የዓለም ብርሃን፣ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ተብሎ የሚጠራው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ክርስቲያኖችን ያለ ልክ የሚያሳድድ አመጸኛ ነበር። ይሁን እንጂ የዋሕ ልቡ በአምላኩ ፍቅር ከተነደፈ በኋላ ግን አለመታዘዝን ሁሉ በመታዘዝ ተበቀለው። ለክርስቲያኖች ገና ስሙ ሲጠራ የሞት መዓዛ የነበረው ሳውል፣ ከንስሐው በኋላ ግን መላው እርሱነቱ ሕይወት የሚሸተትበት የክርስቶስ መዓዛ ሆነ።(2ኛ ቆሮ 2፥15) ንስሐ የበደለ ጳውሎስን እንዳልበደለ አደረገችው።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስማቸውን የምንጠራቸው ቅዱሳን ሁሉ የእግዚአብሔር የመሐሪነቱ ምልክቶች ናቸው። ዛሬ የእግዚአብሔር ወዳጆች ብለን የምናከብራቸው ንጹሐን፣ ትናንትና በሕይወታቸው ወድቀው የተነሡ እና በንስሐ እንባ ታጥበው ይቅርታን ያገኙ ኃጥአን ነበሩ። አሁን በቤተ ክርስቲያን ሰማይ ላይ ሲያንጸባርቁ የምናያቸው ቅዱሳን፣ ውበት የሚሰውረውን የኃጢአት ግርዶሽ በንስሐ አስወግደው በቸርነቱ ብርሃን የደመቁ ከዋክብት ናቸው። አምስት መቶም ይሁን ሃምሳ ብቻ ያልተበደረ እና ምሕረት ያልተደረገለት ጻድቅ አይገኝም።(ሉቃ 7)
ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚነገረው "ከአንዲት ድንግል" በቀር ነው። ይህችም ድንግል ከተፈጠረች ጀምሮ በምንም ምን አልረከሰችም። እንኳን በሥራዋ በሐሳቧም ኃጢአትን የማታውቅ ኅትምት በመሆኗ፣ ከርኩሰት የሚያነጻና ከበደል የሚመልስ ንስሐ አላስፈለጋትም። እርሷ ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ከበረዶ ይልቅ ነጭ ነበረች። በእድገቷም ጊዜ የዚህ ዓለም ክፋት አንዳች አላገኛትም። እርሷ የኃጢአት ጉድፍ ያልወደቀባት ንጹሕ ምንጭ ናች። በመርዙ ብዙዎችን ወግቶ የጣለ አዳኙ(ይጠብቃል) አውሬ ያልተነፈሰባት በመንፈስ ቅዱስ የታጠረች የገነት ተክል ነች። ይህች ድንግል በኃጢአት ተፍገምግመው ለወደቁ የሚነሡበትን የንስሐ ምርኩዝ ለሰጠ የይቅርታ አምላክ እናቱ ናች።
ጻድቃን ሁሉ ከተፈጠሩበት ልዕልና ዝቅ ካሉ በኋላ በንስሐ መሰላልነት ወደ ክብር ሲመለሱ፣ ድንግል ግን ከዚያ ልዕልና ለአንዲት ሰዓት እንኳን ሳትናወጽ በጽናት ኖረች። ስለዚህም የእርሷ ንጽሕና ያለ ንስሐ ሆነ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

+++ "ፍቅርና ፍርሐት"+++
በሰው መካከል ያለ ቀረቤታ ሲጠነክርና ፍቅሩ ያደገ ሲመስል መከባበርና ሐፍረት እቀነሰ ሊመጣ ይችላል። "አሁንማ መፈራራት አያስፈልግም"፣ "እንደ ስሜትህ መሆን ትችላለህ?" የሚሉ ቃላቶችን በጊዜው ለጠበቀው ወዳጅነታቸው መመሪያ ጥቅስ ሊያደርጉትም ይችላሉ። ነገር ግን ጉዳዩ ለከቱን ያለፈ ቀን ይዞባቸው የሚመጣው የጠብ ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚመለስ አይደለም። ሁል ጊዜ በጸና ፍቅር ውስጥም ቢሆን መኖር ያለበት "ንጹሕ ፍርሐት እና ሐፍረት" አለ። እርሱ ደግሞ መከባበርን ያመጣል።
የእግዚአብሔርን ፍቅር በሚገባ ላልቀመሰ ሰው ከገጸ ምሕረቱ ይልቅ ገጸ መዓቱ ይጎላበታል። ስለዚህ ትእዛዛቱን ለመፈጸም የመጀመሪያ ምክንያት የሚሆነው "በሥጋዬ እንዳይቀስፈኝ፣ በነፍሴ እንዳያጠፋኝ" የሚለው ፍራቻው ነው። እንዲህ ያለውን ፍርሃት መጽሐፈ መነኰሳት "ፍርሃተ አግብርት"/"የባሮች ፍርሐት" ብሎ ይጠራዋል። ይህም እንደ እኛ ባሉ ጀማሪ ክርስቲያኖች ኅሊና ውስጥ የሚሯሯጥ ፍርሃት ነው። ፍቅሩን ለሚያስብ የበረታ ክርስቲያን ግን ባላደርግ እቀጣለሁ ብሎ ሳይሆን፣ ፈጣሪውን ስለሚወድ ብቻ ትእዛዙን ይፈጽማል።(ዮሐ 14)
ይሁን እንጂ ከፍቅር ላይ የደረሱም ቅዱሳን ቢሆኑ እግዚአብሔርን መፍራታቸው የማይቀር ነገር ነው። ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር መልሰው እርሱን እንዲዳፈሩት ምክንያት አይሆናቸውም። የቅዱሳኑ ፍርሃት ግን "ምን ያደርገኝ ይሆን" የሚል የባርያ ፍርሃት ሳይሆን፣ "እንዳያዝንብኝ፣ እንዳይከፋብኝ" ከሚለው ልጃዊ ፍቅር የመነጨ ነው።
በተጨማሪም የመለኰቱ ርቀት፣ የባሕርዪው ምልዓት በልብ ታስቦ የማይደረስበት መሆኑን ዐውቀው፣ በልባቸው ጉልበት እየራዱ አይመረመሬነቱን በአንክሮ ማድነቃቸው ነው "እግዚአብሔርን መፍራታቸው"።
ሐዋርያው "ፍጹም ፍቅር ፍርሐትን አውጥቶ ይጥላል" ይለናል።(1ኛ ዮሐ 4፥18) ምን ማለት ነው? ስለ የትኛው ፍርሃት እየተናገረ ይሆን? ቅዱስ ዮሐንስ የሚናገረው አንደኛ "ፍርሐተ አግብርት" ስለተባለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እሳት ስለቱን እንዲሁም በሥጋ የሚመጣውን ስቃይ ተሰቅቆ እርሱን ከመካድ ስለሚያደርሰው "ጎጂ ፍርሐት" ነው።
በቀረው ግን ፍጹም ፍቅር ሥጋዊ ፍርሐትን እንጂ፣ እግዚአብሔርን መፍራትን ከውስጣችን አውጥቶ አይጥልም!

+++ የዘመኑ ፈተና... +++
የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡
ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን?
ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡
ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ ሕፃናትን፣ ጧሪ ያጡ አረጋውያንን ትመለከታለህ፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ነገር እያየህ ፈጣሪ አለ ብለህ ታምናለህ?
በዚህ ጊዜ ጸጉሩን የሚስተካከለው ሰው በዝምታ ተዋጠ፡፡ የተነሡት ማስረጃዎች ሁሉ የማይካዱ የአደባባይ ሐቆች እንደሆኑ ሲያስብ መልስ አጥቶ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጠመ፡፡ ፈጥኖ የእርሱን ሐሳብ መቀበልም አልፈለገም፡፡ የማይጨበጥ ምክንያት ይዞ በጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግተውም አልወደደም፡፡ ብቻ የመረጠው ዝምታን ነበር፡፡ ዝም አለ!
እንዲህ ዝም እንዳለ ጸጉሩን ተስተካክሎ ጨርሶ ወጣ፡፡ የሚደንቀው ግን ወደ ወጣበት ጸጉር ቤት ድንገት ዘው ብሎ ገባ፡፡ ቀጥሎም ጸጉሩን ወዳስተካከለው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭ የለም!›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም በንግግሩ እየተገረመና በድንጋጤ እያየው ‹‹እንዴት? አንተ ራስህ የት ተቆርጠህ ነው እንዲህ የምትናገረው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ደንበኛ ጸጉር ቆራጩን እጁን ይዞ ወደ ውጭ እያስወጣው፣ በጎዳናው ላይ የተንጨባረረ እና ያልጸዳ ጸጉር ወደ ነበረው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭማ የለም፡፡ ጸጉር ቆራጭ ቢኖር ኖሮ ይህ ምስኪን በተቆረጠ ነበር›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም እርማት ለመስጠት እየቸኮለ ‹‹ቆይ ቆይ ወንድሜ አትሳሳት፡፡ ጸጉር አስተካካይማ እኔ አለሁ፡፡ ይህ ሰው ጸጉሩ የተንጨባረረው እኔ ባለመኖሬ ሳይሆን እርሱ ወደ እኔ ስላልመጣ ነው›› እያለ መኖሩን ሊያሳምነው ሞከረ፡፡
ያም ጸጉር ተስተካካይ እንዲህ አለው ‹‹አዎ፤ የዚህ ሰው ጸጉር ያለ ልክ አድጎ የተንጨባረረውና አዳፋ የሆነው አንተ ባለሙያው ስለሌለህ ሳይሆን እርሱ ወደ አንተ ስላልመጣ ነው፡፡ ልክ እንደዚህ ደግሞ ዓለም ችግር ውስጥ የምትወድቀውና ክፉ ነገር የሚያጋጥማት ፍጹም በጎ የሆነ አምላክ ሰለሌለ ወይም የሚጠብቃት ቸር እረኛ ስላጣች ሳይሆን ዓለም ወደ ፈጣሪዋ ስላልመጣች፣ በንስሓም ወደ እርሱ ስላልቀረበች ነው።››
‹እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል›
2ኛ ዜና 15፡2
ወደ አምላካችን እንቅረብ!!!

+++ "በእኛ ውስጥ ያሉ አራዊት" +++
ምክንያታዊ ያልሆኑ (irrational) ዓሦችን ትገዛ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶህ እንደ ነበር፣ እንዲሁ ምክንያታዊ ባልሆኑ ስሜቶችህም ላይ ገዢ ሆነሃል። "የምድር አራዊትንም ሁሉ ይግዙ" ስለተባለ በዚህም በእኔ ውስጥ ያሉት አራዊት ምንድር ናቸው? ትላለህ። በእርግጥም በሺዎች የሚቆጠሩና በዝተው የተጨናነቁ አራዊቶች በአንተ ውስጥ አሉ። ይህንንም ስልህ ንግግሬን ስሜትን እንደሚጎዳ ጽርፈት (ስድብ) አድርገህ አትውሰደው።
ትንሹ አውሬ "ቁጣ" በልብህ ውስጥ በጮኸ ጊዜ ከውሾች ይልቅ የከፋ አውሬ አልሆነም? ማንኛውም ያደፈጠ አውሬን ከመግራት አታላይ በሆነች ነፍስ የሚደረግን የተንኮል ማድፈጥ መግራት የበለጠ አስቸጋሪ አይደለምን? ትምክህተኝነት አውሬ አይደለምን? በስድብ የሰላስ ሰው እንደ ጊንጥ አይደለምን? በበቀል ጥም በስውር ሊያጠቃ የተሸሸገ ከእፉኝት ይልቅ አይከፋምን? ስስታም ሰውስ የሚስገበገብ ቀማኛ ተኩላ አይደለምን? በእኛ ውስጥ የሌለ እንደ ምን ያለ አውሬ ነው? ሴቶችን ባየ ጊዜ የሚቅለበለብስ የተቀለበ ፈረስ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ " እንደ ተቀለቡ ፈረሶች ሆኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ኋላ አሽካኩ" ይላልና።(ኤር 5:8) ነቢዩ ሰዎቹ ከራሳቸው ጋር ካዛመዱት እኩይ ፍትወት የተነሣ ከሴቶቹ ጋር " ያሽካካሉ" አለ እንጂ "ይነጋገራሉ" አላለም። ስለዚህም በእኛ ውስጥ ብዙ አራዊት አሉ።
በውጪ ያሉትን እየገዛህ በውስጥህ ያሉትን ግን ያለ ገዢ ብትተዋቸው በእውነት የአራዊት ገዢ የምትሆን ይመስልሃል? ምክንያተኝነትህን ተጠቅመህ አንበሳን በመግዛትህና ግሳቱንም እንደ ተራ ጩኸት በመናቅህ፣ ነገር ግን ጥርስህን እያፏጨህና ወል የሌለው ድምጽ እያሰማህ በአንድ ጊዜ ተቆጥተህ ለማጥቃት የምትታገል አንተ በእውነት ገዢ ነህ? የሰው ልጅ በስሜቱ ሲገዛ (ሲነበብ ይጠብቃል)፣ ቁጣውም (ንዴቱ) ምክንያተኝነቱን ወደ ጎን ገፍታ ቦታ በማሳጣት በነፍሱ ላይ ስትሰለጥን ከማየት የበለጠ ምን አደገኛ ነገር አለ?
በእርግጥም አንተ የስሜቶች ፣የአራዊት ፣በደረታቸው የሚሳቡና በክንፋቸው የሚበሩ ፍጡራን ሁሉ ገዥ ሆነህ የተፈጠርህ ነህ። ቀላል የሆኑና በኅሊናህ ውስጥ የማይረጉ አየራዊ ሐሳቦች አይኑሩህ። በራሪ በሆኑ ነገሮችም ላይ ትገዛቸው ዘንድ ተሹመሃልና። …የፍጡራን ሁሉ ገዥ ትሆን ዘንድ በቅድሚያ በአንተ ውስጥ ያሉትን ሐሳቦች ግዛ። በእንስሳት ላይ የተሰጠን የገዢነት ሥልጣን የእኛ በሆኑት ነገሮች ላይም ገዢዎች እንድንሆን ያለማምደናል።
ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ ስለ ሰው ተፈጥሮ ካስተማረበት ድርሳን የተወሰደ
ትርጉም : ዲያቆን አቤል ካሳሁን

+++ የተሰጠ እንባ +++
የሰው ልጅ ደካማ ነው። በውስጡ የሚፈራረቁበትን ስሜቶች ተሸክሞ ለማቆየት ይቸገራል። በጣም ሲደሰት ወይም በጣም ሲያዝን እነዚህን ስሜቶች የሚያስተነፍስበት ሳቅ ወይም ልቅሶ ይፈልጋል። ይህ ካልሆነ ግን ሰውነት ይጨነቃል። አዲስ የወይን ጠጅ እንደ ገባበት አሮጌ አቁማዳ እቀደድ እቀደድ ይላል። ከባዱን የስሜት ሰደድ እሳት የሚያበርድበት ትኩስ እንባ ከዓይን ካላዘነመ ዕረፍት የሚባል ነገር አያገኝም። ዓይን አላነባ ሲል የውስጥ ሕዋሳት የሕመም እንባ ማንባት ይጀምራሉ።
የሕክምና ሰዎች እንደሚናገሩት ሦስት ዓይነት እንባዎች አሉ። የመጀመሪያው ዓይን ውስጥ ባዕድ (ቆሻሻ) ነገር ሲገባ የምናነባው ቅጽበታዊ እንባ (Reflex tear) ሲሆን፣ ሁለተኛው ዓይናችን እንዳይደርቅና ራሱን ከinfection ለመከላከል ሲል የሚያመነጨው የማይቋረጥ እንባ (Continuous tear) ነው። ይህም እንባ 98% ውኃ ነው። ሦስተኛውና በጣም ጠቃሚው እንባ ደግሞ የውስጥ ስሜት ፈንቅሎ የሚያወጣው እንባ (Emotional tear) ነው። ተጨማሪ ጥናቶች ቢፈልግም የዘርፉ ሊቃውንት እንደሚሉት በተለይ በኃዘን ጊዜ የሚፈስሰው እንባ ከሌሎቹ እንባዎች በተለየ በሰውነት ውስጥ የተለቀቀውን stress hormone ይዞ በማስወጣት ውጥረትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው። ከዚህ እንባ ጋር ተያይዘው በሰውነት ውስጥ የሚለቀቁት እንደ oxytocin እና endorphins ያሉት ሆርሞኖች ደግሞ መረጋጋትና ዕረፍትን እንድናገኝ ያግዙናል።
ይህን የእንባ ጸጋ ለእኛ የሰጠ የሰውን ድካም የሚያውቅ እግዚአብሔር ነው። ልቅሶውንም ለውስጥ ውጥረት ማስተንፈሻ ብቻ ሳይሆን፣ የነፍሳችንን ጉድፍ የምናጠራበትና ወደ እርሱ ይዘን የምንቀርበው የተወደደ መባ አደረገልን። የፈጣሪን የምሕረት ልቡን የምናውክበትና ፈጥኖ እንዲታረቀን ደጅ የምንጠናበትን የእንባ ምንጭ እርሱ ባለቤቱ ከዓይናችን ሥር አኖረ።(መኃል 6፥5) ሊቁ ዮሐንስ ዘሰዋስው እንደ ተናገረው ይህንንም እንባ ወደ ሰማይ ለምንወጣበት የብርሃን መሰላል አንደኛው እርከን አድርጎ ሰጠን። ልቅሷችንን ለመጽናናት አደረገው። "ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛል"ና (መክ 7፥3)
የምትወደውን ሰው አጥተህ የምታነባ አንተ ሰው "እንዲህ ሳዝን ወዴት አለህ?" ብለህ ፈጣሪህን አትክሰስ። እግዚአብሔርን እንባህ ውስጥ ፈልገው ታገኘዋለህ። የውስጥህን ኃዘን ከሚያበርድበትና ስብራትህን ከሚጠግንበት መንገዶቹ አንዱ "በሰጠህ እንባ" ነው።

+++‹‹በለምጻሙ ስምዖን ቤት ሳለ›› ማቴ 26፥6+++
አይሁድ በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ግቢ ውስጥ ተሰብስበው በጌታ ሞት ላይ ሲመክሩ፣ መድኃኒታችን ግን በቢታንያ በስምዖን ቤት እራት ግብዣ ተቀምጦ ነበር፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ጌታ እራት የተጠራበት ቤት ባለቤት ‹ለምጻሙ ስምዖን› እንደ ሆነ ይናገራል፡፡ ጸሐፊው ስለ ምን ይህንን ሰው ስምዖን ብቻ ብሎ አልጠራውም? ‹ለምጻሙ› የሚለው ገላጭ ቃል መጠቀም ለምን አስፈለገው? በርግጥ ስምዖን በለምጽ ንዳድ የተያዘና በአይሁድ ዘንድም እንደ ረከሰ እና በደለኛ ተቆጥሮ የሚገለል ብቸኛ ሰው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ግን ጌታ ከሐዋርያቱ ጋር ሆኖ በእርሱ ቤት ለእራት በተቀመጠ ጊዜ፣ ቅዱስ ጄሮም እንደሚናገረው ይህ ሰው ካለበት ለምጽ ሁሉ ነጽቶ ነበር፡፡ ታዲያ ወንጌላዊው ስለ ምን ከለምጹ የነጻውን ስምዖን ‹‹ለምጻሙ›› ሲል ጠራው?
ይህ ያለ ምክንያት አልሆነም፡፡ ጌታችን በስምዖን ቤት ለእራት ተቀምጦ ሳለ የሚፈጸም ቀጣይ ወሳኝ ታሪክ ስላለ፣ ‹ለምጻሙ› የሚለው ገላጭ ለዚያ መግቢያ የሚሆን ወሳኝ ቃል ነበር፡፡ ቀጥሎ የምናገኘው ታሪክም አንዲት በኃጢአት የተመረረችና ነፍሷ የጎሰቆለባት ሴት፣ መንፈሳዊውን ምሕረት ፈልጋ ጌታችን ወዳለበት መምጣቷና የያዘችውን እጅግ ውድ የሆነውን ሽቱ ከፍታ በጌታ በራሱና በእግሮቹ ላይ ማፍሰሷን የሚናገር ነው፡፡ ይህች ሴት ቀድሞ በዝሙት ትኖር ነበረች ብትሆንም ዛሬ ግን የሽቱና የእንባን መባ ይዛ ወደ ክርስቶስ ቀርባለች፡፡ በዘመኑ ብዙዎች ያስጨንቃቸውና የክርስቶስን መድኃኒትነት ይፈልጉት የነበረው ለሥጋዊ ሕመማቸው ነበር፡፡ ምንም የሥጋ ሕመም የሌለባት ይህች ሴት ግን ባልተለመደ ሁኔታ የነፍሷን ሕመም (ኃጢአት) በምሕረቱ መድኃኒትነት ለመሻር ወደ ጌታችን ስትሮጥ መጣች፡፡ ይህም ሥራዋ እጅግ በጣም የምትደነቅ መንፈሳዊት ሴት ያደርጋታል፡፡
በዚህ ወንጌል የተጠቀሰችው ባለ ታሪክ ትሠራ የነበረው ሥራ በሁሉ ዘንድ አስነዋሪ የነበረውን፣ እንኳን በአምላክ ፊት ቀርቶ በሰው ፊት እንኳን ቀና ብሎ የማያስቆመውን ዝሙት ነበር፡፡ ታዲያ ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ድፍረት የሰጣት ነገር ምንድር ነው? እንዴት ወደ መድኃኔዓለም ቀርባ ‹‹ማረኝ›› ለማለት በቃች? ካልን መልሱ ቀላል ነው፤ ጌታ ‹በለምጻሙ ስምዖን› ቤት እንደ ተገኘ አይታ ነው፡፡ ክርስቶስ ራሳቸውን ከሚያመጻድቁ ፈሪሳውያን መካከል በአንዱ ቤት ተገኝቶ ቢሆን ኖሮ ባለ ሽቱዋ ማርያም ድፍረት አግኝታ ወደ እርሱ ባልመጣች ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ሰዎች እንደ ርኩስና በደለኛ ቆጥረው ያገሉት በነበረው ስምዖን ቤት ነውሩን ሁሉ አስወግዶለት አብሮት ለእራት እንደ ተቀመጠ ስላየች፣ የሚበዛው ድካሜን አይቶ የበለጠ ይራራልኝ እንደ ሆነ እንጂ ለእርሱ ያደረገውን ቸርነት ለእኔ አይነሳኝም ብላ በተስፋ ወደ ፈጣሪዋ ገሰገሰች፡፡ እጅግ የሚያስደንቅ ተስፋ ነው!!!
ዛሬም መድኃኔዓለም ክርስቶስ በለምጻሙ ስምዖን ቤት አለ፡፡ ስለዚህ ‹አይሰማኝ ይሆን› የሚለውን ጥርጣሬያችንን ትተን ወገባችንን ያጎበጠውን ኃጢአት በንስሐ ከእግሩ ስር ለማራገፍ ፈጥነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ በለምጻሙ ስምዖን ቤት ለእራት የተቀመጠ አምላክ በፍጹም ጸጸት ብንመለስ የእኛንም ቤት (ሰውነት) አይንቅም፡፡ ይልቅ ሳይረፍድ ቶሎ ሄደን ከእግሮቹ ስር እንውደቅ!!!

+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++
በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ በሄደ ጊዜ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም "ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ 'ታርዤ አልብሳችሁኛልና' ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ እየተሰቃየ እንዴት አልፌው እሄዳለኹ?" ብሎ ፈጥኖ ልብሱን በማውለቅ ይለብሰው ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ያዘ እርቃኑን በጎዳናው ዳር ተቀመጠ፡፡ እርሱን የሚያውቀው አንድ የከተማው ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ አዲስ ልብስ ገዝቶ አለበሰው።
ከዚህም በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ሲሄድ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እያንገላቱ ወደ ወኅኒ ቤት የሚወስዱትን አንድ ምስኪን ሰው ተመለከተ፡፡ እርሱም የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጥኖ በመሸጥ የዚያን ሰው ዕዳ ከፍሎ ነጻ አደረገው፡፡ ይህንንም አድርጎ ጉዞውን ሲጀምር እንደ ገና ሌላ የታረዘ ነዳይ ሲለምን ተመለከተ። አባ ሰራብዮንም እንደ ቀድሞው የለበሰውን ልብስ አውልቆ ለነዳዩ በመስጠት እርሱ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መምህራቸውን እርቃኑን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የምታጽናናበት መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን?› ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹በእጄ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ ያለኝ እርሱ ነበር እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡
ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ የምጽዋትን ታላቅነት ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከወደቀበት የሕግ እርግማን የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!!!

+++ "ጠባቡ በር" +++
ብዙ ቅዱሳን እጅግ አጥብቀው ይፈልጓታል። እርሷንም ለማግኘት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ። እስከ ደም ጠብታ ደርሰው ይጋደላሉ። ባገኙዋትም ጊዜ ውስጣቸው በጸጥታ ይሞላል። ሕዋሳቶቻቸውም እንደ አመዳይ የነጹ እንደ ባዘቶም የጠሩ ይሆናሉ። ይህች ቅዱሳኑ ብዙ የሚደክሙላትና ደጅ የሚጠኗት ጸጋ ማን ትሆን? በአጭር ቃል "ዝምታ" ትሰኛለች።
አንዳንድ ሰው "ንግግር ዋጋ ያለው እና የሚጠቅም ነገር ሆኖ ሳለ፣ ታዲያ ለምን ዝምታ ጥሩ እና የበጎ ሥራዎች ሁሉ ቁንጮ ተደርጎ ይወሰዳል?" ሲል ሊጠይቅ ይችላል። ለዚህ መልሱ ቀላል ነው። የሰው ልጅ በጣም በቀላሉና ብዙ ጊዜ የሚበድልበት ሕዋሱ አንደበቱ ነው። የትም ሳይጓዝ፣ ምንም ሳያይ፣ በጣምም ሳይደክም ባለበት ብቻ ጥቂት ተንቀሳቅሶ ትልቅ ጥፋት ሊያደርስ የሚችል በሰው ውስጥ ያለ ትንሽ ነገር ቢኖር ምላስ ነው። ይህ ስለሆነም አንደበት "ዝምታ" የሚባል ንቁ ጠባቂ፣ ጠንካራ ልጓም ያስፈልገዋል።
ሳይንሱ ሰው የንግግር ችሎታውን ማዳበር እንዲችል ብዙ እንዲናገር ያበረታታል። ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ርቱዕ ተናጋሪ ለመሆን ዝምታ ዓይነተኛ መንገድ መሆኑን ታስተምራለች። ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ "በማይቋረጥ የዝምታ ልምምድ ውስጥ ካልተገባ በቀር መልካም ንግግር (ተናጋሪነት) አይገኝም" ይለናል። ቅዱስ ይሩማሲስም "የኋላ ንግግራችንን ማቅናት እንችል ዘንድ ከሁሉ በፊት ዝምታን እንማር" ሲል ይመክረናል። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም ይህን ይለናል "ንግግራችን የዝምታ ያህል ጥቅም ያለው ይሆን ዘንድ እመኛለሁ... እንድናገር ግድ በተባልኩ ጊዜ የሚሰሙትን ወደ ጸጥታ በንግግር እና በዝምታም ጭምር እመራቸው ዘንድ ስለ "ዝምታ" ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር አላወራሁም። ይህም ስለ ዝምታ ያለኝ የእኔ እይታ፣ ስለ ንግግርም ያለኝ የእኔ ፍልስፍና ነው"። በሥጋዊ ጥበብ የዐዋቂነት መገለጫው መናገርና ጥሩ ተሟጋች መሆን ሊሆን ይችላል። በመንፈሳዊው ዓለም ያሉ ጠበብት ግን ብዙ ሲያውቁ ብዙ የማይናገሩ በመሆን ይታወቃሉ። በጣም ሲራቀቁ ደግሞ ዝምታና ተመስጦ መገለጫቸው ይሆናል።
አንደበትን መግዛት ማለት የሥነልቡና ባለሙያዎች "Suppression" እንደሚሉት ዓይነት ስሜትን መጨቆን ወይም ማፈን አይደለም። አንደበትን በመቆጣጠርና ስሜትን በማፈን መካከል በጣም ሰፊ ልዩነት አለ። በውስጥ የሚቀጣጠለውን ፍትወት ከፍርሐት የተነሣ በንግግር ወይም በድርጊት መግለጥ ሳይቻል ሲቀር ስሜትን ማመቅ (Suppression) ይባላል። አንደበትን መግዛት ግን ምላስን ለበጎ ንግግር መለየት፣ ማንጻት ነው። በአጭሩ ያኛው Suppression ይህኛው ደግሞ purification ነው።
ዝምታ ራሳችንን የምናይበት ጥሩ መጽሔት(መስታወት) ነው። አብዛኛውን ሰዓት በወሬ ተጠምዶ የሚውል ሰው ራሱን የሚመለከትበት እድል አይኖረውም። በሌሎች ኃጢአት ሲፈርድ፣ ሲተችና ሲያማ ስለሚውል የራሱን ስህተትና ውድቀት ለማወቅ ይቸገራል። ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲያወራ የሚውል ሰው የሚያሳዝነው ዝም አለማለቱ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅም ነገር የማይናገር መሆኑም ጭምር ነው። ነገር ግን ማር ይስሐቅ እንደሚለው "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ብዙ ማውራት ባቆመ ጊዜ ወደ ራሱ ይመለሳል። በእግዚአብሔርም ፊት ምግባሩን ማቅናት ይጀምራል"።
የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?!
ታዲያ ለብዙ ዘመናት ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚንኳኳውን ትጉህ እረኛ ድምጹን ሰምተን ለማስገባት ለምን ዝም አላልንም? ራሳችንንስ ከሁከት እና ከከንቱ መለፍለፍ ስለ ምን አልጠበቅንም? አንደበትን መግታት ቀላል አይደለማ! በአንድ ወቅት ቅዱስ እንጦንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነበር :- "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጠባቡ በር እንገባ ዘንድ አዝዞናል።አንደበትን ከኃጢአት መጠበቅ ካልሆነ በቀር ይህ ጠባብ በር ምንድር ነው? እንግዲያውስ ደካማ እና ክፉ የሆነውን ቃል እንዳያወጣ እየተጋደልን ለአንደበታችን ብርቱ ዘብ እናቁም"
በጠባቡ በር እንግባ!

"አምላክን በሥጋ የወለድሽ ከልጅነቴ ጀምሮ ተስፋዬ፣ አምባዬ፣ መጠጊያዬ፣ ጉልበቴ፣ የመድኃኒቴ ሽቱ ብልቃጥ፣ የመመኪያዬ አክሊል ክብሬ ገናንነቴ የራሴ ከፍ ከፍ ማያ ሆይ፤ ክርስቲያን ሥርዓት ጠብቂኝ። በክርስቲያን ሃይማኖት አጽኝኝ። ክርስቲያን ልባል። በክርስቲያንነት ልኑር።"
አርጋኖን ዘዓርብ
የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት፣ ስም አጠራሯም ከአንደበቱ የማይጠፋው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የደረሰው
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
አርጋኖን ዘዓርብ
የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት፣ ስም አጠራሯም ከአንደበቱ የማይጠፋው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የደረሰው
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
+++ "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" +++ ፊል 1፥21
እነሆ ምሳሌ፣
በምንኩስና ይኖር የነበረ አባት ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ ገነት ሄደ። ከውጭም ቆሞ እንዲከፈትለት ደጁን ያንኳኳ ጀመር። ወዲያውም "ማን ነህ?" የሚል ድምጽ ከውስጥ ሲወጣ ሰማ። መነኩሴውም "እኔ ነኝ" ሲል መለሰ። ይሁን እንጂ ያንኳኳው በር ግን ሊከፈትለት አልቻለም። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም እንደ ገና ተመልሶ ወደ ገነት በመምጣት ደጁን አንኳኳ። እንዳለፈውም ጊዜ ከውስጥ "ማን ነህ?" የሚል ድምጽ ሰማ። እርሱም እንደ ለመደው "እኔ ነኝ" አለ። አሁንም በሩ ሳይከፈትለት ቀረ።
መነኩሴው በዚህ ተስፋ አልቆረጠም። ይህ ከሆነ ከብዙ ዓመታት በኋላ እርሱም በመንፈሳዊው ጥበብ ጎልምሶ ተመልሶ ወደ ገነት ሄዶ በሩን አንኳኳ። እንደ ከዚህ በፊቱም "ማን ነህ?" የሚል ድምጽ ሰማ። ያም አባት የቀድሞው መልሱን ተወና "በእኔ ውስጥ የምትኖረው አንተ ነህ" ሲል ለጠየቀው አካል መለሰ። በዚህ ጊዜ ተዘግቶ የነበረው በር ተከፈተለት ይባላል።
ክርስትና ምንድር ነው? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ ማብራሪያዎች ሊሰጡ ይችላሉ። በአጭሩ ግን እንመልሰው ካልን፣ ክርስትና ማለት "ክርስቶስ የሚያድርበት መቅደስ መሆን" ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲገልጽልን "እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል" ይለናል።(ገላ 2፥20) ክርስቲያን ማለት "አንተ ማን ነህ?" ተብሎ ሲጠየቅ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "በእኔ የሚኖር ክርስቶስ ነው"፣ "አነ ዘክርስቶስ" - "እኔ የክርስቶስ ነኝ" ብሎ መመለስ የሚችል ነው።
ጌታችን በወንጌል ለደቀ መዛሙርቱ "በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ" ሲል እንደ ተናገረ፣ እኛ ለክርስቶስ መኖር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ይኖርብናል፤ እኛ ለክርስቶስ ማደር ስንጀምር እርሱ ደግሞ በእኛ ያድርብናል።(ዮሐ 15፥4)
እንዲህ ያለውን ሕይወት የሚኖር እውነተኛ ክርስቲያን የሥጋን ሞት አይፈራም። ስለ ሃይማኖቱ መከራ መቀበልን አይሰቀቅም። ክርስቶስን ከሚያሳጣው ሕይወት ይልቅ ወደ ክርስቶስ የሚወስደውን ሞት ይመርጣል። ፈጣሪው ከሌለበት ምቾት ይልቅ ፈጣሪን ይዞ መሰቃየት ለእርሱ ያስደስተዋል።
ሰይፍ ይዘው በሚያስፈራሩትም ጨካኝ ወታደሮች ፊት "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና" እያለ በሐሴት ይዘምራል።(ፊል 1፥21)
በሰይፍ ለሚገድለው ወታደር በኩራት የልብሱን ኮሌታ ከፍ አድርጎ አንገቱን ስለ ክርስቶስ በደስታ የሰጠ፣ የታላቁ ሐዋርያ የቅዱስ ጳውሎስ የአገልግሎቱ ድካም፣ በረከት በሁለችን ላይ ይደርብን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
+++"እንደ አባቶቻችን ከተመለስን ይምረናል"+++
ጥንት በአባቶቻችን ዘመን አስጨናቂ መከራ በተነሣ ጊዜ፣ ልመናን የሚያውቁ አባቶችና እናቶቻችን ራሳቸውን አዋርደው በፍጹም ንስሐ የፈጣሪያቸውን ምሕረት ደጅ ጠኑ። እርሱም ጩኸታቸውን ሰምቶ ዘንበል አለላቸው። መዓቱንም ከእነርሱ መልሶ በገጸ ምሕረቱ ጎበኛቸው። በቁጣው ቀን ተስፋ ያደረጉት ቸርነቱ አላሳፈራቸውም።
ዛሬስ? ዛሬም የእኛ ንስሐ እንደ አባቶቻችን እውነተኛ ከሆነ፣ በፈጣሪያችን ቸርነት ላይ ያለን መተማመን ከቀደሙት እናቶቻችን ካላነሰ፣ አምላካችን እኛን ይቅር ለማለት የታመነ ነው። መድኃኔዓለም መለወጥ እንደሚስማማው ደካማ የሰው ልጅ አይደለም። ልክ በፀሐይና በመሬት መካከል ባለ ዑደት (ዙረት) ምክንያት፣ አንዱ የመሬት ክፍል ከፀሐይ ብርሃን ተቀብሎ ሲያበራ በሌላኛው በኩል ያለው ደግሞ በግርዶሽ እንደሚጨልም እንዲሁ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን (ቸርነት፣ ምሕረቱ) ለአንዱ አብርቶ ለሌላው የሚጋረድ አይደለም። ለብርሃኑ የተዘጋጀና በኃጢአት ጉድፍ ያልታወረ ዓይነ ልቡና እስካለን ድረስ የምሕረቱ ነጸብራቅ ለዘወትር በእኛ ላይ እንዳበራ ነው። ብቻ ንስሐችን እንደ ቀደሙት እናቶቻችን፣ መመለሳችንም በቃልና በተግባር እንደ ተመለሱት እውነተኞቹ አባቶቻችን ይሁን!።
"በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ"
ያዕ 1፥17

"በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። እግዚአብሔርን፡— አንተ መታመኛዬ ነህ፡ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ። እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።"
መዝሙር 91
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com

እጅግ ጥልቅ የጸሎት ሕይወት የነበረው፣ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ የሚጾመው ተሐራሚው ቅዱስ አባ ጳጉሚስ ከእለታት በአንዱ ቀን ይህን ተመለከተ፡፡ ቅዱሱ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር አብዝቶ ይሰግድ ነበር፡፡ ከዓይኑ የሚወርደው እንባ ከሰውነቱ ወዝ ጋር እየተቀላቀለ ወደ መሬት በመውረዱ ምክንያት የሚሰግድበትን ቦታ አረጠበው፡፡ አባ ጳኩሚስም ይህን ወደ ጌታው እያመለከተ "ይኸው አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ" ሲል ተናገረ፡፡ በዚህ ጊዜም መድኃኒታችን ለአባ ጳጉሚስ ተገልጦ "እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ" በማለት በእለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ የተወጋ ጎኑን፣ የፈሰሰ ደሙን አሳየው፡፡ ቅዱሱም የጌታው ሕማም ከሕሊናው በላይ ሆኖበት ወድቆ ምሕረትን ለምኗል፡፡
+++++++++++++
ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን :- ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ›› ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ‹‹መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን?›› ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ‹‹አዎ! አይ ዘንድ እወዳለሁ›› አሉት። ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር። እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል።
‹‹ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ›› - ‹‹ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው!››
እንኳን አደረሰን!!!

"ጌታ በመንግሥቱ እንዲያስብህ በጠየቅህበት በዚያው መንገድ፣ እንዲሁ አንተም በምድር ላይ ልታስበውና ልቡናህን ለፍቅሩ ልታጸና ይገባሃል"
አቡነ ሺኖዳ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
አቡነ ሺኖዳ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
+++ ጆሮ ሽፋን የለውም +++
ጆሯችን የተለያየ መጠን ያላቸውን ድምጾች ለመስማት የሚያስችለን የአካላችን አንደኛው እና አስፈላጊው ሕዋስ ነው፡፡ ከጥቃቅን በራሪ ሕዋሳት ከሚወጡ የሰለሉ ድምጾች ጀምሮ ሁከት እና ድንጋጤን እስከሚፈጥሩት የሰማይ መባርቅት ጩኸት ድረስ የማድመጥ ችሎታ አለው፡፡ ይሁን እንጂ ለእኛ በጣም ቅርብ የሆኑና በሰውነታችን ውስጥ የሚካሄዱትን የልመት ስርዓት ፣የልብ ምት ድምጾችን በመሳሪያ እስካልታገዝን ድረስ አጥርተን አለመስማታችን ደግሞ እጅግ የሚያስደንቅ ነገር ነው፡፡ አስባችሁታል በደም ቧንቧዎቻችን "ሽሽ" እያለ የሚያልፈውን የደም ዝውውር፣ ምግብ ከበላን በኋላ ያለውን የልመት (የመፍጨት) ሥርዓት፣ የማይቋረጥ የልባችንን ምት ሁል ጊዜ የምንሰማ ቢሆን ሰላም የሌለን ተቅበዝባዦች እንሆን ነበር። ተመስገን ነው!!!
እኛ የሰው ልጆች ድምፅን ከመቀበል በተጨማሪም መልእክትን ባዘለ መልኩ በቃላት ሞሽረን የማስተላለፍም ልዩ ስጦታ አለን፡፡ በመሆኑም መስማት እና መናገር ለመግባባት የሚረዱን መሠረታዊ ነገሮች ናቸው፡፡ በጆሯችን በኩል የሚገቡ የድምጽ ሞገዶችን መልእክት ለመለየት የሚረዳ በናላ ላይ የሚገኝ ጣቢያ አለ፡፡ ያለዚህ የናላ ክፍል በፍጹም መልእክት ያለው ድምጽን መስማት አንችልም፡፡
ጆሯችን ከዚህች ዓለም ጋር ለሚኖረን መስተጋብር ልክ እንደ ዓይናችን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የሰው ዘር የሆንን ሁላችንም አጎንብሰን አለመሄዳችን እና ቀጥ ያለ አቋም ያለን መሆኑ ብዙ ነገሮችን እንድናከናውን ረድቶናል። በተለይ የአካልን ሕዋሳት ተጠቅመን ለምንሠራቸው እንደ ንባብ ፣ጽሕፈት ፣ማሽከርከር የመሳሰሉትን ተግባራት በቀላሉ እንድናከናውን ያግዘናል፡፡ ነገር ግን ምንም ቀጥ ያለ አቋም ቢኖረንም ሚዛናችንን ጠብቀን እግራችን ሳይጠላለፍ ሰውነታቸን ሳይዛነፍ ባለንበት መጽናት የምንችለው እና ቀጥ ብለን የምንሄደው ሚዛን ጠባቂው ጆሮ እስካለ ድረስ ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ለምን ባለ ሁለት ጆሮዎች አድርጎ አዘጋጀን? ለመስማት አንዱስ ቢሆን በቂ አይደለምን? የሚል ጥያቄ ጠይቀን እናውቅ ይሆን? ጆሯችን መስማት ብቻ ሳይሆን ድምጹ የመጣበትን አቅጣጫ እና የድምጹ ምንጭ ቋሚ ይሁን ተንቀሳቃሽ ለመለየት ይጠቅማል፡፡ አንድ ሰው ከፊት ለፊቱ የመጣን ድምጽ ፍለጋ ወደኋላ ዞሮ የማያስሰው ሁለት ጆሮዎች ያሉት በመሆኑ ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገር በጥንቃቄ እና በምክንያት መዘጋጀቱን ከሚያመለክቱ የሰውነት ክፍል ሕዋሳት መካከል አንዱ ጆሮ እንደሆነ ተመልከቱ።
ሁላችሁም እንደምታውቁት ደስ የማያሰኘውን ነገር ዓይናችን እንዳያይ የምንከለክልበት የተፈጥሮ የዓይን መሸፈኛ ቆብ አለን። ጆሮአችን ግን ልክ እንደ ዓይናችን ሲፈለግ የሚዘጋ እና የሚከፈት ቆብ ወይም ሽፋን የለውም። ስለዚህም ማንኛውም ሰው በየትኛውም ጊዜ የሚያደርጋቸው ያልተገቡ ንግግሮች በቀላሉ በጆሮአችን አልፈው ለመግባት ሰፊ እድል አላቸው ማለት ነው። በመሆኑም ከአንደበታችን የሚወጣው ክፋ ቃል መዝጊያ ባልተዘጋጀለት በሌላ ሰው ጆሮ አልፎ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ልናደርግ ያስፈልጋል። የምንናገርም ሁሉ የሚያንጸውን እና በጎውን ብቻ እየተናገርን የሰሚዎቻችንን ጆሮ እንታደግ።
እንዲህ ፈጣሪ ጥበቡን አፍሶ የፈጠረው ጆሯችንን ክፉ እየሰማ እንዲባክን አናድርገው!!!