሔር የሚያውቀው ዕውቀት ብዙ ተከፍሎ እንዳለበት እየተረዳ ይመጣል፡፡
በስተመጨረሻም የበለጠ ከቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር እየተቆራኘ ሲመጣ እስከዛሬ የተማረው እና ስለ ፈጣሪው ያወቀው ዕውቀት ሁሉ ወደ ኢምንትነት ይለወጥበታል፡፡ በብዙ ትምህርት ውስጥ ቢያልፍም ምን ያህል አላዋቂ እንደሆነ ይረዳል፡፡

እግዚአብሔር ኪያኪ እመ ኢያትረፈ ለነ እምኮነ ከመ ሰዶም እምኮነ
ዘይቤ ኢመጻእኩ እጸውዕ ጻድቃነ አላ ኃጥአነ ለንስሐ
እግዚአብሔር አንቺን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን ነበር
ኃጢአተኞችን ለንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም እንዳለ
ዘይቤ ኢመጻእኩ እጸውዕ ጻድቃነ አላ ኃጥአነ ለንስሐ
እግዚአብሔር አንቺን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን ነበር
ኃጢአተኞችን ለንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም እንዳለ
ጡቶችዋ የድንግልናን ወተት ማመንጨት በጀመሩ ጊዜ በክንዷ ደግፋ የምታጠባው ሕፃን፣ ፀሐይን እያወጣ ዝናምን እያዘነበ ፍጥረቱን የሚመግብ አምላክ መሆኑን ታውቅ ነበር። በእርሷ ማኅጸን በዝምታ ያደረው ጽንስ፣ በሰማይ ኃይላት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እየተባለ የመድረኩ መሠረት እስኪናወጽ ድረስ በታላቅ ድምፅ የሚመሰገን መሆኑ አልተሰወራትም።(ኢሳ 6፥4) ስለዚህም ራሷን ወደ ሆዷ ዘንበል በማድረግ የመላእክቱን ቅዳሴ ታደምጥ ነበር።
ድንግል ወደ እርሷ ማኅጸን የገባው "የሚሳነው ነገር የሌለ የልዑል ልጅ" እንደ ሆነ ብታውቅም ሁሉን አልጋ በአልጋ እንዲያደርግላት ግን አልተማጸነችውም። የልጇን ሁሉን ቻይነት ወልደው በሚያሳድጉ ሁሉ ከሚደርሰው የእናትነት ጭንቅ ማምለጫ አላደረገችውም። ከጡቶቿ ወተት ፈልጎ እንደ ሕፃናት ሲያለቅስ "አምላክ አይደል አይርበውም" ብላ ቸል አላለችም። ክፉው ሄሮድስ ሊገድለው በፈለገ ጊዜ "የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናቱ" እመቤታችን ድል ነሺነቱ ወዴት አለ? አላለችም። ስለ ሄሮድስ ሠራዊት አስጨናቂነት ጉንጮቿ እስኪቃጠሉ ድረስ አነባች፣ የበኩር ልጇንም አንዴ በጀባዋ አንዴ በጎንዋ እያዘለች የግብጽን ተራሮች እንደ ወፍ ዞረች እንጂ።
በእነዚያ የረሃብ ጊዜያት ድንግል ከሃሊ ልጇ ከሰማይ መና እንዲያዘንምላት ወይም ድንጋዩን ዳቦ እንዲያደርግላት ጠይቃ አልተፈታተነችውም። እስራኤላውያን በበረሃ ጉዟቸው ወቅት የሚከተላቸው (ይዘው የሚጓዙት) ዓለት ነበራቸው። እነርሱም በተጠሙ ጊዜ የሚጠጣ የሚያገኙት ከዚያ ዓለት ከሚፈልቀው ውኃ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ታሪክ በማስታወስ በበረሃ ውኃ ያፈልቅላቸው የነበረው ዓለት በምሥጢር የክርስቶስ ምሳሌ መሆኑን ሲናገር "ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ" ይላል።(1ኛ ቆሮ 10፥3) እመቤታችን የማይቋረጥ የሕይወት ውኃ የሚፈልቅበትን ይህን መንፈሳዊ ዓለት ይዛ ስትሰደድ አንድ ቀን ስለ ጥሟ አላማረረችውም። ራሱን በፈቃዱ ባዶ ላደረገው አምላኳ ከሁሉ ይልቅ በሥጋ ባዶ መሆንን በደስታ ለመቀበል የተዘጋጀ ቆራጥ ኅሊና ነበራት። ስለዚህም በልጇ ምክንያት ከደረሰባት መከራ በአንዱ እንኳን አላማረረችም።
+++ ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ +++

ማርያም ለጴጥሮስ ወለጳውሎስ ጽላሎቱ ሰበን
ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ
"ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር" ሐዋ 5፥15
"እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር" ሐዋ 19፥11